Sunday, January 8, 2017

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ስነድንቁርናን በከፍተኛ መጠን ሥራ ላይ ማዋል ጀምረዋል።

ትክክለኛ ትርጓሜ ስለመሆኑ እርግጠኛ ባልሆንም የእንግሊኛው ቃል “Agnotology” (Agnōsis - አለማወቅ እና logia ከሚሉ ሁለት የግርክ ቃላት የመጣ ነው) “ስነድንቁርና” ብዬ ወደ ተርጉሜዋለሁ።Image may contain: one or more people, people sitting, shoes and outdoor

ስነ ድንቁርና የራስንም ሆነ የሌሎች ሰዎችን አለማወቅ (ignorance) መጠቀሚያ የሚያደርግ “የጥናት ዘርፍ” ነው። ስነድንቁርና “በእውቀት ላይ የተመሠረተ መሀይምነትን” መፍጠር ነው። ስነ ድንቁርና በቢዝነስ ጎጂ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ለማሻሻጫ ይውላል፤ በፓለቲካ ደግሞ ጎጂና ኋላ ቀር አስተሳሰብን ጠቃሚና ዘመናዊ አስመስሎ ለማቅረብ ይረዳል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ስነድንቁርናን በከፍተኛ መጠን ሥራ ላይ ማዋል ጀምረዋል።

አባይ ፀሀዬ የአገራችን ግንባር ቀደሙ የስነድንቁርና ምሁር ነው። የጠ/ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ በመሆኑ የሚያማክረውን ጠ/ሚ ጨምሮ በዙሪያው ያሉት ደናቁርት ድንቁርናቸው “በእውቀት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን” ሌት ተቀን ይለፋል። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በተመለከት የሚሰጣቸው ገለፃዎችና ማስፈራሪዎች “በእውቀት ላይ የተመሠረተ ድንቁርና” ውጤቶች ናቸው። ትንተናዎችን ሲሰጥ ልብ ብላችሁ አዳምጡት። አባይ ፀሀዬ የሚናገራቸው ነገሮች የሰዎችን መሠረታዊ መብቶች መጋፋታቸው ቀርቶ “ህገ-መንግሥት” ተብሎ ከሚባለው ሰነድ ጋር የተጣሉ መሆናቸው “በእውቀት ላይ በተመሠረተ ድንቁርና” ሸፋፍኗቸው ያልፋል።
ሳሞራ የኑስ ለድንቁርናው “መከላከያ” የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝቷል። ሳሞራ የመከላከያ ኤታማዦር ሹም ሆኖ እያለ ስለፓለቲካ በድፍረትና በልበሙሉነት የሚፈተፍተውም የተመሰከረለት የስነድንቁርና ምሁር ስለሆነ ነው።

ስነድንቁርና መረጃዎችን ይሻል። ከተቻለ ያሉትን መረጃዎች አዛብቶ ይጠቀማል፤ አሊያም ይፈጥራቸዋል። ለምሳሌ ኃይለማርያም ደሣለኝ የ 2015 ምርጥ የዓለም መሪ የሆነበት መረጃ እንደተገኘ ሁሉ ማለት ነው። እንዳይበዛ በዚህ ልቋጨው እንጂ ብዙ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ

መልካም የገና በዓል።

No comments:

Post a Comment