Thursday, June 29, 2017

የስራ አመራር ጥበብ እና ተያያዥ ጉዳዮች በተሰኘው የዶ/ር ታደሰ ብሩ መፅሓፍ ሀሳቦች ላይ ከፀሓፊው ጋር የተደረገ ዉይይት ክፍል 2

ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስተሮች ምክር ቤት መጽደቁ ተሰማ


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ፡ ሓሙስ፡ አርብና እሁድ ይከታተሉ
የዕለተ ሓሙስ ሰኔ -22 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

(የአርበኞች ግንት 7 ድምፅ ሬዲዮ)


አገዛዙ ሰሞኑን በአማራዉ ከልል በተለይም በጎንደር የሕዝቡን መሳሪያ ለማስፈታት አቅድ አዉጥቶ አየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ ለዚህም ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ በአሁኑ ሰዓት ቁጥሩ አጅግ ብዙ የሆነ የአጋዚ ጦር በወረታ ከተማ፥ በአዘዞ በዳባትና በእብናት ሰፍሮ እንደሚገኝ ታውቋል ። ይህ አምባገነን ቡድን ከመነሻዉ የአማራን ሕዝብ አንደኛ ጠላት አድርጎ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ያልፈነቀለዉ ድንጋይ የለም፥ በህዝባዊ እንቢተኝነት ላይ ከፍተኛ ሚናን ይጫወቱ የነበሩ ኮረኔል ደመቀ ዘውዱን ቸምሮ ብርቅዬ ወንድሞቻችንና አህቶቻችንን ያለፍርድ በአስርቤት አያማቀቀ ይገኛል፡፡ አሁን ሕዝባችን መሳሪያዉን ከፈታ የመጨረሻ የባርነት ቀንበር አንደሚጣልበት ጥርጥር የለዉም ፥ በመሆኑም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የምትገኙ መሳሪያ ያላችሁ ወገኖች በሙሉ በእየ አካባቢያችሁ ታጥቀዉ አየተፋለሙ ከሚገኑት አርበኞች ጋር አየተቀላቀላችሁ የነጻነት ትግላችሁን አንድታፋፍሙ ጥሪ ቀርቦላችኋል፥ የአገዛዙ ቅጥረኛ ወታደሮች መሳሪያ ለመንጠቅ የሚጠቀሙበት ዘዴ በገበያ ቀናት ወይም በባዕላት ቀን በቀብር ስነስርዓት ላይ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ለመፈተሽ በመሞከር ለምሳሌ፡- ሽፍታ ቤታችሁ ወይም አካባያችሁ ተደብቋል በማለትና በወንጀል ተጠርጥራችኋል እንዲሁም ቤት ውስጥ አባወራ የለም ብለው ባሰቡበት ጊዜ ወደ ሰው ቤት በመሄድ በህገወጥ መንገድ የቤት ፍተሻ በማድረግ መሳሪያ አላቸው ብለው የሚያስቡትን ሰው መሳሪያ ለማስፈታት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ ስለተደረሰበት ህብረተሰቡ ከዚህ እራሱን እንዲከላከልና ትግሉን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀርቧል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) በአርበኞች ግንቦት 7 የባህል ቡድን የተዘጋጀ ሙዚቃ ( ኢትዮጵያ ሃገሬ) የተሰኘ አዲስ ሃገራዊ ሙዚቃ በ2 ሲዲዮች (21 Patriotic Songs in 2 CDs) ተዘጋጅተው በቅርብ ቀን ለህዝብ ይቀርባሉ።

Monday, June 26, 2017

አድርባይነት ዶ/ር ታደሰ ብሩ


1. ትርጓሜ
አድርባይነት ለገዛ ራስ ጥቅም እንጂ ለህሊና ዳኝነት፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት ላላቸው የሥነ ምግባር መርሆዎች፣ ለሌሎች ሰዎች፣ ቡድኖች፣ ትውልድና ሀገር ግድየለሽ መሆን ነው። የግል ዝናውን፣ የግል ሀብቱን ወይም የግል ምቾቱን ለመጨመር ሲል ማድረግ የነበረበትን ማድረግ እየተቻለ ሳያደርግ የቀረ፤ ወይም ማድረግ ያልነበረበትን ያደረገ ሰው፣ ቡድን ወይም ድርጅት አድርባይ ይሰኛል።
አድርባይ የሆነ ሰው ወይ ድርጅት የሥነ ምግባር ልጓም የለውም፤ የሚናገረውን ሆኖ አይገኝም፤ ዋዣቂና ወላዋይ ነው፤ ለምንም ነገር መታመን አይችልም፤ ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ ማዶ ነው፤ ከፍ ያለ ዋጋ ላቀረበ ሁሉ ሊገዛ የሚችል ሸቀጥ ነው። አድርባይ ሰው ወይም ድርጅት ነገሮችን ሁሉ የሚመዝነው ከራሱ ጥቅም አንፃር ብቻ ነው። አድርባይነት በመልካም ማኅበረሰብ የተጠላ፣ የተናቀ፣ የማይፈለግ ብቻ ሳይሆን በህገወጥነት የሚያስቀጣም ባህርይ ነው።
2. አድርባይነትን የት እንፈልገው?
1. ሥልጣን: ተጠያቂነት የጎደለው ሥልጣን ባለበት አድርባይነት ሊኖር እንደሚችል እንጠብቅ። ያልተገደበ ሥልጣን አድርባይነትን ያፋፋል። 
2. ጥቅም: ጥቅም (በተለይም ገንዘብ) ባለበት ቦታ ሁሉ አድርባይነት የመኖሩ እድል ከፍተኛ ነው። አድርባዮች ያለአግባብ ሲበለጽጉ የዳር ተመልካቾች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በማለት ሊቀላቀሏቸው ይችላሉ። 
3. ሁኔታ: ሰዎች አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ ወኔ ሊከዳቸው ይችላል። ለምሳሌ ሰቆቃ (ቶርቸር) የበዛበት ሰው ወይም ከገመተው በላይ ማባበያ የቀረበለት ሰው ህሊናው የሚያዘውን ብቻ የመፈፀም አቅም ሊያጣ ይችላል። “እኔ ባላደርገውም ሌላ ሰው ያደርገዋል” የሚለው ስሜትም ለአድርባይነት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው።

Sunday, June 25, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 የህወሃት ድርጅቶችን የማውድውም ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ፡ ሓሙስ፡ አርብና እሁድ ይከታተሉ

የዕለተ እሁድ ሰኔ -18 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት

Wednesday, June 21, 2017

የአቶ አለምነው መኮንን የግል አጃቢ መገደል በካድሬዎች ላይ ሽብር ፈጥሯል


የክልሉ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ስራውን በፈቃዱ ለቋል
በአማራ ክልል ህዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠሉትና የህወሃት ቀኝ እጅ ተድርገው የሚቆጠሩት የአቶ ዓለምነው መኮንን የግል አጃቢ የሆነው አንዋር ሙሃመድ የተባለው ግለሰብ፣ ባህርዳር ቀበሌ 04 በሚገኘው ግሪንላንድ ሆቴል ውስጥ በጥይት ተመትቶ ተገድሎ ከተገኘ በሁዋላ፣ የብአዴን ካድሬዎችና የአቶ ዓለምነው የቅርብ ወዳጆች ሽብር ውስጥ መግባታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
በመሆኑም ካድሬዎቹን ለማረጋጋት ሲባል የዞኑ የፖሊስ አዛዥ የሆነው ኮማንደር ዋኘው ግለሰቡ ራሱን እንዳጠፋ ተደርጎ እንዲነገር ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለውስጥ አርበኞች አልተባበርም በማለቱ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ምሽት ላይ እንደተገደለ የገለጹት ምንጮች፣ በእለቱ ምሽት ላይ አቶ አለምነው መኮንን በባህርዳር እንደነበርና የግድያው ኢላማም እሱ እንደነበር ገልጸዋል። አቶ አንዋር፣ የአቶ አለምነው አካባቢ ተወላጅ ሲሆን፣ አቶ አለምነውን አሳልፌ አልሰጥም በማለቱ እርምጃ እንደተወሰደበት እነዚሁ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
ግድያው የተፈጸመው የብአዴን ባለስልጣናት በሚዝናኑበት ግሪንላንድ ሆቴል ነው። ከዚህ ቀደምም በዚሁ ሆቴል ግቢ ውስጥ ቦንብ መፈንዳቱ ይታወሳል።
ግድያውን ተከትሎ ትናንት በክልሉ የሚገኙ ደህንነቶች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ የክልሉ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አሰፋ ስንታየሁ “ በዚህ ሁኔታ መሥራት አልችልም” በማለት ስራውን በፈቃደኝነት ለቋል። የኮማንደሩ ከኃላፊነቱ መልቀቅ ተጨማሪ ስጋት ማሳደሩን ምንጮች ገልጸዋል።
ትናንት በነበረው ግምገማ ላይ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባለሸ መሄዱ፣ በክልሉ ያለውን የትጥቅ ትግል መቆጣጠር አለመቻሉ፣ ለመረጃ ከፍተኛ ገንዘብ እየወጣ መረጃ መጥፋቱ ተነግሯል።
እንዲሁም ነገ በፖሊስ ኮሚሽን ላይ ጥቃት እንደማይፈጸም እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ከመድረኩ የተገለጸ ሲሆን፣ ግምገማው ወደ እርሱ ማነጣጠሩን የተረዳው ኮማንደር አሰፋ “ ዛሬ ላይ ማን ለማን እንደሚሰራ አይታወቅም” የሚልና ሌሎችንም ጠንካራ የተባሉ ትችቶችን በመሰንዘር ፣ በገዛ ፈቃዱ ስልጣኑን መልቀቁንና በስራው የመቀጠል ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል።
እንደውስጥ ምንጮች ገለጻ የብአዴን ባለስልጣናት ከህወሃት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ዙሪያ ከሁለት ተከፍለዋል።
አብዛኞቹ የክልሉ ፖሊሶችና ወታደሮች ብአዴን ራሱን ከህወሃት ተጽእኖ አላቅቆ የክልሉን ህዝብ መብትናማንነት እንዲያስከብር ይፈልጋሉ።እንዲሁም የደህንነትና የጸጥታ አባላቱ በክልሉ ከተሰማራው ኮማንድ ፖስት ጋር ያላቸው ግንኙነት በጣም የተደካመ ነው። ይህ ጉዳይ በፌደራል ደረጃ የተቀመጡ የህወሃት ባለስልጣናትን እያሣሰበ መምጣቱን ተከትሎ፣ በቅርቡ ሹም ሽር እንዲካሄድ ቢደረግም ነገሮች እየባሱ እንጂ እየተሻሻሉ አልመጡም።

ኦህዴድ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል!!!

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የህወሓት ታማኞች ሌሎች የኦህዴድ አባላትን ማሳደድና ማሰር ጀምረዋል። 
በኦህዴድ ውሰጥ ያሉ ታማኝ የህወሓት አገልጋዮቸ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የራስ መተማመንን በማዳበር ላይ ያሉትን የኦህዴድ አመራር አባላትን ማደን ጀምረዋል። ኦህዴድ ውስጥ ሆነው ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። ባለፉት 2 ቀናት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ 3 የዞን አመራሮች ታሰረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ 5 የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት አገር ጥለው ወጥተዋል። በተመሳሳይ በርካታ በኦሮሚያ የሚገኙ የዞን አመራሮች መኖሪያ ቤት በደህንነቶች ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጓል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከመሣሪያ ግምጃ ቤት 78 ክላሽ መሳሪያ መጥፋቱ እየተነገረ ይገኛል። በዚህም ምከንያት ኦህዴድ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል። ኦህዴድ ስልጠና በሚል ሰበብ ሃሙስ እለት ካድሬዎችን ለስብሰባ የጠራ መሆኑ ታውቋል።
ዝርዘር መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን

Tuesday, June 20, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በእብናት ከተማ የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች ጊዜያዊ ማዘዣ መምሪያ ላይ ጥቃት ፈፀሙ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በእብናት ከተማ የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች ጊዜያዊ ማዘዣ መምሪያውን ያጠቁ ሲሆን በዚህ ጥቃት በአማራ ክልል የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ዋና አዛዥ ኮማንደር አወቀ የተገደለ መሆኑና 2 ሊሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን የገለፀ ሲሆን ወደ ባህርዳር ለከፍተኛ ህክምና መወሰዳቸውንም ለማወቅ ችለናል።
ሟቹ ኮማንደር አወቀ ወደዚህ ቀጠና የተላከው በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል "ለመደምሰስ" በሚል ነበር። ይህ አዛዥ የወያኔ ነባር አባል የነበረ፣ በተለያዩ ዘመቻዎች እየተላከ ይሰራ የነበረ ሲሆን በመላ ኢትዮጲያ በሚገኙ ክልሎች እየተላከ የወያኔን የጭፍጨፋ ተልዕኮ ሲፈፅምና ሲያስፈጽም የነበረ በህግ መጠየቅ የነበረበት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር የነበረ ነው። በቅርብ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ዜጎችን እዲገድሉ፣እዲታሰሩ፣አድራሻቸው እዲጠፋ፣ በርካታ ንፁሃን ዜጎች በወጡበት እዲቀሩ ትዕዛዝ ይሰጡ ከነበሩ የወያኔ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር አንዱ ነበር፣ በዚህ እኩይ ተግባሩ በአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ልዩ ክትትል ከሚደረግባቸው የህዝብ ጠላቶች አንዱ ነበር። በመሆኑም በአሁኑ ሳዓት አስከሬኑ ወደ ባህርዳር ተጭኖ መወሰዱ ታውቋል ፡፡

Tuesday, June 13, 2017

“ዶክመንተሪው” እና አንሙት አብርሃ


የፀረ-ሽብርና የፌደራል ፓሊስ ጥምር ግብረኃይል ከEBC (የድሮዉ ኢቲቪ) እና ENN ጋር በመተባበር “ታላቅ” የተባለ ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንተሪ) እያዘጋጀ ነው። [መቸም፤ EBCን እና ENNን በእንግሊዝኛ መጥራት ግዴታችን ሆኗል]
የዚህ ዶክመንታሪ ስክሪፕት ፀሐፊ አቶ አንሙት አብርሃም ነው። አቶ አንሙት የፃፈው ስክሪፕት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኩራል:- ፕሮፌሰርን ብርሃኑ ነጋን በኦብነግ በኩል የኦጋዴን አስገንጣይ አድርጎ ማቅረብ እና በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ አሉባልታዎችን መንዛት።
ትኩረት አንድ
ትኩረት አንድ የሚያጠነጥነው ፕሮፌሰርን ብርሃኑ ነጋን በኦብነግ በኩል የኦጋዴን አስገንጣይ አድርጎ ማቅረብ ላይ ነው። ለዚህ እንዲረዳ ኦብነግ ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የተነሳ ድርጅት መሆኑን ያሳምናሉ የተባሉ የቪዲዮ ማስረጃዎች ተሰባስበዋል። “ኢህአዴግ ከኦብነግ ጋር እየተነጋገረ ነው” “የኦብነግ መሪዎች አመጽን አውግዘው ህገመንግስቱን ተቀብለው በህጋዊ መንገድ ለመታገል ምህረት ጠይቀው ገቡ” “ኦብነግ የሚባል ድርጅት የለም” በሚል እና መሰል ርዕሶች ቀደም ሲል የተሠሩ ዜናዎችና ዶክመንተሪዎች በስህተት ተደባልቀው እንዳይገቡ ጥንቃቄ ተደርጓል። የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች በዶክመንተሪው ይሳተፉሉ፤ የሶማሌ ክልል ሕዝብ በፌደራሊዝም ምን ያህል እንደተጠቀመ ይናገራሉ፤ ይህን ወደ ገነት በር ያቀረባቸውን ፌደራሊዝም ሊነጥቅ የመጣን ብርሃኑንና ድርጅቱን አምርረው እንደሚታገሉት ይናገራሉ።
ህወሓት ፕ/ር ብርሃኑን አገር በማስገንጠል ፈርጆ ሲከስ በአድማጮች ጭንቅላት ውስጥ የትኛው ትዝታ ብቅ ሊል እንደሚችል መገመት ለብዙዎቻችን ከባድ ባይሆንም ለስፕሪፕት ፀሐፊውና ለአለቆቹ ግን የሮኬት ሳይንስ ያህል ከባድ ነው። “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ይሏል ይህ ነው።
ትኩረት ሁለት
የትኩረት ሁለት አብኛው ቀረፃ በአማራ ክልል ተደርጎ ተጠናቋም። ይዘቱም በአጭሩ እንደሚከተለው ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 በኤርትራ መንግሥት የሚዘወር መሆኑ፤ መሪዎቹ ነጋዴዎች መሆናቸው እና ድርጅቱ ፀረ አማራ መሆኑ “በማስረጃዎች” ማረጋገጥ ቀዳሚ ዓላማው ነው። እነዚህን አሉባልታዎች “በማስረጃዎች” ለማረጋገጥ በተለያዩ ጊዜያት ከድርጅቱ ተለይተው የሄዱ ወይም በሀሳብ ተለይተን ወጥተናል የሚሉ ሰዎች ቃለመጠይቆች ተካተዋል። የቪዲኦና የድምጽ ማስረጃዎችም ቀርበዋል። አንዳንዶቹ “ማስረጃዎች” የሚያስቁና የሚያሳቅቁ ቢሆንም የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎችን ስም ያጎድፋሉ በሚል ተስፋ ተካተዋል።
ይህ የአድርባይነት ሚና ለመወጣት የአምስት ሚሊዮን ብር በጀት ተመድቧል። ሚሊዮኖች በረሀብ በሚያልቁበት አገር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች ለእንዲህ ዓይነት ተግባራት ይውላሉ።
ጥቂት ዓረፍተ ነገሮች ስለ አቶ አንሙት አብርሃም
በዓመታት በፊት በትምህርት ብልጭታ ፕሮግራም ስለ “አድርባይነት” የጥቁት ተከታታይ ሳምንታት ፕሮግራም አቅርቤዓለሁ። ያኔ ለአድርባይነት ቋሚ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ስፈልግ ከቀረቡልኝ ጥቆማዎች አንዱ አቶ አንሙት አብርሃም ነበር። እንዲያውም “የሚዲያ አድርባይነት” የሚል ራሱን የቻለ ፕሮግራም እንዳዘጋጅ በተመልካቾቼ ሀሳብ ቀርቦልኝም ነበር። እኔ ግን ሽመልስ ከማልና ሬድዋን ሁሴንን መረጥኩ፤ አንሙት አብርሃም ይህን ያህል ዝነኛ አድርባይ ነው።
የድሮው ኢቲቪ በኃይለራጉኤል ታደሰ እና በአሰፋ ፈቃዱ ቡድኖች ቅራኔ ሲናጥ አንሙት አብርሃ ወደአመዘነበት ሲፈስ የነበረ ጅረት ነው። አንሙት በህወሓት ውስጥ ስንጥቅ እየፈለገ መወተፍ ያውቅበታል። ከኢቲቪ ከለቀቀ በኋላም የኃይል ሚዛን እያየ ባላሥልጣኖችን እየተጠጋ መኖርን ብልህነት እንደሆነ አድርጎ ራሱን አሳምኗል። አሁን ባለው አሰላለፍ መሠረት የስብሃት ነጋ “የበኩር ልጅ” ነው። በዚህ ቀረቤታው ምክንያት የENN ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኗል። አሁን ደግሞ “ታማኝነቱ” የሚያስመስክርበት ሥራ ተሰጥቶቻል - ይህ ዶክመትሬ !!!
አለመታደሉ ግን ተስፋ ያደረገበት ዶክመንተሪ ምስጢር እጃችን ገባና ቀደምነው !!!
@ዶ/ር ታደሠ ብሩ

አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ። June 12, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ።

ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓ.ም አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ከቀድሞ ናዝሬት አውቶቡስ ተራ አጠገብ የሚገኘውን የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ። ቦታው ቀደም ባሉ ዓመታት የጉምሩክ መጋዘን ሆኖ ያገለግል ነበር። በቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ቦታው የሚያገለግለው በፌደራል ፓሊስ የመሣሪያ ግምጃ ቤትነትና በስውር ማሰቃያነት ነው።
በርካታ ወገኖቻችን

Sunday, June 11, 2017

Ethiopia National Movement *ENM*Public Discussion And Fundraising Program

Sagantaa Marii.Uummataa Fi Garqaarsa Sochii Biyyaa Itiyoophiyaa *SBI*
Oslo, Norway

June 17th 2017

አዲስ አበባ ካራ ቆሬ የሚገኘው ሮያል እስፖንጅ ፋብሪካ ቃጠሎ መድረሱ ተገለጸ

#ከሠራዊቱ_ድምፅ ከሠራዊቱ ድምፅ ራዲዮ ዘወትር በሳምንትአንድ ቀን ዕለተ ቅዳሜ እየተዘጋጀ ይቀርባል ። አዘጋጅና አቅራቢ #ሻለቃ_አብርሃም_ታከለ ዋሽንግተን ዲሲ

የህወሃት አገዛዝ የመከላከያና የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ከፍተኛ ትርምስ መፈጠሩ ተገለጸ


የአግ7 ድምፅ ስርጭት ዘወትር ማክሰኞ ሓሙስና ቅዳሜ ይከታተሉ
የዕለተ እሁድ ሰኔ - 04 - ቀን ፡ 2009 ዓ/ም የሬድዮ ስርጭት