Wednesday, April 26, 2017

እነሆ ዋዛ እና ቁምነገር፤ ......ያው እንደሚታወቀው ህገራችን ኢትዮጵያ እንኳንስ ሌላው ቀርቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ ምቹ ሁኔታ ቢያገኙ ስደትን የሚመርጡባት ሃገር ወደመሆን ተቀይራለች እና ይሄ የጋራ ችግር ነው… ይሄ ችግር እንዴት ተቀርፎ ሃገሪቱ መማረሪያ ሳትሆን መኖሪያ ትሆናለች የሚለውን ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን ትጋት ሊያደርግ ይገባል… በተለይም መንግስት ልል ነበር ለካስ ዋናው ችግር መንግስት ነው….! ….. ስለዚህ ሃገር ከመቀየር እና በስደት መከራ ከማየት እንደምንም አንድ ግዜ ሆ ብሎ መንግስት መቀየር ሳይሻል አይቀርም የሚለውን አማራጭ…. ብናየው መልካም ሳይሆን አይቀርም!..... .....ትንሽ ሾለ ኢትዮጵያ እና ሾለ አዲሱ ቀሚሷ... ትንሽ ሾለ ኑሮ ትንሽ ሾለ ክልል ባለስልጣኖቻችን በተለይም ሾለ ኦሮሚያው ፕረዘዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ ትንሽ ሾለ ሳውዲ ስደተኞች... እና መሰል ጉዳዮችን ይዘን ተከስተናል! @Abebe Tolla Feyisa

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ሜይ ዴይ - አለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን May - 1 - 2017

#Ethiopia Happy #May Day 2017
የዴሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ዓለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን MAY 1ን ምክንያት በማድረግ
1.- በሐገራችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ከስራ ተፈናቅለው በእስር የሚማቅቁ ወገኖቻችን እንዲፈቱ እና አንባ ገነኑ ስርዓት በአገሪቱ እያደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት ለአለም ለማሳወቅ !!!
2- በኖርዌይ ለሚኖሩ መስራት እየቻሉ በስደተኛ መጠለያ ውስጥ ታፍነው የአእምሮ እስረኛ ለሆኑ ወገኖቻችን የስራ ፈቃድ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቅ!!!
3- የወዛደሩን መብት የሚያስከብረው ሀይል የስደተኝነት ጠያቂው መብት እንዲጠበቅ ይሰራ ዘንድ ለመጠየቅ !!!
በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው ሜይ ፩ እለት በጋራ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ድምፃችንን እንድናሰማ ለመላው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ያስተላልፋል !!!!!!!!

*ሰልፉ የሚጀምረው የፊታችን ሰኞ May 1/2017 ,ከ11:00 - 12:45 ሰዓት ስለሚሆን አስቀድመን እንድንገናኝ እናሳስባለን ::
ቦታው Youngstorget ( Torggata, 0181 Oslo)

Tuesday, April 25, 2017

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ

የዴሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አለማቀፍ የወዛደሮች ቀን ሜይ ፩ ምክንያት በማድረግ 
፩፨ በሀገራች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ብቻ ከስራ ተፈናቅለው በእስር የሚማቅቁ ወገኖቻችን እንዲፈቱ እና አንባ ገነኑ ስርዓት በአገሪቱ እያደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት ለአለም ለማሳወቅ 
፪፨ በኖርዌይ ለሚኖሩ መስራት እየቻሉ በስደተኛ መጠለያ ውስጥ ታፍነው የአእምሮ እስረኛ ለሆኑ ወገኖቻችን የስራ ፈቃድ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቅ
፫፨ የወዛደሩን መብት የሚያስከብረው ሀይል የስደተኝነት ጠያቂው መብት እንዲጠበቅ ይሰራ ዘንድ ለመጠየቅ ፦፦፦ 
በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው ሜይ ፩ እለት በጋራ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ድምፃችንን እንድናሰማ ለመላው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ያስተላልፋል

ሰልፉ የሚጀምረው 11:00 - 12:45 ስለሚሆን አስቀድመን እንድንገኝ እናሳስባለን ::
ቦታው Youngstorget ( Torggata, 0181 Oslo)

የአቅም ችግር ታይቶባቸዋል የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው ነው ተባለ


#AG7የአርበኞች áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ -ማክሰኞ - ሚያዚያ - 17 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Friday, April 21, 2017

በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ


#AG7የአርበኞች áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ -አርብ - ሚያዚያ - 13 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Monday, April 17, 2017

ትራምፕ የባሕር ኃይል አጥቂ ቡድን ወደ ኮሪያ ባሕረ-ሰላጤ አዝምተዋል።

 áˆáŒ… እግሩ ኪም ጁንግ ኡን በበኩላቸው በአያታቸው የልደት ቀን 'አኅጉር ተወንጫፊ ሳይሆኑ አይቀሩም' የተባሉ ሚሳይሎች የታጠቀ ጦራቸውን በፒዮንግያንግ አደባባይ አሰልፈዋል። ተንታኞች የጠባይ መመሳሰል ይታይባቸዋል የሚሏቸው ሁለት መሪዎች በኮሪያ ባሕረ-ሰላጤ ተፋጠዋል።


በፖለቲካ ጉዳይ የታሰሩ እስረኞች የውሻ መርዝ ተወግተው እንደሚገደሉ የስርዓቱ የቀድሞ የደህነት ሹም አቶ አያሌው መንገሻ አጋለጡ


በጎንደር ያሉ የሕወሓት ደጋፊዎች ንብረታቸውን ለሕዝብ ማሰቃያነት እንደሚፈቅዱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሏል


#AG7የአርበኞች áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ -እሁድ - ሚያዚያ - 08 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Sunday, April 9, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ


በደንቢያ ወረዳ ጎርጎራ አካባቢ በሚገኘው የቻይና ካምፕ ላይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ሃይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ኩባንያው ሰራተኞችንና መኪኖችን ወደ ቆላ ድባ ካስወጣ በሁዋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመጓዝ አካባቢውን ማረጋጋቱን በመግለጽ ኩባንያው ወደ ቦታው እንዲመለስ ቢያደርግም በድጋሚ በደረሰ ተጨማሪ የቦንብ ጥቃት ተሽከርካሪዎች እንደገና አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል።
የዕለተ - እሁድ - መጋቢት - 01 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Thursday, April 6, 2017

#ESAT የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር ዞን በደንቢያ ወረዳ ጩሃይት ከተማ መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓም ጀሪ ደበርጋ ጊዮርጊስ የተባለ ቤተክርስቲያን በአካባቢው በሰፈሩ ወታደሮች ተቃጥሏል።


ህዝቡ በድርጊቱ በመቆጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ወታደሮች ድርጊቱን የፈጸሙት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናቸው በማለት ህዝቡን ለማሳመን ቢሞክሩም ፣ ነዋሪዎች ግን አልተቀበሉትም። ወታደሮቹ ድርጊቱን የፈጸሙት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጋዮችን በህዝብ ለማስጠላት መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።በዚህ ወረዳ በቸንከር ቀበሌ ሌሊት 9፡15 ሲሆን ንብረትነቱ የህውሐት የሆነ እስካባተር መኪና በቦንብ ተመትቷል። በዛሬው እለት በሰራቫ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን፣ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሰዋል።

በሰንሜን ጎንደር ዞን በደንቢያ ወረዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጥቃት በመፈጸም በህወሀት ጦር ጉዳት አድርሷል።


#AG7የአርበኞች áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ - ሐሙስ - መጋቢት - 28- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Tuesday, April 4, 2017

በሰንሜን ጎንደር ዞን በደንቢያ ወረዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጥቃት በመፈጸም በህወሀት ጦር ላይ ከፍ ያለ ኪሳራ አደረሱ።


