Wednesday, April 18, 2018

አሁን ባለው የፌደራሊዝም ስርዓት አንድ ጠንካራ ኢትዮጵያን መገንባት አይቻል ( ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም)

 ላለፉት 26 ዓመታት ክልል ከአገር በላይ ሆኖ እንዲታይ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲካሄድ በመቆየቱ፣ ቀላል የማይባል የአዲሱ ትውልድ አባላትና “ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ” ሲሉ የነበሩ ከእኔ በፊት የነበሩና የእኔ ትውልድ ሰዎች ሳይቀሩ “ከአገሬ በፊት ክልሌ” እያሉ ሲዘምሩ እየሰማን ነው። ከወያኔ በፊት የነበሩ ትውልዶች “ክልሌን ላስቀድም ወይስ አገሬን?” በሚል ምርጫ ከራሳቸው ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡበት ሁኔታ አልነበረም፤ እያንዳንዱ ዜጋ ታማኝነቱ ሁሉ፣ አንድና አንድ፣ ለአገሩ ነበር። በጊዜው የነበረው በክፍለሃገር ደረጃ የተዋቀረው አስተዳደር የተለያዩ ብሄረሰቦችን አቅፎ የያዘ በመሆኑ፣ በአንድ ክፍለሃገር ስር ይኖር የነበረ የአንድ ብሄረሰብ ተወላጅ “ከአገሬ ክፍለሃገሬ” የሚልበት ሁኔታ አልነበረም። ዛሬ ክልል የሚባለው አጥር ከብሄር ማንነት ጋር በእጅጉ ተቆራኝቷል። “ክልል ይፍረስ” ብትል “ብሄርህ ይጥፋ” እንዳልክ ተቆጥሮ ጦር ይሰበቅብሃል። ክልልን የብሄር ማንነት መገለጫ አድርገህ ደግሞ “አድልዎ”ን ልታጠፋ አትችልም፤ "አድልዎን አጠፋሁ" ብትል እንኳን ከትችት አታመልጥም። ህዝብ ከክልሉ በፊት አገሩን እንዲያስቀድም ከፈለክ አሁን ያለውን ብሄር ተኮር ፌደራሊዝም መቀየር አለብህ፤ ይህን ሳትቀይር ጠንካራ አገር እገነባለሁ ብለህ የምታልም ከሆነ ህልምህ ህልም ሆኖ ይቀራል… አማራ እና አሮሞው፣ አማራና ሶማሊው፣ አማራና ትግሬው፣ አማራ እና ጋምቤላው ወዘተ በኢትዮጵያ ምድር እንደፈለገ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ፣ ተዝናንቶ እንዲኖር የሚከልለው አጥር ሊኖር አይገባም። የውጭ አገር ድንበር አንሶን በአገራችን የድንበር አጥር እንዲኖር መፍቀድ ማለት በነጻነት ተንቀሳቅሰን የመኖር መብታችንን አሳልፈን ሰጠን ማለት ነው። አንበሳን እንደልቡ ከሚፈነጭበት ጫካ አውጥተህ በጉሮኖ ( zoo) ውስጥ ስላኖርከው መብቱን አከበርክለት ማለት አይደለም፤ ለአንበሳው የሚሻለው አዲሱ የክልል አጥር ሳይሆን መላ ጫካው የራሱ እንደሆነ ተስምቶት እንዲፈነጭበት ስትፈቅድለት ነው...
( ይህ የግል እምነቴ ነው። ሙሉው ጽሁፍ አርብ በሚወጣው የትንሳኤ ሬዲዮ ላይ ይቀርባልና ይከታተሉት

No comments:

Post a Comment