አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
(ምስል ከፋይል)
በመተማ አከባቢ ተከታታይ ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ እየተነገረ ይገኛል።
በጎንደር መተማ በሚገኝ አንድ የጥጥ ምርት ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በተጣለ የእጅ ቦምብ ጉዳት ደርሷል። ፋብሪካው በፍንዳታው በእሳት ጋይቷል ከፍተኛ ንብረትም ጠፍቷል።
ንብረትነቱ የህውሃት/ወያኔ በሆነው በዚህ የጥጥ ማምረቻ ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ሰአት እንደሌለ ሪፓርቶች ይገልጻሉ።
ይህንን ፍንዳታ ተከትሎ አገዛዙ የአከባቢው ነዋሪዋችን በስፋት በቁጥጥር ስር በማዋል አስሯል። በተጨማሪም አገዛዙ ከጥቃቱ በሃላ በመተማና በገንዳ ውሃ አከባቢም በርካታ ወታደሮችን አስፍሯል።
በዚህ ሳምንት እረቡ እለት በፍብሪካው ላይ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደ ግለሰብም ሆነ ድርጅት አልተገኝም። የህዝባዊ እምቢተኝነቱና አመጹ በይበልጥ የአገዛዙን ንብረት ኢላማ ያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል።
ይህም የጥጥ ማምረቻ ፋብሪካ ንብረትነቱ የአገዛዙ መሆኑ ምንአልባት የህዝባዊ አመጹ ኢላማ ሆኖ ተገኝቷል የሚል የብዙዎች ግምት ሆኗል።
በባህር ዳርና በጎንደር በሚገኙ ሆቴሎች ተመሳሳይ የእጅ ቦምብ ፍንዳታዎች መከሰታቸው ይታወሳል። ለነዚህ ፍንዳታዎች ሃላፊነቱን የወሰደ እንደሌለም ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment