Thursday, March 30, 2017

ዛሬ የኢህአዴግ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ 4 ወራት እንዲራዘም ወስኗል ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

 አቶ ሲራጅ ለአዋጁ መራዘም እንደ ምክንያት ያቀረቡት “ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አሁንም ጸረ ሰላም ሃይሎች ይንቀሳቀሳሉ” የሚል ነው። በመላ አገሪቱ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ህዝቡ አዋጁ እንዲራዘም መጠየቁና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድም "አዋጁ ቢራዘም መልካም ነው" የሚል አስተያየት መስጠቱ ተገልጿል።Bilderesultat for fasil yenealem
ህወሃታውያን በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ “ ጸረ-ሰላም ሃይሎችን” በቁጥጥር ስር ማዋል ይችሉ እንደሆን እናያለን። ግን የገረመኝ የአርበኞች ግንቦት7 ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን ለይቶ ውሳኔ ማሰለፉን በሰማሁ በሰዓታት ውስጥ አዋጁ ለ4 ወራት የመራዘሙን ዜና መስማቴ ነው። ያጋጣሚ ነገር ይሆን ወይስ …?

በአንድ ቀን ሦስት የእሳት አደጋዎች በተለያዩ ከተሞች ተከስተው የሕወሃት እና ብአዴን ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

#AG7የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ ሐሙስ - መጋቢት - 21- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

ወያኔ ኢሕአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት ማራዘሙ ታወቀ



በኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወያኔ ኢሕአዴግ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት እንደተራዘመ አስታውቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያትና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲራዘም ያስፈለገበትን ምክንያት ብሎ ያቀረበውን ሀሳብ የአገዛዙ ልሳን የሆነው ፋና በዚህ መልኩ አቅርቧል።

Wednesday, March 29, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ህይል በተለያዩ ቀጠናዎች ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጸ

በሰሜን ጎንደር ኪንፋዝ በገላ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይል ጥቃት ሰነዘረ። ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የሚገኘው ግዚያዊ የወያኔ ጦር ካንፕ ላይ ሲሆን በጥቃቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ የተገለፀ ነገር ባይኖርም በዘመቻው የተሳተፉ ከፈተኛ መሆኑን ገልፀውልናል።
በተደጋጋሚ በተደረጉ ጥቃት በለስ የቀናው የአርበኞች ግንቦት7 ኃይል ወደ ሰሜን ጎንደር በችንፋስዝ በገና ሲናሬ ከተማ ዘልቀው በህወኃት ታጣቂዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በርካታ እስረኞችን ማስለቀቁ እና በከተማው ባሉ በወያኔ ታጣቂዎች እና የድርጅት አቅርቦት ዲፖ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ የህወኃት ወታደሮችን መገደላቸውን ዘግበናል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙ የሚያሳየው በወያኔ ላይ የያዘውን የወታደራዊ የበላይነት ነው፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር በሚወስደው ጥቃት የወያኔ የኃይል ሚዛን አሰላለፍ ያዛባና የውግያ ሞራል የወደቀ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Tuesday, March 28, 2017

የወጣት ማስተዋል እና የአምባሳደር ሀለቃ ፀጋይ ሙግት





ማስተዋል ጥላሁን በእስራኤል ነው የሚኖረው። ሰሞኑን ሀብታሙ አያሌው በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው ክፍለ ጊዜ ላይ ቀርቦ በእስር ቤት ውስጥ በእሱና በሌሎች ታሳሪዎች ላይ ስለሚፈጸመው ግፍ ሲናገር ውስጡ በከፍተኛ ቁጣና ንዴት የተሞላው ማስተዋል፤ ቀጥታ ቴላቪቭ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመሄድ በጽህፈት ቤቱ በር ላይ ተሰቅሎ የነበረውን ባለኮከቡን ባንዲራ አውርዶ በማቃጠል ነው ከቁጣው ለመብረድ የሞከረው።

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ ================================================ መግለጫ =====



#AG7የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ ማክሰኞ - መጋቢት - 19- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Sunday, March 26, 2017

"(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)" ******************************* ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ




የስልጣን ዕድሜን ከማራዘምና ከማራዘም ባለፈ ምንም አይነት ህልም የሌላቸው የወያኔው ቡድን ባለስልጣናት የህዝብና የአገርና ጥቅም ከቶ አይታሰብም። የህዝቡ የኑሮ መሻሻልና የመልካም አስተዳደር ባለቤትነት አስጨንቋቸው አያውቅም። የሃገር ሉዓላዊነት፣ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ወዘተ ለደቂቃም ቢሆን አሳስቧቸው አያውቅም። ስልጣናችንን ይጋፋናል ወይም ይነጥቀናል ብለው የሚሰጉት ማናቸውም በተናጥልም ሆነ በግል የሚደረጉ የህዝባዊ ወገንተኝነት እንቅስቃሴዎች ሁሉ ለማዳፈን የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም። ይገድላሉ፣ያስራሉ፣ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ ይደበድባሉ፣ያስፈራራሉ … በአጠቃላይ አገዛዙ ከህዝብ ጋር የሚያቆራኘውና በስልጣን እንዲቀጥል የሚያስችል ቅንጣት ታክል የሞራል ልዕልና የለውም። በተስፋ መቁረጥ ተዘፍቆ የሚያደርገው ጠፍቶት የሚባዝን ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ስርዓቱ ከሚታወቅበት መሰረታዊ አቋሙ ተንሸራቶ የባጥ የቆጡን ሲዘላብድ ለተመለከተው የዕውር ድንብር ጉዞ ውስጥ እንዳለ ይገነዘባል።
አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተመሰረተ አንስቶ አገርና ህዝብን እያጠፋ ካለው ወሮበላው የወያኔ ቡድን ጋር ሁለንተናዊ ትግል እያካሄደ ይገኛል። 
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለአንድ ሳምንት ባካሄደው ጥልቅ ስብሰባ የንቅናቄውን ስትራቴጂ የፈተሸበትና ወቅታዊ የአገራችንን ሁኔታ በስፋት የታየበት ሙሉ መግባባት የደረሰበት ነው። በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አጠቃላይ ተግዳሮቶችን ነቅሶ በማውጣት ለችግሮቹም የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀመጠበት ነው። በህዝባችን ላይ በሃይል የተጫነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንድምታ የተቃኘበትና ከአዋጁ ጋር በተያያዘ መሰራት ያለባቸውን ስራዎች የወሰነበት ነው። በተለይም አገር ውስጥ ባለው የሕዝባዊ አመጽና የሕዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ላይ አመራሩ ሙሉ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም የለውጥ ትግሉ ለማፋጠን በአገራዊ ወኔ ተነሳሽነት መንፈስ የተነሳበት ነው። በአገር ውስጥና በውጭ ያለው የፖለቲካ አሰላለፍ የታየበትና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ከወዲሁ እነደ ድርጅት በተናጥልና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ስምምነት የተደረሰበት ነው። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከንቅናቄው ስትራቴጂ በመነሳት የስራ ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ከስራው ጋር በተገናኘ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማደላደል በቁርጠኝነት መንፈስና በተናበበ አሰራር የአገር ውስጥ የለውጥ ትግሉ ከነበረው የበለጠ አቅም ለመገንባት የወሰነበት ነው። 
በአብዛኛው የአገራችን ኢትዮጵያ ክፍሎች ህዝቡ ያደረገውንና እያደረገ ያለውን ትግል ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በጭካኔና በጉልበት ለመቀልበስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጣ ቢሆንም ዛሬም ሕዝቡ ለመብቱና ለነጻነቱ ያለውን አይበገሬነት ከበፊቱ በተጠናከረና የወያኔን ጥቃት እንዳመጣጡ በመመከት አኩሪ ተጋድሎዎችን እያደረገ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ከህዝቡ ጋር በመሆን በሁለንተናዊ መልኩ የለውጥ ጥረቱን በመደገፍ፣ በማስተባበርና በመምራት ያለ የሌለ ሃይሉን በመጠቀም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ደራሽነቱን ያረጋግጣል።
አምባገነኑ አገዛዝ በህዝባችን ላይ በግፍ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለመታደግና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መላው የአገራችን ሕዝብ በህዝባዊ እምቢተኝነት፣ በህዝባዊ አሻጥር ፣በህዝባዊ አመጽና በውጪው ዓለም በሚደረገው አገር አድን እንቅስቃሴ ዛሬውኑ በመሳተፍ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣና የተቃዋሚ ሃይላት በትናንሽ ልዩነቶች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ተቀብለውና ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጎናጽፎ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ድርጅቶችን ለስልጣን እስከ ሚያወጣ ድረስ ልዩነቶቻቸውን አጥበው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ በጋራ እንዲነሱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል። 
 የስብሰባው ተሳታፊዎች ፡-
1, አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - ሊቀመንበር
2, አርበኛ ታጋይ መአዛው ጌጡ - ምክትል ሊቀመንበር
3, አርበኛ ታጋይ መንግስቱ ወልደስላሴ - የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
4, አርበኛ ታጋይ ገበየሁ አባጎራው - የመረጃና ደህንነት መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
5, አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኘ - የስልጠናና ትምህርት መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
6, አርበኛ ታጋይ ታሪኩ ግርማ - የአስተዳደር መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
7, አርበኛ ታጋይ ኮማንደር አሰፋ ማሩ - የወታደራዊ መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
8, አርበኛ ታጋይ ኑርጀባ አሰፋ - የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
አንድነት ሃይል ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
መጋቢት 16/2009 ዓ/ም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

#AG7የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ


በደብረ ዘይት የሚገኘው የወያኔ አየር ኃይል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሆነ ምንጮች ገለጹ
የዕለተ እሁድ - መጋቢት - 17- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Friday, March 24, 2017

#AG7የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ


የዕለተ አርብ - መጋቢት - 15- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት
የገጠሩ ህዝብ በወያኔ ኢህአዴግ ጥሪ መቀበል አቁሟል ሲሉ የወረዳ አመራሮች ተናገሩ

አየር ኃይል ውጥረት ውስጥ ገብቷል፤ 11 አብራሪዎች ታስረዋል

በደብረ ዘይት የሚገኘው የአየር ኃይል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሆነ ምንጮች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያውያን ፓይለቶች አታበሩም ተብለው ግራንድ ከተደረጉ በኋላ ከምስራቅ አውሮፓ የመጡ ቅጥረኞች ብቻ እንዲያበሩ መወሰኑን ተከትሎ 40 የሚሆኑ አብራሪዎች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፤ መልቀቂያ ያስቡት አብራሪዎች ግዳጃቸው እስከሚቀጥለው ሐምሌ ወር ድረስ ብቻ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡
የአገልግሎት ጊዜያቸው ገና በመሆኑ ምክንያት መልቀቅ የማይችሉት አብራሪዎች ሥራቸውን ጥለው እየጠፉ እንደሆነ የሚናገሩት የመረጃ ምንጮች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አራት የዐማራና ሰባት የኦሮሞ ተወላጅ አብራሪዎች ሲጠፉ ተይዘው ታስረዋል ተብሏል፡፡ ከታሰሩት አብራሪዎች መካከል አንድ የዐማራ ተወላጅ አብራሪ የደረሰበት እንደማይታወቅና ከጎንደር የሔዱ ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሊያገኙት እንዳልቻሉ ነው የተነገረው፡፡

Thursday, March 23, 2017

አርበኞች ግንቦት7 ጥቃት መሰንዘሩ ታወቀ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ እና ሌሎች አካባቢዎች ባካሄደው ጥቃት የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ተገድለዋል ጥቃቱ የተሰነዘረው በመከላከያ በጸረ-ሽምቅ ሚሊሺያዎችና መደበኛ የፖሊስ አባላት ላይ መሆኑን ምንጮችን ገልጸዋል።
በዚሁ ተከታታት ጥቃትም አካባቢውን ጥለው የሸሹ የስርዓቱ ታጣቂዎች በርካታ ናቸው ተብሏልንቅናቄው በሰሜን ጎንደር በጀመረው በዚሁ ጥቃት 3 ወታደሮች ወዲያውኑ ሲገደሉ ሌሎች ሃኪም ቤት ከገቡ በኋላ የሞቱም እንዳሉ ምንጮች ይጠቅሳሉ።
በተለይ በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ ገደብዬ በተባለች ከተማ በተወሰደው የሽምቅ ጥቃት የአካባቢው ፖሊስ ጽ/ቤት ላይ ጉዳት ደርሷል። በከተማዋ የነበሩት የመከላከያ፣ የጸረ-ሽምቅ እና የፖሊስ ሰራዊት አባላት ለጥቃቱ የተኩስ ምላሽ በመስጠታቸው ውጊያ እንደ ነበር ተገልጿል።
መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓም የግንባሩ ታጋዮች ወደ ጋይንት ከተማ በመግባት ከምሽቱ 2 ሰአት ተኩል ላይ በብአዴን ጽ/ቤት እና ሹመት በተባለው አስተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ መኖሪያ ቤት ላይ ቦንብ በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸውንና ማሽቱም በተኩስ ሲናወጥ ማደሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ከተማ አካባቢ ዳንጉላ ጭንጫዬ በተባለ ቦታ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሸማቂዎችን ለማጥቃት በተደረገ ጥቃት የአገዛዙ ታጣቂዎች ቆስለው የአካባቢው አመራር የነበረው አበበ ታከለ መገደሉ ተነግሯል።
በታጋዮቹ ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ድርጅቱ አስታውቋል።

ታላቅ የድል ዜና!


ስሙን ቆየት ብለን የምንጠቅሰው አንድ ከተማ ላይ በወያኔ ሰራዊት ላይ ሁለት ሌሊት የፈጀ ጥቃት ተሰንዝሯል! ይህ በአይነቱም በመጠኑም ከበድ ያለው ምት ወያኔን ክፉኛ አሸብሯል። ጥቃቱን ያደረሱት ጀግኖች የመንግስትን ጣብያ ሁለት ሌሊት ሙሉ ሲቆሉት አድረው በድል ተመልሰዋል። ይህ የህዝባዊ ትግሉ ያለበትን እመርታ ያሳያል። ዝርዝር ጉዳዮች መዘግየታቸውን አሁንም አስፈላጊነቱን ተቀበሉን።
የነፃነትን ጥያቄ በአፈና ማስቆም እንደማይቻል ወያኔና ጀሌወቹ እየመረራቸውም እየተጋቱት ነው። በማእከላዊና በሌሎች ማሰቃያወች እያደረሱት ያሉት እጅግ አረመኔያዊ ስቃይ ከሰማይም ከምድርም ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም።
ጀግና የማይነጥፍ ሃገር አለንና ደስ ይበላቹህ! ከጎናቸው እንቁም። አምላክ ለተገፋው ህዝባችን የመጨረሻዋን ድል ያጎናፅፍልን።
Asnakew Abebe

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



የዕለተ ሐሙስ- መጋቢት - 14- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Wednesday, March 22, 2017

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ March 21, 2017


መጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ. ም.

ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሠራዊት አባላት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር በህወሓት/ኢህአዴግ የአገዛዝ ሥርዓት ተቋማት ላይ የተቀናጀ የሽምቅ ጥቃት አድርሰዋል። በማክሰኝት፣ በደጎማ፣ በጯሂት፣ በደንቀዝን፣ በበለሳ፣ በአዲስ ወረዳ፣ በደንቢያ፣ አገዛዙ ቀይ ቀጠና ብሎ በሰየመው በመተማ መስመር በጭልጋ ወረዳ፤ በቆላድባ፣ አብራጂራ፣ በቸንከር ቀበሌ በአገዛዙ የፓሊስ ጣቢያዎችና የጦር ሠራዊት ካምፓች እንዲሁም ቀንደኛ የሥርዓቱ አገልጋዮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝሯል፤ በሕዝብ ላይ በደል ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ የሥርዓቱ ቀንደኛ አራማጆች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል። ስለእነዚህ እርምጃዎች በወቅቱ መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያሻም።
ይህ የፍፃሜው ጅማሮ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ህወሓት/ኢህአዴግን በማስወገድ ሕዝብ የፓለቲካ ስልጣን ባለቤት ለማድረግ በሚደረግ ትግል ውስጥ ራሱን ለመስዋዕትነት በግንባር ቀደምትነት አሰልፏል፤ የትግሉ ባለቤት ግን ሕዝቡ ራሱ ነው።
እስካሁን በጎንደር በተደረጉ ትግሎች የታየው የሕዝብ ንቁ ተሳትፎ አበረታች ነው። የጎንደር ሕዝብ ከአብራኩ የወጡትን የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን በመረጃ፣ በስንቅና በቀጥታ በውጊያ በመሳተፍ ረድቷል። ሲራቡ እያበላ፣ ሲቆስሉ እያስታመመ፣ መንገድ እየመራ ግዳጆቻቸውን በስኬት እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል። በተለይ እሁድ መጋቢት 03 ቀን በጎንደር አጼ ፋሲለደስ ስታዲዮም የተገኘው ሕዝብ የአገዛዙን ዛቻ ሳይፈራ ለታጋይ አርበኛ ጎቤ መልኬ የህሊና ፀሎት ማድረጉ ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኗል። ሰሞኑን እየተወሰዱ ያሉትን ዓይነት የሕዝባዊ አመጽ እርምጃዎች ከጎንደር በተጨማሪ ወደ ሌሎችም የአገሪቱ ግዛቶች እንዲስፋፋ ማድረግ ይገባል።

የአገዛዙ ሠራዊት በርካታ አባላትም ታጋዮችን እያዩ እንዳላዩ በማሳለፍ፤ ጥይት አየር ላይ በመተኮስ እና የይስሙላ አሰሳዎችን በማድረግ አባል በሆኑበት ፋሽስታዊ ሠራዊት ላይ ሕዝባዊ የሆነ አሻጥር በመፈፀም ተባብረዋል። ከፊሎች ደግሞ ከዚህም በላይ በመሄድ መረጃ በማቀበል በውስጥ አርበኝነት አገልግለዋል፤ እያገለገሉም ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ለእነዚህ የሠራዊቱ አባላት ያለውን አድናቆትና ክብር ይገልፃል። ለወደፊቱ ከዚህ በላይ የሆነ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል። ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችን ናት፤ የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ስም ይዞ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ጥቅምና ሥልጣን መቆሙ ማብቃት አለበት። በአገዛዙ የጦር ሠራዊት ውስጥ ያለውን የሀሳብ ልዩነት አርበኞች ግንቦት 7 በቅርበት ይከታተላል። “እኛ ሠራዊቱን የተቀላቀልነው ወራሪ ጠላትን ለመከላከል እንጂ መብቶቻቸውን የጠየቁ ዜጎችን ለመፍጀት አይደለም” በማለት የሚከራከሩ የሠራዊቱ አባላት እንዳሉ ንቅናቄዓችን ያውቃል። እነዚህ የሠራዊቱ ወገኖች አብዛኛውን ሠራዊት ለማሳመን እንዲጥሩ ያ ካልሆነም ሠራዊቱን ጥለው በመውጣት ንቅናቄዓችንን እንዲቀላቀሉ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
የህወሓት ተቀጥያ እና ግንባር ቀደም አጋር በሆነው ብአዴን ውስጥም የሕዝብ እሮሮና እንባ እረፍት የሚነሳቸው ወገኖች እንዳሉ ይታወቃል። እነዚህ ወገኖች የህወሓት ሎሌዎች በሆኑ የብአዴን አባላት እየተመነጠሩ ከሥልጣንና ከሥራ እንደሚባረሩ፣ እንደሚታሰሩና እንደሚሰደዱ እያየን ነው። ልቦና ያላቸው የብአዴን አባላት ከሕዝብ ጎን ለመሰለፍ ከአሁን የተመቸ ጊዜ ላያገኙ ይችላሉ፤ ስለሆነም ዛሬውኑ ጎራቸውን እንዲለዩ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደረጋል።
በህወሓት የአገዛዝ ዘመን በአማራ ሕዝብ ላይ የደረሰው በደል ዘርፈ ብዙ ነው። መሬቱ ተዘርፏል፤ ማንነቱ ተደፍሯል፤ በገዛ አገሩ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዜጋ እንዲሆን ክብሩ ተዋርዷል። አማራን እርስ በርሱ በማጣላት እንዲዳከም ብዙ ተዶልቷል፤ እየተዶለተም ነው። በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የዚህ ሁሉ በደል ማብቂያ ቁልፍ መፍትሄ ህወሓትን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ስልጣን ማስወገድ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ በስልጣን ወንበር ላይ እስካለ ድረስ ማናቸውም ዓይነት መብቶች አይከበሩም። በህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የስብዕናና የዜግነት መብትን መጠየቅ በሽብርተኝነት የሚያስከስስ ወንጀል ነው። በህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ሥር ሆነን መብትን ለማስከበር የምናደርገው ትግል የትም አያደርሰንም፤ ያለን መፍትሄ አገዛዙን ማስወገድ ነው። በዚህም ምክንያት መብቶቻችንን ለማስከበር ተገደን ወደ ጦርነት ገብተናል። ድል እስከምናደርግ ድረስ የሚቆም አይደለም። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ የማውጣት ኃላፊነት የወደቀው በአማራ ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ላይ ነው። ስለሆነም አገዛዙን ለማስወገድ የሚደረገው ተጋድሎ ከአማራ ውጭ ወደሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች እንዲስፋፋ አርበኞች ግንቦት 7 ጠንክሮ ይሠራል። መላዋ ኢትዮጵያ ነፃ ካልወጣች አንድ አካባቢ ብቻ ተለይቶ ነፃ ሊወጣ አይችልም።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በታጋይ ወላጆች፣ አያቶች፣ አጎቶች፣ ባለቤቶችና ሕፃናት ልጆች ላይ ፋሺስታዊ ጥቃት ማድረስ እየበረከተ መጥቷል። የበርካታ ታጋዮች ሕፃናት ልጆች ተደብደበዋል፣ ታስረዋል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶቻቸው ተግዘዋል። በአርበኛ ታጋይ ቤተሰቦች ላይ የበቀል እርምጃ በሚወስዱ የሥርዓቱ አገልጋዮች ላይ ምህረት የለሽ አፀፋ የሚሰጥ መሆኑን በደል ፈፃሚዎች እንዲገነዘቡ አርበኞች ግንቦት 7 በጥብቅ ያሳስባል። አርበኞች ግንቦት 7 እንዲህ ዓይነት እጅግ ኃላቀር የሆነ የበቀል ሥርዓት ፈፃሚዎችን ከመቅጣት እንደማይመለስ እንዲያውቁት በአጽንዖት ያስገነዝባል።
ባለፉት ዓመታት ሞቅ ደመቅ ሲል የቆየው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በተደራጀና በተጠናከረ መንገድ እንደገና እንዲቀሰቀስ የማደራጀት፣ የማስተባበርና በግንባር ቀደም የመምራት ተግባር እንዲያከናውኑ አርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎቹን ያሳስባል። ከእንግዲህ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ተደጋግፈው እንዲሄዱ ይደረጋል።
ዛሬ እያንዳንንዱ ኢትዮጵያዊ ጎራውን እንዲለይ የሚጠየቅበት ወቅት ላይ ተደርሷል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውሳኔውን ራሱ መስጠት አለበት። ምርጫው ሁለት ነው። አንደኛው አማራጭ ከበዳዮች፣ ዘራፊዎች፣ ገዳዮች ከሆኑት ህወሓት እና እሱ የፈጠራቸው ድርጅቶች ጎን መቆም ነው። ሁለተኛው አማራጭ ሕዝብን ለስልጣን ባለቤትነት ለማብቃት መስዋትነት እየከፈሉ ካሉት አርበኞች ግንቦት 7 እና አጋሮቹ ጎን መቆም ነው። ሦስተኛ አማራጭ የለም።
በዚህም ምክንያት በግል ተነሳሽነት ጭምር የተሰባሰባችሁ ወገኖች በድርጅት በመታቀፍ ውጤት ለሚያመጣ የጋራ ትግል ኃይላችሁን አስተባብሩ። የተናጠል ትግል እምንመኘው ግብ እንደማያደርሰን ተገንዝበናል። ስለሆነም መተባበር ብቻ ሳይሆን በድርጅት ታቅፎ መታገልን ባህል እናድርገው። በጋራ ትግል አምባገነኑን የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝን አስወግደን የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት እናድርግ።
አንድነት ኃይል ነው !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Tuesday, March 21, 2017

ህዝብን መግደል ይቁም

#Ethiopiaበወያኔ መከላከያ ሰራዊት ተሰግስገው የኢትዮጵያን ህዝብ በመግደልና በማሰቃየት ላይ የሚገኘው ይህ የአገርና የህዝት ጠላት በመሆን የጠባብ ቡድኞችን አጀንዳ የሚያራምዱ ከወታደራዊ ግዳጅ ውጭ የጥቂት ግለሰብና መንደርተኞች የነሱ የግል ጠባቂ ገዳይና አስገዳይ በመሆን እጅግ ኣሳፋሪና ታሪክ ይቅር የማይለው በህዝብና አገር ላይ የሚፈጸም ትልቅ ደባ ነው።

ይህንን እጅግ አሳፋሪ ለአገርና ለህዝብ የገባችሁት ቃል ኪዳን ወደ ጎን የተዋችሁ መሆኑን አውቃችሁ አሁንም ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡና ከሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንድትቆሙ በተለያየ ግዜ ጥሪ መተላለፉ የሚታወስ ሲሆን አሁም ግዜው ሳይመሽ ከነጻነት ሃይሉ ጎን እንድትቆሙ አፈሙዙን በዚህ ዘረኛና ፋሽሽት የህወአት ቡድን ላይ እንድታዞሩ ያለዛ የከፋ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ወቅቱና ግዜው ከናንተ የሚፈለግ አገብጋቢ ጉዳይ ነው።
እትዮጵያን ከዘረኞች እናጽዳ !
ሞት ለዘረኛው ፋሽሽታዊ ወንበዴ የትግራይ ቡድን !

አርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ አበበ ቦጋለ – ከሕብር ራድዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

አራት ወሳኝ ጥያቄዎች ለአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ አበበ ቦጋለ – 

አራት ወሳኝ ጥያቄዎች ለአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ አበበ ቦጋለ ልዩ ቃለምልልስ

አራት ወሳኝ ጥያቄዎች ለአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ አበበ ቦጋለ – ከሕብር ራድዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ | ሊደመጥ የሚገባው ልዩ ቃለምልልስ

ኢሳት የትምህርት ብልጭታ ስለ አሻጥር እና ሕዝባዊ አሻጥር አዘጋጅና አቅራቢ፡ ዶ/ር ታደሰ ብሩ

#AG7የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



በደቡብ ወሎ በደሴ ከተማ ማረሚያ ቤቱ ተሰብሮ እስረኞች ማምለጣቸው ታወቀ
የዕለተ ማክሰኞ- መጋቢት - 12- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Friday, March 10, 2017

ሰበር ዜና የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች ወደ ሰሜን ጎንደር ወረዳ ወረዳ ዘልቀው በመግባት በችንፋስዝ በገና ሲናሬ ከተማ በህወኃት ታጣቂዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በርካታ እስረኞችን አስለቀቁ። ታጣቂዎቹ ትናንት ምሽት ከ4፡00 ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በከተማዋ ባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ የህወኃት ወታደሮችን የደመሠሱ ሲሆን የተወሰኑ የከተማዋ መንግስታዊ ወታደሮች ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ሽፋን በመስጠት በህወኃት ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።

በአማራ ክልል ጋዜጠኞች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ አሰሙ



የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ አርብ- መጋቢት - 01- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ጎንደር ጥቃት ፈጽሞ እስረኞችን አስለቀቀ


የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይሎች በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ ችንፋዝ በገና ሲናሪክ ከተማ ሰርገው በመግባት በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስለቀቁ።
ታጋዮቹ ትናንት የካቲት 30: 2009 አም ምሽት ከ4 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት በከተማ ባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ገድለዋል።
የተወሰኑ የከተማዋ ታጣቂዎች ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ድጋፍ በመስጠት በህወሃት ኢህአዴግ ወታድሮች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ከፊሎችም የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎችን ተቀላቅለዋል።
በዚሁ ጥቃት የተደናገጠው የህወሃት/ኢህአዲግ ጦር ተጨማሪ ወታደሮች በ5 ኦራል መኪኖች ወደ ከተማዋ በማስገባቱ ውጊያው ተፋፍሞ እንደነበረ ምንጮቻችን ገልጸዋል። አርበኞችም ግዳጃቸውን ፈጽመው ወደመጡበት መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ነጋዴ ባህር በተባለው አካባቢና በህወሃት/ኢህአዴግ ቀይ ዞን ተብሎ በተሰየመ ቦታ በአንድ ነዳጅ ጭኖ ከሱዳን በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በዚሁ ጥቃት መነሻነትም ከ50 በላይ ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ነጋዴ ባህር ላይ ቆመው እንንደሚገኙ የኢሳት ምንጮች አስታውቀዋል። ጉዳዩ ያስጨነቃቸው የህወሃት የመከላከላ የጦር አባላት ጀኔራል ሲሳይ በተባሉ አዛዥ ተመርተው ወደ አካባቢው ማምራታቸው ተነግሯል።
ጄኔራሉ በጸጥታ ስጋት ነጋዴ ባህር ላይ የቆሙት 50 ነዳጅ የጫኑ መኪኖች ጉዞ እንዲጀምሩ ትዕዛዝ ቢሰጡም ሹፌሮቹ ፈቃደኛ አለመሆናቸን ለማወቅ ተችሏል። በዚሁ ምክንያት ጀኔራሉ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አንፈልግም በሚል ሹፌሮቹ ተሽከርካሪዎቻቸውን እንዲያንቀሳቅሱ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Thursday, March 9, 2017

Wednesday, March 8, 2017

ለነጻነት በሚደረገው ትግል ኢትዮጵያውያን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

ለነጻነት በሚደርገው ትግል ኢትዮጵያውያን በአቅማቸውና በሙያቸው አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ።
በአራት ድርጅቶች በቅርቡ የተመሰረተው ሃገራዊ ንቅናቄ በዋሽንግተን ዲሲ  ከኢትዮጵያን ጋር ባካሄደው ውይይት በሀገሪቱ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መሰረት ያደረገ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

Saturday, March 4, 2017

Yeserawitu Dimits in collaboration with ESAT Sat 04 Mar 2017

‹‹ስለ እኔ አታልቅሱ!›› by MulukenTesfaw


Image may contain: 1 personየሚፈግ እሳት፤ የማይጠፋ ፋና! አርበኛ ሰማዕት ጎቤ መልኬ (ከ1958 – 2009 ዓ/ም)
ምን ብየ እንደምጀምር አላውቅም፤ ግን እኛ ‹‹ዋዋ›› እያልን ለምንጠራው አባታችን
ቤተሰቦቹ ደግሞ ‹ጃውይ› እያሉ በፍቅር ለሚጠሩት የዘመናችን ታላቅ ሰማዕት የ51
ዓመቱ ጎቤ መልኬ መናገር አለበኝ፡፡ አዎ! ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም
ከሕይወቴ እኩይ ቀኖች በቅድሚያ እመድባታለሁ፤ ተደጋግሞ የተደወለ የስልክ ጥሪ
ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፤ ከስልኩ የሰማሁት ነገር መንቃቴን መልሼ እንድጠራጠር አደረገኝ፤
ምናለ በሕልሜ በሆነ አልኩ!
የአንዳንድ ሰዎች የወገን ፍቅር ይገርመኛል! ሀብትና ንብረት ግድ የማይሰጣቸው ጥቂት
ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ሕይወታቸውን ለወገን አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች ግን ጥቂቶች
ናቸው፡፡ ለእኔ አርበኛው ጎቤ መልኬ እንደዚያ ነው፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ድንበር ላይ የተነሳው ግጭት በቀል በበላይነት የሚቆጣጠረው የደቡብ ምስራቅ እዝ አዛዥ መሆኑ ታወቀ

ሕወሓትበቀጣይነት በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል አዲስ ግጭት ለማስነሳት ማቀዱን ታናግረዋል።

የደቡብ ምስራቅ እዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የበቀል እርምጃ አንዲወስድ ከሳሞራ የኑስ መታዘዙን ወታደራዊ ደህንነቶች ከእዙ ያደረሱት መረጃ ገልጿል።የመረጃ ደንበኞች የሆኑትና ካሁን ቀደም የተለያየ መረጃዎችን የሚያደርሱን ወታደራዊ ደህንነቶች እንደጠቆሙት የእዙ ወታደሮች ተመርጠው የልዩ ሃይሉን ልብስ በመልበስ በ አከባቢው የኦሮሞ ተወላጆች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Friday, March 3, 2017

ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸው ክስ በችሎት ተነበበላቸው - የካቲት 24/2009 *ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።


Bilderesultat for merera gudinaዶ/ር መረራ ለሶስት ወር በማእከላዊ ሲመረመሩ ከቆዩ በኋላ በባለፈው ሳምንት ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል። ክሱ የደረሳቸው ቢሆንም በችሎት እንዲነበብላቸው ለዛሬ የካቲት 24, 2009 ቀጠሮ ተይዞ ነበር። በዶ/ር መረራ ጉዲና ስም የተከፈተው መዝገብ፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ፤ ኦኤምኤን እና ኢሳት የቴሌቭዥን ጣቢያዎችንም አካቷል። በመዝገቡ በአጠቃላይ አራት ክሶች የቀረቡ ሲሆን ከቀረቡት ክሶች ሁለቱ ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ብቻ የቀረቡ ሲሆን አንድ ክስ ሶስቱም (በዶ/ር መረራ ፣ ፕ/ር ብርሃኑ እና አቶ ጃዋር) እንዲሁም ቀሪው ክስ (የሽብር ክስ) ኢሳት እና ኦኤምኤን ላይ የቀረበ ነው።

ኮማንድ ፖስቱ በጎንደርና በባህር ዳር ተጨማሪ ተጽኖ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የዕለተ አርብ - የካቲት - 24- ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት፡


Thursday, March 2, 2017

ሜሮን ጌትነት


እንደማንኛውም
ኢትዮጵያዊ....በእድልህ
ልታድግ "በእድሉ"ተብለህ
ትወለዳለህ።ቂጣና ቆሎህን
እያሻመድክ.....በኩርኩ ም
የሳምንት ውሎህን እስክትረሳ
እየተቆጋክ......።
.
.
ትንሽ ከፍ ስትል ቄስዬ
ትላካለህ....ሃ...ሁ ...በል ኣቦጊዳ
ቀጥል "መልእክተ ሃዋርያው
ወልደ ዘብዲዎስ ቀዳማዊ
ንዜ....." ዝለቅ እንግዲ
እየተባልክ ካለልህም እየተባልክ ካለልህም A=for
apple ን እየሸመደድክ
.....ተማረ ከተማረረ
እየተቀላቀለብህ ደረጃ ቆጥረህ
ትጨርሳለህ....
.
.
ትመረቃለህ
.
.
ለምርቃት የገዛሃት ሾዳ
እስክትተን...ስራ ፍለጋ
ትባዝናለህ
.
.
ስራ ትገባለህ
.
.
ከደመወዝህ ጋ ከወር ወር
ኣብረህ ለመቆየት......ከባድ
ፊዚክስ እንደሚበታትን ሰው.....
መከራህን ትበላለህ
.
.
ትበደራለህ
.
.
ኣብራህ ቢሮክ ውስጥ
ምትሰራውን ቸከስ ኣልያም
በባስ ስትሄድ የተዋወካትን
ዘይት ቆጣቢ የመሰለችህ ቺክ
ጋር ትጠቃለልና.....ልጆች
ትወልዳለህ...እነሱን ለማሳደግ
ኣፈር ትበላታለህ።
.
.
.
ወይንም ደሞ
.
ቂጥህን ወትፈህ ትሰራለህ.....
ትቆጥባለህ 24 ሰኣት
ትጠገራረለህ....
.
.
ወንጀል ትሰራለህ....መንግስት
ታጭበረብራለህ.....ትዘ
ርፋለህ...ግፍ ትሰራለህ
....የራስህን ጥቅም ለሟሟላት
ሰው ታስለቅሳለህ....ሆድህን
ሞልተሃል ...ፅዳ ያለ ቤት
ኣለክ....መኪናና ሸሚዝህ ማች
ነው..... ኣልፎልሃል!!
.
.
ትኖር ትኖርና...ታኗኑርና... ወደ
ማይቀርልህ ቤት
ትነካዋለህ.....ወይ መኪና ኣደጋ
ይደርስብሃል....ወይ ትናንት
ታይተህ በሳይለንት
ትነካዋለህ.....ወይ ደም ግፊትህ
ኣናትህ ላይ ወቶ ጠብ
ያደርግሃል....ኣልያ ጊዜው ደርሶ
ነው ከሞት የሚቀር የለም
በሚለው.....ፅጥ!!!
.
.
ፎቶህ በትልቁ ይታጠባል!!
.
.
ምፅ!!
ቤተሰብ ይደዋወልና
ይሰባሰባል.....
.
.
ጋቢያቸውን ለብሰው
ያለቅሱልሃል...ልጆችህ ኣባዬ
ኣባዬ...ሚስትህ ከለላዬ
...ጓደኞች ጓዴ ጓዴ
.
.
ምፅ!! ሲያሳዝኑ
.
.
ትገነዛለህ.... ኣራት ማዕዘን
ሳጥን ውስጥ ተሸፋፍነህ
ትገባለህ.....ኣንዳች እንኳ
ስልጣን የለህም በራስህ
ላይ....ከነበሩህ ነገሮች ሁላ
የሚወዱህ የነበሩት
ኣይከተሉህም።
.
.
ከምትወዳቸው ደሞ
ኣንዳቸውንም ኣጠገብህ
ማድረግ ኣትችልም።
.
.
ትቀበራለህ!!!!
የምር ምፅ!
.
.
ቀባሪዎችህ.... በቤትህ
የተዘጋጀውን ፅበል
ይቀምሳሉ....ነብስ
ይማር...ምናምን ይባልልሃል!
.
.
ማታ ላይ ድንኳን ውስጥ ካርታ
ይደራል። ቢራ
ይጨለጣል...ይሳቃል...
ይበላል....
.
.
3 ቀን ሲሞላህ ድንኳንህ
ይፈርሳል....ሰው ቀስ በቀስ
ይመናመናል።
.
.
ኑሮ ይቀጥላል!!
.
ህዝቤ ወደ ሌላ ለቅሶ ...ወደ ሌላ
ጉዳይ...አንተ
ተረስተሃል....ሚስትህን
ም...ልጆችህንም የእገሌ ልጅና
የእገሌ ሚስት ይቀርና የሟቹ
ልጆች ....ይባሉልሃል።
.
.
.
.
እና ሟቹ ሆይ ምን ልልህ
መሰለህ?
.
.
ኣንዳንዱ ሰው እንኳንስ
ሞቶ....ኖሮም ታሪክ የለውም!!
ምናልባት ታሪኩ የሚባል ስም
እንጂ!!
.
.
የእኛ ኣባቶች....ግን ለነብሳቸው
እንኳ ሳይሳሱ ከራስ ፍቅር
የሃገር ፍቅርን
ኣስበልጠው....በዱር በገደል
ተዋድቀው....ጠላትን ድል
ነስተው ከመገዛት ....ከባርነት...
ደም ከፍለው ቀና ብለን
እንድንኖር ነፃ ኣውጥተውናል
....ደም ተከፍሎልናል።
.
.
"እየገባን እንጂ ወገን"
.
.
...ሞትና እና ሞትም ይለያያል
ዘመዴ!!!
.
.
.
.
ክብር ከመቃብር በላይ ዘላለም
ለሚኖር ስማቸው.....ክብር
ለጀግኖች ኣባቶቻችን!!!

እንኳን ለ121ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም በክብር አደረሰን!!! ክብርና ሞገስ ለአድዋ ጀግኖች አባቶቻችን!!!



አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



Wednesday, March 1, 2017

Abbay Media is Back

AG7 Public Meeting in Bergen - Norway - 4 March 2017

ጋዜጠኛ አበበ ገላው

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍና በደል በገጠመው በዚህ የጨለማ ዘመን፤ ህዝባችን በህወሃቶች እየተጨፈጨፈ፣ እየተዘረፈና በጅምላ እስር ቤት እየታጎረ ሰቆቃ በሚፈጸምበት በዚህ ክፉ ጊዜ ህዝብን አስተባብሮ ከማታገል ይልቅ መከፋፈል፣ ከማስማማት ይልቅ ማናቆርና የዘር መርዝ በመርጨት ትግሉን የሚያዳክሙ የውስጥ አርበኞች በቃ ሊባሉ ይገባል።
ህዝብን የሚከፋፍሉ፣ መርዘኛ ጥላቻና አለመተማመን ለመርጨት በከንቱ ጊዜ ለሚያጠፉ የቀበሮ ባህታዊያን ጊዜና ትኩረት መስጠት አይገባንም። ትግላችን ከፋሺስቱ የህወሃት ስርአት ጋር እንጂ ከተራ አሉባለተኞች ጋር አለመሆኑ አይዘንጋ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ደጋግሞ ታሪክ የሰራው በህብረት እንጂ በመከፋፈል አይደለም። በየአቅጣጫው የተጀረው ትግል ከዳር እንዲደርስ ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በያለበት የሚቻለውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብ።Resultado de imagen de ጋዜጠኛ አበበ ገላው