Thursday, October 13, 2016

ጀግናው አርበኛ አበራ ጎባው ማን ነው? Muluken Tesfaw


አርበኛ አበራ ጎባው መሰዋቱን የሰማሁት ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዐት አካባቢ ነበር፡፡ ሆኖም የዚህ ጀግና በጠላት መሞት ለኅልውናው የሚታገለውን የዐማራ ገበሬ ሞራል ይጎዳል በሚል ዜና ሳልሰራው ቆየሁ፡፡ ነገር ግን እኔ ብተወዉም ሌሎች ሰዎች የጎባውን ሰማዕትነት ዘገቡት፡፡ ከዚያም በአካባቢው ያሉ የዐማራ ገበሬዎችን እንዴት ነው ተጋድሏችሁ ላይ ምን አሉታዊ ተጽእኖ አለው? በማለት ጥያቄ አቀረብኩላቸው፡፡ ‹‹እንዴ አርማጭሆ እኮ ነው አገሩ! የበለጠ ደማችን በንዴት ተንተከተከ፤ ሺህ አበራዎች አለን›› አሉኝ፡፡ ስለሆነም የአበራ ጎባውን ጉዳይ ዘርዘር አድርጎ ማስረዳቱ የተሻለ እንደሆነ አሰብኩ፡፡
ሰማዕት አርበኛ አበራ ጎባው የትግሬ ወያኔ ፋሽሥታዊ ሥርዓትን ቀድሞ የተረዳ ጅግና ነበር፡፡ ከዛሬ 15 ዓመታት ቀድሞ የወልቃይት ዐማሮች ላይ የሚደርሰውን የትግሬ ወያኔ ጭካኔ አንገሸገሸው፡፡ ዐማራነት የማይከበርበት አገር ውስጥ እስከ መቼ መኖር እችላሉ? ዐማራነት ወንጀል ሆኖ ምን ዓይነት እንቅልፍ ይወስደኛል? አለ፡፡ ጓደኞቹን ጠራና መከረ፡፡ ዱር ቤቴ ብሎ ሕብረቱን ከጫካ ጋር ካደረገ ይኼው 15 ዓመታት አልፈውታል፡፡ 
የአርበኛው አበራ ጓደኛ ጫካ ነው፤ ቤቱ የዛፍ ጥላ ነው፤ ምርኩዙ ክላሽንኮፉ ነው፡፡ ጀግናው አርበኛ አበራ ባሕታዊ ነው- ግላዊ ሕይወቱን ትቶ ከዱር አራዊት ጋር ወዳጅነቱን አጥብቋል፡፡ በአርማጭሆ ጫካዎች ከአሽሬ ማዶ ዶጋው የተከበረው በአበራ ነው፡፡ አርበኛ አበራን አይደለም አርፎበት የነበረውን ዛፍ ማንም ደግሞ አይቀመጥበትም፡፡ 
ሰሞኑን የትግሬ ወያኔ መንግሥት የዐማራውን ትጥቅ ለማስፈታት በአርማጭሆ ሲጀምር እኔ እያለሁ እስኪ ይሞከራል? በማለት የወያኔን ጦር ለመመከት ወደ ወደ አሽሬ ታች አርማጭሆ ሔደ፡፡ አበራ በዚህ አለ ሲባል የሚፍረከረከው የወያኔ ጦር ከ30 በላይ የሚሆን ሠራዊት ከትቶ አበራ ከሁለት ጓዶቹ ጋር አለበት ወደተባለው ዶጋው ሔደ፡፡ የወንዱ ዲካ አበራ እርዳታ መጠየቅ አልፈለገም፡፡ እስካአፍንጫዊ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀውን 30 የወያኔ ጦር ብቻየን ዶጋ አመድ አደርገዋለሁ ብሎ አሰበ፡፡ 
መሣሪያ አተኳኮስ የግሉ ነው፡፡ አንድ ጥይት ተኮሶ ዒላማውን አይስትም፡፡ ሦስቱን አርበኞች ከ30 በላይ የሚሆን የወያኔ ጦር ዛሬ ከረፋዱ ላይ ከበባ አድርጎ ገጠማቸው፡፡ የእነ አበራ ክላሽ አሽካካ፡፡ ዲሽቃና ብሬን በነ አበራ አናት ላይ እሪ አለ፡፡ ጦርነቱ ያለበት አካባቢ ድምጽ አፍኖ በመያዙ ምክንያት ለእነ አበራ ረዳት መድረስ አልቻለም፡፡ 
የመጡትን የትግሬ ወያኔ 30 ወታደሮች አበራና ጓዶቹ አጋደሟቸው፡፡ 20ዎቹ እስከ መጨረሻው አሸለቡ፡፡ 10 አካባቢ የሚሆኑት ደግሞ በጣረሞት ተረፉ፡፡ የሔደው መከላከያ ሲያልቅ የጸረ ሽምቅ ግብረ ኃይል የሚባለው በብዛት ተከተለ፡፡ እነርሱንም አጋደሟቸው፡፡ ከቀኑ 9፡00 ሲሆን አንበሳዎቹ ሩጫቸውን ጨረሱ፡፡ ለሚወዱት ሕዝብ ክብር ሲሉ መስዋእት ሆኑ፡፡ የእነ አርበኛ አበራ ጎባውን አስከሬን ዙሪያ ከ50 በላይ የጠላት በድኖች ወዳድቀው ከበውት ነበር፡፡ ዛሬ አርማጭሆ ይህን ይመስል ነበር፡፡ 
ለጀግና ሞቱ ክብሩ ነው፤ አርማጭሆ የእነ ባሻ ጥጋቡ፣ የእነ አበራ ጎባው አገር ነው፡፡ አርማጭሆ ታሪክ መሥራት ልማዱ ነው፡፡ 
የዐማራ ተጋድሎ እስከ ነጻነት ይቀጥላል፤ የዐማራ ሕዝብ በልጆቹ መስእዋትነት ይከበራል!!
ድል ለዐማራ ሕዝብ

No comments:

Post a Comment