Friday, January 6, 2017

በህወሓት የበላይነት ስር የሚገኘው የኣገር መከላከያ ሠራዊት ከ25 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ January 5, 2017


(በአርበኞች ግንቦት 7 ጥናትና ምርምር ቡድን የተዘጀ) 

ታህሳስ 2009 ዓ.ም.
መግቢያ
የዛሬ ሰባት አመት (እ.ኤአ. 2009) ያኔ “ግንቦት 7- የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ” ይባል የነበረውና አሁን አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ውስጥ የተጠቃለለው ድርጅት በዘር የተደራጀዉን የወያኔ መከላከያ ተቋም አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ብሎም ለዓለም ማኅበረሰብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ያ ጥናታዊ ሪፓርት ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብም ቀርቶ አገዛዙን ትዝብት ላይ በመጣሉ “የመካከያ ሠራዊታችንን ብሄራዊ ተዋጽዖ እናመጣጠንን ነው” የሚል ፕሮፖጋንዳ የወያኔ ኣገዛዝ መንዛት ተጀመረ።
በዝቅተኛና በተራ ውትድርና ደረጃ መመጣጠን መኖሩ ድሮም ጥያቄ ተነስቶበት አያውቅም። ድሮም አሁንም ጥያቄው ያለው በሠራዊቱ አመራር ላይ ያሉት እነማን ናቸው የሚለው ላይ ነው። በዚህ ረገድ በእርግጥ እንደሚባለው ለውጥ አለን? ይህ ጽሁፍ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የተደረገ ጥናት ውጤት ነው።
የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው የአገዛዙ ሠራዊት አመራሮች የብሄር ተዋጽዖ በተመለከተ ዛሬ ሰባት ዓመት ከነበረው እጅግም የተሻለ ነገር የለም። በህወሓት ስር የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላም 6% ብቻ የሆነውን የትግራይን ሕዝብን አንወክለዋለን በማለት በሚነግዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች የበላይ ኃላፊነት፣ እዝና ቁጥጥር ስር ወድቆ እናገኛለን። ይህ ጥናት እንደሚያሳየው የኣሮሞና የኣማራ ብሄሮችም ሆኑ ሌሎችሁ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በመከላከያ ሠራዊቱ የኃላፊነትና የእዝ ቦታዎች ላይ እጅግ ዝቅተኛ ወይንም ከነኣካቴው ምንም እይነት የኃላፊነት ድርሻ የላቸውም። ይህ ያገጠጠ ኢ-ፍትሃዊነት ኣንድምታው ህሊና ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ምን ማለት መሆኑ ግልጽ ነው ብለን እንገምታለን። ዛሬም እንደትናቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ ለፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐት ብቸኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችለዉ በቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነጮች ፈጥረውት የነበረው ዘረኛ (Apartheid) ስርዐት ብቻ ነዉ።
በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ በተለይ በቁጥሩ ከፍተኛ ብልጫ ያለዉና ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነዉ ሠራዊት እጅግ ያኮረፈ፤ የተቆጣና ያመረረ ሠራዊት ከመሆኑ የተነሳ እራሱን የሚመለከተዉ እንደ አገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆን አንደ ህወሓት የቤት ዉስጥ አገልጋይ ባሪያ ነዉ። ይህ የህወሓት ዘረኞች በሠራዊቱ ላይ የፈጠሩት የመገዛትና የበታችነት ስሜት በየቀኑ ከፍተኛ ቁጣና የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ የሚገጥመዉ ቢሆንም ህወሓት በዘረጋዉ ከፍተኛ የአፈና መረብ የተነሳ የሕዝብ መነጋገሪያ አርዕስት መሆን አልቻለም። የህወሓት መሪዎችም ቢሆኑ ይህንን ቁጣና ተቃዉሞ በሚገባ ስለሚያዉቁ “ግምገማ” እያሉ በሚያዘጋጇቸዉ መድረኮች ላይ እንደነዚህ አይነቶቹን የህወሓትን የበላይነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማስተናገድ ቀርቶ ጥያቄዎቹ እንዲነሱም አይፈቅዱም። አንዳንዴ ደፍረዉ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሱ ግለሰቦች ሽብርተኛ፤ የደርግ ስርዐት ናፋቂዎች፤ ጠባብ ብሄረተኞች ወይም የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች የሚል ተቀጥላ ስም ይሰጣቸዋል። ዛሬ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዉ በተለያዩ የወያኔ እስር ቤቶች ዉስጥ የሚሰቃዩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የበቁት በመከላከያ ተቋሞች ዉስጥ ሠራዊቱን በዬትኛዉም እርከን የሚመሩ መኮንኖች አመዳደብ ወታደራዊ አመራር ችሎታን፤ ልምድንና የብሄር ስብጥርን ያካተተ መሆን አለበት ብለዉ ደፍረዉ በመናገራቸዉ ነዉ።

የወያኔን መከላከያ ሠራዊት እየለቀቁም ሆነ ትግሉን አየተቀላቀሉ የመከላከያ ሠራዊት ኣባላት ቁጥር ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል። እነዚህ ወታደራዊ መሪዎች፤ የበታች መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረጎቸችና ተራ ወታደሮች ከጠላት እንከላከላን ብለዉ የማሉላትን እናት አገራቸዉን እየለቀቁ የሚወጡት በወያኔ ጦር ዉስጥ ስር የሰደደዉ ዘረኝነትና በዚህ ዘረኝነት ላይ የተመሰረተዉ አመራር የሚያደርስባቸዉ በደል አንገፍግፏቸዉ ነዉ። ዛሬም አንደትናቱ በየጎረቤቱ አገር ተሰድደዉ በችግር ላይ የሚገኙ ምርጥ የኢትዮጵያ የሚሊታሪ ሳይንስ አዋቂዎች ሁሉም በአንድ ድምፅ የሚናገሩት ሠራዊቱ ዉስጥ ይድርስባቸዉ የነበረዉ ንቀትና ዉርደት የሰዉ ልጅ መሸከም ከሚችለዉ በላይ መሆኑን ነዉ።
በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ በገነባዉ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ የዕዝ፤ የክፍለጦርና የመምሪያዎች አዛዥ ለመሆን ዋነኛዉ መለኪያ የህወሓት አባል መሆን ነዉ እንጂ ችሎታ፤ ልምድ፤ ብቃትና የወታደራዊ ሳይንስ ክህሎት አይደለም። ችሎታ፤ ልምድና ብቃት መመዘኛ ሆነዉ የሚቀርቡት በመጀመሪያ ለሹመት የታጨዉ መኮንን ህወሓትነት ከተረጋገጠ በኋላ ብቻ ነዉ። በህግ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የፓለቲካ ድርጅት አባላት አይሆኑም፤ በተግባር ግን ለሹመት የሚያሳጨው የፓርቲ አባልነት ነው።
አንደሚታወቀው የህወሓት የስልጣን ሞኖፖሊ በወታደራዊ ደህንነት ተቋሞች ላይ ብቻ ተወስኖ አያበቃም። አብዛኛዉን የአገሪቱ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ተቋሞችም ወይ ከላይ አለዚያም ከታች ሆነዉ ይቆጣጠራሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለይስሙላ የተቀመጠና ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የመጡ ሰዎች የሚገኝበት መንግስት አለ፤ በዚህ መንግስት ዉስጥ ደግሞ አገሪቱን ወዳሰኘዉ አቅጣጫ በዘፈቀደ የሚዘዉረዉና ከትግርኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ሌሎች የማይገኙበት በመንግስት ዉስጥ ሌላ መንግስት አለ። የሚገርመዉ ዛሬ እነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፤ አባዱላ ገመዳና ደመቀ መኮንንን የመሳሰሉ ምስለኔዎች ስልጣን ላይ የተቀመጡ ነገር ግን ህወሓት ጌቶቻቸዉ ከሚነግሯቸዉ ዉጭ በራሳቸዉ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉ አሻንጉሊቶች መሆናቸዉን እነሱ አራሳቸዉም የተገነዘቡት ይመስላል።
በዚህ በወቅታዊ መርጃዎች ላይ በመመስረት በኣርበኞች ግንቦት 7 የወታደራዊ ጥናት ቡድን ተሻሽሎና ታድሶ በኣዳዲስ መረጃዎች በተጠናቀረው ጥናት ቀጥሎ የሚቀርበዉ ሠንጠረዥ የተለያዪ የመከላከያ ተቋም የኃላፊነትና የእዝና ቁጥጥር ቦታዎችን፤ በእነዚህም ቦታዎችን እነ ማን እንደተቀመጡና የተወለዱበት ብሄረሰብ ያሳያል።
በዚህ ሠንጠረዥ ያልተመለከተ ሌላ አቢይ ጉዳይም አለ። ይህም በእስር ላይ ከሚገኙ የሠራዊቱ መኮንኖች ውስጥ እጅግ የበዙት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የመሆናቸው ሀቅ ነው። በጄኔራል ተፈራ ማሞና ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጋር በተያያዘ እነሱን ጭምሮ በርካታ ባለከፍተኛ ማዕረግ የአማራ ተወላጆች ታስረዋል፤ ከዚህ በቁጥር የበዙት ከሠራዊቱ ተባረዋል። ከጄኔራል ከማል ገልቹና ጄኔራል ኃይሉ ጎንፋ ጋር ተያይዞ እንደነዚ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ተወላጅ መኮንኖች ታስረዋል፣ ተባረዋል። አገዛዙ ውስጥ ችግር በደረሰ ቁጥር የችግር መወጫ የሚሆኑን የአማራ፣ የኦሮሚያና የሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ተወላጅ የሆኑ መኮንኖች ናቸው።
1. የመከላከያ የበላይ ኃላፊነቶችና እዞች የብሄር ስብጥር
ትግሬአማራኦሮሞኣገውየደቡብ
ሕዝቦች
ኣፋርጋምቤላቤኒ ሻንጉልሶማሊሀረሪድምር
የመከላከያ የበላይ ኃላፊዎችና ኣዛዦች344533ምንምምንምምንምምንምምንም49
የእዝ ኣዛዦችና ምክትል የእዝ ኣዛዦች915ምንም1ምንምምንምምንምምንምምንም16
ሌሎች የኣዝ ከፍተኛ ኃላፊዎች2122ምንምምንምምንምምንምምንምምንምምንም25
የትምህርትና የስልጠና ኃላፊዎች2334ምንምምንምምንምምንምምንምምንምምንም30
የክፍለ ጦር ዋና እዛዦች1251ምንምምንምምንምምንምምንምምንምምንም18
የክፍለ ጦር ከፍተኛ ኃላፊዎች1987ምንምምንምምንምምንምምንምምንምምንም34
የአየር ኃይል ከፍተኛ ኃላፊዎች2994ምንም3ምንምምንምምንምምንምምንም45
ጠቅላላ ድምር147322837ምንምምንምምንምምንምምንም217
ጠቅላላ በመቶኛ (%)6815131.33ምንምምንምምንምምንምምንም

2. አጠቃላይ የመከላከያ የበላይ ኃላፊነቶችና እዞች የብሄር ስብጥር
graph

3. ሰባቱ ዋና ዋና የመከላከያ የበላይ ኃላፊነቶችና እዞች የብሄር ስብጥር
የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦችና የበላይ ኃላፊዎች

ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ጄነራልሳሞራ የኑስየጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹምትግሬ
2.ሌ/ጄነራልአደም መሃመድ (ኤፍሬም)የአየር ኃይል ዋና አዛዥአማራ
3.ሌ/ጄነራልሰዓረ መኮንንየትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ አዛዥትግሬ
4.ሌ/ጄነራልዮሃንስ ገ/መስቀልየህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ አዛዥትግሬ
5.ሌ/ጄነራልብርሃኑ ጁላየሰላም ማስከበር ማስተባበሪያ ማእከል ኃላፊኦሮሞ
6.ሜ/ጄነራልገብሬ አድሃና (ዲላ)የመረጃ ዋና መምሪያ አዛዥትግሬ
7ሜ/ጄነራልኢብራሂም አብዱልጀሊድየሎጂስቲክ ዋና መምሪያ አዛዥትግሬ
8.ሜ/ጄነራልክንፈ ዳኘውየመከላከያ ኢንዱስትሪ ሴክተር ኃላፊትግሬ
9.ሜ/ጄነራልተ/ብርሃን ወ/አረጋይየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ዋና ዳይሬክተርትግሬ
10.ሜ/ጄነራልብርሃኔ ነጋሽየመከላከያ ምኒስትር ዴኤታትግሬ
11.ሜ/ጄነራልማሞ ግርማይየብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ዋና አዛዥአገው
12.ሜ/ጄነራልሃሰን ኢብራሂምበደቡብ ሱዳን አቢዬ የሰላም ማስከበር ኃይል ዋና አዛዥአማራ
13.ሜ/ጄነራልመሃሪ ዘውዴየሰው ኃይል አመራር ዋና መምሪያ አዛዥትግሬ
14.ሜ/ጄነራልመሃመድ ኢሻበሶማሊያ ሰላም ማስከበር የበላይ አዛዥትግሬ
15.ሜ/ጄነራልደስታ አብቹየውጭ ግንኙነት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርኦሮሞ
16.ሜ/ጄነራልገ/ሚካኤል በየነየጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና አዛዥትግሬ
17ሜ/ጄነራልተስፋዬ ግደይየጤና ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
18ሜ/ጄነራልገ/አድሃነ ወለዝሁትግሬ
19ብ/ጄነራልአታክልቲ ወ/ጊዮርጊስየመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋናመምሪያ ም/ል አዛዥትግሬ
20ብ/ጄነራልሙሉ ግርማይየመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ አዛዥትግሬ
21ብ/ጄነራልህንጻ ወ/ጊዮርጊስትግሬ
22ብ/ጄነራልገ/መድህን ፍቃዱየአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥትግሬ
23.ብ/ጄነራልሙላት ጀልዱየአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥ ለአስተዳደርና ፋይናንስኦሮሞ
24ብ/ጄነራልሃብታሙ ጥላሁንአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ስልጠና ማዕከል ዋና አዛዥሃዲያ
25.ብ/ጄነራልአስካለ ብርሃነየመከላከያ የፍትህ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
26ብ/ጄነራልተስፋዬ ወ/ማሪያምየመከላከያ ኢንስፔክሽን መምሪያ ም/ል አዛዥትግሬ
27.ብ/ጄነራልገ/ኪዳን ገ/ማርያምየመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚንኬሽን ዋና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
28ብ/ጄነራልታረቀኝ ካሳሁንየመገናኛ መምሪያ ዋና አዛዥአገው
29ብ/ጄነራልያይኔ ስዩምየመከላከያ ፋውንዴሽን ኃላፊትግሬ
30ብ/ጄነራልጠና ጥሩንቄየብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ም/ል ዳይሬክተርሲዳማ
31.ብ/ጄነራልእንዳልካቸው ገ/ኪዳንየመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች አስተባባሪኦሮሞ
32ብ/ጄነራልመሰለ መሰረትየመከላከያ ህብረት ዘመቻ መምሪያ የኃይል ዝግጅት ኃላፊአገው
33ብ/ጄነራልዘውዲ ኪሮስበደቡብ ሱዳን አቢዬ የሰላም ማስከበር ኃይል ም/ል አዛዥትግሬ
34.ብ/ጄነራልንጉሴ ለማሰላም ማስከበርኦሮሞ
35.ብ/ጄነራልበላይ ስዩምበደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር የዲፍራ ሴክተር ላይዘን ኦፊሰርአማራ
36.ብ/ጄነራልአዲሱ ገ/እየሱስየመከላከያ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
37.ኮ/ልታምራት አንዳርጌአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ስልጠና የቡድን ስልጠናዎች ዲቪዥን ኃላፊአማራ
38.ኮ/ልነጋሽ ህሉፍአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊትግሬ
39.ኮ/ልታዜር ገ/እግዚአብሄርየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ም/ል ዳይሬክተርና የጂኦስፓሻል ደህንነት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
40.ኮ/ልየኑስ ሙሉበመከላከያ የውጪ ግንኙነትና ትብብርና ድጋፍ ቡድን መሪትግሬ
41.ኮ/ልፍጹም ገ/ እግዚአብሄርመከላከያ ፋይናንስ ዳይሮክቶሬትር ዳይሬክተርትግሬ
42.ኮ/ልአለሙ ተካየመከላከያ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት አዛዥትግሬ
43.ኮ/ልምኡዝ አብረሃየመከላከያ በጀትና ፕሮግራም ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
44.ኮ/ልነጋሲ ትኩየመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ፣ የግንኙነት መምሪያ ኃላፊትግሬ
45.ኮ/ልክብሮም ገ/ እግዚአብሄርየመከላከያ የኪነ ጥበባት ስራዎች ኃላፊትግሬ
46.ኮ/ልጸጋዬ ግርማይየመከላከያ ሚዲያ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
47.ኮ/ልበርሄ አረጋይየመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግንኙነትና ስርዓት ደህንነት መምሪያ ኃላፊትግሬ
48.ኮ/ልታደሰ ላምባሞየአጋዚ ኮማንዶና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ም/ል አዛዥ ለሎጀስቲክደቡብ
49ኮ/ልሃጎስ አስመላሽየመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬትትግሬ
የእዝ ዋናና ምክትል አዛዦች
ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ሌ/ ጄነራልአብረሃ ወ/ማሪያም (ኳርተር)የደቡብ ምስራቅ እዝ ዋና አዛዥትግሬ
2.ሌ/ ጄነራልገብራት አየለየሰሜን እዝ ዋና አዛዥትግሬ
3.ሜ/ ጄነራልዮሃንስ ወ/ጊዮርጊስየማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥትግሬ
4.ሜ/ ጄነራልፍሰሃ ኪዳኑየምዕራብ እዝ ዋና አዛዥትግሬ
5.ሜ/ ጄነራልጌታቸው ጉዲናየደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊኦሮሞ
6.ሜ/ ጄነራልማዕሾ በየነየሰሜን እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊትግሬ
7.ሜ/ ጄነራልአጫሉ ሸለመየሰሜን እዝ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊኦሮሞ
8.ሜ/ ጄነራልድሪባ መኮንንየምዕራብ እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊኦሮሞ
9.ብ/ ጄነራልየማነ ሙሉየደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
10.ብ/ ጄነራልኃይለስላሴ ግርማይየደቡብ ምስራቅ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት አመራር ኃላፊትግሬ
11.ብ/ ጄነራልአብረሃ አረጋይየሰሜን እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
12.ብ/ ጄነራልአስራት ዴኔሮየማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊከፊቾ
13.ብ/ ጄነራልአብረሃ ተስፋዬየማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊትግሬ
14.ብ/ጄነራልከፍያለው አምዴየማዕከላዊ እዝ ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊኦሮሞ
15.ብ/ ጄነራልመሃመድ ተሰማየምዕራብ እዝ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊአማራ
16.ብ/ ጄነራልአብዱራማን እስማኤልየምዕራብ እዝ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊኦሮሞ
ከፍተኛ የእዝ አዛዦችና ኃላፊዎች
ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ብ/ጄነራልሙላለም አድማሱየሰሜን እዝ ስልጠና ኃላፊትግሬ
2.ኮ/ልላዕከ አረጋዊየሰሜን እዝ ጤና ዳይሮክትሬት ዳይሬክተርትግሬ
3.ኮ/ልተስፋዬ ብርሃነየሰሜን እዝ መሃንዲስ አዛዥትግሬ
4.ኮ/ልገ/ዮሃንስ ተክሌየሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ጸ/ቤት ኃላፊትግሬ
5.ኮ/ልአስገደ ገ/መስቀልየሰሜን እዝ የመድሃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ኃላፊትግሬ
6.ኮ/ልኪሮስ ወልደስላሴየሰሜን እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊትግሬ
7.ኮ/ልታደለ ገ/ህይወትየሰሜን እዝ ህብረት ዘመቻ ኃላፊትግሬ
8.ኮ/ልመሃሪ አሰፋየሰሜን እዝ የሰው ሃብት አመራር መምሪያ ኃላፊትግሬ
9.ኮ/ልገ/ሚካኤል ኪዳነማሪያምየማዕከላዊ እዝ የህብረት ዘመቻ መምሪያ ኃላፊትግሬ
10.ኮ/ልአሊጋዝ ገብሬየማዕከላዊ እዝ የኢንዶክትኒኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊትግሬ
11.ኮ/ልአደም ሰይድየማዕከላዊ እዝ የህግ ጉዳይ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርአማራ
12.ኮ/ልተመቸው ተስፋዬየማዕከላዊ እዝ የጤና ዳይሮክቶሬትዳይሬክተርአማራ
13.ኮ/ልሃጎስ ሃይሉየማዕከላዊ እዝ የትምህርት ክትትል ኃላፊትግሬ
14.ኮ/ልጥያር በቀለየማዕከላዊ እዝ የስነ ምግባር ኃላፊትግሬ
15.ኮ/ልዮሃንስ ገ/ሊባኖስየምዕራብ እዝ ኢንስፔክሽን ኃላፊትግሬ
16.ኮ/ልተክላይ ገ/ጻድቃንየምዕራብ እዝ ሲግናል ሬጂመንት አዛዥትግሬ
17.ኮ/ልገ/ኪዳን ቸኮልየምዕራብ እዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
18.ኮ/ልበርሄ ኪዳነየምዕራብ እዝ የስልጠና ኃላፊትግሬ
19.ኮ/ልቀለህ ገብረስላሴየደቡብ ምስራቅ እዝ የትራንስፖርት ኃላፊትግሬ
20.ኮ/ልገ/ሜካኤል ገብራትየደቡብ ምስራቅ እዝ የህግ ጉዳይ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተርትግሬ
21.ኮ/ልጥላሁን ወርዶፋየደቡብ ምስራቅ እዝ የስነ ምግባር ክትትል ኃላፊኦሮሞ
22.ኮ/ልአብዱሰላም ኢብራሂምየደቡብ ምስራቅ እዝ የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
23.ኮ/ልተክላይ ገ/እግዚአብሄርየደቡብ ምስራቅ እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
24.ኮ/ልኢሰታ ኢጄታየደቡብ ምስራቅ እዝ የአቅርቦትና ስርጭት ክፍል ኃላፊኦሮሞ
25.ኮ/ልስዩም ተፈራየደቡብ ምስራቅ እዝ ጤና ማበልጸግና በሽታ መከላከል ኃላፊትግሬ
የክፍለ ጦር ዋና አዛዦች
ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ብ/ ጄነራልይብራህ ዘሪሁንየ20ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
2.ብ/ ጄነራልዋኘው አማራየ21ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥአማራ
3.ብ/ ጄነራልአዳምረህ መንግስቴየ11ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥአማራ
4.ብ/ ጄነራልጋይም ሺሻይየ7ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
5.ብ/ ጄነራልአልታወቀምየ23ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ
6.ብ/ ጄነራልሹማ አብደታየ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥኦሮሞ
7.ብ/ ጄነራልከድር አራርሳየ13ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥአማራ
8.ብ/ ጄነራልገ/መስቀል ገ/እግዚአብሄርየ32ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
9.ብ/ ጄነራልአሰፋ ቸኮልየ25ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥአማራ
10.ብ/ጄነራልብርሃኑ ጥላሁንየ12ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥአማራ
11.ብ/ጄነራልሰመረ ገ/እግዚአብሄርየተዋጊ መሃንዲስ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
12.ኮ/ልነጋሲ ተስፋዬየ4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
13.ኮ/ልገ/ጊዮርጊስ መኮንንየ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
14.ኮ/ልወ/ጊዮርጊስ ተክላይየ22ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
15.ኮ/ልዘነበ ክፍሌየ31ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
16.ኮ/ልተክላይ ገ/ጊዮርጊስየ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
17.ኮ/ልገ/እግዚአብሄር ዘሚካኤልየ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
18.ኮ/ልሃጎስ ደስታየ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
19.ኮ/ልይርዳው ገ/መድህንየ2ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥትግሬ
ከፍተኛ የክፍለ ጦር ኃላፊዎች
ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ብ/ጄነራልሲሳይ ውብለኔየ24ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊአማራ
2.ኮ/ልገ/ስላሴ በላይ4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊትግሬ
3.ኮ/ልገ/ጻዲቅ አስረሳሀኝ4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊትግሬ
4.ኮ/ልሰመረ ተክሉየ20ኛ ክ/ጦር ም/ አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊትግሬ
5.ኮ/ልዘነበ ለማየ20ኛ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊአማራ
6.ኮ/ልዋቆ አህመድየ20ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊኦሮሞ
7.ኮ/ልአብዱራሂም እንዲሪስየ20ኛ ክ/ጦር የሰው ሃብት ቡድን መሪኦሮሞ
8.ኮ/ልመብራቱ ሃይለየ21ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊትግሬ
9.ኮ/ልሻምበል ፈረደ21ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊአማራ
10.ኮ/ልህንጻ ገ/እግዚአብሄርየ21ኛ ክ/ጦር የስልጠና ኃላፊትግሬ
11.ኮ/ልካልዩ ሃብቴየ22ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊትግሬ
12.ኮ/ልአሰፋ ይርጋየ31ኛ አደዋ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊአማራ
13.ኮ/ልንጉሴ ወልዱየ33ኛ ክ/ጦር የሎጀስቲክ አቅርቦትና ስርጭት ኃላፊትግሬ
14.ኮ/ልፍቃዱ ጸጋዬየ33ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና ለአስተዳረንና ፋይናንስኦሮሞ
15.ኮ/ልምሳሁ ገብረተክሌየ12ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
16.ኮ/ልገ/ሚካኤል ግርማይየ12ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊትግሬ
17.ኮ/ልተሾመ ሽፈራውየ12ኛ ክ/ጦር ህብረት ዘመቻ ኃላፊአማራ
18.ኮ/ልተክለብርሃን አለማየሁየ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
19.ኮ/ልበላቸው ገዳየ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊኦሮሞ
20.ኮ/ልመሃመድ ጀመላዲንየ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የስራ መሃንዲስ ኃላፊኦሮሞ
21.ኮ/ልዘውዱ ጎሹየ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊትግሬ
22.ኮ/ልድጋፌ እጅጉየ24ኛ ክ/ጦር የመሃንዲስ ኃላፊአማራ
23.ኮ/ልምሩጽ ወ/ሚካኤልየ24ኛ ክ/ጦር ኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊትግሬ
24.ኮ/ልታደሰ በርሄየ24ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
25.ኮ/ልኑሩ ይዘይን ሁሴንየ13ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊኦሮሞ
26.ኮ/ልመኮንን ወልደስላሴየ13ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
27.ኮ/ልተስፋዬ ሃይለየ13ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊትግሬ
28.ኮ/ልመሃሪ በየነየ32ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
29.ኮ/ልገ/ሊባኖስ ገ/ጊዮርጊስ25ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
30.ኮ/ልመኮንን በንቲ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊኦሮሞ
31.ኮ/ልክብረአብ ገብረዋህድየ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊትግሬ
32.ኮ/ልግርማ ክበበውየ6ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊአማራ
33.ኮ/ልኪዱ ተክለየ11ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
34.ኮ/ልትእዛዙ ወንድሜነህየ11ኛ ክ/ጦር ም/ል አዛዥና የሰው ሃብት ልማት ኃላፊአማራ
የትምህርትና ስልጠና ተቋማት አዛዦች
ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ሜ/ጄነራልሃለፎም እጅጉየመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንትትግሬ
2.ሜ/ጄነራልይመር መኮንን አሊየህብረት ወታደራዊ ስታፍ ኮሌጅ አዛዥአማራ
3.ብ/ጄነራልኩመራ ነገሪየሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥኦሮሞ
4.ብ/ጄነራልገ/እግዚአብሄር በየነየብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥትግሬ
5.ብ/ጄነራልሙዘይ መኮንንአዋሽ 40 የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ዋና አዛዥትግሬ
6.ብ/ጄነራልመሸሻ ገ/ሚካኤልየመከላከያ የአዛዥነት መምሪያና የስታፍ መኮንኖች ኮሌጅ አዛዥትግሬ
7.ብ/ጄነራልሰለሞን ኢተፋአዋሽ 7 ጥምር ጦር አካዳሚ ዋና አዛዥኦሮሞ
8.ብ/ጄነራልጀማል መሃመድበሰሜን እዝ የብ/ ጄነራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥትግሬ
9.ኮ/ልብርሃኑ በቀለየመከላከያ የአዛዥነት መምሪያና የስታፍ መኮንኖች ኮሌጅ ም/ል አዛዥኦሮሞ
10.ኮ/ልብርሃነ ተክሌየሜ/ጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥትግሬ
11.ኮ/ልመንግስቱ ተክሉየጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥትግሬ
12.ኮ/ልአደም ትኩየተዋጊ መሃንዲስ ክ/ጦር ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥትግሬ
13.ኮ/ልጎይቶም ፋሩስሜ/ጄነራል ሃየሎም አርያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥትግሬ
14.ኮ/ልመረሳ በርሄሜ/ጄነራል ሃየሎም አርያ ወታደራዊ አካዳሚ የአጭር ኮርስ ስልጠና አዛዥትግሬ
15.ኮ/ልገ/መድህን ተስፋዬሜ/ጄነራል ሃየሎም አርያ ወታደራዊ አካዳሚትግሬ
16.ኮ/ልነጋሲ ጎይቶምአዋሽ 40 የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ም/ል አዛዥትግሬ
17.ኮ/ልበርሄ ኪዳኔየምዕራብ እዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥትግሬ
18.ኮ/ልንጉሴ ሃይሌየምዕራብ እዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥና ለስልጠናትግሬ
19.ኮ/ልዮሃንስ ካህሳይየብላቴ ልዩ ሃይሎች ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥትግሬ
20.ኮ/ልደስታ ሃጎስየልዩ ሃይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥትግሬ
21.ኮ/ልተሾመ ይመርበሰሜን እዝ የብ/ ጄነራል በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛማዕከል ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊአማራ
22.ኮ/ልከበደ ፍቃዱበማዕከላዊ እዝ የፋና ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥትግሬ
23.ኮ/ልገ/እግዚአብሄር ገ/ሰላማበማዕከላዊ እዝ የፋና ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽናል ኃላፊትግሬ
24.ኮ/ልዳኜ በላይየብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊአማራ
25.ኮ/ልጌታሁን ካህሳዬየብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊትግሬ
26.ኮ/ልግርማይ ገ/ጨርቆስየብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊትግሬ
27.ኮ/ልሃይሌ ተስፋዬበደቡብ ምስራቅ እዝ የ38ኛ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥትግሬ
28.ኮ/ልሙሉጌታ ምንይሉበደቡብ ምስራቅ እዝ የ38ኛ ማሰልጠኛ ማዕከል ም/ል አዛዥኦሮሞ
29.ኮ/ልሃጎስ ብርሃነየመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አዛዥትግሬ
30.ኮ/ልሃድጋይ አያሌውየመከላከያ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና አዛዥትግሬ
የአየር ኃይል አዛዦችና ኃላፊዎች
ተ.ቁማዕረግስምየኃላፊነት ቦታብሄር
1.ሌ/ ጄነራልአደም መሃመድ (ኤፍሬም)የአየር ኃይል ዋና አዛዥአማራ
2.ሜ/ ጄነራልአቤል አየለየአየር ኃይል ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊጎፋ
3.ብ/ ጄነራልማዕሾ ሃጎስየአየር ኃይል ም/ል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊትግሬ
4.ብ/ ጄነራልአሰፋ ገብሩየአየር ኃይል ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊትግሬ
5.ብ/ ጄነራልይልማ መርዳሳምዕራብ አየር ምድብ ዋና አዛዥኦሮሞ
6.ኮ/ልሃይሌ ለምለምሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥትግሬ
7.ኮ/ልአበበ ተካምስራቅ የአየር ምድብ ዋና አዛዥትግሬ
8.ኮ/ልሰለሞን ገ/ስላሴማዕከላዊ አየር ምድብ ዋና አዛዥትግሬ
9.ኮ/ልሃይለስላሴ ጸጋይማዕከላዊ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
10.ኮ/ልአስናቀ ብርሃኑማዕከላዊ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊአማራ
11.ኮ/ልመኮንን ብስራትማዕከላዊ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የዘመቻ ኃላፊአማራ
12.ኮ/ልንጉሴ አበራሰሜን አየር ምድብ አቪዬሽን ጥገና ኃላፊአማራ
13.ኮ/ልወርቃለማው አኔቶሰሜን አየር ምድብ ሴፍቲና ኢንስፔክሽን ኃላፊሃዲያ
14.ኮ/ልመንግስቱ ሃድጉሰሜን አየር ምድብ ኢንዶክትሪኒሽን ኃላፊትግሬ
15.ኮ/ልይታያል ገላውየሰሜን አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የዘመቻ ኃላፊአማራ
16.ኮ/ልአድነው እሸቱየሰሜን አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የሎጀስቲክ ኃላፊኦሮሞ
17.ኮ/ልጸጋይ ካህሳይየሰሜን አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
18.ኮ/ልኪዱ ገ/ስላሴምዕራብ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
19.ኮ/ልሙሉ ገብረየምስራቅ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የዘመቻ ኃላፊትግሬ
20.ኮ/ልየአብዬ አብረሃየምስራቅ አየር ምድብ ም/ል አዛዥና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊትግሬ
21.ኮ/ልአለማየሁ ጌታቸውየአየር ኃይል ዘመቻ ስልጠናና ዕቅድ መምሪያ ኃላፊኦሮሞ
22.ኮ/ልሃጎስ ገ/እግዚአብሄርየአየር ኃይል የመረጃ መምሪያ ኃላፊትግሬ
23.ኮ/ልማሞ ወርቁየአየር ኃይል ዘመቻ ስልጠና ኃላፊአማራ
24.ኮ/ልአረጋዊ ባህረየአየር ኃይል የዘመቻ እቅድ ኃላፊትግሬ
25.ኮ/ልጌታቸው ካህሳይየአየር ኃይል የአየር መከላከያ ማስተባበሪያ ኃላፊትግሬ
26.ኮ/ልደሳለኝ አበበየአየር ኃይል የውጊያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊትግሬ
27.ኮ/ልብርሃኔ አበራየአየር ኃይል ኢንዶክትሪኒሽን አስተዳደር ኃላፊትግሬ
28.ኮ/ልሃይሉ ገብረየሱስየአየር ኃይል የሲግናል ሬጅመንት አዛዥትግሬ
29.ኮ/ልሃይሉ ደስታየአየር ኃይል ተሸከርካሪ ጥገና መምሪያ ሀላፊትግሬ
30.ኮ/ልረታ ተ/ማሪያምየአየር ኃይል አሙኒሽን ኃላፊአማራ
31.ኮ/ልወልደስላሴ ስባጋድስየአየር ኃይል ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊትግሬ
32.ኮ/ልግርማይ ደሳለኝየአየር ኃይል የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክተርትግሬ
33.ኮ/ልኢሳያስ ሞገስየአየር ኃይል ወታደራዊ መደብሮች መዝናኛ ክበብ ኃላፊትግሬ
34.ኮ/ልሲሳይ ታደሰየአየር ኃይል የሰው ኃብት አመራር መምሪያ ኃላፊትግሬ
35.ኮ/ልነገራ ሌሊሳየአየር ኃይል አቭዬሽን ጥገና መምሪያ ኃላፊኦሮሞ
36.ኮ/ልታደሰ ይመርየአየር ኃይል ወታደራዊ ፅንሰሃሳብና ቴክኖሎጂ ጥናት ኃላፊትግሬ
37.ኮ/ልሃጎስ ግደይአየር ኃይል አዛዥ ፅ/ቤት ኃላፊትግሬ
38.ኮ/ልጠቅለው ክብረትየአየር ኃይል ኢንዶክትሪኔሽንና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊአማራ
39.ኮ/ልካልአዩ ዘምቸልየአየር ኃይል የጤና ማበልፀጊያና በሽታ መከላከል ኃላፊትግሬ
40.ኮ/ልዜናዊ ይብራህየአየር ኃይል ህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርትግሬ
41.ኮ/ልሙሉጌታ ወ/ሩፋኤልአየር ኃይል ቴክኒክ ኮሌጅ አዛዥትግሬ
42.ኮ/ልካህሳይ በየነየአየር ኃይል ሙዚቃ ሲኒማና ቲያትር አስተዳደር ኃላፊትግሬ
43.ኮ/ልኢሳያስ አሰፋየአየር ኃይል ጤና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተርአማራ
44.ኮ/ልታደሰ ካህሳይየአየር ኃይል በረራ ሴፍቲ ኃላፊትግሬ
45.ኮ/ልአበራ አጭቆየአየር ኃይል ኦዲት ፅ/ቤት ማስተባበሪያ ኃላፊከምባታ

No comments:

Post a Comment