Monday, January 30, 2017

በአዲስ አበባ በ13 ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተናል ይላሉ

በአዲስ አበባ ከወረዳ አንድ እስከ ወረዳ 13 ባሉ አካባቢዎች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤታቸው እንደሚፈናቀሉ ከተነገራቸው በሁዋላ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። ነዋሪዎች እንደገለጹት ከአራት ቀናት በፊት ባለስልጣናቱ መሬቱ ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋል በሚል ቤታቸው እንደሚፈርስባቸው ሰብስበው ነግረዋቸዋል።
http://amharic.abbaymedia.com/%
ይህን ተከትሎም ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ለረጅም ጊዜ የኖርንበትን ቀዬ ትለቃላችሁ በመባላችን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ የሚፈናቀሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አርሶአደሮችም ጭምር ናቸው።

Sunday, January 29, 2017

Professor Berhanu Nega on State of Emergency | RFI

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



የዕለተ እሁድ፡ጥር 21 ቀን፡ 2009 የሬድዮ ስርጭት፡

ለቅሶህም ለቅሶዬ ነው ! ======//========


No automatic alt text available.መግቢያ፡ በየሣምንቱ ቅዳሜ በንቃት ከማዳምጣቸው የሬዲዮ አገልግሎት ሥርጭቶች አንዱና ዋነኛው በሻለቃ አብረሃም ታከለ አዘጋጅነትና አቅራቢነት የሚሰራጨውን የሠራዊቱ ድምፅ ነው ። ለምን ? ይህ ሬዲዮ የእኔና እኔን የመሰሉ የቀድሞው ሠራዊት አባል ልጆች ድምፅም ጭምር በመሆኑ ነው። ስለ ሠራዊቱም መስዋዕትነትና ተጋድሎ ሆነ ስለ ቤተሰቡ ሁኔታ በተጨባጭ ይናገራል። ሥርጭቱን ያላዳመጥኩበት ጊዜ የለም ብል አዘጋጁ ሊኮንነኝ ይችላል ። እ አ አ በወርሃ ጥቅምት መጀመሪያው ሣምንት 2014 እኔም የሬዲዮኑ የሠራዊቱ ቤተሰብ እንግዳ ሆኜ ቃለ መጠይቅ ሰጥቻለሁና ።

Saturday, January 28, 2017

የዕለተ ቅዳሜ የትንሳዔ ሬድዮ ፕሮግራም የትንሳዔ ዜና፣ Tensae Radio Jan 28 2017

እኔ ለነጻነቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት 2017


እኔ ለነጻነቴ!
ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት 2017
30+ ከተሞች በአንድ ላይ ቅዳሜና እሁድ ፌብሯሪ 11 እና 12 2017 ዓ.ም.
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ም ዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህንን ትግል ወደ ወሳኝ ም ዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቴው ጊዜ ይልቅ የሚያስፈልገው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በእየለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔ ዘረኛ አምባገነን ቡድንን አስወግዶ …

Wednesday, January 25, 2017

Ethiopia State of Emergency - News

በኦሮምያ ከ1200 በላይ ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ድርጀቱ አስታወቀ



አባይ ሚዲያ
http://amharic.abbaymedia.com/%
የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ ካለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ በኦሮሚያ 1200 ወጣቶች እናቶችና አባቶች ሲገደሉ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታስረዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ መሰደዳቸውን እንዲሁም በርካታ ሴቶች በአጋዚ ወታደሮች መደፈራቸውንም የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል።በታሃድሶ ስልጠና ስም በርካቶች ወደ ጦላይ ሁርሶ እና ዲዴሳ ካምፖች መወሰዳቸውን የገለጸው ድርጅቱ በእነዚህ ካምፖች በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበው ህይወታቸው አልፏል።ይህ አልበቃ ብሎ የሶማሌ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በኦሮሞ ዜጎች ላይ ተጨማሪ ግድያዎችን እየፈጸሙ ነው ብሎአል። ባለፈው አንድ ወር ልዩ ሃይሉ የሚፈጽመው ግፍ እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጸው ድርጅቱ ልዩ ሃይሉ በጉርሱም ኩንቢ ባቢሌ ቺክሳን ሊባን  ላጋ ዳዋ  ፉናንጋርሱ ኢለሌ ከ150 በላይ ሰዎችን ገድሏል።
የአለማቀፍ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቋል። የሶማሊ ልዩ ሃይል በኦሮምያ ብቻ ሳይሆን በሶማሊ ክልል ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት በመፈጸም ይወነጀላል።
ልዩ ሃይሉ የሚመራው በክልሉ ፕሬዚዳንት ነው። የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከክልሉ ፕ/ት ጀርባ በመሆን ግድያዎችን እንደሚያቀነባበሩ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።

Tuesday, January 24, 2017

በአገራችን ተጠናክሮ የቀጠለው የፖለቲካ አፈና የሠላምና መረጋጋትን ተስፋ እጅግ አጨልሞታል ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ገለጸ

ንቅናቄው ይህንን እምነቱን የገለጸው  ጥር 12 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት በእንግሊዘኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ ባሰራጨው ርዕሰ አንቀጽ ነውBilderesultat for አርበኞች ግንቦት 7።http://amharic.abbaymedia.com/%
ያሳለፍነው የፈረንጆች 2016 በአገራችን ታሪክ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከተመዘገበባቸው አንዱ ነበር በማለት የጀመረው የንቅናቄው ርዕሰ አንቀጽ ከሁለት አሥርተ ዓመት በላይ የዘለቀው ጨቋኝና አግላይ የሆነ የመንግሥት ሥርዓት እንዲቀየር በአራቱም ማዕዘን የሚገኘው በሚሊዮኖች የሚቆጠረው ህዝባችን ፍጹም ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ ተቃውሞውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥቶ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የተለመደው የህወሃት/ኢህአደግ ጨካኝ የጥቃት እርምጃ ሠለባ በመሆን በመቶዎች የሚቆጠሩት ለሞት የተዳረጉበት ከአሥር ሺዎች በላይ ደግሞ ወደ ተለያዩ የታወቁና ያልታወቁ እስር ቤቶች ተግዘው መከራና ሲቃይ በመቀበል ላይ የሚገኙበት ሁኔታ ፈጥሮአል ብሎአል።

አርበኞች ግንቦት 7 ነፃነት ፍትህ ዴሞክራሲና አንድነት ክፍል 4

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



የዕለተ ማክሰኞ፡ጥር 16 ቀን፡ 2009 የሬድዮ ስርጭት፡

Monday, January 23, 2017

ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን አምባሳደር አባረረች

-ሳልቫ ኪር ሰሞኑን በካይሮ ባደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያ አማጽያን በደቡብ ሱዳን እንዲንቀሳቀሱና በጁባ ቢሮ እንዲከፍቱ ከግብጽ ጋር አሲረዋል( ተስማምተዋል) በማለት ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን አምባሳደር ከአዲስ አበባ አባራለች።
http://amharic.abbaymedia.com/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%President Kiir visited Egypt, he discussed import issues with the Egyptian officials
ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት፦”የሤራው አቀናባሪ ግብጽ ናት። ስምምነቱ የተደረገውም ካይሮ ውስጥ ነው” ማለታቸው ተመልክቷል።

አንድ ወጣት አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ገድሎ ተሰወረ


በሰሜን ጎንደር ዞን በአጅሬ ጃኖራ አወቀ ካሴ የተባለ ወጣት ከአርበኛ ማሳፍንት ጋር በተያያዘ ታስሮ ስቃይ ሲደርስበት ከቆየ በሁዋላ፣ ወደ ዋና ከተማው ዳባት ሲመጡት “ ድልድልዬ” ከተባለ ቦታ ላይ፣ ኮማንደር መሰለ ጥጋቡ የሚባለውን ሚሊሺያ መሳሪያ በመቀማት እና በ3 ጥይቶች በመግደል የራሱንና የአባቱን መሳሪያ ይዞ በማምለጥ የነጻነት ሃይሎችን ተቀላቅሏል።
ወጣቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የአጋዚ ወታደሮች በዋልድባ የቅርናምባ ኪዳነምህረት ገዳም ውስጥ በመግባት አስጸያፊ ስራ መስራታቸውን ለወራ

ESAT SPECIAL- WHO ARE ETHIOPIANS'? by Prof Haile Larebo 10 Jan 2017

አፈትልኮ የወጣ ልዩ የወያኔ ደህንነት ሪፖርታዥ!


የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁ እንደሚራዘም ተመክሮበታል!

ወያኔ ከ3 ሳምንት በፊት ከሀገሪቱ በሙሉ ከሚገኙት ዞኖች/ክፍለ ከተሞች በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ብቻ ሳይሆን በህወሃት ስለት የተገረዘ አእምሮ አላቸው ብሎ የሚመካባቸውን በየዞኑ ከ2-5 ካድሬወች በተለይም አማራና ኦሮሚያ ክልል(የህዝብ አመፅ ከሚበዛባቸው) አካባቢ በርካታ ታማኞችን በ4 ማዕከል(አ.አ፣ መቀሌ፣ ባህርዳርና አዳማ) እስከ 24/05/09 ዓ.ም የሚቆይ ብርቱ ስብሰባ ነው። 
መኃላቸውን ከአማራና ከቤንሻንጉል ጉምዝ የመጡት ታማኞች አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ በሚከተለው መልኩ ቆይታቸውን አውስተው በሞቅታ መጫወቻ እንዳረጓቸው የተሻለ የህዝብ ስሜትና ወገንተኝነት የተሰማቸው በብስጭት ከወገናቸው ጋ እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት እንደሚሰራና በተለያየ ሁኔታ ስርአቱን እርቃኑን እንደሚያስቀሩት አቋም መያዛቸው ታውቋል።
ይህን ጉዳይ እንዲህ ነው ያስኬዱት፡-
1. አ.አ ሲቭል ሰርቪስ ዪኒቨርስቲ በፕላዝማ የሚመሩት ካሳ ተክለብርሃን፣ በረከት ስሞኦን እና ሌሎቹ ለታዳሚዎች የተነገረን ጠንቅቀን ማወቅ እና የሞት ሽረት ውጊያችን እስካሁን ያላሸነፈው አንዱ ትግል ቢኖር የነ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ድብቅና የውስጥ ቡርቦራ አካሄድ ነው፡፡ ለዚህም ክፍተቱን በመስጠት ያገዝነው እናንተ እና በየደረጃው የተማረውን ወጣት የስራ ቅጥር እንዲያገኝ ባለመሆኑ ነው ተብለናል፡፡

2. እንዲሁም አማራ ክልል በተለይም ሰሜን ጎንደር ዙርያ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በወልቃይት ሰበብ እነሱ እና ቤተሰቦቻቸው ትግሉን ተቀላቅለዋል። ታድያ ይህን ከስሩ ለማምከን ያሉትን ባስቸኳይ የወጡትን በጥበብ የማስመለስ ሚናው የማንም አይደለም የናንተ እንጂ ተብሏል፡፡
3. ስለእንል ጃዋር መሀመድ ቦታ ሰጠውም አወያዩ በረከት እንዳለው እጅግ ፈጣን አስቸጋሪና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑን እናውቃለን OMN ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለን ስናዘጋ በሌላ ይመጣል። ብዙ የኦሮሚያ ወጣቶችም ይሰሙታል። በዚህም የተነሳ ያላቸውንም ንብረትን በማውደም አሁን ለደረሰው የeconomy መጎሳቆል ጥሎናል፡፡ይህንንም ለማስቆም ሳንፈልግ የወጣቶቹን ሒወት ቀጥፈናል።

Saturday, January 21, 2017

የዕለተ ቅዳሜ የትንሳዔ ሬድዮ ፕሮግራም ወቅታዊ ዜና፣ትንሳዔ ለኢትዮጵያ Tensae Radio Jan 21 2017

ለወገን ይድረስ!…… ከወያኔ ደህንነት አፈትልኮ የወጣ

ከወያኔ ደህንነት አፈትልኮ የወጣ*አዲስ የጥቃት ስልቶች!
መልእክቱ ከትንሽ ማስተካከል ውጭ እንዳለ የቀረበ ነው።
ወያኔ ያልሞከረችው የለም። አሁንም ትልቁ የራስ ምታት የሆኑባቸው ወደ ታች ቆላ ወገራና አዲስ ዘመን አሉ ተብለው ከመንግስት ባልተናነሰ ሁኔታ አቅም ያላቸው ታጋዮች የሚባሉት ያልጠበቁትን ያህል ትጥቅ እና ተከታይ ስለያዙ እንዲሁም በፍጥነት ቦታ መቀየር እና እንዲሁም ተወርውረው INFO..የሚያደርሱ ተቆርቋሪ ስላሉ ተቸግረዋል፡፡
ስለዚህ የሰሜን እዝ ብቻ ሳይሆን ታማኞችም ተቀላቅለው ያችን አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ መስራት ይፈልጋሉ፡፡ በመጀመርያ ለሽፍታ ከአካባቢው ከራቁ ችግር የለም ብለው ነበር። ነገር ግን በታች መረብ ወንዝ ድንበር አሁን ወያኔ እያጠበበው ቢመጣም ቅሉ ትጥቅ ማስገቢያ…ተብሎ ስለታሰበ ቅድሚያ እነሱን ለመደምሰስ ወያኔ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞራል የሌለው ወታደር አስፍሯል፡፡
ይህ አይደለም የሚያስፈራው። ምክንያቱም ታጋዮች ምን ሰርተው እንደ ሚያልፉ ስለሚታወቅ ነው። ግን የሠፈረው ወታደር የሚደርስበት ኪሳራ ማንም የማይገምተው አይነት ስለሆነበት በተለያዮ የማይመሥሉ ዘዴዎች ዘምተዋል። የተባሉ ቤተሰቦችን እንዲሁም ጥላቻ አላቸው የሚባሉትን ወገኖች በመለየት ሲቭል ለብሠው ያሉበትን በማጥናት ላይ ናቸው፡፡
በመቀጠል የአማራን መሣርያ የመንጠቅ ፕሮግራም ከውስኖቹ ያውም ኃላፊነት ካላቸው ውጭ እንዳያውቁት ብቻ ሳይሆን እንዳይገምቱም አድርገው ነዉ ሌት ተቀን የሚሰሩት፡፡ስለዚህ የአማራ አርሶ አደር ሳምንታዊ ገበያ ቀን አይደለም ትላልቆቹ ትንሾቹ ሳይቀሩ ለገበያ ሸክም መረዳዳት ሲባል ሁሉም ይወጣል በዚህ ቀንም ቅስም ሰባሪ የመንጠቅ ስራ ይሰራል። ከገበያም በላይ እሁድ እሁድ ቤተ-ክርስቲያን ከ 1-4 ሰዓት ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ከቤታቸው የሉምና፡NETWRK በማጥፍት ሊሞክሩ ይችላሉ። ደግሞም እኮ ከ3 ወር በፊት ተሞክሮ የተወሰነ ጦር መሣርያዎች ወስደዋል፡፡ሌላው አንድ ለወያኔ ቅርብ የሆነ መረጃ የሚያገኝ ሰው ያለኝ በከፍተኛ ሁኔታ አክቲቪስት ተመድቦ አማራና ቅማንትን ለማጋጨት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ደም ማፋሰስ እና ለሁልጊዜ ቅራኔ መፍጠር እንዲቻል እየሰሩ ነው።


ሙሉነህ ዮሃን

Friday, January 20, 2017

የትንሳዔ ሬድዮ የዕለተ አርብ ፕሮግራም፣ ወቅታዊ ዜና እና መደበኛ ፕሮግራሞች ትንሳዔ ለኢዮጵያ! Tensae Radio Jan 20 2017

በመተማ ንብረትነቱ የወያኔ የሆነ የጥጥ ማምረቻ ፋብሪካ በቦምብ ፍንዳታ መጋየቱ ተሰማ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
(ምስል ከፋይል)
በመተማ አከባቢ ተከታታይ ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ እየተነገረ ይገኛል።
በጎንደር መተማ በሚገኝ አንድ የጥጥ ምርት ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ ጉዳት ደርሷል። ፋብሪካው በፍንዳታው በእሳት ጋይቷል ከፍተኛ ንብረትም ጠፍቷል።
ንብረትነቱ የህውሃት/ወያኔ በሆነው በዚህ የጥጥ ማምረቻ ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ሰአት እንደሌለ ሪፓርቶች ይገልጻሉ።
ይህንን ፍንዳታ ተከትሎ አገዛዙ የአከባቢው ነዋሪዋችን በስፋት በቁጥጥር ስር በማዋል አስሯል። በተጨማሪም አገዛዙ ከጥቃቱ በሃላ በመተማና በገንዳ ውሃ አከባቢም በርካታ ወታደሮችን አስፍሯል።
በዚህ ሳምንት እረቡ እለት በፍብሪካው ላይ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደ ግለሰብም ሆነ ድርጅት አልተገኝም። የህዝባዊ እምቢተኝነቱና አመጹ በይበልጥ የአገዛዙን ንብረት ኢላማ ያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህም የጥጥ ማምረቻ ፋብሪካ ንብረትነቱ የአገዛዙ መሆኑ ምንአልባት የህዝባዊ አመጹ ኢላማ ሆኖ ተገኝቷል የሚል የብዙዎች ግምት ሆኗል።

እኔ ለነጻንቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ



Image may contain: 2 people, textበኖርዌይ ኦስሎ አካባቢ ለምትኖሩ አገር ወዳድ ኢትዬጲያዊያን በሙሉ " እኔ ለነፃነቴ" በሚ
ል መሪ መፈክር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ግልፅ ውይይት ለማድረግና የወያኔን ስርዓት ለማስወገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የነፃነት ሃይሎች ድጋፍ በመስጠት አጋርነታችንን እንድናሳይ፡ የኖርዌይ አርበኞች ግንቦት 7 February - 11 - 2017
Staring From፡ 2pm
የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር፡ አቶ ደባሱ መሰሉ፡ በአካል የሚገኙ ሲሆን እምዲሁም የንቅናቄያችን ሊቀመንበር፡ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፡ ከኤርትራ በርሃ በስካይፕ በተገኙበት በአጠቃላይ....በኢትዬጲያ ውስጥ ያለውን የትግል እንቅስቃሴ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣሉ። በዚህ ስብሰባ ላይ የወያኔን ስርዓት ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን ትግልና ተዛማጅ የሆኑ ማናቸውም አይነት ጥያቄና ሃሳብ የሚስተናገድበት መድረክ ስለሚመቻች በቦታው ተገኝተው ጥያቄዎንና ሃሳቦን እንዲያካፍሉ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።
Addres will be ananouncd soon
Donatin፡ 200kr ፡ 500kr or 1000kr
Contact ifo፡ 4796816160 .4746240132
የኖርዌይ አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላም ትኑር !