ታጋዮቹ በላኩት መግለጫ መጋቢት 25 ለ 26 ሌሊት ከ 7፡00 እስከ 9፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰራቫ ጣና በለስ መስኖ ፕሮጀክት ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  áˆ‹á‹­ መሽጎ በነበርው የህውሐት መከላከያ ሰራዊት ላይ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ ሁለት የገዥው ፓርቲ ወታደሮችን እና ሁለት የመከላከያ ሾፌሮችን ሲገድሉ በስድስት ወታደሮች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ አድርሰዋል።
የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው ወታደሮች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ከመካከላቸው ክፉኛ የቆሰሉት ሁልቱ ወታደሮች ማንቂያ ክፍል መሆናቸው ታውቋል።
በዚህ ድንገተኛ ጥቃት የወያኔ ወታደሮች ሲገለገሉባቸው የነበሩ ስድስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን፤ ሌሎች 11 ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።

Family to see illegally jailed Andy Tsege in Ethiopia after three years

በፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጎንደር ከተማ የቦንብ ጥቃት ተፈጸመ



#AG7የአርበኞች áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ - ማክሰኞ - መጋቢት - 26- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Sunday, April 2, 2017

Ethiopia - Public walking rally against the TPLF government: April 1, 20...

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በህወአት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ቀጥለውበታል



በ22/07/2009 ዓ/ም ሌሊት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ቃኚ ሀይል ለቅኝት በሚንቀሳቀስበት ሰዓት ከሌሊቱ 6፡00 ሲሆን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማን አለፍ ብሎ ከሚገኝው ቁልቋል በር ከከተባለው ቦታ ላይ ሲደርሱ የወያኔ ባለስልጣናትን የያዘ ደብል ጋቢና ፒክአፕ መኪና ለትራንፎርሜሽን እቅዱ መሳካት የተሰጠ የሚል ከጎኑ የተፃፈበት ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል።
 á‰ŁáˆˆáˆľáˆáŒŁáŠ‘ ቆስሎ ባህርዳር ሆስፒታል ለህክምና የገባ ሲሆን አጃቢው ሳጅን አለኸኝ የተባለው ተገድሏል የሟች አስከሬን ወደ አዲስ ዘመን ፎገራ ቀበሌ ለቀብር የተወሰደ ሲሆን ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካወጀበት ጊዜ አንስቶ የጤና ፤ የትምህርት ፤ ግብርና እና ሌሎች የሚንስትር መስሪያቤት በእርዳታ ያገኛቸውን ተሸከርካሪዎች ለፀጥታ ሾል በሚል ህብረተሰቡን ላማፈን ወታደሮች ለማመላለስ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ መስታውቱን ጥቁር በመለጠፍ ከውጭ ወደ ውስጥ ለማየት ፍፁም በሚከለክል ሁኔታ ለአፈናው በዋናነት እየተጠቀመባቸው ይገኛል ፡፡

Saturday, April 1, 2017

መከላከያ ሠራዊቱን የጫነ አንድ ኦራል ወታደራዊ ተሽከርካሪ ከ30 በላይ ወታደሮችን ከመተማ ወደ ቋራ ወረዳ በመጓዝ ላይ እያለ ለምለም ተራራ ላይ ሲደርስ በመገልበጡ ሁሉም ወታደሮች አልቀዋል።


#AG7የአርበኞች áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ እሁድ - መጋቢት - 24- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጥቃት መሰንዘራቸው ታወቀ ================================= ትላት ለሊት መጋቢት 22 ቀን 2009 ዓ/ም የአርበኞች ግንቦት 7 ቃኝ ሃይል በአገዛዙ ተሽከርካሪ ፒካፕ ደብል ገቢና ላይ በነበሩ የአገዛዙ ባለስልጣኖች ላይ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። https://ethsat.com/2017/04/tensae-radio-april-1-2017/

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም የህወሃትን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም ማስተማመኛ ሊሆን አይችልም!!! ==================


አርበኞች ግንቦት 7 ርእሰ አንቀፅ
የኢትዮጵያ ህዝብ ከ26 አመታት የህወሃት አገዛዝ በኋላ እየጠየቀ ያለው "በገዛ አገሬ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሬ ይቁም! አያት ቅድመ አያቶቼ በከፈሉት መስዋዕትነት የባዕድ ወረራን መክታ በነጻነት በኖረች አገሬ ለውጭ ባለሃብቶች እትብቴ ከተቀበረበት ቀዬ መፈናቀሌ ይብቃ! በመንግሥት ሚዲያዎች የሚለፈፈው ልማትና ዕድገት ተጠቃሚው ሥልጣንን የሙጥኝ ያላችሁት እናንተ የህወሃት ልጆችና በአገሪቱ ላይ ለምታካሂዱት ዘረፈ ብዙ የሃብት ዘረፋ ትርፍራፊ እየተወረወረላቸው ሽፋን የሆኑዋችሁ ከዚህም ከዚያም የተገኙ ጥቂት ለግል ጥቅም የተጠጉዋችሁ ግለሰቦች እንጂ እኛ አይደለንም ፤ በአለም አቀፍ ብድር ለተሰሩ ሰፋፊ መንገዶችና ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ለገነባችኋቸው ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ስንል ባርነትን በጸጋ አንቀበልም! ኢትዮጵያ የሁላችን እንጂ ነፍጥ ያነገቡ የትግራይ ተወላጆች የግል ሃብት አይደለችም" ፤ ወዘተ የሚል ነው።
የህወሃት አገዛዝ ለዚህ ፍትሃዊ የህዝብ ጥያቄ እየሰጠ ያለው ምላሽ ግን "ምን ታመጣለህ? ደርግን የመሰለ ዘመናዊ ጦር ያደራጀ ሃይል በነፍጥ አስወግጄ ሥልጣን የተቆጣጠርኩት አንተን ላነግስህ አይደለም፤ ወደድክም ጠላህ እኔው ነኝ እምገዛህ"! የሚል የእብሪት ተግባር ነው። የህወሃቱ ቁንጮ የነበረው መለሾ ዜናዊ "በደም ተዋጅተን ያመጣነውን ሥልጣን የሚመኝ ካለ እኛ በመጣንበት የአመጽ መንገድ ለመምጣት መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት" በማለት እንደተዛባበተብን ምን ጊዜም አንዘነጋውም። ድህረ መለሾ ዛሬ ሥልጣንን ከኋላ ሆነው እየዘወሩ ያሉት እነ ሳሞራ ይኑስ ፤ ጌታቸው አሰፋ፤ ስብሃት ነጋ ፤ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ፤ አርከበ ዕቁባይ፤ አባይ ወልዱ፤ አባይ ጸሃይ ወዘተ በፖለቲካ እይታቸው ብቻ ሳይሆን በትዕቢትና በእብሪት ደረጃቸው ከመለስ ዜናዊ የሚለዩ አይደሉም። ታላቋ ኢትዮጵያ ለነርሱ የሥልጣንና የሃብት ዘረፋ ጥገት ላም መሆኗን ባቆመች ሰዓት መጥፋት ይኖርባታል። በእውናቸውም በህልማቸውም ከዚህ የተለየ ራዕያ ያላቸው ስለመሆናቸው ቢያንስ ያለፈው 26 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ቆይታ አላረጋገጡም። አንድ አገር በደምና በሥጋ ያስተሳሰራቸውን ወንድማማች ህዝቦች በብሄርና በሃይማኖት በመከፋፈል የጠላትነት ግንብ በመካከላቸው ለመገንባት የተሰሠራው እና አሁንም በመሠራት ላይ ያለው የፖለቲካ ሼል ይህንን እምነታቸውን የሚያጋልጥ ነው። 
በተለይ የሁለቱን ታላላቅ ብሄረሰብ አባላት በዘር ለመለያየት የተሄደበት ረጂም ርቀትና የሁለቱን ታላላቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች እርስ በርስ በጥርጣሬና በስጋት እንዲተያዩ ማሴር በኢትዮጵያ ምድር የበቀለ ወገን ቀርቶ ለልሹ አገር ሠላም የሚሻ ጎረቤት አጋሪ እንኳ በእውን ሊያስበው የሚችል ተግባር አይደለም።
እጅግ የሚገርመው በእንዲህ አይነት የለየለት ጠላትነት መንፈስ ውስጥም ሆኖ ህዝባዊ ወያኔ ሃሪነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ የሚጠላትንና አገሬ ብሎ ለመጥራት የሚጸየፋትን አገር በጠመንጃ ሃይል እስከመጨረሻው ለመግዛት ያለውን ዕቅድ ለአፍታም ቢሆን ደብቆ አያውቅም። በዚህ ለዘመናት የመግዛት ዕቅዱ ውስጥ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው ሃይል በእርጅናና በሞት ሲለይ ተተኪ የሚሆን ትውልድ "የኔ ነው" ከሚለውን የትግራይ ክልል ለማፍራት የአገሪቱን ሃብት በሙሉ በመጠቀም በእውቀትና በገንዘብ ሌሎች የአገሪቱ ተወላጆች ሊደርሱባቸው የማይችል ዜጎችን የመፍጠር ሼል በትጋት እየተሰራ ነው። በዚህም የተነሳ ይህንን ዕቅድ ለማክሸፍ የሚንቀሳቀስ ሃይል እንዳይኖር ተቃውሞ ያነሳ ማኛውንም የአገሪቱ ዜጋ በሞት ሊቀጣ የሚችል በኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ገንዘብ ደመወዝ የሚቆረጥለት አጋዚ የተባለ ጦር ከተቋቋመ ሰንብቶአል።
በድህረ ምርጫ 97 ወቅት የገዛ ወገኑን አደባባይ ላይ በጠራራ ጸሃይ በመጨፍጨፍ አቅሙ እነ መለሾ ዜናዊን አንጄት ቅቤ ያራሰው ይህ አጋዚ ጦር ያኔ የሰበቀውን የግድያ ጎራዴ እስከዛሬ ድረስ ወደ አፎቱ አልመለሰም ። ከህዳር ወር 2008 ዓመተ ምህረት ወዲህ በኦሮሚያ ተጀምሮ ወደ አማራ ክልል የተዛመተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማክሸፍ ግዳጅ የተሰጠው ታማኝነቱንና አለኝታነቱን ላረጋገጠው ለዚሁ አጋዚ ለተባለው ጦር ነው ። ባለፈው አንድ አመት ብቻ አጋዚ በሁለቱ ክልሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በጥይት ደብድቦ ገድሎአል። በብዙ ሺ የሚቆጠሩትን ደግሞ ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች በማጓጓዝ አስሮአል፤ ገርፎአል፤ ለአካልና ለሂሊና ቁስል ዳርጎአቸዋል። በታሪካችን ተሰምቶ በማይታወቅ ጭካኔ ደምቢዶሎ ውስጥ ልጅ ገድሎ እናት የልጇ አስከሬን ላይ ቁጭ ብላ ግዲያውን እንድታወድስ ለማስገደድ ተችሎአል። ሰሞኑን የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበረው ወጣት ሃብታሙ አያለው እስር ቤት ውስጥ የተፈጸመበትን አሳዛኝ ሰቆቃ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ሲናገር ያልሰማ ሰው ትልቅ መረጃ አምልጦታል። "በወያኔ ዘመን ያልደረሰብን ንቀት፤ ውርደትና መከራ ምን አለ እና ነው መረጃ አመለጠ የሚያስብለ" ሊባል ይችል ይሆናል።
ሆኖም ግን ህወሃት ይህን ሁሉ መከራና ስቃይ የሚያፈራርቅብን ፤ ተቃዋሚዎቹ በሆን ዜጎች ላይ በታሪካችን ሰምተን የማናውቀው አይነት ሰቆቃ የሚያደርስብን በባሪያ ፈንጋይ ዘመን ባሮች ከጎቶቻቸው እንዳያመልጡ እኔን አይተህ ተቀጣ በሚሉት አይነት የቅጣት ዘዴ አርፈው እንዲገዙ ለማሸማቀቅ የተጠቀሙትን ዜደ በኛ ላይ በመጠቀም በፍርሃት እጃችንን አጣምረን እንድንገዛ ለማድረግ ነው። ይህ ከቶ ሊሆን አይችልም ። እንኳን የሰው ልጅ መብት አለም አቀፋዊ ጥበቃ ባገኘበት የ21ኛው ክፍል ዘመን እየኖርን ቀርቶ በዚያ በጨለማው ዘመን ለነጻነታቸውና ለክብራቸው ሲሉ ተዋግተው በወቅቱ በአለም ሃያል የነበሩትን የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎችን በሽንፈት የሸኙ የነ ቴዎድሮስ፤ ሚኒልክ፤ በላይ ዘለቀ ፤ አብዲሳ አጋ ፤ ሃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴና የእልፍ አዕላፍ ጄግኖች የታሪክ ወራሾች ብቻ ሳንሆን የነርሱ ወኔና ጀግንነት ዛሬም ድረስ በውስጣችን የሚቀጣጠል ነን።
አርበኞች ግንቦት 7 በጥጋብና እብሪት ተወጥሮ ህዝባችንን በማሰቃየት እስከ ወዲያኛው ለመግዛት የሚያስበውን የህወሃት አገዛዝ ለማስወገድና በምትኩ ፍትህ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈነበት ሥርዓት ለማስፈን ከህወሃት አገዛዝ ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ያለ አገራዊ ድርጅት ነው።
ህወሃት በመላው አገራችን ውስጥ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማክሸፍ ያስችለኛል ብሎ ያመነበትንና አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ አገዛዝ ሼር ያስገባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ካለፈው ጥቅምት ወር 2009 ጀምሮ በርካታ ግድያዎችን እየፈጸመ ያለው ለነጻነታቸው ሲሉ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ በሽብርተኝነትና በጸረ ሠላም ሃይል እየፈረጀ መሆኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንደ አርበኞች ግንቦት 7 አገራቸውንና ህዝባቸውን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ የተሰለፉትን ሃይሎች ለማዳከም ነው ብሎ ንቅናቄያችን ያምናል። ጉልበት ጉልበትን ፤ ግዲያ በቀልን እንደሚፈጥር ያልተረዳው የህወሃት አመራር 500ሺ ጦር ያለውን አምባገነን ሥርዓት ለመጣል የሄደበትንና የተጓዘበትን በማወደስ ከሚጠመድ የመሳሪያ ብዛትና የጦር ሠራዊት ጋጋታ በማያግደው የነጻነት ትግል ላለመበላት ወደ ሂሊናው ተመልሶ በሃይል የያዘውን ሥልጣን በክብር ለባለቤቱ ለሰፊው ህዝብ አሳልፎ ለመስጠት ቢያስብ የበለጠ ይጠቀምው ነበር።
ላለፈው 6 ወራት ሰላምና መረጋጋትን ያላመጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንኳን ለ4 ወር ለ4 አመት ቢራዘም የአዋጁ መራዘም ሊያስከትል በሚችለው ጦስ እንደ አረጀ ዛፍ ውስጥ ውስጡን በምስጥ ተበልቶ እንደሚወድቅ አወዳደቁን ያበላሻል እንጂ የሚያድነው አይሆንም። የአፈና መጠናከር የገታው የነጻነት ጉዞ በታሪክ አልተመዘገበምና የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም በምንም ምክንያት የወያኔን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም እንደማይችል አርበኞች ግንቦት 7 ያስገነዝባል።
ኢትዮጵያ አገራችንን ለመታደግና የተዋረደውን ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስመለስ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘን የህወሃትን አገዛዝ ፍጻሜ እናፋጥን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!