Monday, October 31, 2016

አዲስ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009)

በአራት የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ እድገትና ብልጽግናን የሚያመጣ የፌዴራል ስርዓት መገንባት ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታወቀ።
በሃገራዊ ንቅናቄው የምስረታው ስነስርዓት ላይ ያወጣው የጋራ መግለጫ እንደሚያመለክተው ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው የተከበረባትና ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መመስረት የህብረቱ ዋነኛ ዓላም መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ በአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በአፋር ህዝብ ፓርቲ፣ እና በሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያው ንቅናቄ የተፈጠረ ህብረት መሆኑን በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል።
በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በተካሄድው ስነስርዓት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባት ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር  ብርሃኑ ነጋ፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ እና የሲዳማ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ዋዮ ፊርማቸውን በማስቀመጥ ንግግር አድርገዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በበረሃ ትግል በመሆናቸው ንግግር ያደረጉትና ፊርማቸውን ያስቀመጡበት በተቀረጸ ምስል ሲሆን፣ ሌሎች የንቅናቄው አባላት በአካል ተገኝተዋል።
በፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና በሻለቃ ዳዊት ወልደጊዎርጊስ ገለልተኛ ኢትዮጵያውያን አመቻችነት በአራት ፖለቲካ ድርጅቶች የተፈጠረው ሃገራዊ ንቅናቄ ከህወሃት ውድቀት በኋላ ሰላምና መረጋጋት ያለበት የሽግግር ስርዓት እንዲኖር መሰረት የጣለ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ህብረቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል። የአማራውን ህዝብ የሚወክል የተጠናከረ ድርጅት እስኪመጣ ድረስ የቀድሞ የመላ አማራ ህዝብ ድርጅት ተወካይ የነበሩት አቶ ሃይለገብርዔል አያሌው በታዛቢነት ተገኝተዋል።

No comments:

Post a Comment