Thursday, October 13, 2016

ፈተነኝ...! በድምጻዊ - ሰሎሞን ደምሴ ግጥም - ነግሬው ቅሩብ እና ሰሎሞን ደምሴ ዜማ - ሰሎሞን ደምሴ ጉርብትና ብዬ ብይዘው በእቅፌ፣ ሳልሰስት ባጋራው ያለኝን አትርፌ፣ ሞኝ አረገኝና ሞፈር ልቁረጥ አለኝ መጥቶ ከደጃፌ። ተው በሉት ይሄን ሰው ፈተነኝ፣ ምንአድርግ ይለኛል ይተወኝ! (2) ኸረ ጉድ ነው .... ከታፈረው ቤቴ ከድምድሟ ጎጆ፣ ፀሃይ የመሰለች አለች ድማም ቆንጆ። በዚች ድማምና በጥርኝ አፈሬ፣ ድርድር አላውቅም ይመስክር አገሬ። በፍቅር እንጂ ሚዛን ይመተር፣ ልክ አዋቂ ነኝ የማልዛነፍ፣ ክብሬን የነካ ሚስቴን ጌጤን፣ አሳየዋለሁ ማንነቴን። መጎራበቱን ሳለሁ ወድጄ፣ ልቁረጥ ይለኛል ሞፈር ከደጄ። ቆሜ ስታዘብ ሞኝ እንዳልመስለው፣ አያውቅም ስቆርጥ እንደምጥለው። ተው አትፈትነኝ ኸረ አሰልለኝ፣ ታግሼ በኖርኩ ፈሪ አታስብለኝ። ተው አትፈትነኝ ኸረ አሰልለኝ፣ ከመረርኩ ወዲያ ማር እንዳትለኝ! ተው በሉት ይሄን ሰው ፈተነኝ፣ ምንአድርግ ይለኛል ይተወኝ! (2) ደግ መዋል ምነው መጎዳት ባይኖረው፣ መቸሬን ጅልነት አርጎ የቆጠረው፣ ከክፍ ጎረቤት ክፍ ቀን ይሻላል፣ ዘንድሮ ካለፍት ከርሞ ቀለል ይላል። ከስፍር ማጉደል ሃጥያት ነው ቢሉም፣ የሰው ሲመኙ አያስተውሉም። ማር የበዛ እለት ይሆናል እሬት፣ ሲናድ ገደል ነው ደልዳላ መሬት። ስጡኝም ብዬ ደጅ አልጠናሁም፣ የኔን አትንኩ እኔ አልተኛሁም። ካልጠፋ ሸጋ ካልጠፋ ሰው፣ የእኔ ያልኳትን ምን አስመኘው? ተው አትፈትነኝ ኸረ አሰልለኝ፣ ታግሼ በኖርኩ ፈሪ አታስብለኝ። ተው አትፈትነኝ ኸረ አሰልለኝ፣ ከመረርኩ ወዲያ ማር እንዳትለኝ! ያሳደግነው ጥጃ ከምንጭ ውሃ አግተን ከጨሌው አግጠን፣ ያሳደግነው ጥጃ ወተት አጠጥተን ለምለም ሳር አግጠን፣ ፈርገጥፈርገጥ አለ እኛን ሊረግጠን። ****** ማስታወሻነቱ በህወሃት የግፍ ፅዋ የማትተካ ሕይወታቸውን ላጡ ንፁሃን የወልቃይት ሕዝብ ትሁንልኝ!!!! . .Solomon Demise Amharic Music this week 2016

No comments:

Post a Comment