Thursday, April 26, 2018

ሰበር_ዜና ዘመቻ_ነበሮ" ዘመቻ ገዛኸኝ ነብሮ " በሚል ስም በተሰየመ ዘመቻ የአግ7 አርበኞች የህወሓት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈፀሙ!


ሚያዚያ 17 ቀን 2010 ዓም ከምሽቱ 4:25 ሲሆን የአግ7 አርበኞች በጎንደር ከተማ አዘዞ የሚገኘውን የህወሓት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት የፈፀሙ ሲሆን በዚህ ጥቃት በርካታ የህወሓት ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የተኩስ ልውውጡ ከምሽቱ 4:20 እስከ ለሊት 7:40 ማለትም ለ 3:20 ያክል የቆየ ሲሆን በካምፑ የሚገኙ 3 በሮች ማለትም ወደ ጎንደር አዘዞ ድልድይ ወደ ጭልጋ አዲሱ አውቶብስ ማረፊያ እና ከላይ ወደ ሎዛ ማሪያም በኩል ባሉ 3 የጥበቃ ክፍሎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በዚህ ካምፕ የህወሓት የምዕራብ ዕዝ 42ኛ ክፍለጦር መገኛ ሲሆን የአዛዡ ጄኔራል ሲሳይ ጥበቃ ክፍልም ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ይህ "ዘመቻ ነብሮ" ታቅዶበትና ልዩ ዝግጅት ተደርጎበት በተለይም "የአርበኛን ደም አርበኛ ነው የሚመልሰው" በማለት አርበኛ ገዛኽኝ ገብረመስቀል (ነብሮ) ከተሰዋበት ቀን ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ቀጠና የሚንቀሳቀሱ የአግ7 አርበኞች በዚህ ጀግና ስም አንድ የተመረጠ ዘመቻ ለማካሔድ በመነጋገር የተሰራ አኩሪ ስራ ነው፡፡ አሁን እየደረሰን ባለው መረጃ የተኩስ ልውውጡ በምሽት በመሆኑ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም በወቅቱ 2 አንቡላንሶች የሞቱ እና የቆሰሉ ወታደሮቹን እያነሱ እንደነበር የአይን እማኞች አረጋግጠዋል በነበረው ውጊያ በአይን የታዩ የሞቱ የህወሓት ወታደሮች 13 ሲሆኑ ቆስለው ጎንደር ሆስፒታል የገቡ ደግሞ 9 ናቸው፡፡ በዚህ የተኩስ ልውውጥ የፍንዳታ እና ከፍተኛ ድምፅ ይሰማ እንደነበር እንዲሁም ከካምፑ ውስጥ አንድ ክፍል በፍንዳታው እንደፈረሰ የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡ ይህን ዘመቻ የተሳተፉ የቁርጥ ቀን ጀግኖች በሰላም ወደ ቀጠናቸው ተመልሰዋል፡፡ "አርበኛ ቢሰዋም እሱ የተሰዋለትን ዓላማ ከግብ የማድረሱ ትግል ይቀጥላል" በሚል መርህ ተከታታይ ድሎች ይኖራሉ፡፡ በአካባቢው ያለውን ዝርዝር ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃለን፡፡ ድል ለሕዝብ !! የአግ7 ዘመቻ ነፃ ትውልድ፡፡

Tuesday, April 24, 2018

በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል! (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2010ዓ.ም. ፕሮግራሞቻችንየዕለቱ አርዕስተ ዜና
* የጀግናው የገዛኧኝ ገብረ መስቀል (ነብሮ) መሰዋት የነጻነት ጉዞአችንን ይበልጥ እንዲጠናከር ተጨማሪ አደራ ጥሎብን አልፏል ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያ ተናገሩ።


* ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ቢልም እስከ አሁን በተለያዩ እስር ቤቶች በርካታ ታሳሪዎች ያለፍርድ ታስረው ይገኛሉ ተባለ።
* ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ።
፠በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል – አርበኛ ታጋይ ሜሮን አለማየሁ
የተሰኘው መሰናዷችን ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር !!! 
አንድነት ሃይል ነው!

Saturday, April 21, 2018

ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ (የጸጥታ ኃይሎች ዜና (ሚያዚያ 13, 2010 ዓ.ም)

