Thursday, October 15, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ‪#‎በኮንሶ‬ ህዝብ እና በህወሓት አገዛዝ መካከል የከረረ ግጭት ተፈጠረ፡፡ ‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ወደ "ትግራይ ክልል" ቆርሶ ሊያስገባቸው ወዳቀዳቸው "የአማራ ክልል መሬቶች" ከትግራይ ልዩ ኃይል ተውጣጥቶ የተደራጀ ጦር ወስዶ እያሰፈረ መሆኑ ታወቀ፡፡ #የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያ ህዝብን እንደ ማደናገሪያ የሚጠቀምበት የህዳሴ ግድብ መዋጮ ዋንጫ ወደ ጎንደር መጥቶ ህዝቡ ያለፍላጎቱ በግድ ካላወጣህ ተብሎ እየተዋከበ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ ‪#‎በአራት‬ ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች ጥምረት የተቋቋመውን የአገር አድን ንቅናቄ ለማፍረስ ጥቂት ተከታዮቹን ይዞ ለህወሓት አገዛዝ እጁን የሰጠው የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ሞላ አስግዶም በጠና ታሞ ከሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ተረጋገጠ፡፡ ‪#‎በአዲስ‬ አበባ የአዲሰ ክፍለ ከተማ የቀበሌ 08 ነዋሪዎች ከያሉበት በፖሊስ እየታደኑ ወደ ማጎሪያ ቤት እየተወሰዱ መሆናቸው ተዘገበ፡፡ ====================================================


በኮንሶ ህዝብ እና በህወሓት አገዛዝ መካከል የከረረ ግጭት ተፈጠረ፡፡
የቤሄሮችን ነፃነት "እስከ መግንጠል ድረስ አውጃለሁ" ሲል በተደጋጋሚ የሚደመጠው የህወሓት አገዛዝ ነገር ግን እሱ "የደቡብ ብሄርና ብሄረሰቦች" ብሎ በከፈለው ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ጎሳዎች ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ የነፃነት ጥያቄ በማንሳታቸው በክፉ የቅራኔ ረግረግ ውስጥ ተውጦ ይገኛል፡፡ጎሳዎቹም ለ25 ዓመታት የተጫናቸውን የጭቆና ቀንበር ለመስበር ተግባራዊ የነፃነት ትግል ማድረግ ጀምረዋል፡፡
በመሆኑም ህወሓት በደቡብ ኢትዮጵያ ምድር ከልዩ ልዩ ጎሳዎች ጋር ጥይት ሳይተኮስ ውሎ ያደረበት አንድም ጊዜ የለም፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የኮንሶ ህዝብ የዞኑ ዋና ከተማ ጉማይዴ መሆኗ ቀርቶ ኮንሶ መሆን አለበት የሚል እና ሌሎችን የመብት ጥያቄዎች አንስቶ ከአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ከፍተኛ ግብግብ ገጥሟል፡፡ 
በአሁኑ ስዓት በኮንሶና አካባቢው በህዝቡና በአገዛዙ መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ አይሎ ከፍተኛ ውጥረት እንደሰፈነ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ወደ "ትግራይ ክልል" ቆርሶ ሊያስገባቸው ወዳቀዳቸው "የአማራ ክልል መሬቶች" ከትግራይ ልዩ ኃይል ተውጣጥቶ የተደራጀ ጦር ወስዶ እያሰፈረ መሆኑ ታወቀ፡፡
የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ዘረኛ ቡድን የስልጣን ዕድሜውን ለማራዘም እየተጠቀመባቸው ከሚገኙት ስልቶች አንዱ እና ዋነኛው በፌደራሊዝም አስተዳደር ስም የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ፣ በቋንቋና በጎሳ ከፋፍሎ የአንደኛውን ርስት ለሌላው ነጥቆ በመስጠት እርስበርስ አጋጭቶ አንድነቱን ማዳከም ነው፡፡ አሁንም በዚህ እኩይ ተገባሩ ቀጥሎ ቆርሶ ወደ "ትግራይ ክልል" ሊያስገባቸው ያቀዳቸውን አብራሃ ጅራ እና "ሌሎች የአማራ ክልል" መሬቶች ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የትግራይ ልዩ ኀይል ጦር ወደ አካባቢው እየላከ በማስፈር ላይ ይገኛል፡፡
የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያ ህዝብን እንደ ማደናገሪያ የሚጠቀምበት የህዳሴ ግድብ መዋጮ ዋንጫ ወደ ጎንደር መጥቶ ህዝቡ ያለፍላጎቱ በግድ ካላወጣህ ተብሎ እየተዋከበ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
