Tuesday, June 13, 2017

“ዶክመንተሪው” እና አንሙት አብርሃ


የፀረ-ሽብርና የፌደራል ፓሊስ ጥምር ግብረኃይል ከEBC (የድሮዉ ኢቲቪ) እና ENN ጋር በመተባበር “ታላቅ” የተባለ ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንተሪ) እያዘጋጀ ነው። [መቸም፤ EBCን እና ENNን በእንግሊዝኛ መጥራት ግዴታችን ሆኗል]
የዚህ ዶክመንታሪ ስክሪፕት ፀሐፊ አቶ አንሙት አብርሃም ነው። አቶ አንሙት የፃፈው ስክሪፕት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኩራል:- ፕሮፌሰርን ብርሃኑ ነጋን በኦብነግ በኩል የኦጋዴን አስገንጣይ አድርጎ ማቅረብ እና በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ አሉባልታዎችን መንዛት።
ትኩረት አንድ
ትኩረት አንድ የሚያጠነጥነው ፕሮፌሰርን ብርሃኑ ነጋን በኦብነግ በኩል የኦጋዴን አስገንጣይ አድርጎ ማቅረብ ላይ ነው። ለዚህ እንዲረዳ ኦብነግ ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የተነሳ ድርጅት መሆኑን ያሳምናሉ የተባሉ የቪዲዮ ማስረጃዎች ተሰባስበዋል። “ኢህአዴግ ከኦብነግ ጋር እየተነጋገረ ነው” “የኦብነግ መሪዎች አመጽን አውግዘው ህገመንግስቱን ተቀብለው በህጋዊ መንገድ ለመታገል ምህረት ጠይቀው ገቡ” “ኦብነግ የሚባል ድርጅት የለም” በሚል እና መሰል ርዕሶች ቀደም ሲል የተሠሩ ዜናዎችና ዶክመንተሪዎች በስህተት ተደባልቀው እንዳይገቡ ጥንቃቄ ተደርጓል። የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች በዶክመንተሪው ይሳተፉሉ፤ የሶማሌ ክልል ሕዝብ በፌደራሊዝም ምን ያህል እንደተጠቀመ ይናገራሉ፤ ይህን ወደ ገነት በር ያቀረባቸውን ፌደራሊዝም ሊነጥቅ የመጣን ብርሃኑንና ድርጅቱን አምርረው እንደሚታገሉት ይናገራሉ።
ህወሓት ፕ/ር ብርሃኑን አገር በማስገንጠል ፈርጆ ሲከስ በአድማጮች ጭንቅላት ውስጥ የትኛው ትዝታ ብቅ ሊል እንደሚችል መገመት ለብዙዎቻችን ከባድ ባይሆንም ለስፕሪፕት ፀሐፊውና ለአለቆቹ ግን የሮኬት ሳይንስ ያህል ከባድ ነው። “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ይሏል ይህ ነው።
ትኩረት ሁለት
የትኩረት ሁለት አብኛው ቀረፃ በአማራ ክልል ተደርጎ ተጠናቋም። ይዘቱም በአጭሩ እንደሚከተለው ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 በኤርትራ መንግሥት የሚዘወር መሆኑ፤ መሪዎቹ ነጋዴዎች መሆናቸው እና ድርጅቱ ፀረ አማራ መሆኑ “በማስረጃዎች” ማረጋገጥ ቀዳሚ ዓላማው ነው። እነዚህን አሉባልታዎች “በማስረጃዎች” ለማረጋገጥ በተለያዩ ጊዜያት ከድርጅቱ ተለይተው የሄዱ ወይም በሀሳብ ተለይተን ወጥተናል የሚሉ ሰዎች ቃለመጠይቆች ተካተዋል። የቪዲኦና የድምጽ ማስረጃዎችም ቀርበዋል። አንዳንዶቹ “ማስረጃዎች” የሚያስቁና የሚያሳቅቁ ቢሆንም የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎችን ስም ያጎድፋሉ በሚል ተስፋ ተካተዋል።
ይህ የአድርባይነት ሚና ለመወጣት የአምስት ሚሊዮን ብር በጀት ተመድቧል። ሚሊዮኖች በረሀብ በሚያልቁበት አገር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች ለእንዲህ ዓይነት ተግባራት ይውላሉ።
ጥቂት ዓረፍተ ነገሮች ስለ አቶ አንሙት አብርሃም
በዓመታት በፊት በትምህርት ብልጭታ ፕሮግራም ስለ “አድርባይነት” የጥቁት ተከታታይ ሳምንታት ፕሮግራም አቅርቤዓለሁ። ያኔ ለአድርባይነት ቋሚ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ስፈልግ ከቀረቡልኝ ጥቆማዎች አንዱ አቶ አንሙት አብርሃም ነበር። እንዲያውም “የሚዲያ አድርባይነት” የሚል ራሱን የቻለ ፕሮግራም እንዳዘጋጅ በተመልካቾቼ ሀሳብ ቀርቦልኝም ነበር። እኔ ግን ሽመልስ ከማልና ሬድዋን ሁሴንን መረጥኩ፤ አንሙት አብርሃም ይህን ያህል ዝነኛ አድርባይ ነው።
የድሮው ኢቲቪ በኃይለራጉኤል ታደሰ እና በአሰፋ ፈቃዱ ቡድኖች ቅራኔ ሲናጥ አንሙት አብርሃ ወደአመዘነበት ሲፈስ የነበረ ጅረት ነው። አንሙት በህወሓት ውስጥ ስንጥቅ እየፈለገ መወተፍ ያውቅበታል። ከኢቲቪ ከለቀቀ በኋላም የኃይል ሚዛን እያየ ባላሥልጣኖችን እየተጠጋ መኖርን ብልህነት እንደሆነ አድርጎ ራሱን አሳምኗል። አሁን ባለው አሰላለፍ መሠረት የስብሃት ነጋ “የበኩር ልጅ” ነው። በዚህ ቀረቤታው ምክንያት የENN ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኗል። አሁን ደግሞ “ታማኝነቱ” የሚያስመስክርበት ሥራ ተሰጥቶቻል - ይህ ዶክመትሬ !!!
አለመታደሉ ግን ተስፋ ያደረገበት ዶክመንተሪ ምስጢር እጃችን ገባና ቀደምነው !!!
@ዶ/ር ታደሠ ብሩ

No comments:

Post a Comment