አንደኛ፣ በሁሉም አካባቢዎች የሚኖሩ እጅግ አብዛኛው ኢትዮጵያውያን በነጻነትና በእኩልነት መኖር ይፈልጋሉ።
ሁለተኛ፣ ጥላቻና ዘረኝነትን የሚሰብኩ ሰዎች ቢኖሩም፣ እጅግ አብዛኛው ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መኖርን ይሻሉ።
ሶስተኛ፣ ህዝቡ የትግል አቅጣጫ የሚያሳየው ብቻ ሳይሆን ሃላፊነትን በተገቢው መንገድ የሚሸከምና የሚያሸክም የሰከነ መሪ ይፈልጋል።
አራተኛ፣ በፖለቲከኞችና በህዝብ መካከል ያለው አለመናበብ የሰፋ ነው ( በተለይ የብሄር አጀንዳን ከሚያስቀድሙ ፖለቲከኞች ጋር)። በማህበራዊ ሚዲያ የምናነበው መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር በእጅጉ ይለያል። 1 በመቶ ከሚሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች መካከል የብሄር አጀንዳን የሚደግፉ በርካታ ወጣቶች አሉ። እነዚህ ወጣቶች የብሄር ፖለቲካ ለችግራቸው መፍትሄ እንደሆነ ቢያምኑም አፈጻጻሙ ላይ ግን ልዩነት አላቸው። አንደኛው ወገን አካባቢያችንን ( ክልላችንን) ነጻ ካወጣን በሁዋላ ተደራድረን አዲስ አገር እንመስርት ሲል፣ ሌላው ወገን ደግሞ በጋራ መኖር ስለማንችል ተገነጣጥለን እንኑር ይላል። የመጀመሪያው ከሁለተኛው በቁጥር ይልቃል።
አምስተኛ፣ ህዝባዊ አመጽ በሃይል (በጦር መሳሪያ) ካልታገዘ ውጤት አያመጣም ብሎ የሚያምነው ህዝብ ብዙ ነው። መሳሪያ የሚያገኝበትን መንገድም በተደጋጋሚ ይጠይቃል። ወታደሩና ፖሊሱም ስርዓቱን ትቶ ሌሎችን በሃይል የሚታገሉ ድርጅቶች ለመቀላቀል ዝግጁ ነው። እንዴት እንደሚቀላቀላቸው ግን ከፍተኛ የመረጃ እጥረት አለበት።
ስድስተኛ፣ ህዝቡ ከእንግዲህ በዚህ አገዛዝ ለአንድም ቀን ቢሆን ተገዝቶ ማደር አይፈልግም። የገዢውን ፓርቲ ፕሮፓጋንዳ የድርጅቱ አባላት ሳይቀር አይሰሙትም፤ ከፍተኛ የሞራል ውድቀትም ደርሶባቸዋል።
ሰባተኛ፣ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ አካባቢ መጠነኛ ብዥታ አለ። ነዋሪዎች ስልጣን የሚረከብ ድርጅት ማየት ይፈልጋሉ። የደህንነት ክፍተት ይፈጠር ይሆን ብለው የሚሰጉ አሉ። በተለይ መካከለኛ እና ከዚያ በላይ ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች ፍርሃታቸውን ሲገልጹ ይሰማል። አንድ ወታደራዊ ድርጅት ሃይሉን ማሳየት ሲጀምር ሁሉም ነገር በፍጥነት የሚለዋወጥ መሆኑን መረዳት ይቻላል።
በአጠቃላይ ጊዜው ለለውጥ አመቺ ነው። እስካሁን የተደረጉት ተጋድሎዎች አገዛዙን በአንድ ጥፍሩ አቁመውታል። በተለይ መሬት ላይ ደሙን በሚያፈሰው ህዝብ መካከል ያለው የአላማ አንድነት አገዛዙን በማዳከም በኩል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ይህንን አስደማሚ ትግል ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ በጋራ መርቶ ለመጨረሻው ድል ለማብቃት የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት ነው።
No comments:
Post a Comment