As political repression intensifies, peace and stability become more elusive in Ethiopia January 19, 2017


Editorial 19/01/2016

The year 2016 was one of the most climactic in recent history of Ethiopia. After two decades of political repression and economic exclusion, millions of citizens across the four corners of the country decided to engage in a peaceful rebellion demanding fundamental change in the country. Tragically, but not unexpectedly, the TPLF/EPRDF-led regime decided to use brute force against peaceful demonstrators, killing hundreds and throwing into jail tens of thousands who still languish in identified and unidentified prisons scattered across the country.
The suffocating political environment, exacerbated by economic marginalization and exclusion, has created a social atmosphere of hopelessness and desperation for the majority of citizens.
The recent grenade attack and explosions in the northern cities of Bahr Dar and Gonder demonstrate that the people of Ethiopia are being pushed to the limit by the regime supposed to serve and protect them. The relentless brutally deadly measures being taken by forces loyal to the regime has created a situation where people are resorting to self-defense and resistance, at times taking desperate measures as seen recently in the two northern cities.

Thursday, January 19, 2017

በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆና በመተማ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎች ደረሱ ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :

Bilderesultat for ኢሳት የዛሬ ዜናትናንት እና ዛሬ በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ በተባለው ቦታ ሁለት የእጅ ቦንቦች የፈነዱ ሲሆን፣ ነጋዴ ባህር በተባለ ቦታ ላይም ተመሳሳይ ቦንብ ፈንድቷል። ይህን ተከትሎም አካባቢው በወታደሮች የተከበበ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችም ታፍሰዋል። ከትናንት ጀምሮ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ጥቃቱ በነጻነት ሃይሎች መፈጸሙን ከመግለጽ ውጭ በዝርዝር ጥቃቱን ስለፈጸሙት ሃይሎች አልተናገሩም። አንደኛው ቦንብ በህወሃት የጥድ ማዳመጫ ላይ የተወረወረ ሲሆን፣ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ መቃጠሉም ምንጮች ገልጸዋል።

Helen Show: Temsalet - DC Lunch Event

Wednesday, January 18, 2017

ESAT Tigregna News January 18 2017

አምባገነናዊ ዘረፋ በብሔራዊ መረጃ | የውጭ ሃገር ኑሯቸውን ጥለው ሃገር ቤት ለንግድ የገቡ ዲያስፖራዎች ገንዘብና ንብረታቸውን እየተቀሙ ነው | ጥብቅ መረጃ

እኔ ለነጻንቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት


በኖርዌይ በርገን ከተማ
March፡ 4፡ 2017
ሰዓት፡ ከ 14 ፡ሰዓት ጀምሮ
የስብሰባውን ቦታ በቅርቡ እናስታውቃለንImage may contain: 2 people, text
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቸውም ግዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔን ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ ፍትህ በሰፈነበት እኩልነት ያረጋገጠ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል የመጨረሻውን የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።

Tuesday, January 17, 2017

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የቀረበባቸውን ክስ ተቃወሙ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
ነሐሴ 28 ቀን 2008 .ም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ አቃቤ ህግ በበርካታ ግለሰቦች ላይ ክስ እንደመሰረተ ይታወሳል።
500,000 ብር በላይ አገዛዙን በትግል ለመገርሰስ ከሚሰሩ ድርጅቶች በመቀበል በማረሚያ ቤቱ ሁከትን በማነሳሳት ከ120 በላይ ግለሰቦችን አቃቤ ህጉ መወንጀሉም ይታወቃል።
በማረሚያ ቤቱ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ለጠፋው ህይወትና ንብረት ተጠያቂ የስዊድን ዜግነት ባለው በዶክተር ፍቅሩ ማሩ የሚመራው የእስረኛ ቡድን እንደሆነም በክስ መዝገቡ ሰፍሯል።

የአጋዚ ጦር አባላት መከላከያን በብዛት እየለቀቁ ነው ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገዛዙ ወደ ሶማሊያና ሱዳን በሰላም አስከባሪ ስም በሚልካቸው ወታደሮች ላይ የማእረግ ማጭበርበር እየፈጸመ ገንዘብ እንደሚያገኝ የአጋዚ የህግ ክፍል ኤክስፐርት አስታውቋል። የአጋዚ ኮማንዶ እና ልዩ ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ የህግ ሰነድ እና ዝግጅት ኤክስፐርት የነበረው ሃምሳ አለቃ ወደ ሶማሊያ ሰላም አስከባሪ አባል ሆኖ ሲሄድ ሻለቃ ተብሎ የተሰየመው ሃምሳ አለቃ ኃ/ሚካኤል በእውቀቱ ጋሻዬ በአጋዚ ውስጥ ያለውን የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ዘረኝነት፣ ሙስና፣ ብልሹ አሰራር እና ጭካኔ በመቃወም ክፍለጦሩን መክዳቱን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቆይታ አረጋግጧል። ሃምሳ አለቃ ኃ/ሚካኤል በተለይም ሰላም ለማስከበር በሚል በተባበሩት መንግስታት እንዲሁም በአፍሪካ ኅብረት ወይም አሚሶም በሶማሊያ ሴክተር ሶስት በባይደዋ ከመጋቢት ወር 2007 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ ወር 2008 ዓ.ም በቆየበት ወቅት የህወሃት ወታደራዊ አዛዦች በሰራዊቱ ላይ የፈፀሙት ወንጀል እጅግ ዘግናኝ እንደነበር አስታውቋል። በገለጻውም በተለይ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም ባይደዋ በሚገኘው ከቡራካባ 27 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኘው ጁባ በተባለ ስፍራ በኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል ቸልተኝነት እና ዕውቀት ማነስ 42 የአጋዚ አባላት በፈንጂ እና በሌሎች መሳሪያዎች ተገለው አስከሬናቸው በየቦታው ወድቆ ያየበት ሁኔታ በቁጭት እንደሚያስታውሰው አውስቷል። ያለምንም ወታደራዊ ጥናት እና ክትትል ባልተደረገበት ተጠያቂ የሆነው ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል በሃላፊነት ሳይጠየቅ ለተሻለ እድገት የታጨበት መንገድ በሰራዊቱ እልቂት ባሳየው ንቀት እና ትእቢት የተቆጡ ወታደሮች አግተውት በምልጃ መትረፉን ይናገራል። አያይዞም የህወሃት አባል የሆኑት የክፍሉ አዛዦች ለገንዘብ ያላቸው ፍቅር እና ስግብግብነት ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ እንዴት እንዳዋረዱ እራሱን በምስክርነት ያስቀምጣል። እንደ ምሳሌም ካነሳቸው ጉዳዮች መካከል በማእረግ አሰጣጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የሚያጭበረብሩበት ስልት በጣም አስደንጋጭ ነው ይላል። ከሰራዊቱ ተመርጦ በሕግ ኤክስፐርትነት እንዲሄድ ሲነገረው ሃምሳ አለቃ ነበረ። በሰላም አስከባሪ አባል ሆኖ ወደ ሶማሊያ ሲሄድ ሻለቃ በእንግሊዝኛው (Major) አደረጉት። በአጋዚ ክፍለጦር በሃምሳ አለቅነት ሲያገለግል የነበረው ኃ/ሚካኤል በአንድ ጀንበር ከስድስት በላይ እርከኖችን አልፎ ሻለቃ ሲሆን መገረምም መደናገጥም ፈጥሮበት ነበር። የእውነትም መስሎት እንደነበረ ያወሳል። ይሁንና ከተመደበበት ቦታና ስፍራ በስተቀር ደመወዝ የሚከፈለው በሃምሳ አለቃነቱ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግስታት በሻለቅነት የሚከፍለውን የህወሃት ከፍተኛ መኮንኖች የሃምሳ አለቃውን 40% ብቻ እንደሆነ መስክሯል። በተለይ በሶማሊያ የነበሩት የጦር አዛዦች ብርጋዴር ጄነራል መሀመድ አይዘኑ፣ ብርጋዴር ጄነራል ገ/መድኅን ፍቃዱ በቅጽል ስሙ ወዲ ነጮ፣ ብርጋዴር ጄነራል ዮሃንስ እና ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል ከመንግስታቱ የሚመጣውን ዶላር ከሰራዊቱ በመዝረፍ ሰንሰለት በተበጀለት መዋቅር እነዚህን ወታደራዊ አዛዦች ማበልፀጊያ መሆናቸው ያንገበግበዋል። በሶማሊያ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን በየጉድባው ተሽንቁሯል። አስታዋሽ ማጣቱን በሃዘኔታ ያስታውሰዋል። አክሎም በሰላም አስከባሪነት የሄደው የሰራዊቱ አባላት ሲገደሉ የተባበሩት መንግስታት የሚከፍለው በአንድ ሰው ወደ አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ የደም ካሳ ለአንዳቸውም የሟች ቤተሰቦች ሳይደርስ በእነ ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል አስተላላፊነት የህወሃት ጄኔራሎች ቅምጥል ሕይወት ይመሩበታል። ልጆቻቸውንም በአውሮፓ እና በአሜሪካ የሚያስተምሩበት ዶላር ይሰበስቡበታል ሲል አማሯል። አጋዚ በአገር ቤት የስርዓቱ ቀኝ እጅ ሆኖ የስልጣኑ ዋስትና እንደሆነ ይነገራል። በሶማሌ ደግሞ እየተማገደ የማይነጥፍ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆኖ በደሙ ይነገራል በማለት በቁጭት ይተርካል። በአገር ቤት ሃምሳ አለቃ በሶማሌ ሻለቃ ኃ/ሚካኤል ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ከስልጠናው ጀምሮ እስከ ምደባው ያለውን አስፈሪ እና አስከፊነት ሂደቶችን በተመለከተ አብራርቷል። በሁርሶ ሁለት ወር የፖለቲካ ትምህርት፣ ስድስት ወር ወታደራዊ ስልጠና ከዛም ማጣሪያ ወይም ፍሊተሬሽን፣ አስከትሎም በብላቴን 12 ወራት ወታደራዊ የኮማንዶ ስልጠና ወስዶ ይወጣል። በሁርሶ የሁለት ወሩ የፖለቲካ ስልጠና በተመለከተ በሰጠው ምስክርነት ተመልምለው ሰልጥነው የሚወጡት የስርዓቱ ዋነኛ ጠላቶች ተብሎ የሚነገራቸው ”የአማራ ትምክተኝነት፣ የኦሮሞ ጠባብነት” እንደሆነ በመግለጽ ”በቋንቋችሁ እንዳትናገሩ፣ በማንነታችሁ እንዳትከበሩ የሚያደጉት ኃይሎች ዋነኛ ጠላቶች በመሆናቸው እነዚህን አንታገስም!” በማለት ተናዘው፤ በፖለቲካ ራሳቸውን ክደው፣ ስብዓዊነታቸውን አንጠፍጥፈው ወደ አውሬነት የሚቀየሩበት የጨካኞች ማዕከል እንደሆነ ብላቴ እና ሁርሶን በዋቢነት ጠቅሷል። ይህም በመሆኑ ከትግራይ ተወላጆች ውጪ ያሉት የሌላ ብሄር አባላት ክፍለጦሩን በመክዳት የነጻነት ኃይሎችን ለመቀላቀል እንደሚፈልጉ አስታውቋል። በየዓመቱም ከስድሳ በላይ የሰለጠኑ ወታደሮች እየከዱ እና የአጋዚ ክፍለጦር እየፈራረሰ መሆኑን ጠቁሟል። በመጨረሻም ሰራዊቱ ሕዝባዊ አጋርነቱን በማሳየት ”ጥቂት የህወሃት ከፍተኛ መኮንኖች እና ባለስልጣናቱን የተንደላቀቀ ሕይወት ብላችሁ የንጽሁሃንን ወገኖቻችሁን ደም አታፍስሱ” በማለት ጥሪ አቅርቧል። ከዚሁም ጋር አያይዞ በአጋዚ ክፍለጦር ውስጥ ሰራዊቱን በመበደል ሕዝብ ላይም እንዲተኩስ ምክንያት የሆኑትን የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን በተለይ ብርጋዴር ጄነራል ገ/መድኅን ፍቃዱ ወዲ ነጮ፣ ብርጋዴር ጄነራል መሀመድ አይዘኑ፣ ብርጋዴር ጄነራል ዮሃንስ እና ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል ነገ ከሕዝብ ፍርድ እንዲሁም ከሰራዊቱ የበቀል ሰይፍ እንደማያመልጡ አስጠንቅቋል።ESAT Daily News Amsterdam January 17,2017

ጥብቅ መረጃ.. አንባግነናዊ ዘረፋ በብሄራዊ መረጃ! !



ባሳለፍነው አመት 2007 እና 2008 ዓ/ም በአጠቃላይ የመረጃ ስብስብ ዘርፍ ተገቢውን ጥናት አካሂጃለው በማለት በሚኒስቴር ደረጃ እና ለተመረጡ የህውሀት የደህንነት ባለስልጣናት ዝርዝር ሀተታ ያቀረበውን ብሄራዊ መረጃን መሰረት ባደረገ መልኩ በ 2009 ዓ/ም ኢ-አንጻራዊ የውንብድና እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል::
እንደ ብሄራዊ መረጃው ምልከታ ከሆነ በመላው ኢትዮጵያ የተከሰተውን ህዝባዊ አምጽና በአስገራሚ ሁኔታ የተበራከቱትን የነጻነት ሐይሎች በተለይም አርበኞች ግንቦት 7 አሁን ለደረሰበት ከፍተኛ ተጽኖ ፈጣሪነት ያደረሱት ዲያስፓራዋች ናቸው ይላል::
በዚህ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ለዲያስፓራ ኢትዮጵያዊያን የሚሰጡ እና የተሰጡ የኢንቨስትመንት አገልግሎቶች እንዲቋረጡ እና በባንክ የውጭ ገቢ ተቀማጭ ንዋያትና የብድር አሰጣጥ መስተጋብር ይዘት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ከማሳሰብ አልፎ በዲያስፖራዋች የተገዙ ማንኛውም ይዞታዋች እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ ህገ ደንብ እንዲያቅባቸው ያመላክታል::
አያይዞም የህወሀት መንግስት ለዲያስፓራዋች የሚሰጠው ድጋፍ በአስቸኩዋይ እንዲያቆምና ተግባራቶቹን እንዲፈተሽ የሚያስጠነቅቅ ነው::
ይህን ተንተርሶ አጣብቂኝ ፖለቲካዊ ንዝረት ላይ የወደቀው የህወሀት ወያኔ አስተዳደር ከብሄራዊ መረጃው የቀረበውን ሐገር የማጥፋት እቅድ ተግባራዊ ባደረገ መልኩ በዲያስፓራዋች ላይ ወረራ መጀመሩን መረጃ የሰጡን ምንጮች ጠቅሰው ብሄራዊ መረጃው በማንኛውም መልኩ ከውጭ ወደ ሀገር የሚገቡ ዲያስፓራዋች ላይ የማዳከም ስልት እንዲጠቀም የሀገር ውስጥ ጉዳይ ደህንነት ሚኒስቴር ባለስልጥናት ፍቃድ ሰጥተውታል::
በመሆኑም ህጋዊ የአፈና ፍቃድ የወሰደው ብሄራዊ መረጃ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፓራዋችን አፍኖ በመጥለፍ ህገ ውጥ የገንዘብ ክፍያ እንዲፍጽሙ ማስገደዱን አረጋግጠዋል:: በዚህም መሰረት:: 1. ከደቡብ ሱዳን ወደ ሐገር ቤት የገቡ ሁለት ዲያስፖራ ባለሀብቶችን በማፈን ከያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዬን ዶላር መቀበሉን.
2. ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሐገር ቤት የገቡ 6 ግለሰቦችን በማፈን 4.9 ሚሊዬን ራንድ በግዳጅ መቀበላቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ፍንጮች በሰጡት መረጃ መሰረት ለማጣራት እንደሞከርነው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደቡብ አፍሪካ ዲያስፓራ ከአዲስ አበባ ቺቺንያ ከሚባል ሰፈር በደህንነቶች ተጠልፈው አይናቸው በጥቁር ጨርቅ ተጋርዶ ወደማይታወቅ ስፍራ ከተወሰዱ ወዲህ .... ለሳምንት ያህል ታፍነው 1 ሚሊዬን ራንድ ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን አፋኝ ቡድን በተመሳሳይ መንገድ ከተለያየ ሀግር ወደ ሀገር ቤት የገቡ ተጨማሪ 8 ዲያስፕራዋችን ማገቱን ተናግረዋል::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! !
( ጉድሽ ወያኔ

ድርቅ በተከሰተባቸው ክልሎች 24 ሺ አካባቢ የሚደርሱ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ (ጥር 9 ፥ 2009)


አዲስ የድርቅ አደጋ በተከሰቱባቸው አራት ክልሎች ወደ 24 ሺ አካባቢ የሚደርሱ ቤተሰቦች በድርቁ ሳቢያ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ።Bilderesultat for ድርቅ
ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በአፋር ኦሮሚያ፣ ደቡብና የሶማሊ ክልሎች ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች አዲስ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።
ይህንኑ የድርቅ አደጋ መባባስ ተከትሎ 23ሺ 764 ቤተሰቦች ከመኖሪ8ያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለአስቸኳይ የምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ዕርዳታዎች መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርቁን አስመልክቶ ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርቱ አመልክቷል።
በአራቱ ክልሎች በመዛመት ላይ ባለው የድርቅ አደጋ 5.6 ሚሊዮን ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ሲሆን፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ርብርብ ካላደረገ የከፋ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል።
የድርቁ ሁኔታ መባባስን ተከትሎ በደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ዞኖች ቆዳን በሚያሳክክ ወረርሽን እየተጠቁ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች ባለፈው ሳምንት የደረሰውን የቦምብ አደጋ ተከትሎ ውጥረት መንገሱ ተገለጸ (ጥር 9 ፥ 2009)


ሰሞኑን በጎንደርና ባህርዳር ከተሞች የደረሰን የቦምብ አደጋ ተከትሎ በሁለቱ ከተሞች ውጥረት መንገሱን የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ገለጸ።
የጥምቀት በአል አከባበርን አስመልክቶ በሁለቱ ከተሞች ተጨማሪ ጥቃት ሊደርስ ይችላል ሲል ፖሊስ ማሳሰቢያ መስጠቱንም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎቹ ባሰራጨው የጉዞ ጥንቃቄ መረጃ አመልክቷል።
ይሁንና ፖሊስ ሊደርስ ይቻላል ስላለው ተጨማሪ ጥቃት የሰጠው ዝርዝር መረጃ የሌለ ሲሆን፣ በሁለቱ ከተሞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ የሚከበረውን የጥምቀት በአል አስመልክቶ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሃይል መሰማራቱ ታውቋል።
የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ዜጎቹ ወደ አካባቢው በሚደረጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ ዕርምጃን እንዲወስዱ የሰጠው ማሳሰቢያም ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቀጥል በመግለጫው አስፍሯል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በሁለቱ ከተሞች በሚገኙ ሆቴሎች የቦምብ አደጋ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን፣ በጎንደር ኢንታሶል ሆቴል በደረሰው ፍንዳታ የአንድ ሰው ህይወት አልፎ 18 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ፖሊስ ገልጿል።

Monday, January 16, 2017

በተለምዶ ቆራሊዮ እየተባሉ የሚጠሩት የሀገሪቱ ለውጥ በእንጀራ ገመዳቸው ላይ ስጋት መደቀኑን ተናገሩ


በተለምዶ ቆራሊዮ እየተባሉ የሚጠሩት ያገለገሉና አሮጌ ቁሶችን ወደጠቃሚነት የመቀየር ስራ የሚሰሩ ሰራተኞች የሀገሪቱ ለውጥ በእንጀራ ገመዳቸውImage may contain: 1 person ላይ ስጋት መደቀኑን ተናገሩ፡፡

በጎንደር ስትንቀሳቀስ የነበረችው ንግስት ይርጋ እስከ ካናዳ የሚደርስ የትጥቅ መረብ ዘርግታ እንደነበረ ተገለጸ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
ሪፓርተር ጋዜጣ አቃቤ ህግ በአክትቪስት ንግስት ይርጋና በሌሎች አምስት ተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ ዘግቧል።
ጋዜጣው እንዳስነበበን አክትቪስት ንግስት ይርጋ እስከ ካናዳ የሚደርስ መረብ ዘርግታ እንደነበረና በርከት ያለ ገንዘብም ሲመደብላት እንደነበረ አስነብቦናል።
መንግስትን ለመጣል የተቋቋመውን ኮሚቴ በባላይነት በመምራትና የራሷን ግሮሰሪ በአመጽ ትግል ለሚገኙ ቡድኖች ማቆያና መሸሸጊያም ስትጠቀም እንደነበረችም ዘርዝሮልናል።
አገዛዙ በሽብርተኝነት ከፈረጀው ድርጅት አመራሮችም ጋር ግንኙነት እንደነበራትምና ትእዛዝም ስትቀበል እንደነበረም በተጨማሪም አስፍሯል።

ESAT Eneweyay January 16,2017

#ልዩ ዘገባ አንድ ጎንደር ውስጥ ሰርግ የሚመራው በወያኔ ኮማንድ ፖስት ሆነ! ባንዲራና የአርበኛ ልብስ ተከለከለ! ጉድ በል ጎንደር!


ጎንደር ያለ ወራሪው ወያኔ በትላንት ዕለተ ሰንበት ጋብቻውን የፈፅመውን ወጣት ለአጃቢና ለታዳሚ የጥሪ ወረቀት አሰርቶ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ያሸበረቀ ነበር። ነገር ግን ኮማንድ ፖስቱ ሰለጥሪው ወረቀት ማብራሪያ እንዲሰጥበት ተጠይቆ አንዳንድ የሰርጉ ፕሮግራሞችን በኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ እንዲሰረዝ ተደርጓል።Image may contain: one or more people and outdoor
የተሰረዘው ፕሮግራም ሙሽሪትና ሙሽራው በሰረገላ በከተማው ጉዳናዎች የሚያደርጉት ጉዞ እና አባት አርበኞች ለብቻቸው የተሰፋላቸውን እጄ ጠባብ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ያሸበረቀ ባህላዊ ተነፋነፍ እንዳይለብሱ ተደርጓል።
ጉድ በል ሃገር!!!
++++++++++++++++++++++

Saturday, January 14, 2017

የዕለተ ቅዳሜ የትንሳዔ ሬድዮ ፕሮግራም ወቅታዊ ዜና፣ ''የድድ ማስጫው ወግ'' መጣጥፍ ''ኢትዮጵያውያን በአረብ ሃገራት'' የተሰኘ ጥንቅር ''ፒያሳው!'' የሬድዮ ድራማ ክፍል አንድ እና ሌሎችም ትንሳዔ ለኢትዮጵያ Tensae Radio Jan 14 2017

የብኢኮ 90 በመቶ የአመራር ቦታዎች በአንድ አካባቢ ሰዎች የተያዙ መሆናቸውን ሰነዶች አመለከቱ ጥር ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

 በአብዛኛው በቀድሞ መንግስታት የተገነቡትን ስድስት  ወታደራዊ አገልግሎት ሰጪ የማምረቻ ኮምፕሌክሶችን ማለትም  ወታደራዊ ተሸከርካሪዎችን በማደስ ሲሰራ የነበረው- ቢሾፍቱ (40720)፣  ተተኳሾችን በማምረት ሲያገለግል የነበረው-  ሆርማት ፋብሪካ  ፣ ቀላል መሳሪዎችን በማምረት ተልእኮ የነበረው – ጋፋት ፋብሪካ ፣  ወታደራዊ አይሮፕላኖችን ለማደስ የተቋቋመው- ደጀን  ፋብሪካ፣  መለዋወጫዎችን ለማምረት የተመሰረተው – አዲስ ሜታል ፋብሪካ እንዲሁም ወታደራዊ አልባሳት ሲያመርት የነበረውን  አዳማ ጋርመንት ፋብሪካን በአንድ ላይ በመቀላቀል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 183/2002 ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ)፣ በእንግሊዝኛኛ ምህጻረ ቃል ሜቴክ በብር 10 ቢልዮን፣ የተፈቀደ (Autorized capital) እና በብር 3,178,914,604.55 ( ሶስት ቢሊዮን 178 ሚሊዮን 914 ሺ 604 ብር ከ 55 ሳንቲም) የተከፈለ ካፒታል (paid up capital) በ2002 ዓም የተቋቋመ ነው። ድርጅቱ እስከ 2008 ዓም መጨረሻ ድረስ 44 ቢሊዮን 993 ሚሊዮን 691 ሺ 179 ብር ከ41 ሳንቲም ሀብት እንዳለው ከድርጅቱ የ5 አመታት ሪፖርት ለመረዳት ይቻላል።

ኮርፖሬሽኑ  ኢንጂነሮች፣ ሞያተኞችና ድጋፍ ሰጪ አካላትን ጨምሮ 1,437 የሰራዊት አባላት እንዲሁም  2,474 ሲቪል ሰራተኞች በአጠቃላይ 3,9

በአልጣሽ ፓርክ የነጻነት ሃይሎችን ለማጥቃት የተላኩ ወታደሮች ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው ጥር ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :

 ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ አልጣሽ ብ/ፓርክ ውስጥ ለነጻነት የሚታገሉ ሃይሎችን ለመውጋት በሚል የተላኩት ወታደሮች የተወሰኑት ሲሞቱ አብዛኞቹ ደግሞ ከፈተኛ  ጉዳት ደርሶባቸዋል።Bilderesultat for የኢትዮጵያ ወታደር

በ3 ቡድን ተከፍሎ ለጥቃት ወደ ፓርኩ ከገቡት የሰራዊት አባላት መካከል   አብኑን ወይም አምዶክ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የገቡት ወታደሮች  የተጓዙት የእግር መንገድ ከመርዘሙና አብኑን ላይ አለ የተባለው ውሃ ባለመገኘቱ ለከፍተኛ የውሃ ጥም ተደርገዋል። ይህ ተከትሎ ወታደሮቹ  ውሃ ፍለጋ ሲባዝኑ እርስ በርስ አለመግባባት መፈጠራቸውን ምንጮች ይናገራሉ።

Friday, January 13, 2017

የትንሳዔ ሬድዮ የዕለተ አርብ ፕሮግራም፣ ወቅታዊ ዜና እና መደበኛ ፕሮግራሞች ትንሳዔ ለኢዮጵያ! Tensae Radio Jan 13 2017

ያኔ....



የቋራው አንበሳ፣ የጦቢያ ዘበኛ፣
“እጅ አልሰጥም!” ብሎ፣ ላ’ገሬ ደመኛ፣
ሽጉጥ ተንተርሶ፣ መቅደላ ላይ ተኛ።
ከመቅደላ አናት ላይ፣ የታየችው እሳት፣
ወደ ሌላው ምድር፣ አጥታ ‘ሚለኩሳት፣
ኢትዮጵያ ታመመች፣ በእንግሊዝ ትኩሳት።
ዛሬ‹፦
የአንድነቷ ድልድይ ፣ የቤታችን ማገር፣
ዳግም ስትወረር ፣ የመይሳው ሀገር...
“የወገኖቼ ደም፣ደሜ ነው” እያሉ፣
የገብርዬ ልጆች ፣በእምነት ሲጋደሉ....
ጎንደር ስትታጠር፣በሰናክሬም ጭፍራ፣
ተዋበች “ልጆቼን!” ብላ ስትጣራ፣
ከሰሜን ከደቡብ፣ ከምእራብ ከምሥራቅ፣
ያለኸው ወገኗ፣ ዋጥ አድርገህ ምራቅ፣
“አለሁልሽ” በላት፣ ሳታይ ወደ ኋላ፣
ብልጭታዋ ብርሃን፣ ምድሩን እንድትሞላ።(ደረጀ ሀ›)Image may contain: one or more people

አልሸባብ ለኢትዮጵያ ሰራዊት ሲሰልል ነበር ባለው አንድ የሃገሪቱ ተወላጅ ላይ የሞት ቅጣት መፈጸሙን ገለጸ ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2009))


የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ በሃገሪቱ ተሰማርቶ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲሰልል ነበር ባለው አንድ የሃገሪቱ ተወላጅ ላይ የሞት ቅጣት መፈጸሙ ተገለጸ።Bilderesultat for የኢትዮጵያ ወታደር በሞቃዲሾ
ሰይድ መሃመድ አሊ የተባለው የሶማሊያ ተወላጅ የተለያዩ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ ወታደሮች በማቀበል አልሸባብ የጥቃት ኢላማ እንዲሆን ማድረጉን ታጣቂ ሃይሉ ማስታወቁን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ የተካሄደው የሞት ቅጣት በማዕከላዊ የጁባ ግዛት ስር በምትገኘው የቡአሌ ከተማ መሆኑን የአልሸባብ ራዲዮ ጣቢያ የሆነውን አንዳሉንስ ዋቢ በማድረግ አሶሼይትድ ፕሬስ አስነብቧል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ስር ተሰማርቶ ከሚገኘው የሰላም አስከባሪ የልዑካን ቡድን በተናጠል በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በተለያዩ የሶማሊያ ግዛቶች በማሰማራት በታጣቂ ሃይሉ ላይ ጥቃት ስትፈጽም መቆየቷ ይታወቃል።
ይሁንና ከወራት በፊት በርካታ ወታደሮች ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ለቀው የወጡ ሲሆን፣ አልሸባብ የተሰኘው ታጣቂ እነዚሁኑ አካባቢዎች ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ሲገለጽ ቆይቷል።

፡፡ ሌባና ወንጀለኛን የሥልጠና፣ የሴሚናርና የውይይት ብዛትና ዓይነት አይለውጠውም፡፡ የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ከፍተኛ ኣመራሮች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡

 ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!፡፡ ጉዞው ሌቦች የበላይነት የያዙበትና የሌቦች መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!
ሕወሓት መራሹ አገዛዝ ቱባ ባለስልጣናት በተላላኪያቸው ሃይለማርያም በኩል በከፍተኛ አመራሩ ላይ ማስረጃ ስላልተገኘ እርምጃ መውሰድ አይቻልም የሚል ዲስኩር ኣሰምተውናል። ዋናውን የመንግስት ሌብነትና መንግስታዊ ሽብር እየመሩ ያሉት ከፍተኛ የሕወሓት ባለስልጣናት መሆናቸው አይካድም።Image may contain: text
ከተማ ውስጥ ካሉ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ጀምሮ እስከአነስተኛ ንግድ ድረስ ሃገሪቷን የተቀራመቷት እነዚሁ የሕወሓት ሰዎች ናቸው በውጪ ምንዛሬ

ስለሁለገብ ትግል .ከዶ/ር ታደሰ ብሩ



Image may contain: 1 person, standingስለሁለገብ ትግል የተሟላ ግንዛቤ መኖሩ ትግላችንን የምናይበት መንገድ ያሰፋልናል ብዬ አምናለሁ። አንዳንዱ ሁሌ ስለ አንድ የትግል ስልት ብቻ መወራት ያለበት ይመስለዋል። ይህንን ሀሳብ ለማጥራት በግማሽ ገጽ ስለሁለገብ ትግል ለመግለጽ ልሞክር።
ሁለገብ ትግል ቢያንስ የሚከተሉት አምስት የትግል ስልቶች ድብልቅ ነው።
1. ሕዝባዊ ተቃውሞ (Civic Protest) አምባገነኑ ሥርዓት ያወጣቸው ህጎች የሚሰጡት ትናንሽ ክፍተቶችን በመጠቀም አቤቱታን ወይም ተቃውሞን በህጋዊ መንገድ ማቅረብ። ምሳሌዎች አቤቱቶታዎችን በጽሁፍ በኮሚቴዎች አማይነት ማቅረብ፣ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ,፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች፣ የአቋም መግለጫዎች ወዘተ ....
2. ሕዝባዊ እምቢተኝነት (Civic Disobedience) አምባገነኑ ሥርዓትን ያወጣቸው ህጎችን መጣስ የሚያስከፍለውን ዋጋ አውቆና ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅቶ የሚደረግ ህግን ጥሶ “አልገዛም፣ አልታዘዝም“ ማለት። ህግ አድርግ የሚለውን አለማድረግ፤ አታድርግ የሚለውን ማድረግ።
3. ሕዝባዊ አመጽ (Civic Resistance) አምባገነኑን ሥርዓት በመሣሪያ ኃይል ጭምር መገዳደር። ሕዝባዊ አመጽ ከሌላው አመጽ የሚለየው ሕዝብ “ጥሩ ወይም መልካም” ለሚለው ዓላማ የሚደረግ መሆኑ ነው - ይህ ነው civic ያሰኘው።

አርበኞች ግንቦት 7 ነፃነት ፍትህ ዴሞክራሲና አንድነት ክፍል 3

Thursday, January 12, 2017

ታዋቂው ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ከደቂቃዎች በኋላ ዋሽንግተን ዲሲ እንደሚገባ ጋዜጠኛ አበበ በለው ዘግቧል:: ይህን ቭድዮም ተጋብዛችኋል >>>>>>Habtamu Ayalew’s Unforgettable Speech - Hager Malet

ኢትዮጵያ: የጭካኔና ገደቦች አመት (ሂዩማን ራይትስ ወች)

መብቶች ይከበሩ፣ ለህዝብ ቅሬታዎች መልስ ይሰጥ (ናይሮቢ ጥር 12፣ 2017) – እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ቀዉስ ዉስጥ ወድቃለች። ሂዩማን ራይትስ ወች ዛሬ በወጠው የ 2017 ዓ.ም. የአለም ዓቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጀችበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ መብቶችን በመገደብና ሰለማዊ ሰልፈኞች ላይ የከፈተችዉን ደም አፍሳሽ አፈናን  ቀጥላበታለች ብሏል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዘፈቀዳ ማሰርን ይፈቅዳል፣ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ይገድባል፣ አንዲሁም ከውጭ አካላት ጋር መገናኘትን ይከለክላል። በዚህ ዓመት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በኦሮሚያና ኣማራ ክልሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰለማዊ ሰልፈኞችን ገድሏል፣ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩትን ዕስር ቤት ኣጉሯል።

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ይካሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ዕርምጃን ላይ የሚወስድ ሃገር አቀፍ ኮሚቴ መቋቋሙ ተገለጸ ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2009)


አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ይካሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ዕርምጃን የሚወስድ ሃገር አቀፍ ኮሚቴ መቋቋሙ ተገለጸ።Bilderesultat for የውጭ ምንዛሪ ወደ
ከአንድ ሳምንት በፊት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ልዩ ትዕዛዝ የተቋቋመው ይኸው ኮሚቴ ሃገሪቱ ለከፋ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንድትዳረግ አስተዋጽዖ አድርገዋል በተባሉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃን እንደሚወስድ ካፒታል የተሰኘ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ ዘግቧል።
በተለምዶ “ጥቁር ገበያ” ተብሎ በሚጠራው የገንዘብ ልውውጥ ዙሪያ ጥናቱን ያካሄደው የፋይናንስ ደህንነት ማዕከል ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ በህገወጥ መንገድ ከሃገሪቱ በመውጣት ላይ መሆኑን እንደተረጋገጠ ጋዜጣው የማዕከሉን ሃላፊዎች ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጭ ሃገር ዜጎች እንዲሁም በውጭ ምንዛሪ ክፍያን የሚያገኙ ሰዎች ለህገወጥ የገንዘብ ልውውጥና ዝወውር አስተዋፅዖ  ማድረጋቸውን የማዕከሉ ሃላፊ አቶ ገመቹ ወዮማ ገልጸዋል።

በባህር ዳር የባጃጅ ሹፌር የሆነ ወጣት በወያኔዎች ደረቱ ላይ በጥይት ተመትቶ ተገደለ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
በባህር ደር በሁለት ወጣቶች ላይ በደረሰ ጥቃት አንደኛው ወዲያው ነፍሱ ሲያልፍ ሌላኛው ክፉኛ ተጎድቶ በህክምና ላይ እንደሚገኝ ታወቀ።
በአሰቃቂ መንገድ የተገደለው ወጣት በአከባቢው በባጃጅ ሹፌርነት የሚተዳደር እንደነበረም ታውቃል። የሞተውም በደረቱ ላይ  በተተኮሰበት ጥይት መሆኑንም የአይን እማኞች ገልጸዋል።

ሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ግንባር ከትግራይ የተነሳ ሃይል ተደመሰሰ | 16 ሙቶ ብዙ ቆሰለ | ገዱ አንዳርጋቸው በወታደሮች ታጅቦ ደባርቅ ይገኛል



የሙሉነህ ዮሐንስ ዘገባ

ከትግራይ በሽራሮ በኩል ተከዜን ተሻግሮ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ይጓዝ የነበረውን የወያኔ ወታደራዊ ኮንቮይ አድፍጠው የቆዩ የአካባቢው ጀግኖች ከፋኞች ድባቅ መተውታል። እጅግ የሚያስደስተው ደግሞ ወያኔ ይጠቅሙኛል ብሎ ያሰባቸው ያካባቢ ሚሊሺያ ታጣቂወች ከህዝቡ ጋር አብረው ተሰልፈው የወያኔ ሃይል መውጫ እንዳያገኝ አድርገው ቀጥተውታል።
በደረሰን መረጃ መሰረት 16 ወያኔ ተገሎ ወደ 30 ሲቆስል ብዛት ያለው ቀላልና የቡድን መሳሪያወች ተማርከዋል። ሰፊውን የሁመራ ወልቃይት ጥገዴና ጠለምት መሬቶች በገፈፋ ከጎንደር የነጠቀው ወያኔ አሁንም እንደ ግጨው የመሰሉ ሰፋፊ የጠገዴ ተጨማሪ ቦታወችን ወደትግራይ ለመውሰድ ከመሞከር አልቦዘኑም። ተከዜን ተሻግረው ካልሄዱ ጤናም የለ እረፍትም የለ! ጎንደር ወስኗል! አማራ ወስኗል! ኢትዮጵያም ወደ ቀደም ክብሯ ትመለሳለች::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ር ዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሰሜን ደባርቅ ከተማ እንደሚገኝ ታወቀ:: ዛሬውኑ ዳባት ደርሶ ወደጎንደር እንደሚመለስ መረጃ አለ::

Wednesday, January 11, 2017

አሜሪካ ወደ ጎንደር የሚደረግ ጎዞንም አገደች። ለዜጎቻም የደህነት ማስጠንቀቂያ መልክት አስተላልፋለች

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
የአሜሪካ መንግስት በጎንደር ኢንታንሶል ሆቴል በደረሰው የቦምብ ጥቃት መሰረት በማድረግ ለዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያና እገዳ አውጥቷል።
በሆቴሉ በደረሰው ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ወደ ስድስት መጎዳታቸውን የኢትዮጵያን ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ሪፓርት መረዳቱን የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጻል።
በወያኔ ህውሃት በበላይነት በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያ የሚደረግ ጉዞ የሚያስከትለውን አደጋ ለአሜሪካ ዜጎች በየወቅቱ እንደሚገልጽም አሳውቋል።
ህዝቡ ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር በትጥቅ ትግል እየተፋለመባት ወደ ሚገኝው ጎንደር ከተማ የሚደረግ ጎዞንም የአሜሪካ ኤምባሲ ላልተወሰነ ጌዜ ማገዱንም ገልጻል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል የደረሰውን የቦምብ አደጋ ተከትሎ ኤምባሲው የአሜሪካ ዜጎች ወደ ባህር ዳር ጉዞ እንዳያደርጉ ማሳወቁም ይታወሳል።

የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ያሉት አስራ ሁለቱ የኤፍ ቁልፎችና አገልግሎታቸው



F1 ይህን አቋራጭ መንገድ መጠቀሚያ ቁልፍ እርዳታ ሲፈልጉ መጠቀም ይችላሉ።No automatic alt text available.
F1 ቢጫኑ “help” የሚለው አማራጭ ይመጣል ጎግል ክሮም ከሆኑም ክሮም ሄልፕ ሴንተርን ያገኛሉ፤ ከዚያም የፈለጉትን በመጻፍ መጠየቅ ይችላሉ።
F2 ይህ ቁልፍ ደግሞ ተጽፎ አልያም ከኢንተርኔት በማውረድ ኮምፒተርዎ ላይ ያስቀመጡትን መረጃ ወይም ፋይል ስም ለመቀየርና ለማስተካከል ወይም ‘edit’ ለማድረግ የሚጠቀሙበት ነው።
ምናልባት የጻፉትን ነገር ስሙን ማስተካከልና መቀየር ከፈለጉ ያንን ፋይል በመምረጥ F2ን በመጫን ማስተካከል ይችላሉ።
ማይክሮሶፍት ኦፊስ እየተጠቀሙ ከሆነ ደግሞ፥ Alt + Ctrl + F2 በመጫን የፋይል ማህደሩንም መክፈት ያስችልዎታል።
F3 ደግሞ ዊንዶው ኤክስፕሎረር ወይም ኢንተርኔት ላይ ፋይልና መረጃዎችን ለመፈለግ ይጠቅማል።
አድሬስ ባሩ ላይ በመጻፍ አንድን መረጃ መፈለጊያ ‘search’ ማድረጊያ ነው።
ማይክሮሶፍት ወርድ እየተጠቀሙ ከሆነ ደግሞ፥ Shift + F3ን በመጠቀም እንግሊዝኛ እየተጠቀሙ ከሆነ የመረጡትን ጽሁፍ በካፒታል ማስቀመጥ ያስችልዎታል።
F4 ከተጠቀሙ ደግሞ ከፍተውት የነበረውን ወርድ መዝጋት ይችላሉ፤ ለዚህም Alt + F4ን መጫን ነው።
ይህ ቁልፍ በፍጥነት ለመዝጋት ስለሚያግዝ ከፍተውት የነበረውንና ሌሎች እንዲያዩት የማይፈልጉትን የወርድ ፋይል በቶሎ ለመዝጋት ያስችልዎታል።
F5 ኮምፒውተር በተለይም ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ይህን ቁልፍ በሚገባ ያውቁታል።
ይህን ቁልፍ በመጫን ኮምፒውተሩን ‘refresh’ ለማድረግ ያግዛል።
ከዚህ ባለፈም ኢንተርኔት እየተጠቀሙ Ctrl+F5ን ከተጫኑ የከፈቱትን አንድ ታብ ብቻ ‘refresh’ ለማድረግ ያግዛል።
F6 በመጠቀም ማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ ከዴስክቶፑ ወደ ሌሎች ፋይሎች ይወስዳል።
ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ላይ ደግሞ F6ን በመጫን ወደ አድሬስ ባሩ መድረስ ይቻላል።
F7 ብዙ አገልግሎት የለውም
F8 ምናልባት ኮምፒውተሩን እያበሩ ከሆነ ስራ እስከሚጀምር የሚወስደውን ጊዜ ለመቀነስ F8 ሲጫኑ በኮምፒውተሩ Start Menu እንዲገቡ ያስችልዎታል።
F9 ይህ ቁልፍ ደግሞ የኮምፒውተር ፕሮግራመር ለሆኑት የሚጠቅም ነው።
እነዚህ ባለሙያዎች Ctrl+F9 በመጠቀም ፕሮግራሙን በአንድ መሰብሰብና የሚጠቀሙበትን ኮድ ማስጀመር ይችላሉ።
F10 ማይክሮሶፍት ኦፊስ የሚጠቀሙ ከሆነ F10 በመጫን የወርዱ መግቢያ ወይም Menu bar ላይ የፈለጉትን ለመምረጥና ለመገልገል ያስችልዎታል።
ከዚህ ባለፈም Shift + F10ን በመጫን ፋይሉን ኮፒ ለማድረግ እና ለመገልበጥ፣ ለማስተካከል፣ ለማጥፋት የሚጠቀሙበትን ወይም ሌሎች አማራጮችን ለማግኘት ያስችልዎታል።
ይህም ማውዙን በቀኝ በኩል ክሊክ ሲያደርጉት የሚመጡትን አማራጭ Shift + F10ን በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
Ctrl + F10ን በመጫን ደግሞ የሚሰሩበትን ወርድ ማሳነስና (minimize) በማድረግ፥ በኮምፒውተሩ ስክሪን ሌሎች ስራዎችን የመስራት አማራጭ ያስገኝልዎታል።
F11 ቁልፍ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ ከተጫኑት የኮምፒውተሩን ሙሉ ስክሪን እንዲያዩ ያስችልዎታል።
F12 ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ሆነው F12 ሲጫኑ እየጻፉት ያለውን ፋይል ማስቀመጫ መንገድ Save As አማራጭ ይመጣልዎታል።
እርስዎም ከፈለጉ ባለበት አልያም በሌላ አማራጭ ተጠቅመው ማስቀመጥ ይችላሉ።
ምናልባት የጻፉትን ዶክመነት ፕሪንት ማድረግ ከፈለጉ ደግሞ Ctrl + Shift + F12ን መጠቀም ይችላሉ።
ያን ጊዜም የመጣውን አማራጭ ተጠቅመው ፕሪንት ለማድረግ ማዘዝ ያስችልዎታል።
ይህን ፕሪንት የማድረግ አማራጭ በማይክሮሶፍት ኦፊስ ላይ ሲሆኑ፥ Ctrl + P በመጫን ማግኘትም ይችላሉ።

ጥብቅ ማሳሰቢያ! Alert! Share it!


ባለፉት ጥቂት ቀናት በአሜሪካ የሚገኙ የወያኔ አሽከሮች፣ ሆድ አደሮች በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር የአሜሪካ አምባሳደር ሰብሳቢነት ውይይት ተካሂዶ ነበር። ከውይይቱ ተሳታፊዎች አብዛኛዎቹ ትግሬዎች ናቸው።
ለአምባሳደሩ የቀረበለት ጥያቄ ጎንደር ስርአት አልበኛ ሲሆን መንግስት ምን እያደረገ ነው?
መልስ፦
1. መጠነ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ነው ጎንደርን መቀጣጫ ለማድረግ ። በተጨማሪም ከጎንደር ገበሬ ጋር ባለፉት ጦርነቶች ወታደሮች እየከዱ ያስቸግሩን ነበር አሁን ግን የሚከዳ ወታደር እንዳይኖር እያደርግን ነው። በቅርቡ በጎንደር ገበሬዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል። 
 2 ቅማንትን ለማካለል የወሰድነው እርምጃ ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛው የቅማንት ህዝብ አልደገፈነም። አሁን ግን በአዲስ ዘዴ የቅማንትን የማንነት ጥያቄ እንዲነሳ በማድረግ ጎንደርን እናዳክማለን ። ይህም በቅርቡ ይደረጋል ነው።
ማሳሰቢያ ይህ ማስረጃ በአስቸኳይ ለህዝባችን በአስቸኳይ በሚቻለው መንገድ ሁሉ እንዲደርስ ቢደረግ ጥሩ ነው።
ሙሉነህ ዮሃንስ

አሁን የደረሰ ዜና:- ጎንደር አደጋ ላይ ናት


#አሁንም ጎንደር አደጋ ላይ ነት። የቀበሌ 16 ወይም ፅ/ቤት በእሳት ተቃጠለ። ዝርዝሩን እያጣራን ነው። 
#የጎንደር ሆስፒታል አልትራ ሳወነድ ማሽን ጠፋ ተባለ። ህዝቡ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ የተደረገ ደባ ነው።
#ቀበሌ 18 ወጣቶችን ሲያሳስር ሲጠቁም የነበረው ከውትድርና የተመለሰው የቀበሌ አመራር የሆነው ሰው ባልታወቁ ሰወች እርምጃ ተወስዶበታል።
#አሁንም ዳሽን ቢራ ቁጣን ቀሰቀሰ። ከተለያዩ የትግራይ ከተማ ያስመጣቸዉን 8 አባለቱ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ዉስጥ በስራ ሂደት አስተባባሪ እና ቡድን መሪ አድርጎ ሹመት ሰጥቷቸዋል።
#ወያኔ ጎንደር ላይ ከገጠር እስከ ከተማ ሙሉ ጦርነት ከፍቷል።
ሙሉነህ ዮሃንስImage may contain: sky and outdoor

እኔ ለነጻንቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ethiopia

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)




የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በአንባገነኑ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አደረሰ
የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በአንባገነኑ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሷል በታህሳስ ወር ተከታታይ ቀናት ወያኔ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብሎ በሚጠራው አካባቢ ጋማድ በተባለ ልዩ ቦታ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በህወሓት መሳሪያ አንጋቾች ላይ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት 13 የወያኔ ሰራዊቶች ሲገደሉ ከ8 በላይ የቆሰሉ ሲሆን በርካታ የነፍሶከፍና የቡድን መሳሪያ መማረካቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚሁ በቤንሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ክልል በሱዳን ድንበር አካባቢ ልዩ ቦታው መኩዋር ሹሩ ቆሌ በተባለ ስፍራ በዚሁ ታህሳስ 23
ቀን 2009 ዓ.ም. የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄና በአገዛዙ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ከፍተኛ ውጊያ ከ40 በላይ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊሶች ሲገደሉ ከ80 በላይ ደግሞ ቁስለኛ በመሆን አሶሳ ከተማ የሚገኘውን ራሻ ሆስፒታል አጥለቅልቀውታል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለነፃነት ታጋዮች ስንቅና ውሃ አቀብላችኋል በማለት በበርካታ ዜጎች ላይ ድብደባና እስር እንደፈፀመባቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡Image may contain: one or more people, text and outdoor

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)



የህወሓት ተላላኪ ሆኖ በርካታ በደሎችን በህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረው ደረጄ መከታው የተባለው ግለሰብ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ ታወቀ፡፡No automatic alt text available.

ESAT Egna Manen by Serkaddis YARADA LIJ

የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ግዕዝ ማስተማር ጀመረ ጥር 3፡2009



የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ በትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ ዘዊኬንድ የገንዘብ እርዳታ ጥንታዊውን ኢትዮጵያዊ የግዕዝ ቋንቋ ለ25 ተማሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጥንታዊ መፅሀፍት የተፃፉበትን የግዕዝ ቋንቋ በማስተማሩ ዩኒቨርሲቲው የግዕዝ ቋንቋ ከሚሰጥባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ አድርጎታል፡፡
ለዘመናት በቂ ጥናት ሳይደረግበት የቆየውን፣ በርካታ ታሪክና እውቀት ያዘሉ ፅሁፎች የተፃፉበትን የግዕዝ ቋንቋ በማስተማር በማሀል የተዘለለውን ታሪክና እውቀት ለማጥናት ያስችላል ተብሏል፡፡
በዩኒቨርስቲው የሩቅና የመካከለኛው ምስራቅ ስልጣኔዎች ዲፓርትመንት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ራበርት ሆልምስቴድት በቶሮንቶ ለሚገኙ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብና አካባቢ ነዋሪዎች ለተውጣጡ 25 ተማሪች የመጀመሪያውን የግዕዝ ትምርት መስጠት ጀምረዋል፡፡
ምንጭ፡- የቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !Image may contain: one or more people, beard and textImage may contain: 1 person, sitting

Tuesday, January 10, 2017

ESAT Breaking news 10 Jan 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ነፃነት ፍትህ ዴሞክራሲና አንድነት ክፍል 2

አስድንጋጭ ዜና (የአባ ጃሌው)



ይደረስ ለጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ( ጎህ)
ሰሜን አሜሪካ 
በጎንደር ከተማ እድሜያቸው ከ አስራ አምስት ዓመት በታች ላሉ የ ትምህርት ቤት ህፃናት ከ ሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ ክትባት እንዲወስዱ ሲገደዱ የነበረ ሲሆን ፡ብዙዎቹ ክትባቱን የወሰዱ ህፃናት የ ኩላሊት ህመም እና ፊታቸው ላይ የመነፋፋት( የማበጥ) ነገር ታዮቶባቸዋል፡፡ የክትባቱ ምንነት እስካሁን አልታወቀም
እባካችሁ የጎንደር ህብረቶች ለጎንደር ህዝብ ድምጽ ሁኑት ።

Ethiopian PM: Around 20,000 detained under state of emergency

Monday, January 9, 2017

በአዲስ አበባ ከተማ ከንግድ ይዞታቸው የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ለከፍተኛ ስቃይ ተዳረጉ ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

 በልማት ስም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዘመናት ሃብት አፍርተው በንግድ ስራ ላይ ይተዳደሩበት ከነበሩት ይዞታቸው የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ለሶስት ዓመታት በስቃይ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።Bilderesultat for መርካቶ ውስጥ

ነጋዴዎቹ ቤተሰባቸውን ከሚያስተዳድሩበት ይዞታቸው ተነስተው በምትኩ ተለዋጭ ቦታ ይሰጣችኋል ቢባሉም እስካሁን ድረስ መስተዳድሩ የገባላቸውን ቃል አላከበረም። ቁጥራቸው ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑት እነዚህ ነጋዴዎች ከአስር በላይ የአክሲዮን ማኅበራትን መስረተው ተደራጅተው ጉዳያቸውን ቢከታተሉም ሰሚ አካል አላገኙም።
በልደታ ክፍለ ከተማ ሦስት፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስምንት፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሦስት የአክሲዮን ማኅበራት አቤቱታ ቢያቀርቡም ጉዳያቸውን አስመልክቶ ምላሽ የሰጣቸው አካል የለም። ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በልደታ ክፍለ ከተማ ተክለሃይማኖት አካባቢ የነበረው 33 ሄክታር የንግድ ይዞታቸውን ያጡት 122 ነጋዴዎቹ 24 ሚሊዮን ብር በማዋጣት በባንክ አስቀምጠው ‹‹ጥቁር አንበሳ አክሲዮን ማኅበር›› በሚባል ስያሜ የንግድ ድርጅት ያቋቋሙ ቢሆንም በምትኩ የተሰጣቸው ነገር የለም።

በጂጂጋ የተደረገው የጦር አዛዦች ስብሰባ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚደረገው ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳለፈ ጥር ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

 ባለፈው ሳምንት በጂጂጋ ከተማ በተደረገው  የከፍተኛ የጦር አዛዦች ስብሰባ ላይ በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ውሳኔዎችን አሳልፏል።Bilderesultat for ከፍተኛ የጦር መኮንኖች

የምእራብ እዝ ማሰልጠኛ ሰሜን ጎንደር በሚገኘው ሰራባ በሚባለው ቦታ ላይ እንዲሆን የመጨረሻ ውሳኔ  በደቡብ ምስራቅ እዝ በ13ኛ እና 32ኛ ክፍለ ጦሮች ስር የሚገኙ ሁለት ሬጀመንት ጦር ወደ ሰሜን ጎንደር በማምጣት፣ ሰሜን ጎንደርን ሙሉ ለሙሉ የወታደራዊ ቀጠና አድርጎ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ መደምሰስ የሚል ውሳኔም አሳልፏል።
እንዲሁም በጭልጋ የሚቋቋመውን አንድ አዲስ ክፍለ ጦር በፍጥነት አደራጅቶ ወደ እንስቃሴ እንዲገባ የማድረግ ስራን ተቀላጥፎ ይቀጥል ብሎአል። ይህን ተግባር ለማከናወን ለሚቋቋመው አዲስ ክፍል ጦር የሚሆን ሰራዊት ከተለያዩ የጦር ክፍሎች እንዲዋጣ እንዲሁም ታህሳስ 25 ከብር ሸለቆ የተመረቁ 400 የሚሆኑ አዲስ ምልምል ወታደሮች ጭልጋ ላይ በሚቋቋመው ክፍለ ጦር ሰር እንዲጠቃለሉ የተወሰነ መሆኑ ታውቋል።