አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
http://amharic.abbaymedia.com/
የወያኔ ሰራዊት አባላት የሆኑና የሰባት አመት ኮንትራታቸውን የጨረሱ አዲስ የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ የቀረበላቸውን ጥያቄ በአባላቱ ተቀባይነት ያለማግኘቱ ሲታወቅ በመከላከያም በኩል በወቅቱ ከሚገኝበት ሁኔታ ሳቢያ ሰራዊቱን ማሰናበት ያለመፈለጉ ታውቋል፡፡
የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ በ1999 ዓ/ምና 2001 ዓ/ም የተቀጠሩ የፈረሙት የሰባት አመት የስራ ኮንትራት በመጠናቀቁ ምክንያት ሁለተኛ ዙር የሰባት አመት ኮንትራት እንዲፈርሙ ደብዳቤ ቢደርሳቸውም በአብዛኛው የሰራዊቱ አባላት እስካሁን ለመፈረም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ይልቁንም ወደ የቤተሰባቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
መረጃው አያይዞም የመከላከያ ሰራዊቱ አመራር አካላት የምንገኘው በፈታኝ ወቅት ላይ ነው በሚል ኮንትራት የጨረሱትን የሰራዊቱ አባላት አዲሱን ኮንትራት እንዲፈርሙ ለማግባባት ቢሞክሩም እስከአሁን ያልተሳካላቸው መሆኑን ሲያስረዳ በአንፃሩም ሰራዊቱም በዚህ ወቅት ማሰናበት እንደማይችሉ ለአባላቱ የገለጹ መሆኑን ያስረዳል፡፡
በተጨማሪ ኮንትራቱን አንፈርምም ያሉት የሰራዊቱ አባላት በቆይታቸው ሊያገኙት የሚችሏቸውን ማንኛውም ጥቅማ ጥቅም በመከልከል አስገድዶ ለማስፈረም የተለመደው ሙከራ መደረጉ የማይቀር መሆኑን መረጃው ሲያስረዳ በአሁኑ ሰአት የወያኔ ስርአት የገጠመውን ፈተና በሰ ራዊት ሀይል ለመቋቋም በመጣር ላይ መሆኑና ተጨማሪ ሰራዊት መመልመል ያለመቻሉ ተጨማሪ ፈተና በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኮንትራታቸው ን በጨረሱ የሰራዊቱ አባላትን በግዳጅ በስራ ለማቆየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሊፈጥር የሚችለው ችግር ምልክቶች ከወዲሁ እየታዩ መሆኑንም ጨምሮ ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment