Saturday, October 31, 2015

አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር)

ብራቱን አጥፍቼዉ አልጋዬ ላይ የወጣሁት በግዜ ነዉ። አለወትሮዬ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ አልዞር ብሎኝ ከጨለማዉ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠናል። የነፋስ ሸዉታ እንኳን የማይሰማበት ደረቅ ሌሊት ነዉ። ጨላማዉ አይን ይበሳል። እቤቱ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ ሁሉ ተኝቷል። ቀኑን በሠላም ላዋለኝ አምላክ ምስጋና ሰጥቼ ሌሊቱንም አደራ ብዬዉ ፀሎቴን ጨረስኩ። ያ ምቀኛ እንቅልፍ ግን አሁንም እንደከዳኝ ነዉ። ትንሿ አልጋዬ ላይ ግራ ቀኝ እያልኩ ተገለባበጥኩ። እንቅልፍ ተጎትቶ የሚመጣ ይመስል አሁንም አሁንም ላይ ታች እያልኩ አልጋዉ ላይ እራሴን ጎተትኩት . . . እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ጭራሽ አይኖቼ መርገብገባቸዉን ያቆሙ ይመስል ቀጥ ብለዉ ቀሩ። ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ መብራቱን አበራሁና ለመንገድ ከያዝኳቸዉ ሁለት መጻህፍት አንዱን አዉጥቼ ማንበብ ጀመርኩ። እኔ ላንብበዉ ወይ መጽሀፉ ያንብበኝ አላዉቅም። ጧት ስነሳ ግን “The Architecture of Democracy” የሚል መጽሐፍ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ነበር። ሰዐቴን ሳየዉ ከሌሊቱ ስምንት ሰዐት ተኩል ይላል። ከአልጋዬ ላይ ዘልዬ ወረድኩና ሰዉነቴን ታጥቤ ልብሴን ከለበስኩ በኋላ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ “I’m ready” አልኩ። የመኪናችን መብራት ጨለማዉን እየገላለጠዉ የአስመራ ከረንን መንገድ ተያያዝነዉ። መኪናዉ ዉስጥ ከገባሁ በኋላ እንደገና አፌን የከፈትኩት ባሬንቱ ደርሰን ቁ

ሌ/ኮ መንግስቱ ኃይለማሪያም በ‹‹ኑዛዜያቸው›› በርካቶችን ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ አደረጉ -

 ‹‹ስለ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ መናገር ቀርቶ ስሙንም ማንሳት በጣም ያሳፍረኛል›› • ‹‹ጀኔራል መርዕድ ንጉሴ የውጊያ መሰናዶዎቼን ለጠላት አሳልገው ሰጥተዋል • የሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት ፈላሻዎችን በህገ ወጥ መንገድ ሲያስተላልፍ ነበር • ፕሮፌሰር መስፍንና ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ተጠያቂ ከተደረጉት ታላላቅ ሰዎች መካከል ናቸው • እነ ፍስሃ ደስታ፣ እነ ኮሎኔል ተስፋዬ፣ እነ ጀኔራል ስዩም ሊያስገድሏቸው እንደነበር አውስተዋል     ኢትዮ-ምህዳር ጥቅምት 20/2008 (አ.አ)፡- የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ‹‹ኑዛዜ›› ብለው ለህዝብ እንዲደርስላቸው በካሴት ካሰራጩት ድምፅ ተዘጋጅቶ ለንባብ በበቃ ‹‹ከኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም አንደበት›› የተሰኘ መፅሃፍ በርካታ ምሁራንንና የቀድሞ ባልደረቦቻውን በኢትዮጵያ ላይ በማሴርና ለውድቀቱም ተጠያቂ ናቸው ማለታቸውን አስነብቧል፡፡ ኮ/ል መንግስቱ አብዛኛውን ይሸረብባቸው የነበረውን ሴራ የተረዱት ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ እንደሆነ በቁጭት ተናግረዋል፡፡ በተለይ በመፈንቅለ መንግስቱ ወቅት የተገደሉት ጀኔራሎች ለውድቀቱ ዋነኛዎቹ ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡ ከጀኔራሎቹ መካከል እነ መርዕድ ንጉሴ፣ ፋንታ በላይ በስፋት የተጠቀሱ ሲሆን የጀኔራል መርዕድ ንጉሴ ሁለተኛዋ ሚስት ለሻዕቢያ ትሰራ እንደነበር ተግልፆአል፡፡ በተጨማሪም ጀነራል መርዕድ ንጉሴ የውጊያ ስትራቴጅ መሰናዶዎችን ለጠላት አሰልፎ ሰጥቷል ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋቸዋል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) የህወሓት አገዛዝ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትን እየለቀመ ከመከላከያ ኃይሉ እያባረራቸው መሆኑ ታወቀ፡፡



ህወሓት በ1983 ዓ.ም መላ አገሪቱን በነፍጥ እንደተቆጣጠረ በሁለት ያለፉ የኢትዮጵያ መንግስታት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት፣ ዕውቀትና ጉልበት ፈሶበት ለዘመናት በስንት ልፋትና ጥረት የተገነባውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ባደረበት ጭፍን ጥላቻና ቂም ብቻ ተመስርቶ "የደርግ ነው" በሚል ሰበብ ባንድ ጀምበር ንዶ ማፈራረሱን አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ 
ከበረሃ የመጡ ድኩማን ታጋዮቹን ለሙያው የሚመጥን ምንም አይነት ዘመናዊ ዕውቀት ሳይኖራቸው የጀነራልነት ማዕረግ በማሸከም በአየር ኃይሉና በምድር ኃይሉ ውስጥ በሚገኙ የአዛዥነት ቦታዎች ላይ እነሱን ብቻ አስቀምጦ ስልጣኑን ለመጠበቅ ብቻ እንዲተጉለት በማድረግ የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል፡፡
ህወሓት የተባለው ዘረኛ ቡድን ውስጡ በቂምና በጥላቻ ብቻ ተሞልቶ ያፈራረሰውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አደጋ ባንዣበበበት ጊዜ ጥሪ በማድረግ መልሶ ለመሰብሰብ የሞከረ ሲሆን ከጦርነቱ በኋላ ደግሞ አብዛኞቹን ከተጠቀመባቸው በኋላ እንደገና አባሯቸዋል፡፡ 
አሁን ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እያፋፋመው ከሚገኘው የአርበኝነት ትግል ጋር በተያያዘ ከትግራይ ተወላጅ የህወሓት ተጋዮች ውጭ በሆኑ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ዕምነት በማጣቱ የመከላከያ ኃይሉን የማጥራት የወቅቱ አንገብጋቢ ውሳኔውን የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በማባረር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል፡፡
ቂምና በቀሉ መቸም የማይበርድለት ህወሓት በተደጋጋሚ የደም ቁማር ሲቆምርባቸው ከኖሩት የተባረሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አብዛኞቹ የአርበኝነት ትግሉን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡

Friday, October 30, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ




በአርባ ምንጭ ከተማ አፈሳው እና እስሩ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፤ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት በርካታ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ /ማዕከላዊ እስር ቤት/ ተወስደዋል፡፡
====================================================
የህወሓት ጆሮ ጠቢዎች ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ ፎቶግራፎች በማህበራዊ ሚዲያዎች በመሰራጨታቸው እና ወንጀላቸው ለህዝብ በመጋለጡ ምክንያት በአርባ ምንጭ ከተማ ዕረቡ ለሐሙስ አጥቢያ ከእኩለ ሌሊት በኋላ የተጀመረው ወጣቶችን በገፍ እያፈሱ የማሰሩ የህወሓት ደህንነቶች እና ፌደራል ፖሊሶች ተግባር አሁንም ተባብሶ በሰፊው ቀጥሏል፡፡ 
የአርባ ምንጭ ህዝብ እያፋፋመው ከሚገኘው የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ባሻገር ዕልፍ አዕላፍ ወጣት ልጆቹ በረሃ በመውረድ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅለው በታላቅ የአርበኝነት ተጋድሎ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዕለት ከዕለትም ከከተማዋ ወደ በረሃ የሚወጣና ህወሓትን ለመውጋት ነፍጥ የሚያነሳ ወጣት ቁጥሩ በእጅጉ እየናረ መጥቷል፡፡ 
በመሆኑም የህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ኃይሎች አርባ ምንጭ ውስጥ በህዝቡ መካከል ተሰግስገው የሚያደርጉት ጭንቅ ጥብብ ቢላቸው ወደ በረሃ የወጡ አርበኞችን ወላጆች፣ ወንድሞች እና እህቶች እየያዙ ማሰር ጀምረዋል፡፡
ከሐሙስ ዕለት አንስቶ ደግሞ ምስላቸው በኢንተርኔት ለህዝብ ተሰራጭቶ በህዝብ እና በአገር ላያ የፈፀሙት ክህደትና ግፍ የተጋለጠባቸው የህወሓት ጆሮ ጠቢዎች ብስጭታቸው ንሮ አፈናውንና እስሩን አበርትተውታል፡፡ ከዕረቡ ሌሊት ጀምሮ በወቁጥጥር ስር የዋሉት በርካታ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ /ማዕከላዊ እስር ቤት/ ተግዘዋል፡፡
በህወሓት ዘረኛ ቡድን ደህንነቶችና ፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ወደ አዲስ አበባ /ማዕከላዊ/ ከተወሰዱት በርካታ የአርባ ምንጭ ወጣቶች መካከል
• ሉሉ መሰለ /የሰማያዊ ፓርቲ አባል/
• ዓለም ክንፉ /የሰማያዊ ፓርቲ አባል/

Thursday, October 29, 2015

Shambel Belayneh Hizbu Minyelal ethiopia

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
====================================================
በትናንትናው ዕለት ረፋድ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር "የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!" የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን "አልሄድም" ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች፡፡ 
በእነ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ ትዕዛዝ በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እየታፈኑ ወደ ልዩ እስር ቤት እየተወሰዱ ነው፡፡
አቶ አበበ አስፋው፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ ካሳ እና ልጃቸው አየለች አበበ ዛሬ ጠዋት በደህንነቶች እና በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ወደ ወህኒ ተወስደዋል፡፡ በተጨማሪም ደረጀ የተባለ ወጣት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ሉሉ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አባልም በቁጥጥር ስር ውሎ በአሁኑ ሰዓት መኖሪያ ቤቱ በህወሓት ደህንነቶች እና ፌደራል ፖሊሶች በጥብቅ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡
ባጠቃላይ በአሁኗ ሰዓት በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ መሆኑን ከቦታው እየደረሱን የሚገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

.

ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡ ====================================================

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ 
በትናንትናው ዕለት ረፋድ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር "የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!" የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን "አልሄድም" ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች፡፡ 
በእነ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ ትዕዛዝ በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እየታፈኑ ወደ ልዩ እስር ቤት እየተወሰዱ ነው፡፡
አቶ አበበ አስፋው፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ ካሳ እና ልጃቸው አየለች አበበ ዛሬ ጠዋት በደህንነቶች እና በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ወደ ወህኒ ተወስደዋል፡፡ በተጨማሪም ደረጀ የተባለ ወጣት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ሉሉ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አባልም በቁጥጥር ስር ውሎ በአሁኑ ሰዓት መኖሪያ ቤቱ በህወሓት ደህንነቶች እና ፌደራል ፖሊሶች በጥብቅ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡
ባጠቃላይ በአሁኗ ሰዓት በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ መሆኑን ከቦታው እየደረሱን የሚገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ


‪#‎የአርባ‬ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው፡፡
‪#‎ጋምቤላ‬ ጎግ ወረዳ ውስጥ የሞርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰንዝረው አንድ የጦር ሰፈር ደመሰሱ፡፡
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በመላ አገሪቱ ሲያካሄደው በቆየው ስብሰባ ላይ ባልተሳተፉ መምህራን እና ሌሎች ሰራተኞች ላይ የ176 ብር ቅጣት በየነ፡፡
‪#‎በጅንካ‬ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅ ተነስቷል፡፡
‪#‎በኮንሶ‬፣ ቦረና፣ ተልተሌ፣ በና፣ ፀማይ፣ እና ሐመር ከፍተኛ ረሃብ መግባቱ ተሰማ፡፡
===================================================
የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው፡፡

እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ የጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አገልጋይ ባለስልጣናት በክልሉ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተብየ መሪነት ከፍተኛ ስብሰባ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ከአስተዳዳሪው እና ከአፈጉባኤው በስተቀር ሁሉንም የመስተዳድሩ አሻንጉሊት ባለስልጣናት ቦታ የመቀያየር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

Wednesday, October 28, 2015

ቴፒ በተኩስ ስትናወጥ አመሸች


ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ "የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ" በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቆርጫ ህብረት ፍሬ ቀበሌ ማምሻውን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። አንድ የአይን እማኝ እንደተናገሩት ፣ ሰሞኑን እንደገና በብዛት የሰፈሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህብረት ፍሬ በሚባል ቀበሌ የሚገኙ ሴቶችን " ሽፍቶችን የምትቀልቡት እናንተ ናችሁ አውጡ" በማለት ሲደብድቧቸው ፣ መረጃ የደረሳቸው ወጣቶች ፈጥነው በመድረስ ባደረሱት ጥቃት 14 ወታደሮች መገደላቸውንና ከወጣቶች መካከልም 2ቱ መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት የወታደሮች አስከሬን ሌሊት ላይ በ4 መኪኖች ተጭነው ሲወሰዱ ፣ የወጣቶችን አስከሬን ግን ህዝቡ መቅበር እንዳልቻለ ገልጸዋል የወጣቶች አመራሮች ማምሻውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ 20 የልዩ ሃይል አባላትን መግደላቸውንና በእነሱ ወገን 2 ታጋዮች እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል። የሞቱ የመንግስት ወታደሮች ሌሊት ሲጓጓዙ ማደራቸውን የሚገልጹት ወጣቶቹ፣ የተገደሉባቸውን ወታደሮች ስምም ይፋ አድርገዋል። አንደኛው ሟች ቀድሞ የፖሊስ አባል የነበረና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም የወጣቶችን ትግል የተቀላቀለው ሳጅን አብርሃም ፈይሳ ሲሆን፣ ሌላው ሟች ደግሞ ዘሪሁን ባሳ የሚባል ነው። እኩለ ቀን ላይ በከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የሚገኙት የመንግስት ወታደሮች የሁለቱን ወጣቶች አስከሬን ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት ሲጎትቱት ታይተዋል። ኢሳት ሞቱ ስለተባሉት የመንግስት ወታደሮች ከመንግስት ወገን የሚሰጥ መረጃ ካለ ለማጣራት ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም

ቴፒ በተኩስ ስትናወጥ አመሸች

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ "የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ" በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። 

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡



ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ "አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል..." እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ 
ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡

እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም አቶ አንዳርጋቸው እሱ ጋር እንደሌሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ መግለፁ ይታወሳል፡፡
ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ከአቶ ምንዳዬ ጥላሁን በተጨማሪ 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲመሰክሩለት በመፈለጉ፤ እና ፍርድ ቤቱም አቶ አንዳርጋቸው ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲመቸው ተከሳሾቹ እንዲጠቁሙት በገለፀው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ተቋማት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
የሕወሃት ስታይል
"TPLF style " ይሉታል፣ በትግራይ አስተዳደር ያለውን በጣም አስቂኝ እና አሳፋሪ ሁኔታ፣ የለዉጥ ኃይሉ አንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የነበሩት፣ አቶ አስራት አብርሃ ።
አባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት ናቸው። በትግራት አስተዳደር የሚሰራዉን ግፍና ወንጀል፣ ሙስና፣ የገንዘብ ዘረፋ ..ለመቆጣጠር የትግራይ ክልል የጸረ-ሙስና ጽ/ቤት አለው። የዚህ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው እንዲሰሩ የተደረጉት፣ ወ/ሮ ትርፊ ኪዳነ ማሪያም ይባላሉ። ወ/ሮ ትርፉ የሕግ ባለሞያ፣ ገለልተኛ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ለቦታው ብቁ የሆኑ ሰው አልነበረሙ። ወይዘሮዋ፣ የአቶ አባይ ወልዱ ሚስት ናቸው።
"ጥሩ ነው አልጋ ላይ ጭምር ትቆጣጠሯለች!! " ሲል አስራት አብራሃ ምን ያህል በአገራችን ያለው የፖለቲክ ስርዓት አሳፋሪ መሆኑን ይገልጻል።
ወይዘሮ ኪዳነማሪያም በትግራይ የጸረ-ሙስና ሃላፊ ብቻ አይደለኡም። ከባለቤታቸው ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር የሕወሃት ፖሊት ቢሮ አባል ናቸው።

Tuesday, October 27, 2015


ስለአንዳርጋቸው አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየሁ ነው። አንዳርጋቸው በጣም ደህና ነው ። አያያዙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ ቢመጣም፣ በጥሩ መንፈስ ላይ ይገኛል። ህክምና፣ በህግ ባለሙያ መጎብኘት የመሳሰሉት መሰረታዊ መብቶቹ ሊጠበቁለት አልቻለም። የእንግሊዝ አምባሳደር በቅርቡ ቃሊቲ ሄደው ሲጎበኙትም አያያዙ አስከፊ መሆኑን ነግሯቸዋል። በቃልቲ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ ታስሯል። ሃይላችንንና ትኩረታችንን ነጻይቱን ኢትዮጵያን በመመስረት ላይ እናውል እንጅ በአሉባልታ ጊዜያችንን አናጥፋ ። ሁሌም ማዬት ያለብን ግን ትግልና መስዋትነት የማይነጣጠሉ ነገሮች መሆናቸውን ነው። መሰዋትነትን የሚፈራ ትግል አይጀምርም፣ ትግል ውስጥ ያለም መሰዋትነትን ከፈራ ድል አያደርግም፣ ጉዞውም በአጭር ይቀራል። አንዳርጋቸው ማንኛውንም መስዋትነት ለመቀበል ተዘጋጅቶ ወደ ትግል የገባ በመሆኑ፣ የሚረበሽበት አንዳች ምክንያት የለውም። ይህን ደግሞ እኔ

BREAKING NEWS | Document from Ethiopian Govt Lists Oromo Wisdom-Keeper Dabassa Guyo as #1 Target; List Contains Some 131 Oromo Nationals in Kenya as Targets, Including Oromo Artists

የኢትዮጵያ መንግስት ለኬንያ መንግስት የጻፈው የሚስጥር ደብዳቤ ይፋ ሆነ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ጸረ ሽብር ግብረ ሀይል የተጻፈው ይሄ ደብዳቤ 66 የሚሆኑ ዜጎችን አሳልፎ እንዲሰጠው የኬንያን መንግስት ጠይቋል።
እነዚህ ዜጎች በኬንያ በስደት የሚኖሩና ጉዳያቸውም በአለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት በመታየት ላይ ያለ ሲሆን አንዳንዶቹም ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ወቅት ጀምሮ ኑሮዋቸውን በኬንያ ያደረጉ መሆናቸው ታውቋል። የአለም አቀፍ ህጎች ስደተኞች በምንም መልኩ ተላልፈው እንደማይሰጡ የሚደነግግ ቢሆንም የኬንያ መንግስት በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳልፎ በመስጠ ይወቀሳል።
ይህንንሚስጥራዊ ሰነድ ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ። እንዲሁም ሼር በማድረግ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያግዙ። > >> http://goo.gl/ySIv8U

Monday, October 26, 2015

በጎንደር አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በ6 ፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ራሱን አጠፋ

-ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ አምሳሉ ተሾመ የተባለው ታጋይ ሰዎችን በመመልመል ወደ በረሃ ተልካለህ ተብሎ በመጠርጠሩ፣ ፖሊሶች ሊይዙት ሲሞክሩ፣ እጄን አልሰጥም በማለት በያዘው ሽጉጥ አንድ የመቶ እልቅና ያለው መኮንንና ሌላ አንድ ተራ ፖሊስን በመግደል፣ እንዲሁም 4 ታጣቂዎች በማቁሰል በመጨረሻም በያዘው ሽጉጥ ራሱን አጥፍቷል። ወጣቱ ከዚህ ቀደም የአርበኞች ግንቦት7 አባል ነህ በሚል ታስሮ የተፈታ ሲሆን፣ ባለፈው አርብ በድጋሜ ፖሊሶች ሊይዙት ሲመጡ " አትቅረቡኝ ተመለሱ " እያለ ማስጠንቀቁን ያልተቀበሉት ፖሊሶች ፣ እርምጃ ለመውሰድ ሲሞክሩ ታጋዩ ፈጥኖ እርምጃ በመውሰዱ በታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶ በራሱም ላይ እርምጃ መውሰዱን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ፖሊሶች በታጋዩ አስከሬን ላይ የማይገባ ድርጊት ለመፈጸም ሲሞክሩ ህዝቡ " ከባህላችን የወጣ ነው" በማለት ተቃውሞ ማሰማቱንና ሟቹን ጀግና እያለ ሲያወድሰው መሰማቱን ፣ በህዝቡ ግፊትም አስከሬኑ ለቤተሰቡ ተሰጥቶ የቀብር ስነስርዓት መፈጸሙን ለመረጃው ቅርብ የሆኑ ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ግንቦት7 ሬዲዮ በለቀቀው ዘገባ ደግሞ ታጋዩ 7 የኮልት ሽጉጥ ጥይቶችን ይዞ የነበረ ሲሆን፣ በ6ቱም ኢላማውን ከመታ በሁዋላ፣ የመጨረሻውን ጥይት በራሱ ላይ አውሎታል። ሬዲዮው የሟቾቹን ቁጥር 3 መሆኑን ገልጿል።

Amanuel Mengste - Yekwara Anbessa Bahilawi

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡

Friday, October 23, 2015

Paradigm is shifting as Ethiopians take a surprising giant leap -

DSC_0116

by (Yohannes Kifle –ycry98@yahoo.com)
10-22-15

Given the local weather condition, to the vast majority of Eritreans and Ethiopians residing in the Washington, D.C metropolitan area, Sunday, October 18th might have been a gloomy day. However, for those of us who chose to attend the panel discussion that was organized by ESAT and Vision Ethiopia to discuss future Eritrean-Ethiopian relations,

ESAT Special Report on Ethiopia & Eritrea Relations Present & Future Oc...

ኢሳት ዜና

*እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ አምባገነን ሥርዓት ፊት አሸባሪ ነው። ከታሰረበት 2004 ዓ.ም ወዲህ ዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለ4 ጊዜ ለሞያው ባለው ጽናት ሸልመውታል።
የተበባሩት መንግስታት ድርጅት አጣሪ ቡድን የእስክንድር ክስ መብቱን ተጠቅሞ በመናገሩና በመጻፉ ነው ብሎ በህወሓት ፍርድ ቤት የተቀነባበረበት ክስ ፖለቲካዊ እንደሆነ ገልጿል።
ሰሞኑን ፔን ካናዳ ለእስክንድር ሽልማት መስጠቱን ተከትለን አንድ ዝግጅት አሰናድተናል።

*የሎሚ መጽሔት ሥራ አሰኪያጅ ግዛው ታዬ መክስረም 27 2007 ዓ.ም ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት፣ ሀሰተኛ ወሬዎችን አሳትሞ በማሰራጨትና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ በመንቀሳቀስ በሚሉ ወንጀሎች ክሶች በሶስት አመት ከሶስት ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ።
ሰሞኑን ደግሞ በታክስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ተብሎ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት እና የ100 ሺህ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት። ግዛው ከሀገሩ ተሰዷል። ኢሳት አገኝቶት ስለፍርዱ አነጋግሮታል።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ዛሬ እና ነገ በሚል ርዕስ የተካሄደው ውይይት በሲሳይ አጌና ተዘጋጅቷል
ኢሳት የናንተው የሕዝብ ልሳን!

Thursday, October 22, 2015

የኢህአደግ ስረአት የኑሮ ውድነት ለመደበቅ ቢሞክርም ሊደበቅ አልቻልም፣


በሃገራችን በኢሀዴግ ስረአት ብልሹነት ምክንያት የተነሳ የህዝባችን የኑሮ ውድነት ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰና በተለይም ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ካለው የገበያ ውደነትና የሚፈለገው የእህል አይነት ባለ ማገኘታቸው በረሃብና በችግር ውስጥ ሆነው ኑራቸውን ይመራሉ።
ይሁን እንጂ የሃገሪቱ መሪ ተብየው የኢህአዴግ ሰረአት በተለያየ ቦታዎች የሚገኙ ህዝብ በቂ ምርት ባለ መኖሩ የፈጠረዉ ዋጋ ግሽበት እየተሰቃየ ባለበት ውቅት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በዕደገት ጎዳና ላይ እየገሰገስን ነው በማለት በሞተ ቃላት ሲናገር ይሰማል።
በተለይም በአሁን ሰአት ከዝናብ መጥፋት ጋር ተያይዞ በርካታ ዜጎች በቤታቸው ውስጥ እየሞቱ ምንም አይነት የመንግሰት ደጋፍ ያለመደረጉ እንዲሁም በተለያየ የሃገሪቱ ክፍል ከግዜ ወደ ግዜ በፍጠነት እየተባባሰ ያለዉ ኑሮ ዉድነት ትኩረት ሳይሰጠው ህዝባችን አልተቸገረም እያለ በቴሌቭዥን መስኮት መናገሩ ለህዝብ ያልቆመ መንግስት መሆኑን አሰረጂ ነገር ስለ ሆነ ህዝብ በገዡዉ የኢህኣዴግ ስርዓት ያለው እምነት ሙሉ በሙሉ ተሟጦ ተስፋ ቆርጦ ይገኛል።
በተግባር በመስራት ሳይሆን በማሰመሰል የሚታውቀው የኢህአደግ ስርአት ህዝብ በልመና በየመንገዱ ሴት ወንድ ትንሸ ትልቅ ሳይል በየሁቴል ቤቱ የተረፈ ምግብ ለመግዛት ወረፋ ይዞ መገኘቱ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ውድቀትን አመላካች መሆኑን ያስገነዝባል።
ሆኖም ተጎጅው ህብረተሰብ ችግሩን በተደጋጋሚ ቢናገርም ሰሚ አካል ያለማገኘቱ ብሶቱንና ሀዘኑ ከባድ እንዲሆን አድርጎት እያለ ባለሃብቶቹ ደግሞ ደስ ባላቸው ዋጋ በገበያ እየሸጡ በድሃው ህዝብ ላይ የሚፈልጉትን ያህል ዋጋ ስለሚጩንበት ህብረተሰቡ ለመግዛት ከአቅሙ በላይ ሆኖበት በችጋርና ረሃብ እየተሰቃየ ይገኛል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ

http://www.patriotg7.org/wp-content/uploads/2015/10/AG7-radio-22-10-2015.mp3

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ከመከላከያ ሰራዊቱ የሚከዱ አባላትን ጨርሶ መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተረጋገጠ፡፡
‪#‎በጎንደር‬ ወገራ ወረዳ በአራት ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ ደርሶ ነዋሪዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸው እና የቤት እንስሶቻቸውም በማለቅ ላይ መሆናቸውም ተሰማ፡፡
#የህወሓት አገዛዝ የላይ አርማጭሆ ሙሴ ባንብ ነዋሪ የሆኑ 50 ወጣቶችን በስብሰባ ስም በኃይል ጠርንፎ ይዞ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ እያለ በምርመራ እያስጨነቃቸው እንደሚገኝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩት መረጃ አጋለጠ፡፡
#በጎንደር ከተማ ወላጆች ልጆቻቸውን በአገዛዙ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማስመዝገብ ለደላሎች በአንድ ሰው ከ500-1000 ብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ከፍተኛ ምሬት ውስጥ ናቸው፡፡
====================================================
የህወሓት አገዛዝ ከመከላከያ ሰራዊቱ የሚከዱ አባላትን ጨርሶ መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተረጋገጠ፡፡
የህወሓት አባላት በሆኑ የይስሙላህ የጦር መኮንኖች ከታች እስከላይ ተጠርንፎ በጉልበት ተይዞ በአገር መከላከያ ስም እየተጠራ ነገር ግን በፀረ-ህዝብነት ሳይወድ በግድ እንዲሰለፍ እየተደረገ የሚገኘው ሰራዊት ስርዓቱን መክዳቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ፈፅሞ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡
በተለይም ደግሞ ማዕከላዊ ዕዝ እና ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት የከዳባቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ የሰራዊቱ አባላት ስርዓቱን ጥሎ መክዳት ተባብሶ የቀጠለ በመሆኑ የሰራዊቱ አባላት የትምህርት ማስረጃቸውንና ሌሎችን ሰነዶች ለመያዣነት እየተነጠቁ ይገኛሉ፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ በሰፊው እየተተገበረ የሚገኘው ይህ የትምህርት ማስረጃ እና ሌሎችም የግል ሰነዶች ንጥቂያ በተለይም የሙያተኛ መኮንኖችን መክዳት ለመግታት ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ በሰራዊቱ ውስጥ እልህና ቁጣን ቀስቅሶ ይገኛል፡፡ ከጫፍ የደረሰ ኩርፊያም ጭምር አስከትሏል፡፡

Wednesday, October 21, 2015

Patriotic Ginbot7 Radio

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ



‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ከመከላከያ ሰራዊቱ የሚከዱ አባላትን ጨርሶ መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተረጋገጠ፡፡
‪#‎በጎንደር‬ ወገራ ወረዳ በአራት ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ ደርሶ ነዋሪዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸው እና የቤት እንስሶቻቸውም በማለቅ ላይ መሆናቸውም ተሰማ፡፡
#የህወሓት አገዛዝ የላይ አርማጭሆ ሙሴ ባንብ ነዋሪ የሆኑ 50 ወጣቶችን በስብሰባ ስም በኃይል ጠርንፎ ይዞ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ እያለ በምርመራ እያስጨነቃቸው እንደሚገኝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩት መረጃ አጋለጠ፡፡
#በጎንደር ከተማ ወላጆች ልጆቻቸውን በአገዛዙ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማስመዝገብ ለደላሎች በአንድ ሰው ከ500-1000 ብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ከፍተኛ ምሬት ውስጥ ናቸው፡፡
====================================================
የህወሓት አገዛዝ ከመከላከያ ሰራዊቱ የሚከዱ አባላትን ጨርሶ መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተረጋገጠ፡፡
የህወሓት አባላት በሆኑ የይስሙላህ የጦር መኮንኖች ከታች እስከላይ ተጠርንፎ በጉልበት ተይዞ በአገር መከላከያ ስም እየተጠራ ነገር ግን በፀረ-ህዝብነት ሳይወድ በግድ እንዲሰለፍ እየተደረገ የሚገኘው ሰራዊት ስርዓቱን መክዳቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ፈፅሞ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡
በተለይም ደግሞ ማዕከላዊ ዕዝ እና ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት የከዳባቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ የሰራዊቱ አባላት ስርዓቱን ጥሎ መክዳት ተባብሶ የቀጠለ በመሆኑ የሰራዊቱ አባላት የትምህርት ማስረጃቸውንና ሌሎችን ሰነዶች ለመያዣነት እየተነጠቁ ይገኛሉ፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ በሰፊው እየተተገበረ የሚገኘው ይህ የትምህርት ማስረጃ እና ሌሎችም የግል ሰነዶች ንጥቂያ በተለይም የሙያተኛ መኮንኖችን መክዳት ለመግታት ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ በሰራዊቱ ውስጥ እልህና ቁጣን ቀስቅሶ ይገኛል፡፡ ከጫፍ የደረሰ ኩርፊያም ጭምር አስከትሏል፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ ዕና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ ሲከዱ ተይዘው በቁጥጥር ስር የዋሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሰራዊቱ አባላት እንዳሉ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ባልተጠበቀ ሰዓት ጥቃት ሊከፍቱ ይችላሉ ተብሎ በመስጋቱ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ታዞ በአካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ አየተደረገ ይገኛል፡፡
በጎንደር ወገራ ወረዳ በአራት ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ ደርሶ ነዋሪዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸው እና የቤት እንስሶቻቸውም በማለቅ ላይ መሆናቸውም ተሰማ፡፡
ከፉኛ በድርቅ የተመቱት አራቱ ቀበሌዎች ሶምያ፣ ጓሪ፣ ግጭሆ እና ቧግሽ ሲሆኑ ከብቶቹ እንደ ቅጠል እየረገፉበት እና ጠኔ ፀንቶበት የሚገኘው የእነዚህ ቀበሌዎች ህዝብ የአድኑን ተማፅኖ ጥሪውን ድምፅ በተደጋጋሚ ለአገዛዙ ቢያሰማም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠውም፡፡
በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተከሰተው ከባድ ድርቅ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በትንሹ ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በምግብ እጥረት ለርሃብ አደጋ ተጋልጦ በሞትና በህይወት መካከል ይገኛል፡፡
መጠነሰፊና ተከታታይ ድግሶችን በማሰናዳት የአገሪቱን ከፍተኛ ሃብት በማውደም ተግባር ላይ ተጠምዶ የከረመው የህወሓት አገዛዝ ምንም እንኳን መጀመሪያ የሌሎች አካላት ድጋፍ አያስፈልገኝም ሲል በአደባባይ ቢደመጥም አሁን ደግሞ እንደገና በድርቁ የተጠቁ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በመመገብ ነብሳቸውን ለመታደግ 596 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገው ለለጋሽ አገሮች እየተናገረ ነው፡፡
የህወሓት አገዛዝ የላይ አርማጭሆ ሙሴ ባንብ ነዋሪ የሆኑ 50 ወጣቶችን በስብሰባ ስም በኃይል ጠርንፎ ይዞ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ እያለ በምርመራ እያስጨነቃቸው እንደሚገኝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩት መረጃ አጋለጠ፡፡
የአርማጭሆ እና የወልቃይት ህዝብ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለውን ዘረኛ ቡድን መቃወም የጀመረው ገና ከሽፍትነት ዘመኑ አንስቶ ሲሆን አሁንም ለነፃነቱ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ተነግሮ የማያልቅ መሰዋዕትነት መክፈሉን ቀጥሏል፡፡
"እምቢ በኃይል አልገዛም!" "ግፍና በደልን ዝም ብዬ አልጋትም!" በማለት ያልተቋረጠ የነፃነት ትግል እያደረገ የሚገኘውን የአርማጭሆ ህዝብ በመሳሪያ ጉልበት አንገቱን ለማስደፋት በማለም የህወሓት አገዛዝ በአካባቢው ከፌደራል ፖሊስ፣ ከልዩ ኃይልና ከሚሊሻ ታጣቂዎች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ጦር ሰራዊት አስፍሮ ይገኛል፡፡
ህዝቡ ደግሞ በበኩሉ ተወልዶ ባደገበት ቀዬ በሰላም መኖር ስላልቻለ ጠብመንጃውን እየወለወለ በየቀኑ ወደ በረሃ መውረዱን እና ጠብመንጃ ነካሽ የሆነውን የህወሓት ዘረኛ ቡድን በጠብመንጃ መፋለሙን ቀጥሏል፡፡
በመሆኑም በአርማጭሆ ምድር ከያቅጣጫው ፍንዳታ ሳይደመጥ እና ግድያ ሳይፈፀም ውሎ አድሮ አያውቅም፡፡ የሞት መርዶም ያልተሰማበት ዕለት በስህተት እንኳ አይገኝም፡፡
ይህ የአርማጭሆ ህዝብ በአንድነት ተነስቶ እያደረገው የሚገኘው በነፍጥ የተቃኘ የነፃነት ትግል ለስልጣን ህልውናው በዕጅጉ ያሰጋው የህወሓት አገዛዝ በትንሹ 50 የሚሆኑ የሙሴ ባንብ ወጣቶችን በስብሰባ ስም በአንድ ቦታ ላይ አጉሮ "ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ፤ ወጣቶችን እየመለመላችሁ ትልካላችሁ፤ ነገ ከነገ ወዲያ እናንተም ሄዳችሁ መቀላቀላችሁ አይቀርም..." የሚል በዛቻና ማስፈራራት የታጀበ አስጨናቂ ምርመራ አድርጎ ምንም ጠብ ሚል ነገር ሊያገኝ ባለመቻሉ በኃይማኖት አባቶች ጭምር እየተማፀነ ነው፡፡
መስቀል የያዙ የአካባቢው ካህናት ወጣቶች በታጎሩበት ቦታ በግዴታ እንዲገኙ ተደርገው ወጣቶች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ከሌላቸው እንዲምሉ እየተጠየቁ ይገኛሉ፡፡ ካህናቱም ወጣቶቹ ወደፊት ወደ በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት ሰባትን እንዳይቀላቀሉ በግዝት እንዲያስሯቸው በአገዛዙ ካድሪዎችና የታጠቁ ቡድኞች እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
በጎንደር ከተማ ወላጆች ልጆቻቸውን በአገዛዙ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለማስመዝገብ ለደላሎች በአንድ ሰው ከ500-1000 ብር እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ከፍተኛ ምሬት ውስጥ ናቸው፡፡

የኢህአድግ አመራሮዎች በሰሜን አሜሪካ በህግ ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ለአንድ ዶላል በ23 ብር እየቀየሩ ሃብታቸውን በማካበት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።


የኢህአደግ ስረአት ባለ ስልጣኖች ሃብታቸውን ከውስጥ ሃገር ለማውጣት እየተጠቀሙት ያለውን ስልት የኢትዮጵያ ባንኮዎች ከመጉዳት ባለፍ በአሁኑ ወቅት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከባድ ችግር ውስጥ አስገብተውት እንደሚገኙ የገለጸው መረጃ: በአሁን ጊዜ የኢህአዴግ ባለ ስልጣኖች በሙስና ያጠራቀሙት ሃብት ወዲ ዉጭ በመጎጓዝ ላይ ተጠምደው ባሉበት ግዜ ከሰሜን አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከመጠን በላይ በኮትሮ ባንድ ንግድ ለአንድ ዶላል በ23 ብር እንመነዝርላችሁ በማለት በህዝብ ሃብት በመጫወት ላይ ኣንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ኣክለዉ እንዳመለከተው በአሁኑ ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ፤ስያትል፤ዴንቭር፤ሚኒያፖሊስ፤አትላንታ፥ቺካጎ፤በሂውስተን፤ኦሃዮ፤ፓርትላንድ፤ላስቬጋስ፤ካልፎርኒያ እንዲዚሁም በተለያዩ ከተሞች በአሪዞና በተዘረጉት መረቦች መረጃ ዶላል በኮትሮ ባንድ ንግድ በ23ብር እየተመነዘር መሆኑን መረጃው አስታውቀዋል።
በመጨረሻም አንድ የአሜሪካ ዶላር በህጋዊ መንገድ ብ20.85 ብር እየተመነዘር ቢሆንም በሌቦች የኢህአድግ የገዢው ስረአት ባለ ስልጣናት ግን ዶላር ያለ ህጋዊ መንገድ የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ያለ አግባብበ በመቀየራቸው የተነሳ የሃገር ውስጥ መንዛሪ ከፋተኛ እጥርት እያጋጠመ እንዳለ የተለያዩ ህዝቦች በመግለፀ ላይ ይገኛሉ።

ሶማሊያ የሚገኙ የጦር ሠራዊት አባላት ሲበደሉ ያመናል !


የተባበሩት መንግሥታት ማኅበር የሚሰጠው ገንዘብ ህሊናቸውን በሰወራቸው፤ የህወሓት አባላት በሆኑ ጄኔራሎች አዝማችነት ሶማሊያ የገባው ኢትዮጵያዊ ድሃ ወታደር እጣ ፈንታ በጣም አሳዛኝ ደረጃ ላይ ደርሷል። በየእለቱ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች እየተገደሉ፤ አስከሬናቸው በጎዳናዎች እየተጎተተና እየተቃጠለ ነው። ሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ወገኖቻችን ናቸውና በእነርሱ ላይ የሚደርሰው ስቃይ ይሰማናል፤ ሲበደሉ ያመናል፤ ጭንቀታቸው ይጨንቀናል። ወገኖቻችን ናቸውና የደህንነታቸው ጉዳይ ያገባናል።
የህወሓት ጄኔራሎች ሙሉ ትኩረታቸው ያለው በእያንዳንዱ ወታደር ስም ከተባበሩት መንግሥታት በሚያገኙት ገንዘብ መጠን ላይ ነው። ለሶስት ሣምንታት ብለው የገቡበት ጦርነት እነሆ አስር ዓመታት አስቆጥሯል። አንዱ የገቢያቸው ምንጭ ነውና ጦርነቱ ለሌላ አስር ዓመታት ቢራዘም ለእነሱ ደስታቸው ነው። ኢትዮጵያዊው ምስኪን ወታደር ግን አዛዦቹ እንዲያልቅ በማይፈልጉት ጦርነት ውስጥ ገብቶ መስዋዕትነት ይከፍላል፤ ሲወድቅ የሚያነሳው የለም፤ መስዋዕት ሲሆን የክብር አሸናኘት የለውም፤ ቤተሰቦቹም ይኑር ይሙት አያውቁም። ይህ ሁላችንንም ሊያስቆጣ የሚገባ ግፍ ነው።
ኢትዮጵያን ለመታደግ ብሎ የዘመተን ወታደር ስለኢትዮጵያ ግድ በማይሰጣቸው፤ ጥቅማቸውን ብቻ በማሳደድ ላይ ያሉ አዛዦች ቸልተኝነት ምክንያት ለስቃይ፣ ሰቆቃና ውርደት መዳረግ የለበትም። በሶማሊያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የሚደርሰው በደል በሁላችም ላይ የደረሰ በደል ነው፤ በእነርሱ ስብዕና ላይ እየደረሰ ያለው ውርደት በአገራችን ላይ የደረሰ ውርደት ነው።
የጦሩ አዛዦቹ በወታደሩ ስቃይና ሞት ከብረው የከተማ ድሆችን እያፈናቀሉ ሕንፃዎችን እየገነቡ፤ የባንኩን፣ የኢንሹራንሱን፣ የገቢና ወጪ ንግዱን እያጧጧፉ ነው። የወታደር ልብስ ቢለብሱም፤ “ጄኔራል እከሌ” ተብለው ቢጠሩም በተግባር መጥፎ ነጋዴዎች እንጂ ወታደሮች አይደሉም። እነዚህ የስም ጄኔራሎች በጦርነት ውስጥም የሚታያቸው ንግድና ገበያ ነው። በእንደነዚህ ዓይነቶች አዛዦች ተመርቶ ጦርነትን ማሸነፍ አይቻልም።
አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በህወሓት የጦር አዛዦች ብቃት ማነስ፣ ስግብግብነትና ቸልተኝነት ሳቢያ በሶማሊያ እየሞቱ፣ እየቆሰሉ፣ አስከሬናቸው እየተዋረደ ስላለው ኢትዮጵታዊያን የሚሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። 
ከሶማሊያ ውጭም የኢትዮጵያ ወታደር የሚገኝበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነው። በተለይም በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደር እንደ ስሙ “የአገር መከላከያ ሠራዊት” በመሆን ፋንታ ወገንን ማጥቂያ ሠራዊት እየሆነ ነው፤ አገርን በመከላከል ፋንታ ወገንን ማጥቃት የሠራዊቱ የዕለት ተዕለት ተግባር ሆኗል። ለዚህ አሳፋሪ ተግባር ሠራዊቱ ራሱ መላ ሊፈልግለት ይገባል።

ሶማሊያ የሚገኙ የጦር ሠራዊት አባላት ሲበደሉ ያመናል !

def-thumb


October 21, 2015
የተባበሩት መንግሥታት ማኅበር የሚሰጠው ገንዘብ ህሊናቸውን በሰወራቸው፤ የህወሓት አባላት በሆኑ ጄኔራሎች አዝማችነት ሶማሊያ የገባው ኢትዮጵያዊ ድሃ ወታደር እጣ ፈንታ በጣም አሳዛኝ ደረጃ ላይ ደርሷል። በየእለቱ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች እየተገደሉ፤ አስከሬናቸው በጎዳናዎች እየተጎተተና እየተቃጠለ ነው። ሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ወገኖቻችን ናቸውና በእነርሱ ላይ የሚደርሰው ስቃይ ይሰማናል፤ ሲበደሉ ያመናል፤ ጭንቀታቸው ይጨንቀናል። ወገኖቻችን ናቸውና የደህንነታቸው ጉዳይ ያገባናል።
የህወሓት ጄኔራሎች ሙሉ ትኩረታቸው ያለው በእያንዳንዱ ወታደር ስም ከተባበሩት መንግሥታት በሚያገኙት ገንዘብ መጠን ላይ ነው። ለሶስት ሣምንታት ብለው የገቡበት ጦርነት እነሆ አስር ዓመታት አስቆጥሯል። አንዱ የገቢያቸው ምንጭ ነውና ጦርነቱ ለሌላ አስር ዓመታት ቢራዘም ለእነሱ ደስታቸው ነው። ኢትዮጵያዊው ምስኪን ወታደር ግን አዛዦቹ እንዲያልቅ በማይፈልጉት ጦርነት ውስጥ ገብቶ መስዋዕትነት ይከፍላል፤ ሲወድቅ የሚያነሳው የለም፤ መስዋዕት ሲሆን የክብር አሸናኘት የለውም፤ ቤተሰቦቹም ይኑር ይሙት አያውቁም። ይህ ሁላችንንም ሊያስቆጣ የሚገባ ግፍ ነው።

ሶማሊያ የሚገኙ የጦር ሠራዊት አባላት ሲበደሉ ያመናል !


October 21, 2015
def-thumb
የተባበሩት መንግሥታት ማኅበር የሚሰጠው ገንዘብ ህሊናቸውን በሰወራቸው፤ የህወሓት አባላት በሆኑ ጄኔራሎች አዝማችነት ሶማሊያ የገባው ኢትዮጵያዊ ድሃ ወታደር እጣ ፈንታ በጣም አሳዛኝ ደረጃ ላይ ደርሷል። በየእለቱ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች እየተገደሉ፤ አስከሬናቸው በጎዳናዎች እየተጎተተና እየተቃጠለ ነው። ሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ወገኖቻችን ናቸውና በእነርሱ ላይ የሚደርሰው ስቃይ ይሰማናል፤ ሲበደሉ ያመናል፤ ጭንቀታቸው ይጨንቀናል። ወገኖቻችን ናቸውና የደህንነታቸው ጉዳይ ያገባናል።

የህወሓት ጄኔራሎች ሙሉ ትኩረታቸው ያለው በእያንዳንዱ ወታደር ስም ከተባበሩት መንግሥታት በሚያገኙት ገንዘብ መጠን ላይ ነው። ለሶስት ሣምንታት ብለው የገቡበት ጦርነት እነሆ አስር ዓመታት አስቆጥሯል። አንዱ የገቢያቸው ምንጭ ነውና ጦርነቱ ለሌላ አስር ዓመታት ቢራዘም ለእነሱ ደስታቸው ነው። ኢትዮጵያዊው ምስኪን ወታደር ግን አዛዦቹ እንዲያልቅ በማይፈልጉት ጦርነት ውስጥ ገብቶ መስዋዕትነት ይከፍላል፤ ሲወድቅ የሚያነሳው የለም፤ መስዋዕት ሲሆን የክብር አሸናኘት የለውም፤ ቤተሰቦቹም ይኑር ይሙት አያውቁም። ይህ ሁላችንንም ሊያስቆጣ የሚገባ ግፍ ነው።
ኢትዮጵያን ለመታደግ ብሎ የዘመተን ወታደር ስለኢትዮጵያ ግድ በማይሰጣቸው፤ ጥቅማቸውን ብቻ በማሳደድ ላይ ያሉ አዛዦች ቸልተኝነት ምክንያት ለስቃይ፣ ሰቆቃና ውርደት መዳረግ የለበትም። በሶማሊያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የሚደርሰው በደል በሁላችም ላይ የደረሰ በደል ነው፤ በእነርሱ ስብዕና ላይ እየደረሰ ያለው ውርደት በአገራችን ላይ የደረሰ ውርደት ነው።
የጦሩ አዛዦቹ በወታደሩ ስቃይና ሞት ከብረው የከተማ ድሆችን እያፈናቀሉ ሕንፃዎችን እየገነቡ፤ የባንኩን፣ የኢንሹራንሱን፣ የገቢና ወጪ ንግዱን እያጧጧፉ ነው። የወታደር ልብስ ቢለብሱም፤ “ጄኔራል እከሌ” ተብለው ቢጠሩም በተግባር መጥፎ ነጋዴዎች እንጂ ወታደሮች አይደሉም። እነዚህ የስም ጄኔራሎች በጦርነት ውስጥም የሚታያቸው ንግድና ገበያ ነው። በእንደነዚህ ዓይነቶች አዛዦች ተመርቶ ጦርነትን ማሸነፍ አይቻልም።

እንግሊዝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይን “ለንግድ ጥቅሟ ” ስትል እንዳትረሳው ተየቀች


ለእንዳርጋቸው መታፈን ተጠያቂ የተባሉት ዶ/ር ቴዎድሮስን ሎንዶን ላይ መጋበዝ እደጋ አለው ተባለ 
ከታምሩ ገዳhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/47565
ካለፈው አመት የፈረንጆቹ ሰኔ ወር መባቻ ላይ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ የመን(ሰነኣ ) አለም አቀፍ አወሮፕላን ጣቢያ ላይ ታፈነው ለ አዲስ አበባ መንግስት ተላለፈው የተሰጡት እና ቀደም ሲልም በሌሉበት ኢትዮጵያ ውስጥ በ 2009 አኤአ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እጣ ፈንታ ያሳሰበው አንድ ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእንግሊዝ መንግስት “ለጥቅሙ ሲል “የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይን ችላ እንዳይል ዳግም እስጥነቀቀ።

በቴፒ ከተማ ባጋጠመው ግርግር ምክንያት አንድ የፖሊስ አባል ሲገደል አምስት ደግሞ እንደታገቱ ታውቀ።


በመረጃው መሰረት በደቡብ ክልል ቴፒ ከተማና አካባቢው ልዩ ቦታ ሚልንየምና ሚካኤል በተባሉ አውራ ጎደናዎች መስከረም 29/ 2008 ዓ/ም ቅዳሜ ከለሊቱ 6 ስአት ካሳሁን የተባለው ግለሰው የስርአቱ ተላላኪ በሆነው የፌደራል ፖሊስ ኣባል እንደገደለው ገልፆ የፌደራል ፖሊስ አባሉ ወደ ከተማዋ በቅርብ ጊዜ ተመድቦ ሲሰራ እንደነበረ ታውቋል።
ሟዋቹ የፌደራል ፖሊስ የስራ ባልደረቦቹ ሆነ ብለው እንደገደሉት እየተወራ እንኳ ቢሆንም አጋጥሞ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ግን የከተማዋ ወጣቶች እንደገደሉት ሲገልፁ በቴፒ ወረዳ ያለውን በህዝቡና በፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል ግጭት አንድ አመት ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ያለውን ሁኔታ በአካባቢው ያሉት የፌደራል ፖሊስ አባላትና የፌደራል ባለ ስልጣናት ያስደነገጣቸው ሲሆን በግጭቱ ምክንያት አምስት የፌደራል ፖሊስ አባላት በከተማዋ ወጣቶች ታግተው ወደ ማይታወቅ ቦታ እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።

ኢሳት ዜና

-ነዋሪዎች "መሰረታችን ሕገ መንግስቱ ነው ተብሎ የወልቃይት ነዋሪዎች ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገና የሕዝቡን ስነ ልቦናዊ፣ ባሕላዊ ወግን ያላማከለና ያላጠቃለለ ክልላዊ አከላለል በማድረግ የወልቃይት ሕዝብ የማይፈልገውንና የማያምንበትን በመጫን በግድ ወደ ትግራይ እንድንካለል መደረጋችን በውስጣችን ያለውን ማንነታችንን በመጨፍለቅ እንድንቀበል እየተደረግን ነው ፣ዛሬ ስነ ልቦናችን የማይቀበለውን ሕወሃት በዘዴ ማንነታችንን ለማሸማቀቅ እየሞከሩ ነው" ብለዋል ። በማህበራዊ የመገናኝ ብዙሃን በተለቀቁ የስብሰባ ቪዴዮዎች ላይ አንድ ተናጋሪ ''እኛ እንደ ሲም ካርድ እኮ አይደለም አማርኛን የምንናገረው።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ




የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡http://www.patriotg7.org/…/uploads/2015/10/AG7-radio-20-10-…

Tuesday, October 20, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ


(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ


የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Hiber radio news-Analysis-101815-Israel-Palestine