የህወሓቶች ሎሌ የሆኑት የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ባለስልጣናት ጌቶቻቸው የጣሉባቸውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመዋጮ ገንዘብ ገደብ ለማሟላት ህዝቡን ጠይቀው ፈቃደኛ ሳይሆንላቸው በመቅረቱ በጉልበት እያስገደዱት ናቸው ፡፡ 
ሰለዚህ ለማዋጣት ፈቃደኛ ያልሆነው ህዝብ በጠቅላላ 150 ብር ቅጣት የተጣለበት መሆኑ ታውቋል፡፡ በተለይም ደግሞ የአገዛዙ ካድሬዎች የደባርቅ ፣ ዳባት እና ጭልጋ ነዋሪዎችን በግድ ካላዋጣችሁ እያሉ ከድህነታቸው በላይ እያስጨነቋቸው እንደሆነ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
በአራት ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች ጥምረት የተቋቋመውን የአገር አድን ንቅናቄ ለማፍረስ ጥቂት ተከታዮቹን ይዞ ለህወሓት አገዛዝ እጁን የሰጠው የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ሞላ አስግዶም በጠና ታሞ ከሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ተረጋገጠ፡፡
"ተከተሉኝ ስራ አለ" የሚል ድፍን ያለ መመሪያ ብቻ በመስጠት ይዟቸው ወደ ኢትዮጵያ ሊሻገር ካንቀሳቀሳቸው ታጋዮች አብዛኞቹን በጠይት ካስጨረሰ በኋላ ለጥቂት አምልጦ የህወሓትን ዘረኛ ቡድን መልሶ የተቀላቀለው ሞላ አስገዶም እርስበርሳቸው የሚጋጩ፣ ምንም አይነት መሰረት የሌላቸው ነጭ ውሸቶች በህወሓት መገናኛ ብዙኃንና በየሆቴሉ እየተገኘ ሲናገር ለጥቂት ቀናት ቆይቷል፡፡የሞላ ንግግር እራሱንና አገዛዙን በኢትዮጵያ ህዝብ ትዝብት ውስጥ ጥሏቸው አገር አድን ንቅናቄ የመሰርቱትን የነፃነት ድርጅቶች ሞገስ ከፍ አድርጎ ተቀባይነታቸውን አሳድጓል፡፡
በህወሓት ርዕዩተ አለም ይሁዳዊነት የተጠመቀው ሞላ አስገዶም ለኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ከመቅረቡ በፊት በህሊና ፍርድ ተይዞ በገጠመው ድንገተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ቀውስ በጠና ታሞ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ባጣዕር ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ የአዲሰ ክፍለ ከተማ የቀበሌ 08 ነዋሪዎች ከያሉበት በፖሊስ እየታደኑ ወደ ማጎሪያ ቤት እየተወሰዱ መሆናቸው ተዘገበ፡፡
መስከረም 29/2008 ዓ.ም ከመሬት ሃብት ልማት የተወከለ ካድሬ የቀበሌውን ነዋሪዎች ሰብሰቦ "ያላቹህበትን መሬት መንግስት ለልማት ሰለሚፈልገው ቤታቹህን አፍርሳቹህ በአስቸኳይ እንድትለቁ እና በምትኩ ቤት አስከሚገኝላቹህ ድረስ ለቤት ኪራይ ለአያንዳዱ አባውራ መንግስት 11 ሺህ፣ 11 ሺህ ብር ይሰጣል..." በማለት ሊያሳምናቸው ይሞክራል፡፡ ነገር ግን የቀበሌው ነዋሪዎች የካድሬውን ንግግር ፍፁም ተቃውመው፣ "ለዘመናት የኖርነበትን ቤት አፍርሰን እናተን አምነን ልጆቻችን ይዘን ጎዳና ላይ አንወድቅም..." የሚል ምላሽ ሲሰጡ፤ ከዚያም ካድሬው ደግሞ በበኩሉ የቀበሌውን ነዋሪዎች ጸያፍ ሰድቦችን በመሳደብ ለማስፈራራት ሲሞክር የቀበሌው ነዋሪዎች በካድሪው ላይ የኃይል እርምጃ ወስደው ስብሰባው ተበጥብጦ ያለምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ 
በወቅቱ ስብሰባውን ይመራ የነበረው የህወሓት ካድሬ በቀበሌው ነዋሪዎች ክፉኛ ተደብድቦ ሆስፒታል መግባቱን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ 
ከዚህ ጋር ተያይዞ በከፍለ ከተማው የሚገኙ ወጣቶች በፖሊስ እየታደኑ ወደ ማጎሪያ ቤት እየተጋዙ እንዳሉና ክፉኛ እየተደበደቡ እንደሚገኙም ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም አካባቢው በፖሊስ ተወሮና ውጥረት ነገሶ ይገኛል፡፡ 
በመላ አገሪቱ በተለያዩ ከተሞች በተልይም በአዲስ አበባ የዜጎች ቤት በዶዘር እየፈረሰ የህወሓት አገዛዝ ባለቤት የነበሩትን ኢትዮጲያዊያን ለጎዳና ተዳዳሪነት ዳርጎ ቦታውን ለባላሃብቶች ቢሸጥም ባዶ ቦታው ለዓመታት እስከ አሁንድረስ በቆርቆሮ ብቻ ታጥሮ የሚገኝ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ህዝብ ያወቀው እውነት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment