Thursday, October 29, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ


‪#‎የአርባ‬ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው፡፡
‪#‎ጋምቤላ‬ ጎግ ወረዳ ውስጥ የሞርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰንዝረው አንድ የጦር ሰፈር ደመሰሱ፡፡
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በመላ አገሪቱ ሲያካሄደው በቆየው ስብሰባ ላይ ባልተሳተፉ መምህራን እና ሌሎች ሰራተኞች ላይ የ176 ብር ቅጣት በየነ፡፡
‪#‎በጅንካ‬ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅ ተነስቷል፡፡
‪#‎በኮንሶ‬፣ ቦረና፣ ተልተሌ፣ በና፣ ፀማይ፣ እና ሐመር ከፍተኛ ረሃብ መግባቱ ተሰማ፡፡
===================================================
የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው፡፡

እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ የጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አገልጋይ ባለስልጣናት በክልሉ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተብየ መሪነት ከፍተኛ ስብሰባ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ከአስተዳዳሪው እና ከአፈጉባኤው በስተቀር ሁሉንም የመስተዳድሩ አሻንጉሊት ባለስልጣናት ቦታ የመቀያየር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

ጋምቤላ ጎግ ወረዳ ውስጥ የሞርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በአካባቢው ሰፍሮ በሚገኝ የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰንዝረው አንድ የጦር ሰፈር ደመሰሱ፡፡
ባለፈው ሳምንት ዕረቡ ጥቅምት 10 ቀን 2008 ዓ.ም የሞርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የህወሓትን የጦር ካምፕ ሙሉ በሙሉ ደምስሰው በቁጥጥር ስራቸው አድርገው ለተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ የጦር ተሸከርካሪ ከነሹፌሩ ማርከው ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡
በሌላ በኩልም በጋምቤላ ክልል አስተዳደር የብሄርና ብሄረሰቦችን በዓል በጋምቤላ ለማክበር የአኙዋክ፣ መዠንገር እና ኑዌሪን ባህል የሚወክሉ አራት የእሳር ጎጆዎች በአራት ሚሊዮን ብር ወጭ አሰራሁ ማለቱ የክልሉን ህዝብ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
የህወሓት አገዛዝ በመላ አገሪቱ ሲያካሄደው በቆየው ስብሰባ ላይ ባልተሳተፉ መምህራን እና ሌሎች የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ የ176 ብር ቅጣት በየነ፡፡
መምህራንና ተማሪዎችን በአንድ ለአምስት በመጠርነፍ ቀፍድዶ ይዞ በየጊዜው አስገድዶ እየሰበሰበ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የማጥመቅና አባላትና ደጋፊዎችን የመመልመል ተግባር በሰፊው ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
በያዝነው ዓመት በተደረገው የተለመደ ርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ማጋበሻ እና እድሜ መቀጠያ ስብሰባ ላይ በአጠቃላይ በአገሪቱ ከሚኙገት መምህራን 60 በመቶዎቹ ጨርሶ ያልተገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ ስብሰባውን የተካፈሉ መምህራን ደግሞ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ በየመድረኩ ሲደሰኩርላቸው የከረመውን ዲስኩርም አገዛዙ አስገድዶ ሊግታቸው እንደማይችልና እደማይዋጥላቸው ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡

በጠራው ስውር የፖለቲካ አጀንዳ ያነገበ ስብሰባ ላይ በተገኙ ጥቂት መምህራንና ሌሎች የአስተዳደር ሰራተኞች ሲናጥ የቆየው የህወሓት አገዛዝ ያልተገኙትን 60 በመቶ የአገሪቱን መምህራን 176 ብር ከደሞዛቸው በመቁረጥ ሊቀጣቸው ወስኗል፡፡
በጅንካ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅ ተነስቷል፡፡
የህወሓት አገዛዝ በጅንካ የተነሳውን ጠንካራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ለማርገብ ከሌላ አካባቢ የፌደራል ፖሊስና ልዮ ኃይል ጦር ጭኖ በአካባቢው አስፍሯል፡፡ ሆኖም አመፁን በኃይል ለማብረድ በአካባቢው ለሚገኙ የህወሓት የታጠቁ ኃይሎች ህዝቡ በአንድነት ተባብሮ ምግብና ውሃ መሸጥ በማቆሙ የፌደራል ፖሊስና የልዩ ኃይል አባላት በአካባቢው ለመቆየት በእጅጉ ተቸግረው ይገኛሉ፡፡
አገዛዙ ከሌላ አካባቢ ምግብና ውሃ ገዝቶ በማቅረብ ችግሩን በማቃለል የታጠቁ ኃይሎቹን በአካባቢው ለማቆየት ጥረት እያደረገ ነው፡፡

በኮንሶ፣ ቦረና፣ ተልተሌ፣ በና፣ ፀማይ፣ እና ሐመር ከፍተኛ ረሃብ መግባቱ ተሰማ፡፡
በበርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ምክንያት ከ16 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለምግብ እጥረት ተዳርጎ የሚደርስለት ጠፍቶ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ ከፍተኛ እልቂት እያንዣበበበት ይገኛል፡፡ ነገር ግን የህወሓት አገዛዝ አሁንም ቢሆን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም ለሚያስችሉት ተግባራት ከፍተኛ ወጭ እያፈሰሰ በረሃብ የሚያልቀው ኢትዮጵያዊ ምንም ደንታ አልሰጠውም፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመድፋት ከፍተኛ ድግስ ማሰናዳቱን እና በከፍተኛ የውሎ አበል ክፍያ በያዳራሹ በስብሰባ ስም መመሸሸጉን አሁንም ቀጥሎበታል፡፡

ህወሓት ድርቅንና በህዝብ ላይ የሚመጣን የረሃብ እልቂት እንዳውም ለገቢ ምንጭነት የመጠቀም የቆየ ልምድ እና ባህል እንዳለው ብዙዎቹ በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
በተለይም ደግሞ አሁን በኮንሶ፣ ቦረና፣ ተልተሌ፣ በና፣ ፀማይ፣ እና ሐመር የገባው አደገኛ ጠኔ ከሌሎች አካባቢዎች የከፋ እና ጊዜ የማይሰጥ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment