(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በእብናት ከተማ የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች ጊዜያዊ ማዘዣ መምሪያውን ያጠቁ ሲሆን በዚህ ጥቃት በአማራ ክልል የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ዋና አዛዥ ኮማንደር አወቀ የተገደለ መሆኑና 2 ሊሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን የገለፀ ሲሆን ወደ ባህርዳር ለከፍተኛ ህክምና መወሰዳቸውንም ለማወቅ ችለናል።
ሟቹ ኮማንደር አወቀ ወደዚህ ቀጠና የተላከው በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል "ለመደምሰስ" በሚል ነበር። ይህ አዛዥ የወያኔ ነባር አባል የነበረ፣ በተለያዩ ዘመቻዎች እየተላከ ይሰራ የነበረ ሲሆን በመላ ኢትዮጲያ በሚገኙ ክልሎች እየተላከ የወያኔን የጭፍጨፋ ተልዕኮ ሲፈፅምና ሲያስፈጽም የነበረ በህግ መጠየቅ የነበረበት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር የነበረ ነው። በቅርብ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ዜጎችን እዲገድሉ፣እዲታሰሩ፣አድራሻቸው እዲጠፋ፣ በርካታ ንፁሃን ዜጎች በወጡበት እዲቀሩ ትዕዛዝ ይሰጡ ከነበሩ የወያኔ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር አንዱ ነበር፣ በዚህ እኩይ ተግባሩ በአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ልዩ ክትትል ከሚደረግባቸው የህዝብ ጠላቶች አንዱ ነበር። በመሆኑም በአሁኑ ሳዓት አስከሬኑ ወደ ባህርዳር ተጭኖ መወሰዱ ታውቋል ፡፡
No comments:
Post a Comment