በፓርላማ ውድቅ የተደረገው ነገር ግን ህወሃት በጉልበት ያጸደቀው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገበት የካቲት 9/2010 ዓ.ም ጀምሮ አገራችን ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቃ እየማቀቀች እንደሚገኝ ይታወቃል። በመሆኑም ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በበላይነት የሚያስፈጽሙትና የሚቆጣጠሩት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣የመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ፣ የመከላከያ ሚኒስተሩ፣ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም እንዲሁም የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነር ናቸው።Image may contain: 1 person, closeup
በዚህም መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተገኙ ውጤቶች፣ የጠፉ ጥፋቶች፣በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም እንዲገመገሙ በየቀጠናው የተሰበሰቡ መረጃዎች ተጠቃለው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ዝርዝር ሪፖርት እንዲደረግ ያዛል።
ይሁን እንጂ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት የሚቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዦች የሆኑት የህወሃት ወታደራዊ አዛዦች ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር መረጃ እንዲሁም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በመላ አገሪቱ ስለታሰሩት ዜጎች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ለዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲሁም ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አናደርግም ማለታቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
የመረጃ ምንጮቻችን አክለው የህወሃት ሰዎች ለዶክተር አቢይ ሪፖርት ብናቀርብ ነገሮችን ያበላሽብናል ብለው መስጋታቸውን አብራርተዋል። በተለይ ጄነራል ሳሞራ የኑስ <<ትላንት ለእኔ በተጠንቀቅ ሰላምታ ይሰጠኝ ለነበረ ለአንድ ተራ ወታደር ዛሬ ገና ለገና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ ብየ ሪፖርት አላቀርብም >> ሲል መናገሩ ተከትሎ ሁኔታው ዶ/ር አቢይ አህመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ያበላሽብናል ከሚል የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነሳሞራ አንሸነፍም ባይነት እንዲሁም የመታብይና የበታችነት ስሜት የተቀዳ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል። በዚህም ምክንያት በእነሳሞራ በአጠቃላይ በህወሃት ሰዎች ጥርስ ውስጥ የገቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ከተሰየሙ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስተሩ አልቀረበም ተብሏል።
በህገመንግስቱ መሰረት አንቀጽ 74 ንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የጦር ሃሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው ይላል። ስለሆነም የመከላከያ ሰራዊቱ ኤታ ማዦር ሹም ዝርዝር ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስተሩ የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት ያስገድዳል። ነገር ግን ህወሃት ህግ የሚያወጣው እራሱ እንዲገዛበት ሳይሆን ሰዎችን እያስፈራራ ሰጥ ለጥ አድርጎ ለመግዛት እንዲያመቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህም ነው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር አፈጻጸምና ስለታሰሩ ሰዎች ሪፖርት አላቀርብም ያለው ሲሉ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት እየገለጹ የሚገኙት።
በተጨማሪም ዶክተር አቢይ በበአለ-ሲመታቸው እለት <<በተለያየ ጊዜ መስዋእትነት ለከፈሉ የመብት ተከራካሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ በቅጡ ሳይቦርቁ ህይወታቸውን ለተቀጠፉ ለውጥ ፈላጊዎች፣ ለስነልቦናና ለአካል ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ>> በማለታቸው የመከላከያ ያሉ የህወሃት የጦር አዛዦችን በጣም ማስቆጣቱን ከመከላከያ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በዚህም ምክንያት እነሳሞራ የኑስ እንዲህ አይነት አቋም ላለውና እኛን ሆንብሎ በህዝብ ለማስጠላት ለቆመ ጠቅላይ ሚኒስተር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተመለከተ አፈጻጸምም ሆነ፣ ስለታሰሩ ሰዎች እንዲሁም እርምጃ ስለተወሰደባቸው አካላት ምንም አይነት ሪፖርት ላለመስጠት እያንገራገሩ እንደሚገኙ ታውቋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ውስጥ ጄነራል ሳሞራ ከስልጣኑ ይነሳል በማለት በሰፊው እየተወራ እንደሆነ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።

Wednesday, April 18, 2018

ESAT DC Daily News Wed 18 Apr 2018

አሁን ባለው የፌደራሊዝም ስርዓት አንድ ጠንካራ ኢትዮጵያን መገንባት አይቻል ( ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም)

 ላለፉት 26 ዓመታት ክልል ከአገር በላይ ሆኖ እንዲታይ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲካሄድ በመቆየቱ፣ ቀላል የማይባል የአዲሱ ትውልድ አባላትና “ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ” ሲሉ የነበሩ ከእኔ በፊት የነበሩና የእኔ ትውልድ ሰዎች ሳይቀሩ “ከአገሬ በፊት ክልሌ” እያሉ ሲዘምሩ እየሰማን ነው። ከወያኔ በፊት የነበሩ ትውልዶች “ክልሌን ላስቀድም ወይስ አገሬን?” በሚል ምርጫ ከራሳቸው ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡበት ሁኔታ አልነበረም፤ እያንዳንዱ ዜጋ ታማኝነቱ ሁሉ፣ አንድና አንድ፣ ለአገሩ ነበር። በጊዜው የነበረው በክፍለሃገር ደረጃ የተዋቀረው አስተዳደር የተለያዩ ብሄረሰቦችን አቅፎ የያዘ በመሆኑ፣ በአንድ ክፍለሃገር ስር ይኖር የነበረ የአንድ ብሄረሰብ ተወላጅ “ከአገሬ ክፍለሃገሬ” የሚልበት ሁኔታ አልነበረም። ዛሬ ክልል የሚባለው አጥር ከብሄር ማንነት ጋር በእጅጉ ተቆራኝቷል። “ክልል ይፍረስ” ብትል “ብሄርህ ይጥፋ” እንዳልክ ተቆጥሮ ጦር ይሰበቅብሃል። ክልልን የብሄር ማንነት መገለጫ አድርገህ ደግሞ “አድልዎ”ን ልታጠፋ አትችልም፤ "አድልዎን አጠፋሁ" ብትል እንኳን ከትችት አታመልጥም። ህዝብ ከክልሉ በፊት አገሩን እንዲያስቀድም ከፈለክ አሁን ያለውን ብሄር ተኮር ፌደራሊዝም መቀየር አለብህ፤ ይህን ሳትቀይር ጠንካራ አገር እገነባለሁ ብለህ የምታልም ከሆነ ህልምህ ህልም ሆኖ ይቀራል… አማራ እና አሮሞው፣ አማራና ሶማሊው፣ አማራና ትግሬው፣ አማራ እና ጋምቤላው ወዘተ በኢትዮጵያ ምድር እንደፈለገ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ፣ ተዝናንቶ እንዲኖር የሚከልለው አጥር ሊኖር አይገባም። የውጭ አገር ድንበር አንሶን በአገራችን የድንበር አጥር እንዲኖር መፍቀድ ማለት በነጻነት ተንቀሳቅሰን የመኖር መብታችንን አሳልፈን ሰጠን ማለት ነው። አንበሳን እንደልቡ ከሚፈነጭበት ጫካ አውጥተህ በጉሮኖ ( zoo) ውስጥ ስላኖርከው መብቱን አከበርክለት ማለት አይደለም፤ ለአንበሳው የሚሻለው አዲሱ የክልል አጥር ሳይሆን መላ ጫካው የራሱ እንደሆነ ተስምቶት እንዲፈነጭበት ስትፈቅድለት ነው...
( ይህ የግል እምነቴ ነው። ሙሉው ጽሁፍ አርብ በሚወጣው የትንሳኤ ሬዲዮ ላይ ይቀርባልና ይከታተሉት

በዜጎች ላይ የሚደርስ እልቂትና መፈናቀል ይቁም፤ ለዘላቂ መፍትሄ እንታገል!!! (አርበኞች ግንቦት 7 )

ሚያዝያ 9 ቀን 2010 ዓም በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተወረወረ ቦንብ እና በጭፍን በተተኮሱ ጥይቶች ሳቢያ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፤ ወደ 70 በሚጠጉ ዜጎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳቶች ደርሰዋል። የከተማዋና አካባቢ ነዋሪዎች በሆኑ የቦረናና የገሪ ብሄረሰብ ተወላጆች መካከል የተከሰተ ግጭትን መነሻ በማድረግ ይህንን ኢሰብዓዊ ድርጊት የፈፀሙት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያስታጠቃቸው ወታደሮች መሆናቸው የከተማው መስተዳደር የሥራ ኃላፊ መግለፃቸው ሁኔታውን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል።
ሁለት ወራት እንኳን ባልሞላው ጊዜ ውስጥ በዚሁ ከተማ የኮማንድ ፓስት አባላት ነን የሚሉ የአገዛዙ ወታደሮች በዜጎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽመው በርካቶች ሕይወታቸው ሲያልፍ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ጎረቤት አገር ኬኒያ መሰደዳቸው ይታወቃል። ወደ ጎረቤት አገር የተሰደዱ ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው አልተመለሱም። ያ ቁስል ሳይሽር ይኸኛው መደገሙ ሁኔታውን እጅግ አሳዛኝ ያደርገዋል።

የኢትዮጵያ ሶማሊ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥታት በምስራቅና በደቡብ የአገራችን ክፍሎች ለሚፈጠሩ ማኅበራዊ ግጭቶች መፍትሄ በመስጠት ፋንታ የችግሩ አካል እየሆኑ መታየታቸው የዜጎች ሰላም እና የሀገር አንድነት አደጋ ላይ መውደቃቸው አመላካች ነው። በእነዚህ ተከታታይ ግጭቶች ሳቢያ ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ቁጥር ለሞት፣ ለአካልና ስነልቦና ጉዳቶች እና ለጅምላ መፈናቀል እየዳረጉ በመሆናቸው ችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሻ ነው።
ይህ የማያባራ የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ውጤት እንደሆነ ንቅናቄዓችን ይገነዘባል።
በሌላ በኩል ደግሞ በጉጂ ዞን በጉጂ እና በጌዲዮ ተወላጆች መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት ለበርካታ ዜጎች ህልፈት፤ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀልና ለበርካታ መንደሮች በእሳት መጋየት ምክንያት ሆኗል። ግጭቱ ከዕለት ዕለት አድማሱን እያሰፋ መሆኑ አርበኞች ግንቦት 7ን ያሳስበዋል። እዚህም የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥቶች ግጭቶችን ማብረድ አልተቻላቸውም። እዚህም የኮማንድ ፓስት አባላት ግጭቱን ሲያባብሱ እንጂ ሲያረግቡ አልታዩም።
ተመሳሳይ ችግሮች በአማራና በትግራይ እና በትግራይና በአፋር ክልላዊ መንግሥቶች መካከልም ይታያል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፈጠረው የመታፈን ስሜት ግጭቶችን እያሰፋ መሆኑ ዘወትር የሚስተዋል ክስተት እየሆነ ነው። ማኅበራዊ ግጭቶች በተለመደው ባህላዊ መንገድ ብቻ መፈታት የማይችሉ፤ መዋቅራዊ መፍትሄ የሚሹ ሀገራዊ አጀንዳዎች ሆነዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 የዜጎች ደህንነት በማናቸውም ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጠው እንደሆነ ያምናል። የመንግሥትን ሥልጣን የያዘው አካልም ከዚህ የሚያስቀድመው ጉዳይ ሊኖር አይገባም ብሎ ያምናል።
ህወሓት/ኢህአዴግ በህገወጥ መንገድ ለሁለተኛ ግዜ በአገራችን ላይ ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፀጥታን በማስፈን ፈንታ የሕዝብን ሰላም እያደፈረሰ መሆኑ አርበኞች ግንቦት 7 ይገነዘባል፤ የኮማንድ ፓስት አባላት በተለያዩ ስፍራዎች ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት የአገዛዙ እድሜ ለማራዘም የሚያደርጉትን ጥረት አጥብቆ ያወግዛል፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዚህ መሠረታዊ ችግር ስር ነቀል መዋቅራዊ መላ እንዲሹለትም ይመክራል።
አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ሳቢያ ሕይወታቸው ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፤ በእነዚህ ግጭቶች ምክንያት ለአካልና ስነልቦናዊ ቀውስ ለተዳረጉ እና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን አጋርነቱን ይገልፃል። በዚህ ወንጀል እጃቸው ያለበት ሁሉ በህግ ፊት እንዲቀርቡና እስከዛሬ በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ላለው ሰቆቃ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያስታውቃል።
በአገራችን ለሚከሰቱ ማኅበራዊ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው ስር ነቀል የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ብቻ እንደሆነ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። በዚህም ምክንያት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ ትኩረቱን የፓለቲካ ሥርዓቱን ለመለወጥ በሚያስችለው ትግል ላይ እንዲያደርግ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Tuesday, April 17, 2018

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል!
(ሚያዚያ 09 ቀን 2010)

የግንቦት ሰባት መስራች አባልና የንቅናቄው ዋና ጸሀፊ በሆነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሚያጠነጥን አጠር ያለ ዝግጅት.... ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው።
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
አገራችን በልጆቿ ነጻ ትወጣለች!

( የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 09 ቀን 2010ዓ.ም. ፕሮግራሞቻችን
************************
የዕለቱ አርዕስተ ዜና
* የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት የህወሓት ታጣቂ ሰራዊት ላይ ከባድ እርምጃ መውሰዳቸውን ዘመቻ ነጻ ትውልድ ዘገበ።
* የህወሓት የዘር ፖለቲካ ቀውስ አሁንም በድጋሚ በጉጅና በጌዲዮ ብሄሮች መካከል መቀስቀሱ ታወቀ።
ቀጣዩ 
በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል!

የተሰኘው መሰናዷችን ትከታተሉት ዘንድ ግብዣችን ነው
www.patriotg7.org ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
አንድነት ሃይል ነው!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

Monday, April 16, 2018

”ቢቢሲ ሃርድ ቶክ” ቆይታ ህወሓት እና “የብሄራዊ ጥቅም” ( አቶ ነዓምን ዘለቀ )

በቅድሚያ ምስጋና፦
ባለፈው ሳምንት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነው የቢቢሲ ሃርድ ቶክ/BBC Hardtalk ጋር ቆይታ ማድረጌ ይታወቃል። የፕሮግራሙ ይዘት ጠንከር ያሉ ሙግቶችን ተሞርኩዞ ምላሽ የሚሰጥበት በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ የሚደፈር አለመሆኑም ይተወቃል። ወደ ኋላ ሔዶ ለማስታወስ ያህል የፕሮግራሙ አዘጋጆች ከወያኔ ቁንጮ ከነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊና የቅንጅት ሊ/መንበር ከነበሩት ኢንጂነር ሐይሉ ሻወል ጋር እንደዚህ አይነት ፖለቲካዊ ሙግት ያደረገው የዛሬ 12 አመት በምርጫ 97 ማግስት ነበር። ከዛ ወዲህ በአገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሚዲያው ቀርቦ ሙግት የገጠመው ኢትዮጵያዊ አላስታወስም።Bilderesultat for neamin zeleke
ይህን በመመልከት ይመስላል የንቅናቄያችን አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች፤ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶት ውስጥ ያላችሁ አመራሮችና አባላት፤ የስርአት ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያንና በርካታ ምሁራ ስሜታችሁን ገልጻችሁልኛል። በአካል፣ በስልክ በማህበራዊ ድረ-ገጽና አስተያየቶች ደርሰውኛል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚሰጡ ድረ-ገጾች እንዲሁም እንደ ኢሳት ያሉ የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት “የቢቢሲ ሃርድ ቶክ” ፕሮግራሙን ተመስርተው ውይይትም በማድርግ በተለያየ ምልከታዎችን እንዳይ ስላደረጋችሁኝ በድጋሚ ለድረ-ገጾቹም ሆነ ለሚዲያ ተቋማቱ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለሰጣችሁኝ አበረታች ግብረ-መልስ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ከወዲሁ ማቅረብ እወዳለሁ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አክብሮታችሁን የላካችሁልኝ የንቅናቄያችን አባላትም ሆነ የተቀራችሁ ኢትዮጵያውያን አንድ ነገር አስምሬ ልነግራችሁ የምፈልገው ጉዳይ አለኝ። ኣኔ ብዙሃን ወደማይደፍሩት የቢቢሲ ሞጋች ፕሮግራም ላይ ለመቅረብ ፍቃደኛ የሆንኩት ዋነኛ ምክንያት በመኖሩ ነው። ይኸውም አመራር የሆንኩት አርበኞች ግንቦት ሰባት ነድፎ የሚታገልባቸው የማታገያ ነጥቦች መዳረሻ ግልጽ ስለሆኑ ነው። ለሁሉም ግልጽ ኣንደሆነው ንቅናቄያችን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ አንድነት፣ እንዲሁም ብሄራዊ ጥቅም ለድርድር የሚያቀርብ አይደለም። 

ESAT Tikuret - Yikulkulet Zemen የቁልቁለት ዘመን by Tamagne Beyene (Ethiopia)

አለማቀፍ የኢሳት ክብረ በአል በስዊድን! ESAT Sweden 2018

ኢትዮጵያዊነት ማለት አንዱዓለም ተፈራ (እስከመቼ)

“ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።”
አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም የሚለውን ጥያቄ አይደለም። በየቦታው፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ በየዕለቱ በሕዝቡ ላይ የሚደረገውን በደል እናውጠነጥናለን። ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይንም አይደሉም የሚለው ከጥያቄያችን መካከል አይደለም። መቼም አርባ ዓመት ሙሉ፤ በአረመኔው መንግሥቱ ኃይለማርያምና በወገንተኛው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል ገና ብዙ ፀሐፊዎች ብዙ ይውሉበታል፣ ሊቃውንት ይቀኙበታል፣ አንጎርጓሪዎች ይደረድሩበታል፣ ሰዓሊዎች ያቀልሙታል፣ ገጣሚዎች ይሰነኙበታል፣ መጽሐፎች ይደረሱበታል። ያ ግን፤ ከኛ ቀጥለው የሚመጡት ኢትዮጵያዊያን፤ ስለኛ ስለቀደምናቸው ኢትዮጵያዊያን ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ውጤት ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናችን ወይም ኢትዮጵያዊ ስላለመሆናችን አይደለም።
እንግዲህ የአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? የሚለውን በደንብ መረዳት አለብን። ይኼን ስናደርግ፤ የሀገራችንን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሀቅ በትክክል እንረዳና፤ በኢትዮጵያዊነታችን፤ ምን ማድረግ እንዳለብንና ማን ኢትዮጵያዊነቷን እየተወጣች እንደሆነች እንገነዘባለን። ትናንትም፣ ዛሬም ነገም ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ሀገርን ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ወራሪ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ፤ ይህ ግዴታ፤ ወደ መኖር ወይንም አለመኖር የሕይወት ትንቅንቅ ስለሚያመራ፤ አማራጭ የማይሠጥ ጥሪ ይሆናል። ይህ ፖለቲከኛ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ታጋይ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ሀገራዊ ግዴታን ነው የሚገልጸው። ይህ የኢትዮጵያዊ ሕይወት፣ የትናንት፣ የዛሬና የነገ ሕልውና ጥያቄ ነው። አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ኢትዮጵያዊ መንግሥት የለም። ሕግና ሥርዓት የሚያከብር ቡድን አይደልም በሥልጣን ላይ ያለው። ራሱ የሚያወጣቸውን ሕጎች የሚያፈርስ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳ ክፍል ነው በሥልጣን ላይ የተቀመጠው። ኢትዮጵያዊያንን እየከፋፈለ፣ አንድነት እንዳይኖረን የሚጥር መንግሥት በሥልጣን ላይ አለ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ፤ “ኢትዮጵያዊ ነኝ። አልከፋፈልም። ጠላታችን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ነው።” እያለ ትግል ይዟል። ስለዚህ፤ የአሁኗ ኢትዮጵያዊትና የአሁኑ ኢትዮጵያዊ፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን፤ ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያዊያን መንግሥት ከታጋዩ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ማስወገድ ነው። ሕዝባዊ ንቅናቄ ከፊታችን ተደግኗል። የውዴታ ሳይሆን ግድ ሆኖብን፤ የምርጫ ሳይሆን አማራጭ ሳይኖረን ንቅናቄው አፍጥጦብናል። የዴሞክራሲ ቅንጦት ሳይሆን የሀገር አድን ጥያቄ ቀርቧል።
ባጭሩ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ወራሪ መንግሥት ማወገድ ነው። ይኼን የኔ ብሎ ያልተነሳ ግለሰብ፤ ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው? በርግጥ ትግሉ ረጅም ነው። ትግሉ የተመሰቃቀለ ነው። በሥልጣን ላይ ተቀምጦ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍናውና መመሪያው የሆነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቻ ሳይሆን፤ ይኼኑ ፍልስፍናና መመሪያ የራሳቸው ያደረጉ ሌሎች ክፍሎችም የኢትዮጵያዊነት ትግላችን አንድ ክፍል ናቸው። በትግሉ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ይኼን ሀቅ አጥብቀን መያዝ አለብን። ኢትዮጵያ ለዘመናት መንግሥት ኖሯት ስትተዳደር የነበረች ሀገር ለመሆኗ አጥጋቢ መረጃዎች አሉ። እኒህ መንግሥታት በየተከሰቱበት የታሪክ ወቅት፤ በጎም ሆነ በጎነት የጎደለው ተግባር አከናውነው አልፈዋል። በዚህ ረጅም ታሪካችን፤ የመንግሥታዊ ማዕከላቸውን በሰሜን ወይንም በደቡብ፤ በምሥራቅ ወይንም በምዕራብ እንደታሪካዊ ወቅቱም ተንቀሳቃሽ በማድረግ፣ የተለያዩ የጦር አሠላለፍን በማዘጋጀት፣ ጥንካሬያቸው እንደፈቀደላቸው፤ የሀገሪቱንም ደንበር ሲያሠፉና ስትጠብባቸው ነበር። አንዱ ከሌላው ጎጥ፤ ሃይማኖት ሳያግደው፣ የዘር ሐረግ ሳይከለክለው፣ እንደ ጥንካሬያቸውና የፖለቲካ ግኘታ አመቺነታቸው ሲጋቡና ሲዋለዱ ነበር። በኢትዮጵያዊነት ገዝተዋል። እናም በተለያዩ ጊዜያት፤ በተለያዩ መንግሥታት ዘመን፤ የተለያዩ ህዝባዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ሕዝባዊ አመፆች ተካሂደዋል። መፈንቅለ መንግሥት ተደርገዋል። በንጉሥ ላይ ንጉሥ ተነስቷል። ንግሥታት ዘውድ ጭነው ገዝተዋል።

Yekulkulet Zemen የቁልቁለት ዘመን Part 1of 4

Sunday, April 15, 2018

ሀገር ማለት የኔ ልጅ - (በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)


ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣
እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣
የተወለድሽበት አፈር፤
እትብትሽ የተቀበረበት ፣ ቀድመሽ የተነፈሽው
አየር፤
ብቻ እንዳይመስልሽ።
ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
አገር ውስብስብ ነው ውሉ።
ሀገር ማለት ልጄ ፣
ሀገር ማለት ምስል ነው ፣በህሊና የምታኖሪው፤
ከማማ ማህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ ፤
በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ ፣
በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤
በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣
በተሻገርሽው ዥረት ፤
በተሳልሽበት ታቦት ፣ወይ በተማፀንሽው ከራማ ፤
በእውቀትሽና በህይወትሽ፣
በእውነትሽና በስሜትሽ ፣
የምትቀበይው ምስል ነው ፣ በህሊናሽ
የምታኖሪው፤
ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፡፡
ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።
ሀገር ማለት የኔ ልጅ ፣
ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤
በጆሮ አያዳምጡት፤
አማርኛ ኦሮሞኛ ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤
ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት ።
የኔ ልጅ፣
አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው ፣
ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤
ያለገባው እንዳይመስልሽ ፣ ሀዘን ደስታሽን
ያልተጋራ።
የየልቦናችንን ሀቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤
ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ፡፡
ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤
ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ፣ ሲደላሽ ትኳኳየዪበት ።
የኔ ልጅ ፣
አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ
አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣
ሲያቀና ወረቱን፤
ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን፤
ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤
ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ . . .
ከሁሉም የጦቢያ ልጆች ፣
አጥንቱን እየማገረ፤
ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣
ሲያቆይልሽ፤
በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣
ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ!
እና የእኔ ልጅ፣
ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ
የሚያስፈልግሽ፤
ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤
ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ፣ ለተወጠነው
እድገትሽ።
እና ልብ በይ ልጄ ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣
ባንደበት አይናገሩት፤
በጆሮ አያዳምጡት።
ከሁሉም በላይ ልጄ ፣
ተፈጥሮ ከቸረው በረከት ፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤
ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ።
ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤
የሰብዕናሽ ግማሽ ውል ፣ወገን ነው ማሕተምሽ፡፡
ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ።
መሬትማ የእኔ ልጅ፣
በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤
ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ ፣ለተስፋሽ
ካልተመገብሽው፤
መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤
ለተስማማው የሚስማማ።
ዥረቱም ግድ የለውም ፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል
ተራራውም ደንቆሮ ነው ፣ ለቦረቦረው ይበሳል።
መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው
ሃገርሽ፤
ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ
አፈር ሚያለብስሽ።
በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤
ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ።
እና የኔ ልጅ፣
ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።

ESAT Tamagn beyene yekulkulet zemen

ESAT DC Daily News Sat 14 Apr 2018

Saturday, April 14, 2018

የለውጥ እንቅስቃሴን ለማራመድ ለሀገር አቀፍ ሕዝባዊ እምቢኝነት ዝግጁ እንሁን (የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕሰ አንቀጽ)

የዶ/ር አብይ አህመድ በጠ/ሚኒስትርነት መሾም በሕዝባዊ ትግሉ ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በርካታ ወገኖች ጥያቄ አቅርበዋል።

በንቅናቄዓችን ሰነዶች ላይ በግልጽ እንደሰፈረው የአርበኞች ግንቦት 7 ራዕይ “እያንዳንዱ  ኢትዮጵያዊ  ዴሞክራሲያዊና  ሰብዓዊ  መብቱ  የተከበረበት፤  የኢኮኖሚ ብልፅግናና  ማኅበራዊ  ፍትህ  የሚገኝበት፤  የዜጎች  ሕይወት፣  ደህንነትና  ጥቅም  የተከበረበት  እና  የሕዝቧ  አንድነትና  ትስስር የጠነከረበት ሃገር ኖሮት ማየት ነው።”
የአርበኞች ግንቦት 7 ተልዕኮ ደግሞ “የመንግሥትና  የፖለቲካ  ሥልጣን  በሰላማዊና  ዴሞክራሲያዊ  ሂደት  የሚያዝበት፤ የሃገሪቱ  ዜጎች  ምርጫ  በተግባር  የሚገለፅበት፤  ማኅበራዊና  የፖለቲካ  ችግሮች  በዲሞክራሲያዊ  መንገድ  የሚፈቱበት  እና ዲሞክራሲያዊ ባህል የሚበለፅግበት ብሄራዊ የፖለቲካዊ ሥርዓት እንዲገነባ ማገዝ ነው።”
የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ከንቅናቄዓችን ራዕይና ተልዕኮ የተለየ አይደለም። አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገሩ ባለቤት መሆን ይፈልጋል፤ መሪዎቹን በነፃነት መምረጥና መሻር እና በአገራችን ማኅበራዊ ፍትህ ሰፍኖ ማየት ይሻል።
ዶ/ር አብይ አህመድ ይህን የሕዝብ ፍላጎት ማሳካት የሚችሉ መሪ ናቸውን?

የለውጥ እንቅስቃሴን ለማራመድ ለሃገር አቀፍ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዝግጁ እንሁን

የዶክተር አቢይ ነጥብ መጣል! (ኤርሚያስ ለገሰ)

#ነጥብ አንድ : " የወርቅ ፍልቃቂ!"
ዶክተር አቢይ በመቀሌ ጉዞውና ከተመረጡ የህውሓት አባላት ጋር ባደረገው ምክክር በርካታ ነጥቦች ጥሏል። አንዳንዶቹ በጣም የሚያስደነግጡ ናቸው። ለምሳሌ የአቶ መለስ ዜናዊን የሙት መንፈስ የወረሰ በሚመስል ሁኔታ " የትግራይ ሕዝብ በእሳት የተፈተነ ወርቅ ነው!" በማለት ሲናገር የተሰብሳቢው ጭብጨባ አስደማሚ ነበር። መቼም ይሄ ከናዚዝም የሚቀዳ አነጋገር አቶ መለስን ምን ያህል ራቁቱን እንዳሳየው ዶክተር አቢይ ያጣው አይመስለኝም።
ዶክተር አቢይ አንድን ብሔረሰብ አግንኖ ለማውጣት ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚካሄድ ጥረት ሁሉ ከፍተኛ አደጋ ሊያመጣ እንደሚችል የሚያጣው አይመስለኝም። አንደዚህ አይነት አባባል በሌሎች ላይ ጥላቻ ያሳድራል። የወርቅ ፍልቃቂ የተባለው ጐሳ የገዥነት፣ ከሕግ በላይ የመሆን መንፈስ እንደሚፈጥርበት ሳይታለም የተፈታ ነው። በሂደትም ወደ ነሀስና ብር ብሎም ወደ ጨርቅ የወረደው ሀይል ወደ አመፅ በመሄድ የጥቃት ሰለባ ሊያደርጋቸው ይችላል።
እንደ አንድ ሞጋች ደጋፊው ዶክተር አቢይ ከአቶ መለስ በፍፁም መውረስ የለበትም ብዬ ከምመኘው የመጀመሪያው ነገር " የወርቅ፣ ነሀስ፣ብርና ጨርቅ ብሔር" ጽንሰ አሳብ ነበር። ይሄ ጽንሰ አሳባ አደገኛ ከመሆኑም ባሻገር የንቀት፣ ጥላቻ፣ የብዝበዛና የጭቆናና ኢፍትሐዊነት ይፈጥራል። በዚህ አደገኛ አባባሉ ዶክተር አቢይ ሊያፍር ይገባል። ከእንደዚህ አይነት ከፋፋይና አስቀያሚ ንግግር ራሱን ማቀብ ይኖርበታል። የኢትዬጲያን ሕዝብ በወርቅና ጨርቅ በመከፋፈል ለአንዱ ኩራት ለሌላው ውርደት የፈጠረውን፣ አደህይቶ የገዛውን፣ አገርን ታሪክ አልባ ያደረገውን፣ አሰቃይቶ መግዛት ፓሊሲው ያደረገውን መለስ ዜናዊ በአንደበቱ ማሞካሸት ያሳፍራል። ያሳቅቃል።
#ነጥብ ሁለት: " ማይ መቐለ!"
ዶክተር አቢይ አህመድ በዛሬው የመቀሌ ንግግሩ፣
" የመቀሌን ውሃ በተመለከተ ምንም የማውቀው ነገር የለም። የመቀሌ ውሃ መቼ ተጀመረ፣ የት ደረሰ ሚስጥሩን አላውቀውም። የትግራይ ህዝብ እንዲያውቅ የምፈልገው አንድ ጉዳይ ቢኖር የመቀሌም፣ የአክሱምም፣ በሙሉ በትግራይ ያለ የመጠጥ ውሃ ጉዳይ የፌዴራል መንግስትን አይመለከትም። መቶ ፐርሰንት የክልል ስራ ነው" ነበር ያለው።
ይሄንን የዶክተር አቢይ ምላሽ ስሰማ በጣም ደንግጫለሁ። ዶክተሩ ተረጋግተው መቀመጥ ባለመቻላቸው አጠገባቸው ምን እየተሰራ እንደሆነ ማወቅ አለመቻላቸውን አመላክቶኛል። "በሙሉ በትግራይ ያለ የመጠጥ ውሃ ጉዳይ የፌዴራል መንግስትን አይመለከትም፣ መቶ ፐርሰንት የክልሉ መንግስት ነው" ማለታቸው ከመረጃ እጥረት የመነጨ ወይንስ ሽምጥጥ አድርጐ መካድ ይሆን የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል። እንደ ሞጋች ደጋፊነቴ ላምናቸው ስለምፈልግ ዶክተሩ ተረጋግቶ ባለመቀመጥ ምክንያት የመረጃ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብዬ ማመን እፈልጋለሁ።
እናም ለዶክተሩ መረጃውን ልሙላላቸው።
#የህውሓት ንብረት የሆነው ሬዲዬ ፋና ከትላንት ወዲያ እንደዘገበው የፌዴራል መንግስቱ የመቀሌን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በሁለት እጥፍ ለማሳደግ 8ቢሊዬን ብር ከቻይና መንግስት ተበድሮ የግድብ ግንባታ ጀምሯል። በዘገባው መሰረት " የሰሜኗ ኮከብ መቐለ!" በየቀኑ የሚያስፈልጋት የውሃ መጠን 50ሺህ ሜትር ኪዩብ ነው። በአሁን ሰአት እየቀረበላት ያለው ደግሞ 25ሺህ ሜትር ኪዩብ ( 50 በመቶ) ያህል ነው።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት በራሱ በጀት 18ሺህ ሜትር ኪዩብ የሚያስገኝ ግድብ አጠናቋል። ከላይ ከተጠቀሰው ጋር ስንደምረው " የሰሜኗ ኮከብ!" የቀን አቅርቦቷ 43ሺህ ሜትር ኪዩብ ይሆናል። መሰረታዊ የሂሳብ ስሌቶችን ተጠቅሞ መደመርና መቀነስ ለሰራ ( አባዱላን አይመለከትም) መቐለ የቀን ፍላጐቷን ለማሟላት የሚቀራት 7ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ብቻ ነው።
አሁን ወደ ፌዴራሉ የቻይና ብድር እንመለስ። የፌዴራል መንግስቱ ከቻይና ተበድሮ ( ወለዱ ስንት እንደሆነ አልተገለጠም) ለመቐሌ በሚሰጠው 8ቢሊዬን ብር ተጨማሪ በየቀኑ 147ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ውሃ አቅርቦት ይኖራል። አሁንም መደመርና መቀነስ ሲሰራ በአጠቃላይ በመቀሌ በቀን የሚመነጨው የመጠጥ ውሃ መጠን ከፍላጐቱ በ140ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ብልጫ ይኖረዋል።
እንግዲህ ፍርዱን ለዶክተር አቢይና አንባቢያን እተዋለው። ፌዴራል መንግስቱ በመቶ ሚሊዬን የኢትዬጲያ ህዝብ ስም 8 ቢሊዬን ብር ተበድሮ ( ያውም የወለድ መጠኗ እስከ 35% የምታደርሰው ቻይና) ለመቐሌ እየሰጠ እውቀት የለኝም ማለት ምን ማለት ነው? በፓርቲ ሚዲያ ለአለም ህዝብ የተገለጠ መረጃ አለማንበብ ማለት ምን ማለት ነው? ፌዴራል መንግስቱ ያን ያህል ገንዘብ ተበድሮ ሲያበቃ " ክልሉ እንጂ ፌዴራል አያገባውም!" ብሎ መናገር አያሸማቅቅም ወይ? ሐይለማርያም ደሳለኝ ( የቀድሞ ተጠቅላይ በሉኝ ብሏል!) በአንድ ወቅት መረጃዎች አይደርሱኝም ብሎ ከተናገረው በምን ይለያል?
#ተጨማሪ ነጥቦች
የንፁህ መጠጥ ውሃን በተመለከተ የቀረምኳቸውን አንዳንድ መረጃዎች ለዶክተር አቢይ ላካፍለውና የመጀመሪያ ክፍል ፅሁፌን ላጠናቅ። ተጨማሪ መረጃዎች ካሉ እባካችሁ አንባቢያን ጨምሩለት።
#አንደኛ: -የከተሞችን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ብድር የተገኘው በፈረንጆቹ አቆጣጠር Nov 2011 ከቻይና መንግስት ነው። የብድሩ መጠን 100 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን የብድሩ ተጠቃሚ አዲስ አበባ ነበረች። ሁለተኛው ብድር የተገኘው May 2012 ከአለም ባንክ ሲሆን የብድሩ መጠን 150 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር ነው። የብድሩ ተጠቃሚ የሆኑ ከተሞች አዲሳአባ፣ ጐንደር፣ ሐዋሳ፣ መቐሌ፣ ጅማ፣ ድሬደዋ ነበሩ። የከተሞች የህዝብ ብዛት በቅደም ተከተል አዲሳአባ፣ አዳማ፣ ጐንደር፣ መቀሌ፣ ሐዋሳ መሆኑን ማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን ያሳውቃል።
#ሁለተኛ :- በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በውሃ ጉዳዬች ላይ ጥናት በሚያደርግ water.org ጥናት መሰረት 61 ሚሊዬን የሚጠጋው የኢትዬጲያ ሕዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ አያገኝም።
#የመፍትሔ ሐሳብ
ሞጋች ደጋፊ ስህተቶቹን ብቻ ነቅሶ የሚያወጣ ሳይሆን የመፍትሔ ሃሳቦችንም ይጠቁማል። በዚህ መሰረት ዶክተር አቢይ በተሰጠው ስልጣን ማእቀፍ ውስጥ ሆኖ የሚከተለውን እንዲያደርግ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል።
#1: የፌዴራል መንግስት ፕሮጀክት ድልድል በህዝብ ብዛትና በቆዳ ስፋት ከሆነ በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይሆናል ያለውን አቶ አባይ ፀሀዬ ከመንግስታዊ ስልጣኑ በአስቸኳይ ማባረር።
#2: የህውሓት ስራ አስፈፃሚና የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትር የሆነውን ዶክተር አብርሃም ተከስተ መጥራት። ለከተሞች ፌዴራል መንግስት ባለፋት 5 አመታት ለመጠጥ ውሃ የተወሰዱ ብድሮችን ለኢትዬጲያ ሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ማድረግ። በፓርላማም ቀርቦ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ማድረግ። 
…//…