Thursday, October 20, 2016

; Breaking News

#AmharaResistance;
በምዕራብ አርማጭሆ አቡጢር የዐማራ ገበሬዎችን ለመግደል የሔደው የወያኔ ጦር ተደመሰሰ፤
ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ በምዕራብ አርማጭሆ ለሱዳን ከተሰጠው አቡጢር ከተባለ ቦታ ሲያርሱ የነበሩ የዐማራ ገበሬዎችን ለመያዝ ሁለት ኦራል፣ አንድ ፒክ አፕ እንዲሁም አንድ ታንክ በመያዝ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር መደምሰሱን አሁን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
ገበሬዎችን ለማፈን በአካባቢው በሚኖሩ ወያኔዎች ጥቆማ የመጣው ጦር ሠራዊት አባለት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲገደሉ ከዐማራ ገበሬዎች ግን ምንም የተጎዳ አለመኖሩን ጦርነቱን ሲመሩ የነበሩት ገበሬዎች የጎበዝ አለቃ በስልክ አረጋግጦልናል፡፡ የጎበዝ አለቃውን ስም መጥቀስ አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ስሙን በዜናው ላይ ማስገባቱን ትተነዋል፡፡ እንደ ጎበዝ አለቃው በውጊያ ላይ የነበሩ ገበሬዎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን ጦርነቱን በድል ተወጥተዋል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የዐማራ ገበሬዎች በተጠንቀቅ ነቅተው እንዲጠብቁና ተጨማሪ ኃይል ሊመጣ ስለሚችል እርዳታም እንዲደርሳቸው አሳውቀዋል፡፡
አቡጢር በምዕራብ አርማጭሆ ድንበር አካባቢ ያሉ ገበሬዎችን በማፈናቀል ለሱዳን የተሰጠ መሬት ሲሆን የዐማራ ገበሬዎች ለዓመታት ድንበራችን አናስነካም በማለት ብዙ የሕይወት መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡
Muluken TesfawBilderesultat for ወታደር

No comments:

Post a Comment