Friday, October 16, 2015

ለ539 ቀናት የተንገላቱት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የቀረበባቸው ክስ ምንም ደጋፊ ማስረጃ ስላሌለው ነጻ ወጥተዋል:: (ከሳልሳዊ ገፅ) እውነት አሸነፈች:

ለ539 ቀናት የተንገላቱት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የቀረበባቸው ክስ ምንም ደጋፊ ማስረጃ ስላሌለው ነጻ ወጥተዋል:: (ከሳልሳዊ ገፅ)
እውነት አሸነፈች:: 
ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን:: የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ሰላሳ ስምንተኛው የካንጋሮ ፍርድ ቤት የ539 ቀናት የብይን ድራማ :: ከተለያዩ አለማቀፍ ሚድያዎች የመጡ ጋዜጠኞች ዲፕሎማቶች የጦማርያኑ ቤተሰቦች እና ወዳጆች እንዲሁም አገር ወዳ ወገን ወዳድ የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን ጉዳይ ለመከታተል በፍርድ ቤቱ የተገኙ ሲሁን ሁኔታው አላመች ያላቸው በስልክ እና በማህበራዊ ድህረገጾች ሂደቱን ልመከታተል ተገኝተዋል::ጦማርያኑ ወደ ወያኔው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጊዜ ባይደርሱም ዛሬ ዳኞች ወደ ስልጠና አልሄዱም::የካንጋሮ ዳኞች የሆኑት ሸለመው;ዘሪሁን እና ታረቀኝ በፍርድ ቤቱ ተገኝተዋል::

ባልሰሩት ጥፋት እና ወንጀል የተክሰሱት ጦማርያን የሚፈለገው ፍትህ ሳይሆን በነጻ እንዲለቀቁ ነው::ዜጎችን በማንገላታት እና በማሰር ስራ ላይ የተሰማራው የስርዓቱ አገዛዝ ፍትህን እንደ ሸቀጥ እየቸበቸባት ንጹሃንን በጠበንጃ ሃይል መዝጋትን አጀንዳው አድርጎ ይዞታል::ጦማርያኑ ወደ ችሎት የገቡ ሲሆን ጉዳዩን ለመከታተል የመጡ ወረፋ በመያዝ ሲገቡ አርፍዶ የመጣው አቃቢ ህግ ብርሃኑ ወደ ችሎቱ ሲገባ እንደ እብት እየተጉተመተመ ብቻውን እያወራ ነበር::ዳኞቹ በግቢው ውስጥ የነበሩ ቢሆንም ወደ ችሎቱ ሲገቡ ግን አርፍደው ነው::የበላይ መመሪያ እና ትእዛዝ በስልክ ሲቀበሉ ችሎቱን አዘግይተውታል::

ዳኞቹ ወደ ችሎት እንደገቡ ዘሪሁን የተባለው የስርዓቱ ዳኛ ከሃሰተኛ ክሱ ጀምሮ የዶክመት ማስረጃዎቹን እንዲሁም የሰው ምስክሮችን አስመልክቶ አንብቦታል::በሚያነብበት ወቅት ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ፊት ፈገግታ እና በራስ መተማመን ይታያል::ዳኞቹ ንባቡን እያቋረጡ ይንሾካሾኩ ነበር::በችሎቱ የታደሙ ብይኑን ለመስማት በጉጉት ሲጠብቁ ታይተዋል::ሁለት በሞባይላቸው ትዊተር ተጠቅመአል የተባሉ ወጣቶች በፖሊስ ተገደው ከችሎት ወጥተዋል::ዳኛው እስካሁን እያነበበ ያለው ነገር እንደሚጠቁመው ጦማሪያኑ ምንም ወንጀል እንዳልፈጸሙ የሚያሳይ ቢሆንም የማስመሰል ድራማው ግን ሕጋዊ ለማድረግ የሚባዝኑት በብይኑ ላይ መሆኑን ያመልክታል::
በብይኑ መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ መከላከል ሳያስፈልጋት በነፃ እንድትሰናበት ብይን ተሰጥቷል። እንዲሁም በፍቃዱ ሃይሉ በነጻ የተሰናበተ ሲሆን ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፍ ብርሃነ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ተሰጥቷል።እንዲሁም አቤል ዋበላ መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ተሰናብቷል::የቀረበባቸው ክስ የሃሰት ሲሆን ማስረጃውን ለክሱ ምንም ድጋፍ እንዳልነበረው ከፍርድ ቤቱ ዳኞች የተነበበው የብይን ውሳኔ ዝርዝር ሂደት ይጠቁማል::ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን::

No comments:

Post a Comment