ኢሳት ዜና

//cdn.playwire.com/bolt/js/zeus/embed.js

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ ተሸላሚ ሆነ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ ተሸላሚ ሆነ
በሽብርተኝነት ተከስሶ 18 አመት የተፈረደበትና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ ደረጃ አንድ ሰብዓዊነት (PEN Canada’s One Humanity Award) ሽልማት ተሸላሚ መሆኑን ፔን ካናዳ ይፋ አድርጓል፡፡
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በፈረንጆቹ ግንቦት 2012 የባርባር ጎልድ ስሚዝ ሽልማት እንዲሁም በሰኔ 2014 የጎልደን ፔን ሽልማትን ተሸላሚ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ በካናዳ ቶሮንቶ እየተደረገ በሚገኘው 36ኛው ዓለም አቀፍ የፀሃፊዎች ፌስቲባል የፔን ካናዳ ደረጃ አንድ ሰብዓዊነት ሽልማትን ተሸልሟል፡፡

Patriotic Ginbot7 fundraiser event in Sweden, Stockholm

የኢሳት ዜና

ጫት የምቅመው የረኀቡን ስሜት ለመግደል ነው"በድርቁ ምክንያት ካሉኝ 8 ከብቶች መካከል 4ቱን ሽጬ እህል ገዝቻለሁ። በሦስት የዘር መዝርያ ጊዜ የዘራሁት በቆሎ እና ገብስ መና ቀርቷል:: ሰዎች አካባቢውን ጥለው እየሄዱ አንተ ሰውዬ እዚህ የምትሆነው እስክትሞት ድረስ ነው ወይ?" ይሉኛል
*በሐረርጌ ሚኤሶ የሚኖሩት አቶ ያሲን መሐመድ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ "የገበሬዋ ሀገረ ኢትዮጵያ በአደገኛ የድርቅ አደጋ ውስጥ ገባች" በሚል ርዕስ ስር በተጻፈው ጽሑፍ ላይ የሰጡት ቃለምልልስ ነው።በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ዳይሬክትር በ2016 የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 15 ሚሊዮን እንደሚደርስ ገልጸዋል።
*አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በብሪታኒያ አምባሳደር ለ5ኛ ጊዜ ተጎብኝተዋል። ለአንድ ዓመት ያህል በጨለማ ቤት ስውር ቦታ ታስረው የነበሩት የነፃነት ታጋዩ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ከተዘዋወሩ በኋላ ከቤተሰባቸው የሚጎበኛቸው ቢኖር 80 ዓመት ያለፋቸው አባታቸው ብቻ ናቸው። እህታቸው ወይዘሮ ብዙአየሁ ተጨማሪ መረጃ ይሰጡናል።
*በተክለኀይማኖት እና በአሜሪካን ግቢ አካባቢ የንግድ ቤቶች ሁሉ ሊፈርሱ ታሽገዋል። ለማህበረሰቡ ምንም መረጃ ሳይሰጥ የተወሰደው እርምጃ ግብታዊነት እንደሆነ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ነዋሩዎች የመገበያያ ቦታ አጥተዋል።
ኢሳት የናንተ፣ የሕዝብ ድምጽ!

Monday, October 19, 2015

ይህ የምናደርገው መሰዋእትነት በሂዎታችን ለአንዴና ለመጨረሻ የሚደረግ ታሪካዊ መሰዋእትነት ነው ፤ ይህ የመጨረሻው እንደሚሆን አትጠራጠሩ ትግሉ እየፈጠነ ነው.. አቶ ናእምን የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የውጪ ዘርፍ ሃላፊ በሜኒሶታ ካደረጉት ንግግር
Oct 19, 2015

እነ ማቲያስ መኩሪያ በፍርድ ቤት እየተጉላሉ መሆናቸውን ገለጹ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


አይ.ኤስ.አይ.ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እነ ማቲያስ መኩሪያ በፍርድ ቤት እየተጉላሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጥቅምት 8/2008 ዓ.ም በመናገሻ ፍርድ ቤት የቀረቡት በእነ ማትያስ የክስ መዝገብ የሚገኙት አራቱ ተከሳሾች ክረምቱን በተረኛ ችሎት ይቀርቡበት ከነበረው አራዳ ፍርድ ቤት ተዛውረው እንደገና ወደቀደመው ችሎት መናገሻ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡
ተከሳሾች እስካሁን ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱ ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፡፡ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛ የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው በጠየቁት መሰረት ቪዲዮው ይቅረብ አይቅረብ በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ለወራ ተከታታይ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፤ እስካሁን ግን ብይኑ አልተሰጣቸውም፡፡
በዚህም ተከሳሾቹ ከታሰሩ ስድስት ወራት እንደሞላቸው በማውሳት ቤተሰቦቻቸው ለእንግልት፣ እነሱም ለእስር መዳረጋቸው አግባብ አለመሆኑን ለፍርድ ቤት አስረድተዋል፡፡ በዚህም አፋጣኝ ፍትህ እንደሚሹ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን አሁንም በዚሁ በቪዲዮ ማስረጃው ላይ ብይን ለመስጠት በሚል ለጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ሌላ ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለዛሬው ቀጠሮ የሰጠበት ምክንያት ‹‹መዝገቡ ከእጄ ወጥቶ ስለነበር አልመረመርኩትም›› የሚል ሆኗል፡፡
በእነ ማቲያስ መኩሪያ መዝገብ የተከሰሱት 1ኛ ማቲያስ መኩሪያ፣ 2ኛ መሳይ ደጉሰው፣ 3ኛ ብሌን መስፍን፣ 4ኛ ተዋቸው ዳምጤ ሲሆኑ ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡

Sunday, October 18, 2015

Mesay Mekonnen
Edited · 
The second strong man in TPDM has returned to Asmara.
ታጋይ ግደይ አሰፋ የትህዴን ቁልፍ ሰው ነው። የፕሮፖጋንዳ ክፍሉ አንቀሳቃሽ ሞተር ነው። የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በመሆን ይስራ እንጂ የትህዴን ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሚናው ከፍተኛ ነው። ባለፈው ሞላ የከዳ ጊዜ ግደይም አብሮት እንደነበረ ስሰማ በጣም ነበር የገረመኝ። ሞላ በፍጹም ግደይን ሊያታልለው አይችልም። ግደይ አብሮት ሄዷል ሲባል የታወሰኝ ከግደይ ጋር ከአስመራ ምጽዋ ያደረግነው ጉዞ: ራስ አሉላ የጣሊያኑን ወራሪ ጦር ድባቅ የመቱበት በመንገዳችን ላይ ያየነውን ታላቁን የዶጋሊ ስፍራን በስሜት ሆኖ ያጫወተኝ አጋጣሚ ነው። ግደይ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነው። ከሌሎች ሃይሎች ጋር ትህዴን በጋራ እንዲሰራ አቅሙም ስልጣኑም የፈቀደውን ያህል ሲጥር ታዝቤአለሁ። እናም በሞላ አቅም ተወናብዶ ህወሀትን ይቀላቀላል የሚል ጥርጣሬ ለአፍታም ውስጤ የሚገባ አይደለም። የዚያን ሰሞን ከሞላ ክህደት በላይ የግደይ አብሮት ሄዷል መባል አስገርሞኝ ነበር።
.
.
ከአንድ ወር በኋላ ከወደ አስመራ የሰማሁት ያልተጠበቀ መረጃ ነው። ግደይ ወደ አስመራ ተመለሰ.......ዝርዝሩ ገና አልደረሰኝም። ግደይ ትግሉን ዳግም መቀላቀሉን ግን አረጋግጬአለሁ። ሞላ ከመሄዱ ይልቅ የግደይ አብሮ ሄዷል መባሉ ለእኔ ጥሩ ወሬ አልነበረም። አሁን ደግሞ አለመሄዱ ተሰምቷል። ....ላገኘው እሞክራለሁ።

[HOT] Abdu Kiar Tikur Anbessa ጥቁር አንበሳ New Ethiopian Music 2015

http://www.aradatimes.com/watch.php?vid=c6e9f104e
Pause
Current Time
2:31
/
Duration Time
6:35
Loaded: 0%
Progress: 0%
Fullscreen
00:00
Mute
auto