Monday, October 31, 2016

“ ቅድሚያ አዲስአባ! የቅድሚያ ቅድሚያ ኢትዮጵያ!!” ኤርሚያስ ለገሰ

ማስታወሻ
*** ይህ ጽሁፍ ከራሴ ውጭ የምሰራበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬዲዮ (ኢሳት)ን ጨምሮ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም::
“የአዲስ አበባ ነዋሪ” (“አዲስ አበቤ”) የሚለው ቃል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሆኖ በአዲስ አበባ የሚኖር አሊያም ለወደፊት መኖሪያውን አዲስ አበባ ለማድረግ የፈለገን በሙሉ የሚያጠቃልል ነው።

1. መንደርደሪያ
የዛሬ ሦስት ወራት አካባቢ ከኦሮሞ አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ ጋር በኢሳት ስቱዲዮ ለአጭር ሰዓታት ኢ-መደበኛ ወግ ጠርቀን ነበር። ገረሱ በወጋችን መሀል “ለጋራ መፍትሔ ግልፅና ደፋር ውይይት የማድረጊያው ሰዓት አሁን ነው” በማለት ይናገር ነበር። መልሶ መላልሶም “የጋራ ችግር አለብን፤ ያልተነጋገርናቸው እና በይደር ያቆየናቸው ድፍረት የሚጠይቁ አጀንዳዎች ከፊታችን ተቆልለዋል። በግልፅና በሐቅ ተወያይተን መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል” እያለ የቀጣይ ስጋቱን ይዘረዝር ነበር። የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገንም ጭምር። የነገንም ብቻ ሳይሆን የተነገወዲያውም። ለልጅና ልጅ ልጆቻችን!
ከቀናቶች በኋላ ይሄንኑ አባባል በኦሮሞ ጉዳዮች ላይ ብዙ ምርምር ከሰራውና የወቅቱ የኦሮሞ ጥናት ማዕከል ፕሬዝዳንት ከሆነው ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ ሰማሁት። ርግጥ ከላይ ከተገለጠው የገረሱ አባባል ጋር ቃል በቃል የተገለጠ አይደለም። መንፈሱ ግን ተመሳሳይ ነው። አገር አደጋ ላይ ወድቃለችና የልባችንን አውጥተን እንነጋገር፤ እንመካከር የሚል ነው። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ የማያሳስበው ዜጋ ያለ አይመስለኝም። በሌላም በኩል ወርቃማ የለውጥ ሁኔታን በብስለት ካልያዝነው ከእጃችን ሊወጣ ይችላል የሚል ነው። የህዉሃት መራሹ መንግስት የአገዛዝ ፖሊሲ መሰረት ያደረገው የኢትዮጵያ የለውጥ ሃይሎች የማይተባበሩ፣ በፖለቲካ ስልጣን፣ ብሄርና ሃይማኖት ተከፋፍለው የውስጥ ሽኩቻ የሚያደርጉ የሚለው ክስ ወደ እውነት እንዳይቀየር ነው።
“ግልፅ ውይይት” የሚለው አባባል በጽሁፍና በቃል ሲገለጽ ቀላል ሊመስል ይችላል። ወደ ተግባር ሲገባ ግን እጅግ ከባድና ውስብስብ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አይቀርም። ከባድ የሚያደርገው ወደ ተግባር የማይቀየር ስለሆነ አይደለም። ይልቁንስ ከባድ የሚያደርገው ይህን አስተሳሰብ አቅጣጫ የሚለውጥ ውይይት ለማድረግ ለሚጠይቀው መስዋዕትነት ምን ያህል ተዘጋጅተናል የሚለው ይመስለኛል። የተለያዩ ጥቅሞችና ፍላጎቶችን ለማጣጣምና ለጋራ ድል (win- win) በሁላችንም ዘንድ ምን ያህል ፍቃደኛነቱ አለ የሚለውም በተዛማች ሊነሳ የሚችል ነው። ህወሐት የሚባል የጋራ ጠላት ላይ በሚደረገ ርብርብ (ትክክል እንደሆነ አምናለሁ) በተቀየሰ ስልት በአርምሞ

ሲራጅ ፈርጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ የታሰሩትን ሰዎች ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደሉም ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009)


Bilderesultat for ሲራጅ ፈርጌሳበኢትዮጵያ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎችን ቁጥር ለመግለጽ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተዘገበ።
የኮማንድ ፖስቱ ዋና ጸሃፊ ተደርገው የተሰየሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ዕሁድ በሰጡት መግለጫ፣ 2ሺህ ሰዎች ምክር ተሰጥቷቸው ተለቀዋል ቢሉም የታሰሩትን ቁጥር ለመገለጽ ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተመልክቷል።
በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ አፈሳ የታሰሩ መሆኑ ይታወቃል።
በተለይም በመደበኛው የህግ ስርዓት ሃገሪቱን መምራት የተሳነው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው።
ባለፉት 10 ቀናት ብቻ 2ሺህ 6 መቶ ሰዎች መታሰራቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ተከትሎ የማህበራዊ ሚዲያና ሌሎች የኢንተርኔት ግንኙነቶች እገዳ እንደተጣለባቸው ይታወቃል።

አዲስ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009)


በአራት የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ።
በሃገራዊ ንቅናቄው የምስረታው ስነስርዓት ላይ ያወጣው የጋራ መግለጫ እንደሚያመለክተው ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው የተከበረባትና ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መመስረት የህብረቱ ዋነኛ ዓላም መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ በአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በአፋር ህዝብ ፓርቲ፣ እና በሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያው ንቅናቄ የተፈጠረ ህብረት መሆኑን በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል።
በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በተካሄድው ስነስርዓት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባት ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር  ብርሃኑ ነጋ፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ እና የሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ዋዮ ፊርማቸውን በማስቀመጥ ንግግር አድርገዋል።

ሶማሊያ የሚገኙ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ትእዛዝ አንቀበልም በማለት ገሚሶቹ ሲጠፉ ሌሎች ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም አሉ


ጥቅምት ፳፩ (ሃያ አንድ ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-Bilderesultat for የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ የኢሳት የወታደራዊ የደህንነት ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊያ በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ስም ያልታቀፉትና ላለፉት 4 አመታት ከአልሸባብ ጋር ሲዋጉ ከነበሩት ወታደሮች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት ትእዛዝ አንቀበልም በማለት አምጸው ከቀዩ በሁዋላ ከ70 ያላናሱት የጦር መሳሪያዎቻቸውን ሸጠው ባህር ተሻግረው ወደ አረብ አገራት ሰያቀኑ፣ ቀሪዎቹ ወደ አገሩ ከተመለሰው ጦር ጋር አብረን አንጓዝም በማለት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መበታተናቸውን ገልጸዋል።
አመጹ ለወራት የዘለቀ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ወታደሮች ከሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች መካከል ዘረኝነትና የክፍያ መቋረጥ ዋነኞቹ ናቸው። በአመጹ ውስጥ የተሳተፉት ወደ ኢትዮጵያ እንደመለሱ ለማግባባት ሙከራ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ወደ አገራቸው ሲመለሱ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በመግለጽ ማግባባቱን ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

Ethiopia: State of Emergency Risks New Abuses (HRW)

(Nairobi) – An Ethiopian government directive under a state of emergency contains overly broad and vague provisions that risk triggering a human rights crisis, Human Rights Watch said today in a legal analysis. The government should promptly repeal or revise all elements of the directive that are contrary to international law.

Sunday, October 30, 2016

Ethiopia | Dr Berhanu Nega Speech for the establishment of Ethiopian Nat...

ኮንትራታቸውን የጨረሱ የወያኔ ሰራዊት አባላት አዲስ ኮንትራት አንፈርምም አሉ!

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰBilderesultat for ወታደር

http://amharic.abbaymedia.com/
የወያኔ ሰራዊት አባላት የሆኑና የሰባት አመት ኮንትራታቸውን የጨረሱ አዲስ የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ የቀረበላቸውን ጥያቄ በአባላቱ ተቀባይነት ያለማግኘቱ ሲታወቅ በመከላከያም በኩል በወቅቱ ከሚገኝበት ሁኔታ ሳቢያ ሰራዊቱን ማሰናበት ያለመፈለጉ ታውቋል፡፡
የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ በ1999 ዓ/ምና 2001 ዓ/ም የተቀጠሩ የፈረሙት የሰባት አመት የስራ ኮንትራት በመጠናቀቁ ምክንያት ሁለተኛ ዙር የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ ደብዳቤ ቢደርሳቸውም በአብዛኛው የሰራዊቱ አባላት እስካሁን ለመፈረም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ይልቁንም ወደ የቤተሰባቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
መረጃው አያይዞም የመከላከያ ሰራዊቱ አመራር አካላት የምንገኘው በፈታኝ ወቅት ላይ ነው በሚል ኮንትራት የጨረሱትን የሰራዊቱ አባላት አዲሱን ኮንትራት እንዲፈርሙ ለማግባባት ቢሞክሩም እስከአሁን ያልተሳካላቸው መሆኑን ሲያስረዳ በአንፃሩም ሰራዊቱም በዚህ ወቅት ማሰናበት እንደማይችሉ ለአባላቱ የገለጹ መሆኑን ያስረዳል፡፡
በተጨማሪ ኮንትራቱን አንፈርምም ያሉት የሰራዊቱ አባላት በቆይታቸው ሊያገኙት የሚችሏቸውን ማንኛውም ጥቅማ ጥቅም በመከልከል አስገድዶ ለማስፈረም የተለመደው ሙከራ መደረጉ የማይቀር መሆኑን መረጃው ሲያስረዳ በአሁኑ ሰአት የወያኔ ስርአት የገጠመውን ፈተና በሰ ራዊት ሀይል ለመቋቋም በመጣር ላይ መሆኑና ተጨማሪ ሰራዊት መመልመል ያለመቻሉ ተጨማሪ ፈተና በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኮንትራታቸው ን በጨረሱ የሰራዊቱ አባላትን በግዳጅ በስራ ለማቆየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሊፈጥር የሚችለው ችግር ምልክቶች ከወዲሁ እየታዩ መሆኑንም ጨምሮ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያደረጉት ጥሪ በመከላከያ ሰራዊቱ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነትን እያገኘ መምጣቱ ታወቀ!

አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያምBilderesultat for መከላከያ ሠራዊት

የአርበኞች ግንቦት ሰባትሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ  ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የፌደራለ እና የክልል ፖሊስ አባላት፤ለአጋዚ ልዩ ጦር አባላት እና ለሌሎች ስርአቱ ታጣቂዎች ያደረጉት  ጥሪ  በሰራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ  ከመሆኑም በተጨማሪ ሰራዊቱ ከህዝብ ጋር ለመቆም የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገዉ ጥሪ ነዉ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰዋል።የተደረገዉን ጥሪ መቀበላቸዉን ለማመላከት ሀሳባቸዉን የገለጹት የሰራዊቱ አባላት እንዳሉት “ መከላከያዉ የህዝብ ሳይሆን የህዉሀት ቡድን አገልጋይ እየሆነ መምጣቱን ሙሉ በሙሉ ያወቁበት ደረጃ ላይ መድረሳቸዉን እና ሊቀመንበሩ እንዳሉት ሰራዊቱ የቁም እስረኛ ሲሆን በተለይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ምን እንደሚያደርግ እና ወዴት እንደሚሄድ የጠራ አቅጣጫ ባለማግኘቱ እና ባለበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ አማራጭ በማጣት በሰራዊቱ ዉስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የደህንነት ሹሙ የሕወሓትን ጉድ ማፍረጥረጣቸውን ቀጥለዋል – “አብዛኛው ስልክ ጠላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው – አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕ/ትም ስልክ ጠለፋ ተምሯል” | ያድምጡት

የደህንነት ሹሙ የሕወሓትን ጉድ ማፍረጥረጣቸውን ቀጥለዋል – “አብዛኛው ስልክ ጠላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው – አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕ/ትም ስልክ ጠለፋ ተምሯል” | ያድምጡት
(ዘ-ሐበሻ) ቢቢኤን ቴሌቭዥን ከቀድሞ ከፍተኛ የደህንነት አባል አቶ አያሌው ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በርካታ ምስጢሮችን እያወጡ ነው:: ቃለምልልሱን ያድምጡት::

Friday, October 28, 2016

የአጋዚ ጦር እየተበታተነ ነው ተባለ


Bilderesultat for አጋዚ ወታደርጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በቅርቡ አጋዚ ክፍለጦርን ለቀው የወጡ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት ጦሩ ከምንጊዜው በላይ እየተበታተነ ይገኛል። አብዛኛው የሰራዊቱ አባል በክፍለጦሩ ውስጥ የሚታየውን ፍጹም ዘረኝነት በመጥላት እየጠፋ ፣ ክፍለጦሩን አመናምኖታል። በአሁኑ ሰአት 2 ሺ የሚሆኑ አባላት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ ከ2007 ዓም ጀምሮ እስካሁን ወደ 3 ሺ የሚደርሱ የአጋዚ ወታደሮች ጥለው ጠፍተዋል። በተለይ ጦሩ ሶማሊያ ገብቶ ከወጣ በሁዋላ አብዛኛው የሰራዊት አባላት አጋጣሚውን ተጠቅመው ጥለው ጠፍተዋል። በእያንዳንዱ ቲም ውስጥ ቀደም ብሎ 10 ወታደሮች የነበሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት 3 ብቻ ይገኛሉ።

Reeyot Alemu receives her 2012 courage in journalism award ESAT News (October 28, 2016)



Ethiopian journalist Reeyot Alemu received her 2012 courage in journalism award at a ceremony in New York on Wednesday.
Every year, the International Women’s Media Foundation (IWMF) recognizes journalists for their extraordinary bravery, strength of character and pioneering spirit.
Reeyot was not able to receive her award in 2012 as she was imprisoned by the tyrannical regime in her country that does not allow free press and speech. She was imprisoned for over four years under trumped up charges of terrorism, a charge the regime uses to silence critical journalists and dissents.
She was released last year after serving four years of her 14 year sentence following uproar and condemnation by Ethiopians and the international community.

Wednesday, October 26, 2016

የዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ October 26, 2016ESAT Daily News Amsterdam October 26,2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀ የዘመናዊ ባርነት አዋጅ ና በሕዝባዊ ትግሉ የሚወሰዱ እርምጃዎችና ዋና ዋና ዒላማዎች


መግቢያ
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፤

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከሰተው ስር የሰደደ የፖለቲካ ቀውስ በሰለጠነ የውይይትና የድርድር መንገድ እንዲፈታ ለሀገር ደህንነት ከሚያስቡ የአገር ሽማግሌዎችም ሆነ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ወዳጆቹ ጭምር የቀረበለትንና የሚቀርብለትን ጥሪ አሌ ብሎ፤ ይህ እኩይ የጥቂት ሽፍቶች ሥርዓት ለ25 ዓመታት ሲያካሄድ የቆየውን የሕዝብና የሀገር ሀብት ዝርፊያ ከማቆም ይልቅ “ሀገሪቷን መዝረፍ ካልቻልኩ አቃጥያት እጠፋለሁ” ብሎ የመጨረሻው የሆነውን የጥፋት መንገድ ከሰሞኑ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” በሚል ስያሜ ባወጀው “የባርነት አዋጅ” ለሁሉም ግልጽ አድርጓል። ይህንን የወያኔ የዘራፊዎች ቡድን ለረጅም ጊዜ በቅርብ ስንከታተልና በተግባርም ስንፈትነው ለቆየነው የነፃነት ኃይሎች ይህ እርምጃው ስንጠብቀውና ስንዘጋጅበት የነበረ ስለሆነ በእውነቱ በፍጹም አልገረመንም። ትንሽም ቢሆን ያስገረመን ይህንን የመጨረሻ ጥይቱን እንደዚህ በቶሎ መጠቀሙ ነው። የመጨረሻ ጥይቱ ነው የምንለው ከዚህ በኋላ ሊጠቀምበት የሚችለው ምንም ሌላ መሳሪያ እንደሌለው ስለምናውቅ ነው።
በእርግጥ በዚህ አዋጅ ውስጥ አገዛዙ ሊወስዳቸው ያሰባቸው እርምጃዎች አብዛኛዎቹ ከዚህ በፊትም እራሳቸው ካወጧቸው ህጎችና ህገመንግስቱ

አርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ የመከላከያና ፓሊስ ሠራዊት አባላት የተደረገ ጥሪ


የተከበራችሁ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፤ የፌደራልና የክልል ፓሊስ አባላት፤ የአጋዚ ልዩ ኮማንዶ ጦር አባላትና ሌሎች የሥርዓቱ ታጣቂዎች። አገራችን በለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ለእናንተ ቀጥታ መልዕክት ማስተላለፍ የሚገባ ሆኖ ስላገኘሁት ይህንን አጭር መልዕክቴን በጥሞና እንድታዳምጡኝ፤ የሰማችሁ ላልሰሙት እንድታደርሱልኝ እጠይቃለሁ። 
የአገር መከላከያ ሠራዊት አባል መሆን ከፍተኛ ክብር ያለው ሙያ እንደነበር የምታውቁት ነው። ለሀገር ዘብ መቆም መልካም ዜጎች ሁሉ የሚመኙት ተግባር ነው። አንድ ሰው ቃለ መሀላ ፈጽሞ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ከለበሰ በኋላ ተራ ዜጋ አይደለም። አገሪቷ በዜጎቿ ማየት የምትፈልጋቸውን መልካም እሴቶችን ሁሉ በወታደሮቿ ማየት ትሻለች፤ ለሕዝብ ተቆርቋሪነት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ፍትሀዊነት፣ ጀግንነት፣ ታማኝነት በወታደሮቿ ማየት ትሻለች። ለዚህም ነው በብዙ አገሮች ውስጥ ያሉ ሕፃናት “ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ሲባሉ ከሚሰጧቸው መልሶች ግንባር ቀደሙ “ወታደር” የሚሆነው። በሀገራችንም ዘመናዊ ጦር ከመደራጀቱ በፊት አያት ቅድም አያቶቻችን ራሳቸውን በወታደርነት አሰልጥነው፤ ወራሪ ሲመጣ በየጎበዝ አለቆቻቸው እየተቧደኑ ዘመናዊ ጦሮችን ሳይቀር ተዋግተው በማሸነፍ የአገራችንን ሉዓላዊነት አቆይተውልናል። ዘመናዊ ጦር ከተደራጀ ወዲህም እስከ ህወሓት አገዛዝ የነበሩ አስተዳደሮች ብዙ እንከኖች ቢኖርባቸውም እንኳን የመከላከያ ሠራዊትን የአገር መከላከያ ሠራዊት አድርገውት ቆይተዋል። የሠራዊቱን ክብርና ሞገስ ለመጠበቅም የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። ይህ ጥረት ግን በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ሙሉ በሙሉ ተቀልብሷል። 

Tuesday, October 25, 2016

የዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ October 25, 2016 ESAT Daily News Amsterdam October 25,2016

#Ethiopia*የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በህወሓት ጭቆና ቀንበር ውስጥ ሆኖ በሕዝብ ዘንድ እንደጠላት ለሚታየው መከላከያ ሰራዊት ጥሪ አቀረቡ ESAT Prof. Berhanu Nega message to Ethiopian army Oct. 25, 2016 Ethiopia

#Ethiopiaየአርበኞች ግንባት 7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለመከላከያ ሰራዊቱ ወሳኝ የሆነ ጥሪ አቅርበዋል።ESAT Radio 30 Minute Tue Oct 25 2016

ESAT Religious Leaders on Ethiopian Issues part 1 October 25 , 2016

የዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ ESAT DC Daily News Mon 24 Oct 2016

Sunday, October 23, 2016

በጀርመን አገር ቩርዝቡርግ ከተማ ላይ ኢትዮጵያውያን ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ - October 22,2016

አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ




የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ

ወታደራዊ መረጃ እና የጌታቸው አሰፋ “ልጆች” እጣ ፈንታ ከዶ/ር ታደሰ ብሩ



Bilderesultat for የጌታቸው አሰፋየአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሳሞራ የኑስ ቡድን የበላይነት መያዙ የሚያረጋግጥ ነው። ይህ በህወሓት የስለላ ተቋማት ሥራ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ምንድነው?
ህወሓትን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚያውቁት ከመለስ ዜናዊ “መሰዋት” በኋላ ድርጅቱ ውስጥ ሁለት ቡድኖች ጎልተው ወጥተዋል። አንደኛው ቡድን ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ ቢሆን የህወሓት ፈላጭ ቆራጭነት መጠበቅ አለበት የሚሉ፤ ህወሓት እና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው እያሉ በአደባባይ የሚሰብኩ፤ የይስሙላ ስልጣን ቢሆንም እንኳን የኃይለማርያም “ጠ/ሚኒስትር” ተብሎ መጠራት ምቾት የማይሰጣቸው፤ ለአገሪቱ የፓለቲካ ችግሮች ሁሉ መፍትሄው ጉልበት ነው ብለው የሚያምኑ ከፍተኛ የአስተሳሰብ ችግር ያለባቸው ሰዎች የተሰበሰቡበት ነው። የዚህ ቡድን መሪ ሳሞራ የኑስ ነው። ሌላኛው ቡድን ደግሞ የህወሓትን የበላይነት ለማቆየት የሚቻለው በዘዴና በጥበብ እንጂ በጉልበት አይደለም፤ ስለሆነም ትንሽ እንለሳለስ ባይ ነው። የዚህ ቡድን መሪ ጌታቸው አሰፋ ነው።

Saturday, October 22, 2016

ትንሳኤ ራዲዮ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ የስርጭት ሞገዶች ላይ የሚተላለፍ ነጻ ራዲዮ ነው Tensae radio October 22 2016

የወያኔ የመጨረሻው እስትንፋስ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀ የዘመናዊ ባርነት አዋጅ! – ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መለዕክት October 22, 2016


dr-berhanu-Nega
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፤

በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከሰተው ስር የሰደደ የፖለቲካ ቀውስ በሰለጠነ የውይይትና የድርድር መንገድ እንዲፈታ ለሀገር ደህንነት ከሚያስቡ የአገር ሽማግሌዎችም ሆነ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ወዳጆቹ ጭምር የቀረበለትንና የሚቀርብለትን ጥሪ አሌ ብሎ፤ ይህ እኩይ የጥቂት ሽፍቶች ሥርዓት ለ25 ዓመታት ሲያካሄድ የቆየውን የሕዝብና የሀገር ሀብት ዝርፊያ ከማቆም ይልቅ “ሀገሪቷን መዝረፍ ካልቻልኩ አቃጥያት እጠፋለሁ” ብሎ የመጨረሻው የሆነውን የጥፋት መንገድ ከሰሞኑ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” በሚል ስያሜ ባወጀው “የባርነት አዋጅ” ለሁሉም ግልጽ አድርጓል። ይህንን የወያኔ የዘራፊዎች ቡድን ለረጅም ጊዜ በቅርብ ስንከታተልና በተግባርም ስንፈትነው ለቆየነው የነፃነት ኃይሎች ይህ እርምጃው ስንጠብቀውና ስንዘጋጅበት የነበረ ስለሆነ በእውነቱ በፍጹም አልገረመንም። ትንሽም ቢሆን ያስገረመን ይህንን የመጨረሻ ጥይቱን እንደዚህ በቶሎ መጠቀሙ ነው። የመጨረሻ ጥይቱ ነው የምንለው ከዚህ በኋላ ሊጠቀምበት የሚችለው ምንም ሌላ መሳሪያ እንደሌለው ስለምናውቅ ነው።
በእርግጥ በዚህ አዋጅ ውስጥ አገዛዙ ሊወስዳቸው ያሰባቸው እርምጃዎች አብዛኛዎቹ ከዚህ በፊትም እራ

የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወያዬ:: በጉዳዩ ላይ ሠኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል


U.S. State Department (Photo by Alex Wong/Getty Images)WASHINGTON, DC - SEPTEMBER 12:  A sign stand outside the U.S. State Department September 12, 2012 in Washington, DC. U.S. Ambassador to Libya J. Christopher Stevens and three other Americans were killed in an attack on the U.S. Consulate in Benghazi, Libya.  (Photo by Alex Wong/Getty Images)
የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ዛሬ ረፋድ ሲወያዬ አርፍደዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የኢህአዴግ አባል ስለጉዳዩ እንደገለፁልኝ ከሆነ በአሜሪካዋ አምባሳደር ፓትሪሽያ ኃስላች ሰብሳቢነት በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከኢህአዴግ በኩል አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ደብረፅዮን፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎችም የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የተወሰኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የተለያዩ የሲቪል ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ስብሰባው በዋነኝነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ በተከሰቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ሲሆን ስለጉዳዩ የመንግ

ይቅርታን ከእምየው ❖❖❖


- አጼ ምኒልክ ከመቅደላ ወጥተው ወደ አንኮበር ሊገቡ ሲሉ የሸዋ ገዥ የነበረው
አቶ በዛብህ አይገቡም ብሎ ተዋጋቸው፡፡ አጼ ምኒልክም ድል
አርገውት አንኮበር ከገቡ በኋላ ሁሉን ረስተው ለአቶ በዛብህ
ይቅርታ አደረጉለት፡፡

Thursday, October 20, 2016

የዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ October 20, 2016

የዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ October 20, 2016

ህወሃት/ ኢህአዴግ እየወሰደ ያለው እርምጃ የተስፋ መቁረጥ እንደሆነ ተገለጸ ኢሳት (ጥቅምት 10 ፥ 2008)


በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ እንደሆነ የቀድሞ የአየር ሃይል አባላት ገለጹ።
የቀድሞ አየር ወለድ 2041ኛ ብርጌድ የነበሩት ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴና፣ የቀድሞ አየር ሃይል አብራሪና የበረራ መምህር የነበሩት ካፕቴን ተሾመ ተንኮሉ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ህዝብ ነጻነቱን ወደ እጁ ለማስገባት እየተዘጋጀ ባለበት ጊዜ ህወሃት እንደማንኛውም አምባገነን ስርዓት እየተፍጨረጨረ እንደሆነ አስረድተዋል።
ህወሃት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ህዝብ በፊትም የሰጠው የዴሞክራሲ መብት የለም አሁንም የከለከለው ነጻነት የለም ያሉት የቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተንተርሶ አገዛዙ እያደረገ ያለው የመብት ጥሰት ቀድሞ ሲያደርግ ከነበረው የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል። በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለህዝባዊ ተቃውሞ የወጣው ህዝብ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በፈቀደለት ነጻነት ሳይሆን በገዘ ፈቃዱ እንደሆነ ተናግረዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ሻለቃ ሱራፌል ዘውዴ፣ አዋጁ አስጊ በሆኑ ወታደራዊ ቀጠናዎች የሚወጣ አዋጅ እንጂ፣ አሁን ወያኔ እንዳደረገው በመላ አገሪቷ የሚታወጅ እንዳልነበር ገልጸው፣ አዋጁ መላዋን አገሪቷን የጦር ቀጠና አድርጓታል ብለዋል። በመሆኑም፣ ለአገዛዙ አዲስ አበባን ጨምሮ አስጊ ያልሆነ ቦታ እንደሌለ አመላካች እንደሆነ የሚያስረዳ ነው ሲሉ ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ ተናገረዋል።

''የባንዲራ ታሪክ ''

; Breaking News

#AmharaResistance;
በምዕራብ አርማጭሆ አቡጢር የዐማራ ገበሬዎችን ለመግደል የሔደው የወያኔ ጦር ተደመሰሰ፤
ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ በምዕራብ አርማጭሆ ለሱዳን ከተሰጠው አቡጢር ከተባለ ቦታ ሲያርሱ የነበሩ የዐማራ ገበሬዎችን ለመያዝ ሁለት ኦራል፣ አንድ ፒክ አፕ እንዲሁም አንድ ታንክ በመያዝ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር መደምሰሱን አሁን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
ገበሬዎችን ለማፈን በአካባቢው በሚኖሩ ወያኔዎች ጥቆማ የመጣው ጦር ሠራዊት አባለት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲገደሉ ከዐማራ ገበሬዎች ግን ምንም የተጎዳ አለመኖሩን ጦርነቱን ሲመሩ የነበሩት ገበሬዎች የጎበዝ አለቃ በስልክ አረጋግጦልናል፡፡ የጎበዝ አለቃውን ስም መጥቀስ አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ስሙን በዜናው ላይ ማስገባቱን ትተነዋል፡፡ እንደ ጎበዝ አለቃው በውጊያ ላይ የነበሩ ገበሬዎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን ጦርነቱን በድል ተወጥተዋል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የዐማራ ገበሬዎች በተጠንቀቅ ነቅተው እንዲጠብቁና ተጨማሪ ኃይል ሊመጣ ስለሚችል እርዳታም እንዲደርሳቸው አሳውቀዋል፡፡
አቡጢር በምዕራብ አርማጭሆ ድንበር አካባቢ ያሉ ገበሬዎችን በማፈናቀል ለሱዳን የተሰጠ መሬት ሲሆን የዐማራ ገበሬዎች ለዓመታት ድንበራችን አናስነካም በማለት ብዙ የሕይወት መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡
Muluken TesfawBilderesultat for ወታደር

እኛ ማነን ?ESAT Egna manen What does Peace mean By Serkaddis October 20 2016

Wednesday, October 19, 2016

የዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ October 19, 2016

UK foreign secretary refuse to address the case of Andargachew Tsige ESAT News (October 19, 2016)


UK’s Foreign Secretary, Boris Johnson, has on Tuesday refused to answer questions in the House of Commons about the case of Andargachew ‘Andy’ Tsege, a British father of three who is held on Ethiopia’s death row, Reprieve, an organization following the case of Andy said in a release.
Mr Johnson and other Foreign Office ministers on Wednesday faced several oral questions from MPs about why their department has not requested the return of Mr Tsege.
Mr Tsege was kidnapped at an airport in June 2014, and is now held in Ethiopia under a sentence of death imposed in absentia in 2009.

Asking Mr Johnson about the case,

ሰበር ዜና፤ #AmharaResistance;


Muluken Tesfaw
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ወጣ፤
የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንትና የሰሜን ምዕራብ ቀጠና ኃላፊ የነበረውና በቅርቡ ከወራት ስቅይት በኋላ ከእስር የተፈታውን አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ 78 በሚሆኑ የጎንደር ዙሪያ ወጣቶች ማደኛ መውጣቱን ዛሬ ሰምተናል፡፡ እነ ዘመነ ምሕረት ላይ የወጣው ማደኛ ግለሰቦቹን መያዝ ካልተቻለም በተገኙበት እንዲገደሉም ትዕዛዝ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአቶ ዘመነ ምሕረት ጋር በተፈላጊነት ስማቸው ከወጣው ዐማሮች መካከል 18ቱ የብአዴን አባላትና በአመራርነትም ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡ 
አቶ ማሙሸት አማረን እና አቶ አብርሃም ጌጡን ጨምሮ የመኢአድ ሕጋዊ አመራሮች በተለያየ ጊዜ ታስረው የተሰቃዩ ሲሆን በቅርቡም ብዙ የፓርቲው አባላት በእስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከቀናት በፊት አቶ ጫኔ ዘየደ እና አቶ ኢዮብ ታስረው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡ 
በተያያዘ ዜና ደግሞ በወገራ፣ በበለሳና አርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ ገበሬዎችን ይቅርታ አድርገንላችኋል በሚል ትጥቃቸውን ለመቀማት አዲስ ስትራቴጂ መነደፉን ሰምተናል፡፡ መረጃውን ያቀበሉን ሰዎች እንደሚሉት ገበሬዎቹ ይቅርታውን ከተቀበሉ ለተሀድሶ በሚል ሰበብ ወደ ብር ሸለቆ ወስዶ ለማሰር እቅድ መኖሩን ጭምር ነግረውናል፡፡

በኖርዌይ /ኦስሎ ለሚኖር ለኢሳት ቤተስቦች በሙሉ የቀረበ ጥሪ

esat-norwayየኢትዮጵያ ህዝብ አይን እና ጆሮ የሆነውን የ ኢሳትን ራዲዮ እና ቴሌቪዥንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ አስተዋጽዖ ለማድረግ የኢሳትስድስተኛ አመት ምክኒያት በማድረግ  በኖርዌይ /ኦስሎ የሚኖርኢትዮጵያውያን ቅዳሜ / 12 th November ,2016 ታላ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አዘጋጅቶል  ። እርዎም በዚህ ፕሮግራም በመገኘት እንዲሁም ወዳጅ ዘመድወችን በመጋበዝ እየተዝናኑ ኢሳትን ይርዱ 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
ዘጋጅ ኮሚቴው

Tuesday, October 18, 2016

የጣሊያን ጀነራል የማረኩ ብርጋዴር ጀነራል ለማ ገ/ማርያም አረፉ

(ሙሉጌታ ኃይሌ)
ብርጋዴር ጀነራል ለማ ገ/ማርያም ይባላሉ፡፡ የማይጨው ዘማች ነበሩ፡፡ በተወለዱ በ99 አመታቸው መስከረም 23 2009 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ከማይጨው ዘመቻ ተርፈው እስካሁን በሕይወት ይኖሩ ከነበሩት የመጨረሻው እሳቸው ነበሩ፡፡
ከነፃነት በፊት ሜጀር የሚለው የወታደር ማዕርግ ያገኙ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ከነፃነት በኋላም የመጀመሪያውየአባዲና ፖሊስ ምሩቅ ሆነው የፖሊስ ሠራዊትን ወደ ዘመናዊነት ከአሸጋገሩትአንዱና ዋናው ነበሩ፡፡
በዘመናቸው ከሚታወቁበት ታሪካቸው አንዱ፣በ1934 ዓም ጎንደር ላይ የፋሽስትን የጦር መኮንኖች ለመማረክ በተደረገው የቤት ለቤት አሰሳ ላይ በአደረጉት አስተዋፆ ነው፡፡
ከነበሩበት አሳሽ ቡድን ፊት ቀደም ብለው ከሩቅ የነጭ ባንዲራ ወደሚውለበለብበት ባንኮ ዲሮማ ጠጋ ብለው በሩን ከፍተው ቢገቡ፣የጣሊያን ከፍተኛ መኮንኖች መሠሪያቸውን መሬት ላይ አስቀምጠው ጠረጴዛ ከበው ካርታ ሲጫወቱ ያያሉ፡፡ ይሄን ሁሉ መኮንን በአንድጊዜ መማረክ ስለማይችሉ እርዳታ ለመጠየቅ በሌላ በር ሊወጡ ሲሉ፤ በአንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ የሸዋ ገዢ የነበረውን ጀነራል ናዚን፣ቤተወደድ አስፋሐ ወ/ሚካኤል(ኤርትራዊው አስተርጎሚ) እና አቶ አሊ (የጀነራል ናዚ ልብስ አልባሽ)በአንድ ላይ አዝነው እንደተቀመጡ ይመለከታሉ፡፡ እነዚህን መማረክ እችላለሁ ብለው “እጅ ወደ ላይ”ሲሉ፣ቢትወደድ አስፋሐ “እንደ ጀነራል ናዚ አይነት ከፍተኛ መኮንን በአንተ ሳይሆን በእንግሊዝ ከፍተኛ መኮንን ነው መማረክ ያለበት”ብለውሲያንገራግሩ ወዲያው የእንግሊዝጦር ደርሶ ሁሉም አንድ ባንድ እጃቸውን ሊሰጡችለዋል፡፡
የእንግሊዝ ጦር ጄነራል ናዚን ማረከንብለው እንዳይኩራሩ በጎንደር ከተማ ለነበሩት ለልዑል አልጋወራሽ አሰፋወሰን ኃ/ሥላሴ ምርኩኞቹ በሙሉእንዲተላለፉ አድርገዋል፡፡
ይህም ስራቸው ልዑል አልጋወራሽ ከነፃነት በኃላ የሙሉ ጄነራልነት ማዕርግ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥምይሄ ሹመት ለመጀመሪያጊዜ መሰጠቱ ነበር፡፡
ለዚህ ታሪክ እውነታ ቢትወደድ አስፋሐ ወ/ሚካኤልለጀነራል ለማ በሰጡት የምስክርነት ደብዳቤ ላይ ተረጋግጦል፡፡

የጄነራል ለማ ገ/ማርያም አጭር የሕይወት ታሪክ
ጄነራል ለማ ከአባታቸው ከጎጃሙ ተወላጅ ከአለቃ ገብረ ማርያም አለምነህና ከእናታቸው ከቡልጋዋ ተወላጅ ከወ/ሮ ፋንታዬ ዘለሌ በ1910 ዓም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችው የኬኒያ ሞያሌ ከተማ ተወለዱ፡፡ በኪኒያ የተወለዱበት ምክንያት አባታቸው በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሐከል የነበረውን የወሰን ክልል አስከባሪ ስለነበሩ ነው፡፡
ጄነራል ለማ እድሜያቸው ለትምሕ

የጎሳ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ውድቀት ESAT Special Ethiopia A FAiling State A Translation - ኢሳት ልዩ ኢትዮጵያ አንድ...

State of emergency is militarized response: rights researcher ESAT News (October 18, 2016)


A senior researcher with Human Rights Watch says the state of emergency declared by the TPLF regime in Ethiopia meant a militarized response that will have a counterproductive effect in the long term stability of Ethiopia.
Felix Horne, senior researcher for the Horn of Africa with HRW also said that by declaring the state of emergency, the regime showed that it is not willing to take steps for change. “It is a message that they are not willing to open up the political space. They are not willing to address many of the grievance. It is a very worrying development,” Horne said in an exclusive interview with ESAT.

የዳሽን ቢራ አዲሱ ታክቲክ



ዳሽን ቢራ ንብረትነቱ የህወሃት ነው። ለትግራይ ህዝብ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፋብሪካዎችን ገንብቶ በምትኩ የተከለብን የሹፈት የብቅል ፋብሪካ ነው።
ከፋብሪካው ትርፍ በተገዛ ጥይት ለጋ ወጣቶቻችን በወያኔ ትግሬ አልሞ ተኳሽነት ተመተው ወድቀው ደማቸው በጎንደር ፒያስ ወደ አውቶፓርኮ አቅጣጫ ያለማቋረት እንደጅረት ፈሷል።
የዳሽን ቢራ የሚቀልባቸው የወያኔ ትግሬ ወንበር ጠባቂዎች መፈክር አንግቦ የወጣን የባህርዳር ማርቆስ ዳንግላ ማርቆስና ፍኖተ ሰላም ወጣት ጭንቅላት ይሄው ራሱ ፋብሪካው በገነባው ማማ ላይ ተጠልለው ጭንቅላታቸውን አፍርሰዋል። የዳሽን ቢራ ጥይት ወልቃይትን ቢረሳ ቀኙ እንድትረሳው ቃል ገብቶ አደባባይ የወጣውን አበበ ገረመውን በአጭሩ አስቀርቶብናል።
ታድያ ይህ መቀመጫውን ዐማራ ክልል አድርጎ ለትግሬ ግብር የሚከፍል፥ ጥሬ እቃን እኛው ጋር በርካሹ አጋብሶ በትርፉ ለህወሃት የአብሪ ጥይትን የሚገዛው የቢራ ፋብሪካ እስካሁን ቆሞ መገኘቱ ሳያንስ ምርቴን ተጠቀሙልኝ የሚል ማስታወቂያ እየሰራ መሆኑን ከወደ ጎንደር እየሰማን ነው።
የሚከተለውን ያካፈለኝ ጎንደር የሆነውን የታዘበ በቅርብ የማውቀው ሰው ነው
"የዳሽን ቢራ የህወሃት ካድሬዎችን ስፖንሰር በማድረግ የተለያዩ ቡና ቤቶች እየዞሩ ዳሽን ብቻ እንዲያዙ፤ ሲጠጡም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው "የጎንደር ህዝብ ግን ምንኛ ሞኝ ነው ዳሽን እኮ ለጎንደር ብዙ ልማቶችን እየሰራ ያለ ፋብሪካ ነው" እያሉ እንዲያወሩ እየተደረገ ነው።
የምሰማውን ማመን አቃተኝ። የወንድሞቸ ደም የሆነውን ቢራ በፈለከው ቋንቋ ብትገልጸውም ጉሮሮየን ከፍቸ ልጠጣው አልችልም። በየማጎሪያ ቤቱ እየተሰቃዩ ያሉ ወንድሞቸ ሰቆቃ ላይ የሚያፌዙትን ካድሬዎች መስማት ስላልቻልኩ የነበርኩትን ቦታ ስቀይር ሌላኛው ቤትም ተመሳሳይ ሁኔታ ገጠመኝ።
የዐማራ ደም በውስጥህ ይዘህ እንዴስ ብለህ የዳሽንን ቢራ ትጠጣለህ? እንዴት ተደርጎ? ያለመጠቀም አድማችን እስከወዲያኛው መሆን ነው ያለበት!!
ይህን ሁሉ ግፍ ከተፈጸመብን በዃላ ዳሽንን የምንጠቀም ሆኖ ከተገኘ "የመንድሞቻችን አጥንት ይውጋን ደማቸውም እንደደራሽ ዉሃ ይውሰደን" በሚል ምህላ ተማምለን ምርታቸውን እስከወዲያኛው ማቆም አለብን።"

State of emergency is state of slavery, says Prof. Berhanu Nega ESAT News (October 17, 2016


The leader of an armed opposition group on Monday described the state of emergency declared last week by the regime in Ethiopia as “a state of slavery” imposed on the people of Ethiopia as it curtails all human, political and God given rights.
Professor Berhanu Nega, chairman of Patriotic Ginbot 7, an armed group based in Eritrea said in a video message that the rights prohibited by the state of emergency law in Ethiopia were already curtailed by the regime even before the declaration of the law.
He said the regime in power had already been violating the constitution and other laws in perpetrating extrajudicial killings, mass incarcerations, muzzling the press and liquidating opposition political parties, among other crimes.
There could be no political solution to the crises in the country when there is an emergency law put in effect, Prof. Berhanu said.

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር ዙሪያ ወታደሮቿን አሰማራች ኢሳት (ጥቅምት 7 ፥ 2009)


የኢትዮጵያ ወታደሮች እሁድ የኬንያ ድንበር አቋርጠው መግባታቸውን ተከትሎ ኬንያ ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት የድንበር ዙሪያ ወታደሮቿን አሰማራች።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ታጣቂዎችን ፍለጋ በሚል ወደ 100 አካባቢ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዕሁድ ከሰዓት በኋላ ማርሳቤት ተብሎ ወደሚጠራ ግዛት መግባታቸውን የግዛቲቱ ባለስልጣናት ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
የማርሳቤት ግዛት ፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ማርክ ዋንጀላ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያ ድንበርን ጥሰው በገቡ ጊዜ በአንድ ወጣት ላይ ግድያ መፈጸውማቸውን እንዳስታወቁ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል።

የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ባልደረባ የነበሩ እንዲሁም የአማራ ክልል ደህንነት ሃላፊ ESAT Yesamintu Engeda Ato Ayalew Mengesha October 18 2016

Monday, October 17, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማክሸፍ ማለት የወያኔን ህልውና መጨረስ ማለት መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ


ጥቅምት ፯ (ሰባትቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ህወሃት መራሹ መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ  አዋጁ “ ሰው ሆኖ መኖርን የናፈቀውና ካሁን በኋላ ያለነፃነት በፍጹም አልኖርም ብሎ ፍርሀትን በሚገርም ጀግንነት አሸንፎ ውድ ሕይወቱን እየከፈለና እየታገለ ያለውን፤ ከሞላ ጎደል መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ እንደገና በፍርሀት ቆፈን ውስጥ መልሶ በመክተት ከቀድሞውም በባሰ ባርነት ውስጥ ዘፍቆ ለመግዛት” ታልሞ የወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

Gondar strikes defying state of emergency ESAT News (October 17, 2017)


Schools, businesses and transportation were shut down on Monday as residents of Gondar began a three-day strike defying the state of emergency declared last week.
Organizers told ESAT that the strike was a dismissal to the state of emergency which bans any strikes, protest demonstrations and public gatherings. They said the strike was also aimed at denouncing the recent massacres and gross violations of human rights being perpetrated across Ethiopia, mainly in Amhara and Oromo regions,including the mass murder of Irreecha festival goers.

#Ethiopiaየአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ESAT Yetimihirt Bilichita Tadesse Biru Strategy of War Strategy October ...

የሰራዊቱ ድምጽ Army show 121 october 1, 2016

የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ከመግለጫው የተወሰደ


" ከዚህ በኋላ የፍትህና የነፃነት ኃይሎች ዋና ተግባር ያላቸውን አቅም ሁሉ አስተባብረውና ነፃነት የራበውንና የጠማውን ሕዝባቸውን ከጎናቸው አሰልፈው፤ ጊዜውና ሁኔታው የሚፈቅደውን ተለዋዋጭና ተለማጭ የትግል ስልት እየተጠቀሙ ይህ አዋጅ በፍጹም ተግባራዊ እንዳይሆንና እንዳይሳካ ማድረግ ነው። ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም በመሪነትና በዋና አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች፤ ይህ የባርነት አዋጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተገበርና እንዲሳካ ለማድረግ የሚሞክሩ ወይንም ከዚህ ዘራፊ ሥርዓት ጋር በጥቅም ተሳስረው ከዚህ የባርነት አዋጅ ጋር የሚተባበሩ ማናቸውም ኃይሎች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ የሕዝባዊ ትግሉ ቀንደኛ ዒላማዎች መሆናቸውን ግልጽ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚሳተፉ የሕዝብ ወገኖችም ሆነ ይህንን ዘራፊ ሥርዓት የሚያግዙ ኃይሎች በደንብ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ይህን አዋጅ አከሸፍነው ማለት የወያኔ ሥርዓት አከተመለት ማለት እንደሆነ ነው። ይህ አዋጅ ተሳካ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተወሰነ ጊዜ በባርነት መቀመቅ ውስጥ ሊኖር ተፈረደበት ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን የገባንበት ትግል የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ነው የምንለው።"

Sunday, October 16, 2016

ትንሳኤ ራዲዮ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ የስርጭት ሞገዶች ላይ የሚተላለፍ ነጻ ራዲዮ ነው.

በአገሪቱ የበጀት ውዥቀት ተከሰተ፤ በባሕር ዳር 67 ሆቴሎች የባንክ ብድር መመለስ አንችልም ብለዋል .#AmharaResistance




Bilderesultat for ባህር ዳር ከተማመንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ኪሳራ ውስጥ ገብቻለሁ አለ፡፡ የ2009 ዓ.ም የካፒተል በጀት እስካሁን ድረስ አልተለቀቀም፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለስራ ማስኪጃ እና ለፅህፈት መሳሪያዎች መግዥያ የሚገለገሉበት በሀገሪቱ የሚጠበቀው የካፒታል በጅት በ2009 ዓ.ም ሊለቀቅ አይችልም፡፡ ሲሉ የአማራ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አየነው በላይ ተናግረዋል፡፡ 
መንግስት በዚህ ስዓት ለድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ በሚል ከመንግስት በጀት ለሚልሻዎች ቀለብ እና ለወታደሩ የምግብ ሂሳብ ወጭ ያደረገ ሲሆን ይህም የወረዳዎችን በጀት እንዳናጋባቸው እና በአሰተዳደራዊ ስራው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን በበአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ላይ አንስተዋል፡፡
በተያያዘ በአማራ አካባቢ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የሚገኙ ኢንቨስትምንት እና ሆቴሎች በቀን ሻሂ እንኳን መሸጥ አልቻልንም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል፡፡

EthiopianForumin Colorado ጉድ ኮሎራዶ በጉያዎቻችን ያሉ የወያኔ ሰላይና ተላላኪዎችን ከዚህ ቪዲዮ ውስጥ በማየትና በመለየት እንዲረዱን እንጠይቃለን። https://www.youtube.com/watch?v=qQ1KpeI-9DM

ትንሳኤ ራዲዮ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ የስርጭት ሞገዶች ላይ የሚተላለፍ ነጻ ራዲዮ ነው Tensae Radio Oct 15 2016 P16

#EthiopianRevolutionየዕለቱን የኢሳት ዜና ያድምጡ ኢሳት የኔም፣ ያንቺም፣ የሁላችንም ነው ኢሳትን ይርዱ ! Sat 15 Oct 2016

Saturday, October 15, 2016

Ethiopian authorities release details of state of emergency ESAT News (October 15, 2016)


One week after declaring a six-month state of emergency, Ethiopian authorities released details of the law on Saturday prohibiting exchange of electronic messages and banning public gatherings and demonstrations among others.
The state run media outlets on Saturday published details of the law as presented by the head the command post secretariat in charge of the state of emergency and minister of defence, Siraj Fergessa.
The emergency law prohibits the exchange of messages and information via the internet, cell phones, social media, television and radio.
Publishing and distributing documents, holding demonstrations, showing protest gestures, importing and exporting published materials were also prohibited by the law.
The law specifically mentioned two independent media outlets abroad and banned the public from watching and listening to television and radio programming by the Ethiopian Satellite Radio and Television (ESAT) and Oromo Media Network. The law gives power to security forces to monitor and block messages transmitted via television, radio and movie theatres.
According to the law, strikes by workers as well as businesses and closing government offices in protest are illegal. The law says protests by students in universities, colleges and higher institutions of learning are also outlawed. The law gives power to security forces to take any action they deemed necessary against students who stage protest rallies.
The emergency law stipulates that diplomats cannot travel beyond 40 kms radius outside the capital without prior authorization and permission from the command post.
Members of the police and security forces cannot take leave of absence or resign in the duration of the state of emergency.
A curfew is in effect from 6 p.m. to 6 a.m. local time in areas where there are economic infrastructures, factories, agricultural projects and other investments. The law also authorizes security forces to take whatever measure necessary against people who violate the curfew.
Areas 50 k.m. inside the the country’s border are designated as red zones. The carrying of firearms are banned in the red zone. Other restrictions imposed in the rest of the country are also applicable in the red zone.
Carrying firearms within 25 meters of highways connecting the capital Addis Ababa to major towns and destinations are also forbidden.
Security forces are given permission to search and arrest anyone and confiscate possessions without a court warrant, according to the law.
The emergency law also give security forces the power to take any action to defend themselves from any threat or attack.
The Ethiopian regime last Sunday declared a state of emergency after a wave of anti-government protests flared up again following the massacre early this month of hundreds of festival goers in Bishoftu, 45 kilometers outside the capital, at a religious festival of the Oromos.
Local political parties estimate close to 700 people were killed in a stampede as security forces shot tear gas to disperse protesters. Witnesses also say security forces shot and killed several people, who used the occasion to express grievances against the tyrannical government.
A year long protest in the Oromo region, which was joined this summer by the people in the Amhara region has left hundreds dead as security forces use lethal force to disperse demonstrators, who demanded an end to a dictatorial rule.

