Wednesday, August 31, 2016

ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው የብሄር ፌዴራሊዝም ከፍተኛ ፈተና ተጋርጦበታል ተባለ ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008)



በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ግንባር ቀደምትነት በኢትዮጵያ በስራ ላይ እየተተገበረ ያለው ያለው ፌዴራሊዝም፣ አዋጪነቱ በምዕራብያውያን ዲፕሎማቶችና የፖለቲካ ተንታኞችን አጠያያቂ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ። 
ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው ፌዴራሊም በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ እንዲውል ያደረገው፣ አገራዊ አጀንዳ ያላቸው ድርጅቶች እንዳያንሰራሩ ለመደፍጠጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በቀጣይ ሊቀሰቀሱ የሚችሉ ብሄር ተኮር ተቃውሞዎችን ከፋፍሎ ለመምታት ታስቦ እንደሆነ ፎሪይን አፌይስ ትናንት ባወጣው ዘገባ አስረድቷል። ድርጊቱ ለተወሰኑ አመታት ተግባራዊ ሆኖ አዋጪ መስሎ የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን ኢትዮጵያን ወደ ውድቀት ጎዳና እየመራት እንደሆነ በድረገጹ ላይ የወጣው ትንታኔ ያስረዳል። 

ዐማራ ዛሬ (ነሃሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም) Muluken Tesfaw #AmharaResistance


አገዛዙ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ ጦርነት አውጇል፤ በባሕር ዳር የሰባታሚት ማረሚያ ቤት ዐማሮች በጅምላ ተቀብረዋል
• የአብራጂራ ሕዝብ የመከላከያ ታንክ ላይ ሰንደቅ ዓላማ ተከለ 
• የዐማራ ተጋድሎ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ሒዷል፤ የጋይንት፣ የቋሪትና ግምጃ ቤት አካባቢዎች ከጠላት ቀጣና የጸዱ ናቸው 
• የትግሬ መከላከያ ሠራዊት በወገራ አውራጃ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል
• የደባርቅ፣ የመተማ፣ ሸኽዲና ሽንፋ ከተሞች በቃጠሎ ታፍነው ውለዋል
• በቡሬ ትንሳኤ ሆቴል ግቢ 2 አስከሬን ተደብቆ ተገኘ
• በወንበርማ ሽንዲ ወረዳ የዐማራ ተጋድሎ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል
• በእጅባራ ሕዝብና መከላከያ ተፋጠዋል
ባሕር ዳር
ከወደ ባሕር ዳር ያገኘነው መረጃ አስደንጋጭ ነው፡፡ የትግራይ መንግሥት የጅምላ ጭፍጨፋ በዐማራው ሕዝብ ላይ በይፋ ማወጁን ተከትሎ ትናንት ብዙ ቁጥር ያላቸው ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡ የባሕር ዳር፣ ጢስ ዓባይ፣ መሸንቲና መራዊ ከተሞች ከፍተኛ እልቂት ከደረሰባቸው ቀዳሚዎቹ ሆናዋል፡፡ 
ትናንት በነበረው የዐማራ ተጋድሎ የሰባታሚትና የጢስ ዓባይ ገበሬዎች በገፍ ታፍነው ታስረው የነበሩ ወጣቶችን ማስለቀቃቸው የታወቀ ቢሆንም ቁጥራቸው ያልታወቁ ወጣቶችን ግን ከማምለጣቸው በፊት በጥይት ተጨፍጭፈዋል፡፡ አንድም የተገደለ ዐማራ አስከሬን ወደ ሆስፒታል ያልተወሰደ ሲሆን የሟቾች ቁጥር አገዛዙን ያሳጣል በሚል የትግሬ መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ በጅምላ በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ መቅበራቸውን ነው የዐይን ምስክሮች የገለጹት፡፡ ትናንት ከተሰውት ዐማሮች የሁለት የጢስ ዓባይና የሰባታሚት ገበሬዎች አስከሬን ብቻ ነው የወጣው ተብሏል፡፡ የሁለቱን አስከሬን ለማውጣት የገቡ የዓይን እማኞች እንደሚሉት በጣም ብዛት ያላቸው ዐማሮች አስከሬን መመልከታቸውን እና ሁሉም እዚያ ግቢ እንደተቀበሩም እንደሚያውቁ አክለው ተናግረዋል፡፡ የፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የሚሠሩ ባለሙያዎችን የተባለውን ያክል አስከሬን በእነርሱ በኩል ማለፍ አለማለፉን የጠየቅን ሲሆን አሁን አሁን የተገደለውን ሰው ሁሉ ወደ እኛ ሳያመጡ ማፈን የተለመደ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ 

በአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ገበሬዎች የአጋዚ ወታደሮች ጋር እየተጋፈጡ ነው ኢሳት ( ነሃሴ 25 ፥ 2008)



በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና ምስራቅ ጎጃም የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ ወደሌሎች ዞኖች እየገሰገሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት መደበኛ ጦር በማንቀሳቀስ ተቃውሞን ለማፈን እየሞከረ መሆኑ ተነገረ። 
በአማራ ክልል የሚገኘው ህዝብ ተቃውሞውን በቤት ውስጥ አድማ በማድረግ የትግል ስልቱን መቀየሩና ሌሎች አካባቢዎችም እንደሁኔታው የትግል ስልታቸው እየቀያየሩ እንዲታገሉ ጥሪ ቀርቧል። 
ከሁለት ሺ በላይ መደበኛ ጦር በአማራ ክልል ያሰማራው ህወሃት የሚመራው መንግስት፣ ህዝባዊ ተቃውሞን ለማዳከምና ብሎም ለማስቆም በወሎ በኩል ብዛት ያለው ጦር ወደ አማራ ክልል በኩል ለማስገባት የሞከረ ሲሆን፣ ይህ ጦር ወደ ጎንደር እና ጎጃም እንዳያልፍ (እንዳይገባ) የጋይንት ህዝብ ድልድዩን በመስበሩ ጨጨሆ አካባቢ ጉዞው ተሰናክሎ እንዲቆም ተደርጓል።
ከህውአት ቢሮ የወጣ መረጃ በውስጥ መስመር ደርሶናል።
የቀድሞው የህውአት አባልና አዳዲሶቹ የህውአት አባሎች በዝግ ስብሰባ ተጠምደዋል። በስብሰባውም ብዙ የተከራከሩበትና ያልተስማሙበትን ውሳኔ በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አሳልፈዋል።
#በአማራ ክልል
የአማራ ክልል እንቅስቃሴ በጣም ጠንካራ እና ከባድ እንቅስቃሴ እና አስጊ ናቸው ብለው ስጋታቸውን እና ፍራቻቸውን አስቀምጠዋል። የአማራው ህዝብ የሚወሰዱት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በሚኖሩት አባሎች ላይ ከፍተኛ ፍራቻ እና ጉዳት እያስከተለ ነው። ይህ በእንድህ ከቀጠለ በአማራ ክልል የሚኖሩትን አባሎቻችን *ሰላዮች * ካጣን መረጃዎቻችን ማግኘት ስለማንችል ህውአት የሚባለው በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን አጣ ማለት ነው። ትግሉ በዚህ ከቀጠለ ለኛ የሞት ሞት ነው በማለት በአማራው ክልል የሚደረገው እንቅስቃሴ ባለ በሌለ ሃይላችን ከአማራ ክልል መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቀብለን በሃይል ማንበርከክ እና የተቃጣብንን አደጋ መቀልበስ አለብን በማለት ውሳኔ አስተላልፈዋል።
በሌላ ጎኑ በአማራ ህዝብ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍለንና መቀልበሻው ሊያጥረን የሚችልበት እንዳይሆን ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ጦሩነቱን በግልጽ በአማራው ላይ ካወጅነው ህዝብ በአንድነት እንዲነሳብን ማድረግ ይሆንብናል በተጨማሪም ብዙ ደም ከተፋሰሰ በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ እና መጨረሻ የሌለው አደጋ መጋበዝ ይሆንብናል በማለት ያላቸውን ፍራቻ ተንጸባርቋል። በሁሉም ክልል በሚኖሩት የትግራይ ተወላጅ ላይ የሚያመጣው አደጋ እና ተጽዕኖ ቀላል አይደለም እንደውም የመጥፋት አደጋ በራሳችን ማህበረሰብ ላይ ማወጅ እንዳይሆንብን በማለት ስጋታቸውን በስብሰባው ተነስታል።
የሆነው ሆኖ ከ95% በላይ የህውአት አባሎች በኃይል የሚወስደው እርምጃ ላይ ተስማምቶ ከዛ በኋላ የሚመጣውን ነገር አብረን እናየዋለን የሚል አቃም በመያዝ ወደ ተግባር እንዲለወጥ መወሰድ ያለባቸው ቅድሚያ ዝግጅት ይወሰድ ብለዋል። የትግራይ ወጣቶችንም እንዲዘጋጅ ጥሪ ማድረግ እንዳለባቸውም ወስነዋል።

ከህውአት ቢሮ የወጣ መረጃ በውስጥ መስመር ደርሶናል፡


የቀድሞው የህውአት አባል አዳዲሶቹ የህውአት አባሎች በዝግ ስብሰባ ተጠምደዋል፡ በስብሰባውም ብዙ የተከራከሩበትና ያልተስማሙበትን ውሳኔ በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አሳልፈዋል፡
በአማራ ክልል፡
የአማራ ክልል እንቅስቃሴ በጣም ጠንካራ እና ከባድ እንቅስቃሴ ናቸው፡ የሚወስዱት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በሚኖሩት አባሎች ላይ ከፍተኛ ፍራቻ እና ጉዳት እያስከተለ ነው፡ ይህ በእንድህ ከቀጠለ በአማራ ክልል የሚኖሩትን አባሎቻችን *ሰላዮች * ካጣን መረጃዎቻችን ማግኘት ስለማንችል ህውአት የሚባለው በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን አጣ ማለት ነው፡ ያኔ ለኛ የሞት ሞት ነው፡ በማለት በአማራው ክልል የሚደረገው እንቅስቃሴ ባለ በሌለ ሃይላችን ከአማራ ክልል መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቀብለን በሃይል ማንበርከክ እና የተቃጣብንን አደጋ መቀልበስ አለብን ብለዋል ፡
በሌላ ጎኑ ደግሞ ይሄ እርምጃ በጣም ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍለንና መቀልበሻው ሊያጥረን የሚችልበት እንዳይሆን ጦሩነቱን በግልጽ ካወጅነው ህዝብ በአንድነት ከተነሳብን እና ብዙ ደም ከተፋሰሰ በሃላ ከዛ በሃላ ይሄ ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ አደጋ መጋበዝ ነው፡ በሁሉም ክልል የሚኖሩት ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ቀላል አይደለም የሚሊም በስብሰባው ተነስታል።
የሆነው ሆኖ ከ95% በላይ የህውአት አባሎች በሃይል የሚወስደው እርምጃ ተስማምቶ ከዛ በኋላ የሚመጣውን ነገር አብረን እናየዋለን የሚል አቃም በመያዝ ተስማምተው ወደ ተግባር እንዲለወጥ መወሰድ ያለባቸው ቅድሚያ ዝግጅት ይወሰድ ብለዋል።
በኦሮሚያ የኦሮሚያ ጉዳይ ብዙም አያሰጋም የሚፈልጉትን ነገር ከሰጠናቸው ዝም ሊሉ ይችላሉ በዚህ ሰዓት የኦሮሞን ጉዳይ እንዲቀጣጠል ማድረግ የለብንም የጠየቁትን በሙሉ መንግስታችን እንደሚፈጽምላቸው በመናገር ማዘግየት እና ማራጋጋት አለብን ነገሮች ክተረጋጉ በሃላ መልሰን እቅዳችንን ወደምናሳካበት እና በእንቅስቃሴ ውስጥ ንኪኪ ያላቸውን በሙሉ ለቅመን ዋጋቸውን እንሰጣችቸዋለን በማለት ዘግተዋል።
ሌላው በጣም የተከራከሩበትና ያጣላቸው ጉዳይ በንብረት ሃብት ጉዳይ ነው፡
አማራ እና ኦሮሚያ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ የተደናገጡት የህውአት ቢሊዬነሮች አባላት በኦሮሚያና በአማራ ሲዘርፉት የነበሩት ሃብት ስለተቋረጠባቸው ይሄ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ወደ ፊት ሊኖረን የሚችለው ድረስ እንዴት ነው ምክንያቱም በከፍተኛ ሁኔታ ሃብት የምንሰበስብባቸው አካባቢዎችን ካጣን ወደ አንድ መንደር ልንገባ ነው በዚህ አግባብ ደግሞ የምንፈልገውን እና ሁላችንንም እንደፈለገ ሊያንቀሳቅሰን የሚችል ሃብት የለም ለተተከሉትም ማሽነሪዎችንም ጥሬ ዕቃ አቅርቦት የለም ሁሉም ህዝባችን ወደዚህ አካባቢ የመሰባሰቡ ግዳጅ ከመጣብን ከፍተኛ የሆነ የእህል አቅርቦትም ያጥረናል እና ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንገባለን በዛ ሰዓት ምን አይነት እርምጃ ነው መውሰድ ያለብን የተሰበሰበው ሃብትስ እንዴት ነው የምንከፋፈለው በማለት ጠንካራ ክርክር የተነሳበት ነበር በዚህ ላይ ሁሉም የህውአት አባል የተለያየ ሃሳብና አቋም በመያዝ ተፈረካክሰዋል ጸብ ቀረሽ ንግግር ሲያደርጉም ተስተውለዋል በመላው ኢትዮጵያ የተሰገሰገው የህውአት ሃብት ምዝበራ ወደ ትግራይ ሲገቡ የሚመዘብሩት ስለሌለ ያለንን በምን መልኩ እንካፈል በሚል በመለያየታቸው አንዱ አንዱን በጠላትነት እንዲተያዩ አድርጓል ።
በስተመጨረሻ ግን አሁን መጀመሪያ እድል ስላለን እንደዚህ ሰጣ ገባ ውስጥ መግባት የለብንም ሙሉውን የትግራይ ወጣት በመቀስቀስ የተቃጣብንን አደጋ መወጣት የምንችልበትን ስራ መስራት አለብን በሚለው ያልተስማሙበትና የተለያዩበትን ስብሰባ ዘግቷል።
የግሌ ሃሳብ፡
ኢትዮጵያኖች ከመቸውም ግዜ በላይ በህውአት ሞት ተደግሶልናል፡
በጣም የገረመኝና የደነቀኝ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርጉት ንቀትና በአማራው ህዝብ ላይ ለመጨፍጨፍ የተነሱበት አላማ ነው፡ የኦሮሞም ሆነ የአማራ ህዝብ ብሎም ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ከናንተ አስተሳሰብ እና ከፋፍለህ ዝረፍ፦ ከፋፍለህ ግደል ፦ከፋፍለህ ግዛ፦ ዕቅዳችሁን ካወቀ በጣም ቆይቷል፡ የኦሮሞ ጥያቄ የአማራም ብሎም የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው። የሁላችንም የኢትዮጵያ ጥያቄ ደግሞ ወያኔ በቃን ከእንግዲህ በሃላ ህዝብንና ህዝብን አጣልተህ እና አናክሰህ መኖር አትችልም ስልጣኑን ለህዝብ በቃን ወያኔ ከአሁን በኋላ አይገዛንም እያለ ነው፡ እንጅ የህዝብን ጥያቄ መመለስ መቻል አይደለም ሞራሉም እንደሌለህ ለመናገር እወዳለሁ፡ ከእንግድህ በኋላ በወያኔ ሃሳብ ተስማምቶ ወደ ሞት የሚነዳ ኢትዮጵያዊ የለም።
ስማ፦ ስማ፦ ስማ ፦የሰማ ላልሰማ ያሰማ !!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !1
ሞት ለገዳይ ወያኔ !!
ከመርጋ ደጀኔ

ሰበር ዜና የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••


የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና ከፍተኛ የህወሓት ሹማምንቶች እምነት የሚጣልባቸው የፓርቲው ወጣት አባላትን ስብስበው ጠንካራ ትእዛዝ አስተላለፉ::
"በእናቶቾቻችሁ፥ በአባቶቻችሁ፥ በእህት፥ ወንድሞቻችሁ ደምና አጥንት ማንነታቸሁ ተከብሯል:: ደርግ ወንበዴ እያለ ሲጨፈጭፈን መስዋዕትነት ከፍለን በሰላም የምትኖሩበት፥ የምትማሩበት፥ የምትሰሩበት እና በክብር ወጥታችሁ የምትገቡበት ናጽነት አግኝተናል::
አሁን ግን የጥፋት ኃይሎች በሻእቢያ እና ግብጽ በመታገዝ ደርግን መልሰው ሊያመጡብን ትግራዋይ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጀዋል:: ስለዚህ ይህን የመመከት ኃላፊነት በእናንተ ወጣቶች ላይ ተጥሏል::
ወላጆቻችሁ ትምክህተኞችን ጠባቦችን ደምስሰው በኢትዮጵያ ሰላም ልማት እና ዲሞክራሲ አንዳሰፈኑት ሁሉ እናንተም አኩሪውን ታሪክ የመድገም ግዴታ አለባችሁ:: አለበለዚያ የተጋሩ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል ብሎም ከላይ የሻእቢያ ከታች የትምክህተኞች ጥቃት መፈንጫ ሆኖ እንደ ሕዝብ የመቀጠል እድል የማይታሰብ ይሆናል:: በተለይ በ አሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ሁከት በተጋሩ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ይህንኑ ያመላክታል::
ይህን አውቃችሁ ህወሓትንም ትግራይንም ከጥፋት በማዳን የተጋሩን ቀጣይነት አረጋገጡ:: ባለራዕዩ መሪያችን መለስ ዜናዊ የጣለብንን አደራ እንወጣ::በእናንተ ፍጹም እምነት አለን::"

በትላንትናው ዕለት ገዢው ስርዓት በግልጽ አማራ ክልል በወታደራዊ እዝ ስር እንደሚሆን በመግለፅ በከባድ መሳሪያ የታገዘ መከላከያ ሰራዊት ወደስፍራው አሰማርቷል ::
ኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ክፍሉ በህወሓት ሰራዊት የታጠረ መሆኑ ይታወቃል::
የህወሓት ትእዛዝ ፈጻሚ የሆነው ብአዴን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አያፈነገጠ በመምጣቱ እና ሕዝባዊ ንቅናቄው ላይ የሚጠበቀውን የኃይል እርምጃ ባለመወሰዱ በኦህዴድ አመራሮች ላይ እንደደረሰው የመባረር እጣ የሚገጥማቸው ባለስልጣናት ይኖራሉ:: በተጨማሪ የብአዴን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ በህወሀት ቁጥጥር ስር ይሆናል::

Fasil Demoz - 25 Amet | New Ethiopian Music 2016

Ethiopian regime deploying massive military to the Amhara region as uprising continue unabated By Engidu Woldie ESAT News (August 31, 2016)


Reports reaching ESAT from Ethiopia say the TPLF regime is deploying thousands of its troops and Agazi Special Forces to the Amhara region where uprising against the regime is gaining momentum as more towns and localities removed local administrations and the security, and replaced them with interim administrations elected by the people.
Thousands of troops in a dozens of convoys and heavy machinery were seen heading towards northern Gondar via Wuchale, Wollo as the alternative and direct routes were closed by protesters, according to a sources who spoke to ESAT.

Tuesday, August 30, 2016

የሕወሃት ብጥብጥ እና ሽሽት – ከውስጥ አዋቂ ምንጭ | ከክንፉ አሰፋ

TPLFሕዝባዊ አመጹ ያመጣውን ቀውስ ተከትሎ በህወሃት ከፍተኛ አመራር ውስጥ ከፍተኛ መበጣበጥ እና የርስ-በርስ ፍጥጫ መከሰቱን ከታመነ የውስጥ አዋቂ 
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/65072
ምንጭ መረጃ ደርሶናል። ­­­
“አመራሩ ክፉኛ ከመከፋፈሉ የተነሳም የርስበርሱ ችግራቸው ላይ ተወጥረዋል።” ይላል መረጃው። ቀንደኞቹ የህወሃት አባላት ስርዓቱ እንዳበቃለት ስለተገነዘቡ ንብረት እና ልጆቻቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው።

ሕዝቡ ሁሉ እንደተፋቸው በግልጽ እየነገራቸው ስለተገነዘቡ፤ የህወሃት የደህንነት አባላት ሕዝቡን ተተው የራሳቸውን ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሰልሉ ተነግሯቸዋል። “ተጠርጣሪ” የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በነዚህ ሰላዮች ስለተከበቡ በፍርሃት መወጠራቸውን ከራሳቸው አንደበት እየተሰማ ነው።
የርስበርስ ው

አንድ የቀድሞ ከፍተኛ የአጋዚ ክ/ጦር አዛዥ፣ ጦሩ አፈሙዙን ወደ አዛዦቹ እንዲያዞር ጠየቁ ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008)


በአማራና በኦሮሚያ ክልል በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት በመንግስት የግድያ ትዕዛዝ የተሰጠው የአጋዚ ጦር ወደ ህዝቡ እንዳይተኩስ እና መሳሪያውን ወደ አዛዦቹ እንዲያዞር አንድ የቀድሞ ከፍተኛ የአጋዚ ክ/ጦር አዛዥ ጠየቁ። 
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ መንግስት ያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎች ህዝቡን በመግደል ላይ መሆናቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ለኢሳት የገለጹት የቀድሞ አጋዚ ክ/ጦር መስራችና አመራር ኮሎኔል አለበል አማረ፣ የክ/ጦሩ አባላት ከህዝቡ ጋር በመወገን ታሪክ የመስሪያው ጊዜ አሁን መሆኑን ተናግረዋል። 

በውስጥ መስመር የደረሰን መረጃ፡ ጎንደር፡


ጎንደር ሙሉውን ከወያኔ ነብሰ በላ ጋር እየተናነቅን እንገኛለን መውጫ መግቢያ መንገድ በሙሉ በህዝባችን እየተዘጋ ነው፡ ትግሉም ከፍ ወደ አለ ደረጃ በማድረስ አጋዚዎችን እየደመሰሰ ህዝቡ የአጋዚን መሳሪያ እየታጠቀ ይገኛል ጎንደር የገባ አጋዚ ወታደር መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶት በየቦታው እየተበተነ ይገኛል፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ህዝቡ እየተቀላቀለ ይገኛል፡ ጎንደር ገበሬውን በሙሉ መሳሪያውን ታጥቆ በየተራራው ላይ በመሰባሰብ ነቅቶ እየጠበቀ ነው፡ ትግሉ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሆኗል ወይ ወያኔ ወይም ደግሞ እኛ እንኖራለን በማለት ከፍተኛ ፍልምያ ውስጥ ነው፡ በጣም ብዙ የአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል በጣም ብዙ ቆስለዋል የጎንደር ህዝብ ታጣቂው የጎንደር ገበሬ በአድነት የነጻነት ትግል እያደርግን ነው፡ ከአጋዚ የተማረኩ መሳሪያዎች ህዝብ እየታጠቀ ወደ ትግሉ ጎራ በቁርጠኝነት እየገባ ነው፡ በጎንደር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎች በሙሉ እየተለያዩ የወያኔ መገልገያ እና የወያኔ ሰራዊት የሚያገለግሉት ላይ ህዝባችን እርምጃ እየወሰደባቸው ነው፡ ትግሉ የህዝብ ትግል ከሆነ ቆይቷል የታሰሩ ወገኖቻችንን እስር ቤት ታጣቂው እየሰበረ እያስፈታ ይገኛል።
ጎጃም፡

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ በተለይ ለአዲስ አድማስ Written by አለማየሁ አንበሴ

ስለ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና መንስኤያቸው ያብራራሉ 
          ጭቆናን ለማጥፋት የሚደረግ ትግል ኖሮ አያውቅም 
          ህዝብ ቋቱ ሲሞላ ነው አልችልም፤ በቃኝ ያለው 
          አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተናገረው የሚያስደንቅ ነው Bilderesultat for ፕ ር መስፍን ወ ማርያም፤

http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_
   በሦስት መንግስት ውስጥ አልፈዋል - ታዋቂው ምሁርና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፡፡ በአገራቸው ፖለቲካ ውስጥ ዛሬም በሽምግልና ዕድሜያቸው ንቁ ተሳታፊ ናቸው፡፡ በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸውም ይታወቃሉ፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተነሱ ተቃውሞዎችና ግጭቶች፣ በተቃውሞዎቹ መንስኤና ባህሪያት እንዲሁም በመንግስት ምላሽ አሰጣጥና በችግሮቹ መፍትሄ ዙሪያ ሃሳባቸውንና ዕይታቸውን ለአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በቃለ-ምልልስ መልክ አጋርተውታል፡፡ እነሆ፡-

     በእርስዎ ዕይታ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎች መንስኤው ምንድን ነው?
የህዝቡ ጥያቄ 25 ዓመት የፈጀ ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ቡድን በፈለገው መንገድ የህዝቡን ግንኙነት በጎሳ ብቻ እንዲሆን፤ በኑሮውም (በቤት፣ በመሬት፣ በስራ፣ወዘተ---) መቶ በመቶ ቁጥጥር አድርጎ ሰውን ነፃነት የነሳበት፤ ጋዜጣ፣ መፅሄት፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን በአንድ አገዛዝ ስር የወደቀበት ጊዜ ነው ያለፈው፤25 ዓመት፡፡ አሁን ግን እዚህ ላይ ሲደርስ የታመቀው መተንፈሻ ሲያጣ ገንፍሎ ፈነዳ። እየሞቀ … እየሞቀ … እየሞቀ ሲሄድ ድንጋይም ይቀልጣል፡፡ ቀልጦ ቀልጦ ሲሞቅ ይፈነዳል፡፡ እሳተ ገሞራ ሆኖ የሚወጣው የቀለጠው ነው፡፡ አሁን በሀገሪቱ የምናየው ይሄንኑ ነው፡፡ 
ተቃውሞዎቹ የተነሱት በምርጫ ሙሉ በሙሉ ማሸነፉን ባወጀ ማግስት መሆኑ አንደምታው ምንድን ነው? 
ምን ምርጫ አለና! ይሄ መቶ በመቶ አሸንፈናል ያሉበትን ነው የምትለው?
አዎ! የ2007 ምርጫ----
በ“ወያኔ” ዘመን ምርጫ አልነበረም፤ የለም፡፡ ከደርግ ጊዜ የተሻለ አይደለም፡፡ በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ደግሞ ከሁለቱም የተሻለ ነበር፡፡ ፓርቲዎች ባይኖሩም ምርጫው በጣም ጥሩ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምርጫ የሚባል ነገር የለም፤እንዲሁ ለይስሙላ ነው። 
በኦሮሚያ የተቃውሞው መነሻ ማስተር ፕላን ሲሆን  በአማራ ክልል ደግሞ የወልቃይትና የኮሚቴው ጉዳይ ነው፡፡ እርስዎ እውነተኛ ምክንያቶቹ እነዚህ ናቸው ብለው ያምናሉ?
ኦሮሚያ ለተነሳው ተቃውሞ ምክንያቱ ማስተር ፕላን ነው ተባለ… ማስተር ፕላኑ ከዚህ በፊት አልነበረም? አዲስ ነው? ቤቶች ሲፈርሱ አልነበረም? ሰዎች መንገድ ላይ እንዲሁ እንደዋዛ ሲጣሉ አልነበረም? አሁን በቃ ቋቱ ሞላ፤ ይሄ ነው ምክንያቱ። ቋቱ ሲሞላ ህዝብ አልችልም፤ በቃኝ ነው ያለው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ግፍ መቀበል አንችልም ነው፡፡ የወልቃይትም ጉዳይ ቢሆን በተለይ የታሰረው ኮ/ል ደመቀ ጎበዝ ሰው ነው፡፡ እሱ ነው ይሄን ነገር የጫረው፡፡ ግን የወያኔ ኮሎኔል ነው እሡ፡፡ በስርአቱ የነበረ የስርአቱ መሳሪያ ሆኖ የቆየ ሰው ነው፡፡ እንግዲህ ቋቱ ሲሞላ እሱም በቃኝ አለ፤ ሌሎችም በቃን እንዲሉ አደረገ፡፡ እና ምንም አዲስ ነገር የለም። ሁሉም ቋቱ ሲሞላ ነው ወደዚህ ደረጃ የደረሰው፡፡ የማስተር ፕላንና የወልቃይት ጉዳይ ብቻ አይደለም።
አሁን ያለው ተቃውሞና ግጭት ከቀጠለ የአገሪቱ እጣ ፈንታ ምን የሚሆን ይመስልዎታል?
ይሄ የሚያስፈራ ጥያቄ ነው፡፡ “ወያኔ” ተቃዋሚ ድርጅቶች እንዳይዳብሩ እንዳይበረቱ አድርጎ፣ አሁን ተቃዋሚ አለ የማይባልበት ደረጃ ላይ ነው ያለው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በእንደዚህ አይነቱ ጊዜ ድምፃቸው ሊሰማ የሚችል፣ የሚከበሩ የሚደመጡ ሽማግሌዎች  እንዳይኖሩ አድርገዋል፡፡ አሁን ታዲያ ማንን ይስማ? ወያኔ አሁን ቢሰማ፣ የሚሰማው ፈረንጆቹን አሜሪካንን፣ እንግሊዝን ነው፡፡ ቸርችል በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ያለው አንድ ጥሩ አባባል ነበር፡- “let dog eat dog.” (እርስ በርሳቸው ይባሉ ምንም አይደለም) ፈረንጆቹም በተመቻቸው ሁኔታ እንድንሆንላቸው ይፈልጋሉና ምንም አያደርጉም። ስለዚህ አስታራቂ ሊኖር አይችልም፡፡ ወያኔም የሚሰማው ጡንቻው መሳሪያው ብቻ ነው፡፡ ያንን መሳሪያ እስከያዝኩ ድረስ አልሸነፍም በሚለው አስተሳሰቡ ፀንቷል፤ከደርግ አልተማሩም፡፡ ደርግ የትየለሌ መሳሪያ ነበረው፤ህዝብ ግን አልነበረውም። ህዝብ ከሌለ የትም መድረስ አይቻልም፡፡ እነሱም ይሄንን አልተረዱትም፡፡ አሁንም ለእርቅ፣ ለሰላም የተዘጋጁ አይመስለኝም፡፡ እንደ በፊቱ በጡንቻችን ረግጠን እንቀጥላለን፤ብለው ነው የሚያስቡት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ አገዛዙና ህዝቡ ደም ተቃብቷል። ይሄ ወደ ኋላ የሚመለስ አይመስለኝም። እየባሰ እየከረረ የሚሄድ ይመስለኛል፡፡ 
በዚህ መሃል ግን አጠቃላይ የትግራይ ተወላጆች ጉዳይ አለ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተገቢው መንገድ ውይይት እየተደረገ አይደለም፡፡ ልንወያይበት ልንነጋገርበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆች በደቡብ በኩል በጎንደር፣ በወሎ ወንድሞቻቸው ድሮ ችግር ሲመጣ የሚሄዱበትን ቦታ ሁሉ አሁን ጠላት እንዲሆኑ አድርጓል ወያኔ፤ በሰሜን በኩል ያሉ ኤርትራውያን ወንድሞቻቸውን ጠላት አድርጓል። የትግራይ ህዝብ በዚህ መሃከል ነው ያለው፤ እንደ ቡሄ ዳቦ፡፡ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡ 
ለዚህ ችግር መፍትሄው ምንድን ነው ይላሉ?
ህዝቡ ራሱን ሊያወጣ ይችላል፡፡ ህወሓትን በመቃወምና ከሌላው ጋር በአጋርነት በመቆም ከዚህ አጣብቂኝ ራሱን ሊያወጣ ይችላል፡፡ “ትግሬ ህውሓት ነው፤ ህውሓት ትግሬ ነው” የሚባለው ለኔ ትክክል አይደለም፡፡ 
ህዝባዊ ተቃውሞው ባለቤት የለውም፣ እንቅስቃሴዎቹ ጎልቶ የወጣ መሰረታዊ ጥያቄ የላቸውም የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?
እንቅስቃሴው ዋና እምቡጥ የለውም የሚለው ጉዳዩን ካለመገንዘብ የመጣ ነው፡፡ 25 ዓመት ሙሉ ሲጠራቀሙ የመጡ በርካታ ጥያቄዎች ናቸው የእምቡጡ መሰረቶች፡፡ 
በየተቃውሞዎቹ የሚነሱ የማንነትና የብሄር መብት ጥያቄዎችስ አቅጣጫቸው ወዴት ነው?
የማንነት ጥያቄ የተምታታ ነው፡፡ እንኳን በአጠቃላይ በህዝቡ ቀርቶ ተማርን በሚሉት፣ አስተማሪ ነን ምሁራን ነን በሚሉትም ዘንድ ብዙ ውዥንብር አለ፡፡ ኢትዮጵያ መቼም የምታስደንቅ ሀገር ነች፤ በዚህ ውዥንብር፣ ተማርኩ የሚለው ሰው ሁሉ በተወናበደበት ጊዜ ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ የተናገረው ነገር የሚያስደንቅ ነው፡፡ ብዙ ምሁራንን ዜሮ ያደረገ ንግግር ነው የተናገረው፡፡ “እኔ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ነኝ” ነው ያለው፡፡ ሌሎቹ የማይሉትን ነው የተናገረው፡፡ ምሁራ ነን የሚሉት ሁለቱን ማገናኘት አይፈልጉም፡፡ ይሄ አትሌት ግን ድርቅ ያለውን እውነት አውጥቶታል፡፡ ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ የተጋባባት፣ የተዋለደባት ሀገር ነች ኢትዮጵያ፡፡ ብዙዎች ዛሬ አለን የሚሉት ማንነት ሲፋቅ ሌላ ማንነት ይወጣዋል፡፡ 
በብሄር ተቧድኖ የሚቀርቡ ተቃውሞዎችና ጥያቄዎች ሀገሪቱን አደጋ ላይ አይጥሏትም?
አደጋ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ግን እንደ ፈይሳ አይነት ሰዎች በብዛት የሚኖሩ ከሆነ ምንም አይፈጠርም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እውነት የሚገባቸው እንደ ፈይሳ ያሉ ሰዎች ካየሉ ስጋት አይኖርም፡፡ ዘር ከፋፋዮች ከሆነ የሚመሩት የተሰጋው ሊደርስ ይችላል፡፡ እንደኔ ግን 90 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኦሮሞ፣ እንደ ፈይሳ የሚያስብ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እኔ የማገኛቸው ኦሮሞዎች ሁሉ እንደዛ ናቸው፡፡ 
ከ97 ምርጫ በኋላ ያለው የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እንዴት ይገለጻል?
“ወያኔ” ብልሃት ብሎ ሃገር ውስጥ ተቀናቃኝ ቡድኖች እንዳይፈጠሩ እንዳያድጉ አደረገ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ተቃዋሚዎቹን ከሃገር አስወጣቸው። አንዳንዱ ፈርቶ ስደት ወጣ፡፡ ያኔ ኢህአዴግ ይጠቅመኛል ብሎ ያመጣው ብልሃት አሁን የሚጎዳው ነገር ሆኗል። ትልቁ የተቃዋሚ ጎራ ያለው ውጭ ሃገር ነው፡፡ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያ ደቡብ አፍሪካ ነው የተቃውሞው መቀመጫ፡፡ ተቃውሞው በጣም ከመጠንከሩ የተነሣ አሁን እነሱም ወደ ውጭ ሃገር ሄደው መስራት አልቻሉም፡፡ እዚያም ተቃውሞ ይገጥማቸዋል። የበለጠ ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ተቃውሞ ነው ከውጭ ሃገር እየገጠማቸው ያለው። እዚህ ሊቆጣጠሩት ይችሉ የነበረውን ተቃውሞ ገደልን ብለው ወደ ውጪ እንዲሄድ አደረጉት። ወደ ውጭ የገፉት ተቃውሞ ደግሞ ጊዜውን ጠብቆ እነሱኑ ሽባ አደረጋቸው፡፡ ሆቴል እየተከተሉ ማዋረድ ሆነ ነገሩ። ‹‹ተንጋሎ የተፋው ለራሱ ከረፋው›› አይነት ነገር ነው የሆነው፡፡ የተፉት መልሶ መጣባቸው፡፡ አሁን ያንን ሊያቆሙት አይችሉም። እነሱ ካልተለወጡ ያኛው እየተባባሠ ይሄዳል እንጂ በምንም መንገድ አይለወጥም፡፡ ሊደርሱበት ሊቆጣጠሩት አይችሉም። 
በአገር ውስጥ ያለው የተቃውሞ እንቅስቃሴስ?
አገር ውስጥ ስላሉ የፖለቲካ ቡድኖች ምንም የምናገረው ነገር የለም፡፡ ማን አለና ነው የምናገረው? ማንም የለም፡፡ ሠማያዊም ሌላውም የሉም፤ የሚረቡ አይደሉም፡፡ አላማቸውም ሌላ ነው፡፡ 
በሦስት ስርዓቶች ውስጥ ያሣለፉ እንደመሆንዎ ተቃውሞዎች በንጉሡ፣ በደርግና በኢህአዴግ መንግስታት ያላቸው አንድነትና ልዩነት እንዴት ይገለጻል?
በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ህዝቡ አልተንቀሳቀሰም። ተቃዋሚ የሚባለው ተማሪውና አስተማሪው ነበር፡፡ እሱም በአብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ ህዝቡ ግን አብዛኛው የአፄ ኃይለስላሴ ደጋፊ ነበር፡፡ ግፉንም በደሉንም አልተረዳም ወይም የበደሉ አካል ነበር ማለት ይቻላል። ጭቆና፤ ጨቋኝና ተጨቋኝ በሚል ርዕስ በመፅሃፌ ገልጨዋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጭቆናን ለማጥፋት የሚፈልግ የለም፤ትግሉ ሁሉ ተጨቋኙ ጨቋኝ ለመሆን ነው፡፡ ጨቋኙ ደግሞ ጨቋኝ መሆኔን አልለቅም እያለ ጨቋኝ ለመሆን ተጨቋኝና ጨቋኙ ይታገላሉ እንጂ ጭቆናን ለማጥፋት የሚደረግ ትግል ኖሮ አያውቅም፡፡ አሁንም የሚደረገው ጨቋኙን ወያኔን አውርደን፣ እኛ ጨቋኝ እንሁን ነው፡፡ ጭቆናን እናስወግድ የሚል ትግል አይደለም፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ተጨቋኙ ከጨቋኙ ጋር የተባበረ ነው፡፡ ፈልጎ ነው ያንን የሚያደርገው፡፡ ስንት ሺህ ሰው ባለበት 5 ፖሊሶች አንዱን መንገድ ላይ ይዘው ይደበድቡታል፡፡ እንደዚያ ሲያደርጉ 1ሺ ሰው ምንም አያደርግም፡፡ ይሄ ለኔ የጨቋኝ ተጨቋኝ ስምምነት ነው፡፡ “ለምን ትመታዋለህ?” የሚል የለም። ያ ሁኔታ እስካለ ድረስ ጭቆና ይቀጥላል፡፡ 
መንግስታቱ ለተቃውሞዎች የሚሰጡት ምላሽስ በንጽጽር ምን ይመስላል?
በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ አይታሰብም፡፡ ንጉሱ የኢትዮጵያ ስምም ሆነ የሳቸው ስም በውጭ ሀገራት በክፉ እንዲነሳ አይፈልጉም፡፡ ራሳቸውን ስለሚያከብሩ ሀገሪቱንም ያከብራሉ፡፡ ለራሳቸው የሚሰጡት ክብር ነው ሀገሪቱን እንዲያስከብሩ የሚያደርጋቸው፡፡ አሁን ያ የለም። የአትሌት ፈይሳ ድርጊት በስንት የዓለም ሚዲያ ነው የተነገረው? ግን ምን ተሰማቸው? ፈይሳ የበለጠ ነገሩን አፈነዳው፡፡ ይሄ ውርደት ግን አይሰማቸውም። ይሄ ህዝቡ የሚደበደበውና አስከሬኑ በየሚዲያው የሚታየው ያሳፍራቸዋል? በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ይሄ በጣም የሚያሳፍር፣ ሀገሪቱን ህዝቡን ክፉኛ የሚያዋርድ ነገር ነበር፡፡ ንጉሡ ይሄን አይፈልጉትም ነበር፡፡ ፖሊስ ከተማሪ ጋር ይጣላ የነበረው በዱላ ነው እንጂ በመትረየስ አልነበረም፡፡ እንግዲህ የሁለቱ የአፀፋ መልስ አሰጣጥ ከክብር ጉዳይ የሚመነጭ ነው፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ ታሪካቸውን ራሳቸውን የሚያስከብሩ ስለነበሩ ክብራቸውን ይጠብቃሉ፡፡ አሁን ያሉት ራሳቸውንም ህዝቡንም አያከብሩም፤ታሪካቸውንም አያከብሩም፤ የሚታያቸው ጡንቻ ብቻ ነው፡፡ 
በአፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ የሰብአዊ መብት ጉዳይ በጨዋነት የተያዘ ነው እንጂ በወረቀት ላይ ብቻ የሰፈረ አልነበረም፡፡ ይሄን ማድረግ ሀጢያት ነው፤ ብልግና ነው፤ ነውር ነው---ነበር የሚባለው፡፡ ከሥነ-ምግባር የሚመነጭ ሰብአዊነት ነበር፡፡ ጡንቻ የተጀመረው በደርግ ዘመን ነው፡፡ በጥይት መጋደል ተጀመረ። እውነት ለመነጋገር ከሆነ፣ ያንን ያመጣው ደርግ አልነበረም፡፡ 
የስልጣን ተቀናቃኝ ሆነው የገቡት ኢህአፓና መኢሶን ነበሩ ግብግቡን የጀመሩት፡፡ እነዚህ አካላት የሶስትዮሽ ድብድብ ሲገጥሙ መሳሪያ ያደረጉት ወጣቶችን ነበር፡፡ #ወያኔ”ም የኢህአፓ የመኢሶንና የደርግ ርዝራዥ ነው፡፡ እምነታቸውም የጡንቻ ነው፤ እስካሁን የሰሩትም በዚያው ነው። የሚለያየው የያዛቸው የውጭ እጅ ብቻ ነው፡፡ ሶቭየት ህብረት ደርግን መሳሪያ እየሰጠ ለግድያ ነፃ አድርጎት ነበር፡፡ እነዚህ ደግሞ በአሜሪካ ይደገፋሉ። አሜሪካ ደግሞ ግልፅ ግድያ አይፈልግም ነገር ግን እነዚህ በኃይል እየወጡ ጉልበታቸውን እያሳዩ ነው፡፡ 
በእንዲህ ያለ የፖለቲካ ቀውስ ወቅት የምሁራን ሚና ምን መሆን አለበት?
መጀመሪያ ፍርሃት መወገድ አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለህዝብ ነፃነት መቆም ያለባቸው ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን አሁን በፍርሃት ቆፈን የተያዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ራሳቸውን ነፃ ካላወጡ ሌላው ነፃ አይወጣም። የምሁራኑ በዚህ ውስጥ ነው ያለው፡፡ 
በአገሪቱ ላይ መረጋጋት እንዲፈጠር መፍትሄው ምንድን ነው ይላሉ? 
ከኃይለኛ ጋር ስትጋፈጥ መፍትሄው ሁሉ የሚኖረው በኃይለኛው እጅ ነው፡፡ መፍትሄው ሁሉ ያለው በ“ወያኔ” እጅ ነው፡፡ ከ“ወያኔ” በስተጀርባ ደግሞ በአሜሪካ እጅ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ልስበር ካለ መጥፎ ነው፤መጫረስ ነው የሚሆነው፡፡ በተለይ ደግሞ ወያኔን ትግሬ እያደረጉ፣ ትግሬን ሁሉ ወያኔ እያደረጉ የሚኬድበት ሁኔታ መታረም አለበት፤ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡ መፍትሄው ግን በ“ወያኔ” እጅ ነው ያለው፤ ህዝቡን ማዳመጥ አለባቸው፡፡

በአዊ ዞን በቲሊሊ ከተማ የወያኔ ካድሪን አንፈልግም በማለት ዛሬ ከፖሊስ ጋር በመሆን የራሱን የጎበዝ አለቃ በምረጥ አስተዳደሩን ተረክቧል።

Monday, August 29, 2016

ልጅ ግሩም




አሜሪካን ሀገር በዘረኝነቷ ምክንያት ከስራዋ የተባረረቸው "ሔለን ሀይሉ" (ዮዲት ወልደሩፋኤል) የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቃ መኖሪያ ፈቃድ ያገኘችው ኤርትራዊ ነኝ ብላ መሆኑ ሌላ ቀውስ ፈጥሮባታል። በለቀቀችው ቪዲዮ ላይ እኛ ትግራዮች እያለች እና የህዋሃትን ባንዲራ መያዟ እንደ ማስረጃ ቀርቦባት ኤርትራዊ አለመሆኗን በማጋለጧ በሃሰት መረጃ ያገኘችውን የመኖሪያ ፈቃድ ተነጥቃ ወደ ኢትዮጵያ በግዴታ ልትመለስ መሆኑን ታውቋል።
ልጅ ግሩም

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተከትሎ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እየወጡ ነው ተባለ ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008)



በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱ አስፍቶ መላው ሰሜን ጎንደርን፣ ደቡብ ጎንደርን፣ ምዕራብ ጎጃምን፣ አዊን እና ምስራቅ ጎጃምን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እያወጣ መሆኑ ተገለጸ። 
በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ጨጭሆ፣ ጎብጎብ፣ ፍላቂት፣ ደራ ሐሙሲት፣ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የአገዛዙ መዋቅር እየፈራረስ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። 

Amhara region intensifies uprising against TPLF, several killed by regime forces By Engidu Woldie ESAT News (August 30, 2016)


The blue skies over the city of Bahir Dar were covered in smokes on Monday, on this deadly day of protest against TPLF oligarchy, as people in the Amhara region of Gondar and Gojam intensified their defiance against the Tigrayan minority rule. Trails of smokes were rising all day into the skies of the city of Bahir Dar as protesters burnt tires on the streets and set ablaze businesses affiliated with the regime as well as houses of officials and spies of the regime.

ተው ተው ሲሉት ሲመክሩት ካልሰማ

አሜሪካ፡ “ህወሃት አብቅቶለታል”

የታቀደ፣ ግን ድንገተኛ የሚባል መፈንቅለ መንግሥት ይጠበቃል

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣarmy-in-addis-e1472451071352-620x310A
army-in-addis-e1472451071352-620x310

"የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ" ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ ገፅ ፡152-153



"አፄ ምኒልክ ደም መፈሰስን እናስቀር ብለው ንጉሥ ጦናን ለመኑት።ንጉሥ ጦና ግን ኃይሉን አሟጦ መዋጋት ስለመረጠ በምኒልክ ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። በመጨረሻ ግን ቆሰለና ተማረከ።ዳግማዊ ምኒልክ ጦናን አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣትና መንግስቱንም አሽቀንጥረው ጥለው ሥልጣኑን ለጦር መሪዎቻቸው ከመስጠት ይልቅ ደግነት የተሞላበት ምህረት አድርገውለት እንደሚገብርላቸው ቃል ካስገቡት በኃላ ወደ ሥልጣኑ መለሱት። ምኒልክ ተበቃይ አልነበሩም ።ይቅር በይ፣ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ አስተሳሰብ የነበራቸው እና ራሳቸውን እነደ ጥሩ ክርስቲያን የሚያዩ ሰው ነበሩ።በጦርነት ላይ የሴት ልጅ ጡት መቁረጥ ፍጹም ከባሕሪያቸው ውጪ ነው።እንዲህ ዓይነቱ ውንጀላ መሰረተ―ቢስ እና ከተንኮለኞች የመነጨ ነው።የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አምጸው ጦርነት አነሱና ቆስለው ተማረኩ።ምኒልክ የቆሰለውን ምርኮኛ ገድሎ በመጨረስ ፈንታ ቁስላቸውን ራሳቸው አክመው ፣አጠገባቸው አስቀምጠው አብረዋቸው እንዲመገቡ በማድረግ ፍቅር ነው ያሳዪአቸው።ሥልጣናቸውንም አልወሰዱባቸው፤ ያለማመንታት መልሰውላቸዋል። በርግጥ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሩኅሩኅ ነበሩ።አገራቸውን ለመውረር የመጡ ምርኮኞች ጣልያኖችን እንኳ በርኅራኄና በደግ አያያዝ ነበር የያዟቸው።እኝህን ሰው ጡት ቆርጠዋል/አስቆርጠዋል/ ብሎ መፈረጅ አግባብነት የሌለው ትንሽ የፓለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት የሚነዛ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው።ምኒልክን ጡት ቆርጠዋል ብለው ለማስጠላት ሀውልት ያቆሙ አካላት በድርጊታቸው ማፈር እና ያንን አሳፋሪ ሀውልትም ማፍረስ ይገባቸዋል። ምኒልክ በግላቸው እንደዚያ ዓይነት ተግባር ጨርሶ አይፈጽሙም።"

ሁለት ታላቅ መረጃ በውስጥ ምስመር ደርሶናል!!!


የመጀመሪያው #ከአማራ ክልል
የአማራ ህዝብ በአሁን ሰአት ከወያኔ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ለማላቀቅ በከፍተኛ ሁኔታ በመዋደቅ ላይ ይገኛል። በዚህም ጀግናው የአማራ ህዝብ ጎንደርና ጎጃም ከፊል ሸዋ ላይ ከወያኔ አገዛዝ ነጻ በማስወጣት የራሱን የጎበዝ አለቃ በመሾም ላይ ይገኛል። ይህ ትግል እንደቀጠለ ባለበት ወቅት ቀላል ቁጥር የማይባሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ህዝቡ እየተቀላቀለ የወያኔ አጋዚ ጦር እየተፋለመው ይገኛል። ከአማራ ክልል የተላለፈው መልዕክት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በብዛት ወደ ህዝቡ በሚቀላቀልበት ሰዓት የተወሰኑት መሃል ሰፋሪ ሆነዋል ወደ ህዝብም አንተኩስም ወደ ህዝቡም አንቀላቀልም ያሉ አሉ። ህዝብ ሁልግዜም አሸናፊ ሰለሆነ በአፋጣኝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለህ የጠላትን የወያኔ አጋዚ ጦር መድረሻ እንድታሳጣው ታላቅ ጥሪ ከህዝቡ እየተላለፈለት ይገኛል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሆይ አንተ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ጠባቂ እንጅ የጠላት ወያኔ ጠባቂ ስላልሆንክ የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን ታሪክ ሰሪ በመሆን ከህዝብህ ጎን እንድትሰለፍ ህዝብ ጥሪ አቅርቦለሃል። ብዙ የመከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ጥሪ በመቀበል ከህዝቡ ጋር እየተቀላቀለ ይገኛል።
ሁለተኛው #ከኦሮሚያ ክልል
በኦሮሚያ ከዳር እስከዳር ሊጠራ ለታቀደው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወያኔዎች ከፍተኛ ፍራቻ ላይ እና ድንጋጤ ላይ እንዳሉ ይታወቃል። ባለስልጣኖችም ቪዛ ለማስመታት በየኤንባሲው በር እየታዩ እንደሆነ ይታወቃል። ይሄ የሚያሳየው በቅርቡ ሁሉም ባለስልጣን አገር ጥለው ለመፈርጠጥ ዝግጅት ላይ ናቸው ማለት ነው።
ይህ በእንድህ እንዳለ በኦሮሚያ ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ትልቅ ወከባ እና ማስገደድ እየተደረገባቸው ነው። ህዝብ ላይ አንተኩስም ብለው አፍ አውጥተው የተናገሩት ሰራዊት የት እንደሚወሰዱም አይታወቁም። ሁሉም ሰራዊት በሚያስብል መልኩ ከህዝብ ጋር እንደሚሰለፍ እያረጋገጠ መሆኑን እና ቀላል ቁጥር የማይባሉ የመከላከያ ሰራዊት ከግዳጅ ቦታ ላይ እየጠፉ እንደሆነ መልዕክት እየደረሰን ነው። የኢትዮጵያ ሰራዊት በሙሉ ከህዝብ ጎን ለመሰለፍ ኦሮሚያ ውስጥ ለግዳጅ ከተሰማራው ከአብዛኛው ሰራዊት የመጣ መረጃ ያመለክታል። የህዝብን ጥሪ በቀበል ከህዝብ ጋር እንደሚሰለፉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የግሌ አስተያየት
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህዝብ ጎን ለመሆን ፈጣን ምላሽ የሰጣችሁ የሰራዊት አባሎች በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ምስጋና በማቅራብ ላይ ይገኛል። የተቀራቹ የመከላከያ ሰራዊት በሙሉ ወሳኝ ግዜና ወቅት ላይ ስለሆንን በፍጥነት የህዝቡን ትግል በመቀላቀል ወንድምህን፣ እህትህን፣ እናትህን፣ አባትህን፣ ብሎም ወድ አገርህን፤ እየገደለ ያለውን ወያኔ በመፋለም ከህዝብህ ጎን በመቆም የተለመደው ጀግና አኩሪ ታሪክህን በመድገም በደማቁ ትጽፈው ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አቅርቦለሃል።
ስማ!! ስማ!! የሰማ ላልሰማ ያሰማ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ሞት ለገዳይ ወያኔ !!!

"ወታደሩ ጓዴ አንተ ያገሬ ሰው ወንድሜን አትግደል ብረቱን መልሰው " ከህዝብ ጎን የቆሙ አርቲስቶች ብቅ ብቅ እያሉ ነው እንዴት ደስ ይላል አርቲስት መስፍን በቀለን ከልብ እናመስግናለን ።

ትንሳኤ ራዲዮ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ የስርጭት ሞገዶች ላይ የሚተላለፍ ነጻ ራዲዮ ነው

Sunday, August 28, 2016

አቶ አብዲራህማን ማጎዲ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር *ኦብነግ*የውጭ ግንኙነት ሃላፊና የህዝባዊ አን ድነትና ዲሞክራሲ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ሃላፊ ስለ ድርጅቶቹ ሚና ዓላማና ግቦች ይናገራሉ

አቶ አብዲራህማን ማጎዲ የኦጋዴንብሄራዊ ነጻነት ግንባር *ኦብነግ*የውች ግንኙነት ሃላፊና የህዝባዊ አንድነትና ዲሞክራሲ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ሃላፊ ስለ ድርጅቶቹ ሚና ዓላማና ግቦች ይናገራሉ SBS Radio Presents ONLF Foreign Secretary Abdirahman Mahdi

ህዝባዊ እምቢተንነት በተመለከተ የአርቲስቶች አስተዋጽዎ በሁሌ አዲስ ESAT Radio Hule Addis Sat 27 Aug 2016

ህዝባዊ እምቢተንነት በተመለከተ የአርቲስቶች አስተዋጽዎ በሁሌ አዲስ ESAT Radio Hule Addis Sat 27 Aug 2016

ኢሳት፦ አጋዚ በቀድሞ መስራችና አመራር ሲፈተሽ ከቀድሞ የአጋዚ ክ/ጦር መስራችና ሃላፊ መኮንን ከሆኑት ኮ/ሌ አልበል አማረ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ESAT HR- AGAZI's incrimination by its ex-founder and leadership - 28 Aug...

Abebe Gellaw ቅኝ አንገዛም!


እራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ብሎ የሚጠራው ዘራፊና ፋሺስታዊ ቡድን እንደ ነጋበት ጅብ መግቢያና መፈናፈኛ እያጣ ነው። 
ህወሃት አላማዬን አሳክቻለሁ ትግራይን ነጻ አውጥቻለሁ እያለ ቢያቅራራም ከመረብ ባሻገር ያለውን ህዝብና አገር ልክ እንደ ቅኝ ገዢ እየዘረፈ፣ በግፍ እየገደለና እያሰቃየ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል። ህወሃት አላማው ትግራይን ነጻ ማውጣት ስለሆነ (ከማን ነጻ እንደሚያወጣ ባይታወቅም) ከትግራይ ባሻገር መሬት መቀማት፣ ማስገበር፣ አድሏዊ ስርአት ማንሰራፋት፣ መጠነ ሰፊ ዘረፋ ማካሄድ፣ መግደል፣ በዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ሰቆቃ መፈጸም፣ ህዝብ ማፈናቀል፣ መከፋፈል እና በዘረኝነት ህዝቦችን መፈረጅ አይነተኛ ባህሪያቶቹ ናቸው። 
ህወሃት ገና ሲፈጠር ገንጣይና አስገንጣይ ስለሆነ ህዝቡ ከፈቀደ ትግራይን መገንጠል ይችላል። እንደውም እውነቱን ለመናገር ትግራይ በአሁኑ ግዜ ሙሉ በሙሉ የህወሃት እርስት መሆኗ ግልጽ ነው። ያለህወሃት በትግራይ ላይ ማንም አያዝም። በቅርቡም ሳሞራ ዩኑስ ህወሃት ከሌለ የትግራይ ህዝብ የለም ብሎናል። ይሁንና የትግራይ ህዝብ አገሩን አጥቶ ብቻውን በህወሃት ፋሺስታዊ አገዛዝ ስር ይቀጥላል ብሎ ማመን ይከብዳል። ፈቃዱ ከሆነ ግን ማንም ሊያስቆመው አይገባም።
ህወሃት በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በነጻነትና በእኩልነት ስም የጫነው ፋሺስታዊ ቅኝ አገዝ ጭቁኑ ህዝብ በቃኝ ብሏል። በየአደባባዩ አሻፈረኝ ብሎ የተነሳው ህዝብ "ጠባቡና ትምክተኛው የትግራይ ነጻ አውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይሰራል?" ህወሃት እስከመቼ የኢትዮጵያን ህዝብ ደም ይመጣል? እስከ መቼስ እየገደለና እየዘረፈ መቀጠል ይችላል? የሚል መሰረታዊ ጥያቄ እያነሳ ነው። የህወሃት ቅኝ አገዛዝ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የጸረ ቅኝ አገዛዝ ተግሉ በመላው ኢትዮጵያ ይፋፋም። ህዝቡ ግብር መክፈል ያቁም። በህወሃትና በቅጥረኞቹ የንግድ ተቋማት ላይ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማእቀብ ይደረግ።

ወቅታዊ መልዕክት የመጀመሪያ ትግል!!!


ይሄ መለዕክት በመላው ኢትዮጵያ የሚጠራው ታላቅ ህዝባዊ እንቅስቃሴ አካል ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ገዳዩ ወያኔን በአጭር ግዜ ጠራርጎ ለማባረር የታቀደ ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው።
ለዚህ የህዝብ እምቢተኝነት ወሳኝ እና ቀጣይነት ያለው ትግል ስለሆነ ሁኔታዎች እንደሚፈቅደው በማስ ሚዲያ እንዲሁም በሚስጥር የሚተላለፉ ዕቅዶች ያሉት ስለሆነ ከወድሁ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪ እየተደረገ ነው።
መላው ኢትዮጵያ በሚጠራው ታላቅ ህዝባዊ አመጽ ከመደረጉ በፍት ሊሰሩ የሚገቡ መልዕክቶችን በየክፍሉ እየተከፋፈለ ለመላው ኢትዮጵያዊ እንደአስፈላጊነቱ ለህዝብ እናሳውቃለን። በሚስጥር የሚሰሩት በተጠናና በተቀነበባበረ ሁኔታ እየተሰራ ስለሆነ መገለጽ ያለባቸው ብቻ በመግለጽ እስከ ነጻነት የሚቀጥል የማይቆም ትግል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
የመጀመሪያው መልዕክት *ክፍል አንድ*
1. በአገር ቤትም ሆነ በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊ በተቀናጀ መልኩ ፍራቻን አስወግደው ፊት ለፊት በመፋለም ወያኔዎችን እና ተላላኪዎችን መውጫ መግቢያ እያሳጡ ነው። ይሄ እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደሙ በተጠናከረ መልኩ እንቀጥሉ ማድረግ እና ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡበትን ስራ መስራት።
2. የወያኔ ሰላዮች እና ተላላኪዎች ዘር ሳይለይ በየአካባቢ ያሉትን እነዚህን የህዝብ እኩያንና የህዝብ ጠላት የሆኑትን መሃላችን ሆነው ህዝባችንን በማያስጠቆም የሚያስገድሉ እና የሚያሳስሩ የወያኔ ስርዓት እንዲቀጥል መሰረት ሆነው የሚያገለግሉ የህዝብ ጠላት ስለሆኑ እንደዚህ ያሉትን ተላላኪዎች የመለየት ስራ መስርት።
3. የወያኔ ሰላያዮች እና ተላላኪዎች በመኖሪያ ቤታቸው ገዳይ የሆነውን የአጋዚ ወታደር በመደበቅ ምግብ የሚመግቡ ህዝባችን እንዲገድሉ ለገዳዮችን ምቹ ምሽግ በመሆን እየሰሩ ስለሆነ ቤታቸውን በለየት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ።
4. በአማራው ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ብሄሮች ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ብሄሮችን የወያኔ አቃጣሪ ከሆነው ውጭ ህዝቡ ከለላ እንዲያደርግላቸው ያስፈልጋል። የሌሎችም ማህበረሰብም ትግሉ ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት ስለሆነ አብረው እንዲነሳ እንዲታገል ማድረግ።
5. በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በአ/አ፤ ያሉትን ወታደራዊ ተቃማትን ያሉበትን ሁኔታ በማጥናት መግቢያ መውጫውን እንድሁም አካባቢውን ለይቶ በማወቅ በሚስጥር ለተደራጁት ታጋዮች መንገር። እንዲሁም ህዝቡም እራሱን እንዲያደራጅ እና ወደ ትጥቅ ትግሉ እንዲገባ ማስቻል።
6. በመላው ኢትዮጵያ በሚደረገው ህዝባዊ እንቢተኝነት ሰልፍ ላይ ገዳይ አጋዚ መነሻውንና መድረሻውን በማጥናት ለታጣቂዎች ማሳወቅ። ይሄን ማድረግ ህዝባችን ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጭፍጨፋ ማስቆም ብሎም እስከመጨረሻው ማጥፋት የሚቻልበት ታክቲክ ስለሆነ የአጋዚ ጦር መውጫና መግቢያውን መነሻና ማረፊያውን ለአጋዚ ወታደሮች ምግብና መጠጥ በየት በኩል እንደሚገባላቸው በማጥናት በሚስትር ለህዝቡ እንድሁም ለታጋዮች ማሳወቅ።
7. ይሄ የመጀመሪያው ስልት ዕቅድ ነው ይሄንን በመስራት ወያኔ የተደገፈበት መረብ በአጭር ግዜ በመበጣጠስ ነጻ ክልሎችን መፍጠር ይቻላል። ነጻ የወጡትን አካባቢዎች መዋቅሮች እየተዘረጋ ወታደራዊ ሃይሎችን እያጠናከሩ ወደ ሚቀጥለው ምዕአፍ መሄድ።
ይሄንን መልዕክት ኮፒ በማድረግ እያባዛን ለመላው ኢትዮጵያዊ እንዲበተን እና እንዲደርስ ማድረግ የሁላችንም ድርሻ ነው።
የሰማ ላልሰማ ያሰማ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ሞት ለገዳዩ ወያኔ!!!

Patriotic Ginbot 7


የወያኔን ዘረኛና አድሎአዊ አገዛዝ በቃን በማለት በመላው የሀገራችን ክፍል የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድማሱን እያሰፋ መዳረሻውን ነጻነት ፤ ፍትህ ፤ እኩልነት እና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ይገኛል። ይህንንም የነጻነት ትግል ከግብ ለማድረስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብርና አስተዋጽዖ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም። የሕውዓት ዘረኛ አገዛዝ በ25 ዓመት የአገዛዝ ዘመኑ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሕዝብን ከሕዝብ በሀይማኖት ፤ በበብሄርና በጎሳ በማለያየት ለማጋጨት ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልወጣው አቀበት አልነበረም ። ነገርግን አርቆ አስተዋዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘረኛና ከፋፋይ አምባገነን አገዛዝ በቃን ወግድልን በማለት በማንነቱ ሳይለያይ ከጫፍ እስከ ጫፍ አንድ አይነት ድምጽ በማሰማት የዘረኞችን አገዛዝ አስወግዶ ነጻነቱን በዕጁ ለማስገባት ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል። 
ይሁንና የወያኔው አገዛዝ እጁ ረዥም በመሆኑ ሰላዮቹን እና አንዳንድ ከህሊናቸው ይልቅ ሆዳቸው የቀደመባቸውን ደካሞች በማሰባሰብ የተጀመረውን የነጻነት ትግል አቅጣጫ በማሳት ከተቻለ የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም ካልሆነም ወዳላስፈላጊ እርስ በርስ ግጭት እንዲያመራ ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ይገኛል። 
በመሆኑም የተጀመረው የህልውናና የነጻነት ትግል ከብሄርተኝነት ወይም ከጎሳ ይልቅ ሰብዓዊነትን ያሥቀደመና ለአብሮነታችን ጽኑ መሰረት የሚጥል ሐገራዊ ፋይዳ የሚኖረው ይሆን ዘንድ ትንቅንቁ ከሕውዓት አገዛዝ ጋር ብቻ ሳይሆን ሕውዓት ላለፉት 25 አመታት ከዘራው የዘረኝነት አስተሳሰብ ጭምር ጋር መሆን ይኖርበታል።
ሰላም ፤ ፍትሕ ፤ ዴሞክራሲ እና እኩልነት የሰፈነባት የሁላችንም የሆነች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ዘረኝነትን ወይም የብሄርተኝነት አስተሳሰብን ልንጸየፈው ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

ሁሉም ሰው ሊያየው የሚገባ ድንቅ ትእይንተ ህዝብ በፍራንክፈርት Ethiopian protest against TPLF Regime ,in Frankfurt Germany 26.8.2016

Message to the Ethiopian Defense Forces

Message to the Ethiopian Defense Forces

Saturday, August 27, 2016

ከተለያዩ ኢትዮጵያዊያን በውስጥ መስመር የደረሰን መልዕክቶች፡


በመላው አማራ እና ኦሮሞ ደቡብና አ/አ ላይ ታላቅ የውስጥ ለውጥ ስራ እየተሰራ ነው፡
በሁሉም አካባቢ የሚኖሩትን ህዝባችንን በመሰለል እና በማስገደል ስራ ላይ የተሰማሩ የወያኔ ተላላኪዎች በሙሉ ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለን ግዜውና ሁኔታ በፈቀደ ሰዓት እርምጃ የሚወሰድባችው እንደሆንን በማረጋገጥ ህብረተሰቡ አንድነቱን በማጥበቅ የወያኔን ሴራ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከኢትዮጵያ ምድር ለማትፋት ታላቅ ስራዎችን እየተሰራ ነው፡ ከእንግድህ በሃላ በህዝብ ሃብት እየኖረ መልሰው ህዝብን የሚያስበሉ የወያኔ ብችሎች ከእንግድህ በሃላ ለደቂቃዎች የሚታገስ ኢትዮጵያዊ ጠንካራ ስራዎች እየተሰራ ስለሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ ሰላዮች እና አቃጣሪውን ለማጥፋት ስራዎች ስለተጀመረ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዝህ ታላቅ ህዝባዊ ትግል ወያኔን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት እና የሁላችንም ኢትዮጵያ እኩል የሆነች ለመመስረት እየተሰራ ስለሆነ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የወያኔ አቃጣሪዎች በማጋለጥ እና እርምጃ በመውሰድ የወያኔን መረብ መበጣጠስ ተጀምራል ሁሉም በዝህ ስር ነቀል ለውጥ በቁርጠኝነት ይነሳ የሚል መልዕክት ከተለያዩ ማህበረሰብ ደርሰውናል፡
ከእንግድህ ወድህ በኢትዮጵያ ገሎ እና አስገድሎ በሰላም መኖር የለም፡ በነዝህ በገዳይና በአስገዳይ ላይ ህብረተሰቡ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል ትግሉ ወያኔ ከኢትዮጵያ ምድር እስከሚጠፋ በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላል፡
ያልተነሳህ ተነስ ተነስ ትግሉ በፍጥነት እየተቀጣጠለ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ሞት ለወያኔ እና አቃጣሪዎቹ

ሰበር ዜና


በገዢው ሥርዓት ህወሓት-ኢህአዴግ የተገደሉ ንፁሐን ዜጎችን ለማሰብ ብሔራዊ የኀዘን ጥሪ ያቀረቡት በቂሊንጦ የሚገኙ በዞን 1 ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ጨለማ ቤት መወርወራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ገለጹ::

ጥሪውን በዋናነት ያቀረቡት በዞን 4 የሚገኙት 9 የፖለቲካ እስረኞች(በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ አበበ ኡርጌሳ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ) ቅጣት ቤት ይገኛሉ::

አስቸኳይ መልእክት (ብሥራት ደረሰ – ከአዲስ አበባ)

ነፃነት ቆራጥነትንና እልህን ትፈልጋለች፡፡ ነፃነት ሸረኝነትና ተንኮልን ያዘለ ፉክክርን አትሻም - የነፃነት ፍልሚያ ውጤታማ እንዲሆን በቀናነትና በእኔ እብስ አንተ ትብስ የጋራ መግባባትና መተሳሰብ መቃኘት አለበት፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በስሜትና በሞራል ከተሳተፈ የነፃነት ቀን ቅርብ ናት፡፡ ነገር ግን “ቆይ እነእንትና ይለይላቸው፣ እነሱ ሲያዳክሟቸው እኛ እንቀጥልና የመጨረሻ ግብኣተ መሬታቸውን እናሳያቸዋለን…” በሚል የማይረባ ሥልት በተናጠል መጓዝ ካለ መቼም ቢሆን ነፃነት አትገኝም፡፡ ነፃነት በእልህ አስጨራሽ የጋራ ትግል እንጂ በብልጣብልጥነትና ከጋራ ትግል በመሸሽ ልትገኝ አትችልም፡፡ በአንዱ ሞት ሌላው ነፃ እንዲወጣ ተደብቆ ወይ አሸምቆ ቢጠባበቅ ደግሞ ከኅሊናም ከሃይማኖትም አንጻር ወንጀልና ኃጢኣትም ነው፡፡ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፡፡ “ማን ይጠይቀኛል? ማንስ ያየኛል?” የሚሉት ጥያቄዎችም የጅል ፈሊጦች ናቸው፤ በመጀመሪያ ዋናው ጠያቂ ኅሊናችንና የሚሰውት ወገኖቻችን ነፍሳት ናቸው፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ሁሉም ዐይን ነውና እንዳንታለል፡፡

አለ ገና!!!!!! ይነጋል ይነጋል ይነጋል አይመሽም፣ ቆርጠን ተነስተናል ወደኋላ አንልም። ዳዊቴ መኮንን #OromoProtests**NEW**Dawite Mokonen - Fayis - Lilesa #OromoProtest (2016)

Friday, August 26, 2016

Documentary U S Policy ETHIOPIA A FAILED STATE! 2016

Documentary U S Policy ETHIOPIA A FAILED STATE! 2016

“የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል” ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ


“የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል” ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
በተለያዩ ክልሎች ላለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እና ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠ አገሪቱ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ልታመራ እንደምትችል የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስጋታቸውን ገልጹ።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

TPLF forces shot and kill a college student in Finote Selam as protest spreads in Gondar, Gojam By Engidu Woldie ESAT News (August 25, 2016)


Regime forces shot and killed a college student in Finote Selam, West Gojam on Thursday as they used lethal force to disperse protesters who took to the streets for the second day to show solidarity with the Amhara and Oromo people who demand an end to the TPLF brutal rule.
Finot Selam, sitting on a major connecting route in northern Ethiopia, has become the latest town to join the increasing and relentless uprising against a minority tyranny that inflicted economic, political and social malice on the people of Ethiopia who are now saying enough to 25 years of persecution.

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፤ ስለ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ የጋዜጠኛነት ሙያ ሕይወቱና የአውስትራሊያ ጉብኝቱ ይናገራል።


ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፤ ስለ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ የጋዜጠኛነት ሙያ ሕይወቱና የአውስትራሊያ ጉብኝቱ ይናገራል።

Thursday, August 25, 2016

http://video.ethsat.com/?p=27495 “… በእውነት ነፃ ለመውጣት እድል እንዳለን ተስፋ አደርጋለሁ። ከእንግዲህ ወደ ነበርንበት ባርነት የምንመለስ ከሆነ ግን አሁንም ባልወለድ፤ ሌላው ኢትዮጵያዊም ባይወለድ በተሻለ ነበር። “ግን ተስፋ አንቁረጥ። አንድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሆነን ተፈጥረናልና!”

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ማጠናቀቂያ ወቅት ላሳየው የፖለቲካ ተቃውሞ የሚወስደው እርምጃ እንደሌለ ማረጋገጡ ታወቀ ኢሳት (ነሃሴ 19 ፥ 2008)



የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ማጠናቀቂያ ወቅት ላሳየው የፖለቲካ ተቃውሞ የሚወስደው እርምጃ እንደሌለ ማረጋገጡ ታወቀ። 
የቢቢሲ የስፖርት ዝግጅት ክፍል ከኮሚቴው የተገኘው ማላሽን ዋቢ በማድረግ በአትሌቱ ላይ የተካሄደ ምርመራ መዘጋጀቱንና የሚወስድ እርምጃ አለመኖሩ አመልክቷል። 
አትሌቱ በወቅቱ ያስተላለፈው ፖለቲካዊ መልዕክት ከኦሎምፒክ ህግጋት ጋር የሚጻረር ሊሆን ይችላል በማለት የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጉዳዩን እንደሚመለከተው መግለጹ ይታወሳል።

Latest News August 25, 2016

Latest News August 25, 2016

ለጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እንዲህም ተቀኝቶለታል!

"በእውነት መንግስት እየተናገረ ያለውን ታምናላችሁ?" የፈይሳ ለሌሳ እናት ስለልጃቸው መመለስ ጉዳይ የሮይተር ጋዜጠኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ ፈገግ ብለው በጥያቄ ሲመልሱ... የፈይሳ እናት ልጃቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጣ እዛው ሰላም ይሁን ብለዋል። ------------------------------ (Reuters)— The family of Olympic marathon silver medalist Feyisa Lelisa voice concern over his safety after he made an anti-government gesture in Rio. Natasha Howitt reports. #EthiopiaProtests #OromoProtests

http://ecadforum.com/2016/08/25/ethiopian-olympians-family-warn-against-return/
(Reuters)— The family of Olympic marathon silver medalist Feyisa Lelisa voice concern over his safety after he made an anti-government gesture in Rio.…
ECADFORUM.COM

Attempt by TPLF forces to take custody of a leader of the Amhara resistance fail By Engidu Woldie ESAT News (August 25, 2016)


Aided by ground forces and helicopters, the TPLF regime forces approached the Angereb jail in the city of Gondar on Wednesday to take custody of Col. Demeke Zewdu, the symbol of the revolt in the Amhara region. The local defense forces however refused to transfer his custody.

Wednesday, August 24, 2016

ሕዝባችን እይተቀጠቀጠ በሄደ ቁጥር ይበልጥ ይጠብቃል!! August 24, 2016


def-thumb
ኢትዮጵያን ላለፉት 25 ዓመታት አፍኖ የሚገዛው ሕወሐት ብዙ ጊዜ ለቆዩና ሕዝቡን ላንገሸገሹት ችግሮች መፍትሔው ይበልጥ ማፈን መቀጥቀጥና ጥያቄዎቹ እንዳይነሱ ማዳፈን እንደመፍትሔ ቆጥሮታል። በመላ ሀገሪቱ ዙሪያ ሰላማዊ ጥያቄ እንስተው ባዶ እጃቸውን አዳባባይ ለወጡ ወገኖቻችን ሁሉ መልሱ በጥይትና በዱላ መጨፍጨፍ ከሆነ ስንበተ። የህወሀት አምባ ገነኖች ስልጣንና በስልጣን ያገኙት የዝርፊያ ጥቅም አሳውሮ ግድግዳ ላይ የተጻፈ ግልጽ ነገር ማንበብ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። ግድግዳው ላይ የተጻፈው ጽሑፍ የአፈና የዝርፊያ ይማጭበርበርና በህዝብ ደም እየጨቀዩ የሚኖርበት ዘመን በምድረ ኢትዮጵያ እያከተመ መሆኑን ይናገራል። ብዕብሪት የታወረ አይናቸው ግን ሊያየው አልቻለም።

በጎንደር አንገረብ እስር ቤት የሚገኙትን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን ለመያዝ የሲቪል ልበስ ለብሰው የገቡ የደህንነት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ነሃሴ ፲፰ ( አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-


የደህንነት አባላቱ አንዴ ታዘን ነው ሌላ ጊዜ ደሞዝ ልንከፈል ነው የመጣነው ቢሉም ፣ የዞኑ ልዩ ሃይልና መከላከያ ሰዎች የምናውቀው ነገር የለም በማለት እነዚህን ሰዎች ማገታቸው ታውቋል። ሁሉም የደህንነት አባላት ሽጉጥና ሌሎችንም የጦር መሳሪያዎችን መያዛቸው ታውቋል።
በአሁኑ ሰአት እስር ቤቱ አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት እንደሚታይ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ከጎንደር ከተማ አውጥቶ ለመውሰድ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሲደረጉ ቢቆዩም አልተሳኩም። የአሁኑ ድርጊትም የከተማውን ህዝብ ማስቆጣቱ ታውቋል። ህዝቡ በቤቱ ቁጭ ብሎ አድማ እያደረገ ባለበት ሰአት ኮሎኔሉን ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በደንብ የታሰበበት ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ተናግረዋል።