Monday, January 9, 2017

በባህርዳር ወህኒ ቤት የተገደሉት 4 ወጣቶች ያስከሬን ምርምራ ሳይደረግላቸው ተቀበሩ

በአማራ ክልል በሁሉም ከተሞች አሁንም ህዝቡ ወደ መደበኛ ህይወቱ መመለስ አልቻለም። ወታደራዊ እዙ በየጊዜው ወጣቶችን እየያዘ ማሰሩ እንዲሁም “ ጸጉረ ልውጦች ገብተዋል” በሚል ሰበብ የሚደረገው ፍተሻ ህዝቡን በእጅጉ እያማረረ ነው።
http://amharic.abbaymedia.com/
በሌላ በኩል በባህርዳር ወህኒ ቤት የተገደሉት 4 ወጣቶች ያስከሬን ምርምራ ሳይደረግላቸው እንዲቀበሩ ተደርጓል። በአዲስ ቅዳም ወረዳ በሚገኘው መሰናዶ ትምህርት ቤት ያስተምር የነበረው መምህር አሸናፊ ሸዋረጋው እና ሌሎች 3 እስረኞች ጠዋት ላይ ቁርስ በልተው ስፖርት በመስራት ላይ እያሉ ለየብቻ እየተጠሩ መርፌ መወጋታቸውን ከዚህ በሁዋላ ሁሉም ህይወታቸውን ማለፉን ምንጮች ለኢሳት ገልጸው ነበር።

እስረኞቹ መሞታቸው ከታወቀ በሁዋላ ፖሊሶች የእስረኞችን ቤተሰቦች ጠርተው እስረኞቹ በህመም እንደሞቱ ለማስረዳት ሞክረዋል። የእስረኛ ቤተሰቦች ግን አስቀድመው ከሌሎች እስረኞች ባገኙት መረጃ መሰረት እንዲሁም ሰዎቹ ስለመታመማቸው አንድም ቀን ሳይነገራቸው እንዲሁም አራቱም ተጥረተው ሲመለሱ መሞታቸውን በመጥቀስ ታመው ሞቱ የሚለውን እንደማይቀበሉት ተናግረዋል። ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ቤተሰቦች  ይህን አምናችሁ ማትቀበሉ ከሆነ በራሳችሁ ላይ ሌላ ችግር ትፈጥራላችሁ ተብለው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።
የሟች መምህር አሸናፊ እናት ልጃቸውን እንዲያዩ ቢጠይቁም አስከሬኑን አጅበው የሄዱት ፖሊሶች የልጃቸውን ፊት ብቻ እንዲያዩ በማድረግ ሌላውን የሰውነት ክፍሉ እንዳይከፈት አድርገዋል። አስከሬን ምርምራ እንዳይደረግ በማድረግ የቀብር ስነስርዓቱ ተፈጽሟል።
የመምህር አሻነፊ ጓደኞች ለምንጮች እንደገለጹት መምህሩ ስለአገሩ የሚጨነቅና ለነጻነቱ ሲል ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነበር። በእስር ቤት ውስጥ እስረኞችን ታሳምጻለህ እየተባለ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው ቆይቷል። የእሱን አሟሟት ለማጣራት ወደ ማረሚያ ቤቱ በሄዱበት ወቅት በየጊዜው ተመሳሳይ ግድያዎች እንደሚፈጸሙ እንደነገሩዋቸው ተናግረዋል።
4ቱ ወጣቶች 7 ሆነው አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ወደ በረሃ ሲሄዱ ከመካከላቸው አንደኛው ጠቁሙ አስይዟቸዋል። ጠቁዋሚው በአሁኑ ሰአት የመንግስት ስልጣን ተሰጥቶት በስራ ላይ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment