Tuesday, October 18, 2016

የዳሽን ቢራ አዲሱ ታክቲክ



ዳሽን ቢራ ንብረትነቱ የህወሃት ነው። ለትግራይ ህዝብ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፋብሪካዎችን ገንብቶ በምትኩ የተከለብን የሹፈት የብቅል ፋብሪካ ነው።
ከፋብሪካው ትርፍ በተገዛ ጥይት ለጋ ወጣቶቻችን በወያኔ ትግሬ አልሞ ተኳሽነት ተመተው ወድቀው ደማቸው በጎንደር ፒያስ ወደ አውቶፓርኮ አቅጣጫ ያለማቋረት እንደጅረት ፈሷል።
የዳሽን ቢራ የሚቀልባቸው የወያኔ ትግሬ ወንበር ጠባቂዎች መፈክር አንግቦ የወጣን የባህርዳር ማርቆስ ዳንግላ ማርቆስና ፍኖተ ሰላም ወጣት ጭንቅላት ይሄው ራሱ ፋብሪካው በገነባው ማማ ላይ ተጠልለው ጭንቅላታቸውን አፍርሰዋል። የዳሽን ቢራ ጥይት ወልቃይትን ቢረሳ ቀኙ እንድትረሳው ቃል ገብቶ አደባባይ የወጣውን አበበ ገረመውን በአጭሩ አስቀርቶብናል።
ታድያ ይህ መቀመጫውን ዐማራ ክልል አድርጎ ለትግሬ ግብር የሚከፍል፥ ጥሬ እቃን እኛው ጋር በርካሹ አጋብሶ በትርፉ ለህወሃት የአብሪ ጥይትን የሚገዛው የቢራ ፋብሪካ እስካሁን ቆሞ መገኘቱ ሳያንስ ምርቴን ተጠቀሙልኝ የሚል ማስታወቂያ እየሰራ መሆኑን ከወደ ጎንደር እየሰማን ነው።
የሚከተለውን ያካፈለኝ ጎንደር የሆነውን የታዘበ በቅርብ የማውቀው ሰው ነው
"የዳሽን ቢራ የህወሃት ካድሬዎችን ስፖንሰር በማድረግ የተለያዩ ቡና ቤቶች እየዞሩ ዳሽን ብቻ እንዲያዙ፤ ሲጠጡም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው "የጎንደር ህዝብ ግን ምንኛ ሞኝ ነው ዳሽን እኮ ለጎንደር ብዙ ልማቶችን እየሰራ ያለ ፋብሪካ ነው" እያሉ እንዲያወሩ እየተደረገ ነው።
የምሰማውን ማመን አቃተኝ። የወንድሞቸ ደም የሆነውን ቢራ በፈለከው ቋንቋ ብትገልጸውም ጉሮሮየን ከፍቸ ልጠጣው አልችልም። በየማጎሪያ ቤቱ እየተሰቃዩ ያሉ ወንድሞቸ ሰቆቃ ላይ የሚያፌዙትን ካድሬዎች መስማት ስላልቻልኩ የነበርኩትን ቦታ ስቀይር ሌላኛው ቤትም ተመሳሳይ ሁኔታ ገጠመኝ።
የዐማራ ደም በውስጥህ ይዘህ እንዴስ ብለህ የዳሽንን ቢራ ትጠጣለህ? እንዴት ተደርጎ? ያለመጠቀም አድማችን እስከወዲያኛው መሆን ነው ያለበት!!
ይህን ሁሉ ግፍ ከተፈጸመብን በዃላ ዳሽንን የምንጠቀም ሆኖ ከተገኘ "የመንድሞቻችን አጥንት ይውጋን ደማቸውም እንደደራሽ ዉሃ ይውሰደን" በሚል ምህላ ተማምለን ምርታቸውን እስከወዲያኛው ማቆም አለብን።"

No comments:

Post a Comment