(Picture obtained from social media showing some of the bodies killed at the Ireecha festival in Bishoftu)

ESAT Menalesh Meti, with Tewodros Kabtimer DC task force October 15 2016

የህወሀትን መሰሪ አላማዎች ለማክሸፍ ባንድነታችን እንጽና!!! Patriotic Ginbot 7




ይህወሀት ኢሕአዴግ መንግስት ባለፈው እሁድ ባሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካይነት የተገለጸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መላ ሀገሪቱ ላይ አውጇል። ያስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ የሚያውጁ መንግስታት በመሰረቱ ህገመንግስትን እንደመንግስት ልጓም የሚያዩና የሚያከብሩ መንግስታት ሲሆኑ አዋጁ ልዩነትም ትርጉምም ይኖረዋል። እንደወያኔ አይነት ለህግና ሕገ መንግስት ግድ የሌለው ሕገወጥና ለሕግ ክብር የሌለው መንግስት ፣ ራሱ ያወጣውን ህግ አልመች ባለው ቁጥር ሁሉ እንደልቡ የሚሽር መንግስት የሚያውጀው አዋጅ የህዝብ መብት ገፈፋውን ለማፋፋም ቅልጥፍና ይጨምርለት እንደሆን እንጂ በመሰረቱ አዋጁ የሚፈጥረው እንዳች ለውጥ የለም። ወያኔ አትዮጵያን በሀይል እንጂ በህግ አስተዳድሮ አያውቅም። የወያኔ አላማ ግልጽ ከሆነ ሰንብቷል። በግፍና በግፍ መንገድ ብቻ የህዝቡን ጥያቄ ለማስቆም ቆርጦ መነሳቱን አረጋግጦልናል። ሕዝባችን የጀመረው የነጻነት ትግልም በዚህ ምክንያት ወደኋላ ይሄድልኛል ብሎ ገምቷል። ለወያኔ ጨካኝ ገዥዎች ያልተገለጸላቸው ነገር የግፍ ብዛት ትግል የሚያስቆም ቢሆን ኖሮ ትግሉ አሁን በደረሰበት ደረጃ ፈጽሞ የሚደርስ እንዳልነበር ነው። እሁን የግፉ የበደሉና የዝርፊያው ጽዋ ሞልቶ ከፈሰሰ በሁዋላ የኢትዮጵያ ህዝብ መብቱን ሳይጎናጸፍ ተመልሶ ቤቱ ይገባልኛል ብሎ ማሰብ የታሪክን አካሄድ ከማይረዱ ጭፍን እምባ ገነኖች የሚጠበቅ ነው።
ሀገራችንን የሚገዛው የወሮበሎች መንግስት ካፈና የተለየ የፖለቲካ አማራጭ ማሰብም ስራ ላይ ማዋልም ከቶ እንደማይችል ማረጋገጫው አንዱ ይህ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው። ይህንን ያስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ይልቁንም የህዝቡን ተገቢና ሰላማዊ አመጽ በደም የመበከል አባዜውን ለማርካት ብዙ ደም ለማፍሰስ እየተዘጋጀ ያለ መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶችም መረጃዎችም እየታዩ ነው።

የአርበኞችግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ October 14, 2016


ag7-logo
ጥቅምት 1 ቀን 2009 ዓ.ም.

የአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. አካሂዶ በወቅቱ የአገራችን ሁኔታዎች ተነጋግሮ ውሳኔዎችን አሳልፏል፤ ሠራዊቱንም አነጋግሯል።
ሥራ አስፈፃሚው የአገራችን ፓለቲካዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጡ መሆኑና ተከታታይነት ያለው ወቅታዊና ውጤታማ አመራር መስጠት የሚገባ መሆኑ አጽንዖት ሰጥቶበታል። እንደ ሥራ አስፈፃሚው እምነት፣ በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ደርሶ ወደማያውቅበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕዝብ ለሚያቀርባቸ ጥያቄዎች ሁሉ ምላሹ ጥይት፣ እስርና ጉልበት የሆነው የህወሓት አገዛዝ በሚሰጣቸው ፋሽታዊ ምላሾች ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንተሰውተዋል፤ በአስር ሺዎች የሚገመቱት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል። በዚህም ምክንያት ለውጥ ፈላጊው ሕዝብ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከሕዝባዊ አመጽ ጋር ለማቀናጀት ተገዷል፤ ሰላማዊ ዜጎች ራሳቸውን ለመከላከል መሣሪያ ለማንሳት ተገደዋል። ለፖለቲካ ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ችግሩን በኃይል እወጣዋለሁ ብሎ እየሄደበት ያለው መንገድ ፈጽሞ እንዳይሳካ ማድረግና ይልቁንም ውድቀቱን የሚያፋጥን እንዲሆን ማድረግ የንቅናቄዓችን የጊዜው አብይ ተግባር መሆኑን ሥራ አስፈፃሚው አምኖበታል።ይህን እውን ለማድረግድርጅታችን የሕዝቡን ትግል በአግባቡ ማቀናጀትና መምራት ቀዳሚ ሥራው እንደሆነ የአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ስምምነት ላይ ደርሷል።

Friday, October 14, 2016

“የለውጥ ሃይሎች” ግልፅና ደፋር ውይይት ለመፍትሔና የጋራ ድል!! (“ታሳቢ ሦስት”) – ኤርሚያስ ለገሰ ለህዝብ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ (ቺካጎ/ኢሊኖይ)


ኤርሚያስ ለገሰ
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ራዲዮ(ኢሳት)
ጥቅምት/2016

  ማስታወሻ       

*ይህ ጽሁፍ ከራሴ ውጭ የምሰራበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬዲዮ (ኢሳት)ን ጨምሮ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም::
**“የአዲስ አበባ ነዋሪ” (“አዲስ አበቤ”) የሚለው ቃል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሆኖ በአዲስ አበባ የሚኖር አሊያም ለወደፊት የመኖሪያውን አዲስ አበባ ለማድረግ የፈለገን በሙሉ የሚያጠቃልል ነው።

  1. መንደርደሪያ

revolution-satenaw-news
የዛሬ ሦስት ወራት አካባቢ ከኦሮሞ አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ ጋር በኢሳት ስቱዲዮ ለአጭር ሰዓታት ኢ-መደበኛ ወግ ጠርቀን ነበር። ገረሱ በወጋችን መሀል “ለጋራ መፍትሔ ግልፅና ደፋር ውይይት የማድረጊያው ሰዓት አሁን ነው” በማለት ይናገር ነበር። መልሶ መላልሶም “የጋራ ችግር አለብን፤ ያልተነጋገርናቸው እና በይደር ያቆየናቸው ድፍረት የሚጠይቁ አጀንዳዎች ከፊታችን ተቆልለዋል። በግልፅና በሐቅ ተወያይተን መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል” እያለ የቀጣይ ስጋቱን ይዘረዝር ነበር። የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገንም ጭምር። የነገንም ብቻ ሳይሆን የተነገወ ዲያውም። ለልጅና ልጅ ልጆቻችን!

ከቀናቶች በኋላ ይሄንኑ አባባል  በኦሮሞ ጉዳዮች ላይ ብዙ ምርምር ከሰራውና የወቅቱ የኦሮሞ ጥናት ማዕከል ፕሬዝዳንት ከሆነው ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ ሰማሁት። ርግጥ ከላይ ከተገለጠው የገረሱ አባባል ጋር ቃል በቃል የተገለጠ አይደለም። መንፈሱ ግን ተመሳሳይ ነው። አገር አደጋ ላይ ወድቃለችና የልባችንን አውጥተን እንነጋገር፤ እንመካከር የሚል ነው። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ የማያሳስበው ዜጋ ያለ አይመስለኝም። በሌላም በኩል ወርቃማ የለውጥ ሁኔታን በብስለት ካልያዝነው ከእጃችን ሊወጣ ይችላል የሚል ነው። የህዉሃት መራሹ መንግስት የአገዛዝ ፖሊሲ መሰረት ያደረገው የኢትዮጵያ የለውጥ ሃይሎች የማይተባበሩ፣ በፖለቲካ ስልጣን፣ ብሄርና ሃይማኖት ተከፋፍለው የውስጥ ሽኩቻ የሚያደርጉ የሚለው ክስ ወደ እውነት እንዳይቀየር ነው።