የኢትዮጵያ መንግስት ለኬንያ መንግስት የጻፈው የሚስጥር ደብዳቤ ይፋ ሆነ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ጸረ ሽብር ግብረ ሀይል የተጻፈው ይሄ ደብዳቤ 66 የሚሆኑ ዜጎችን አሳልፎ እንዲሰጠው የኬንያን መንግስት ጠይቋል።
እነዚህ ዜጎች በኬንያ በስደት የሚኖሩና ጉዳያቸውም በአለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት በመታየት ላይ ያለ ሲሆን አንዳንዶቹም ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ወቅት ጀምሮ ኑሮዋቸውን በኬንያ ያደረጉ መሆናቸው ታውቋል። የአለም አቀፍ ህጎች ስደተኞች በምንም መልኩ ተላልፈው እንደማይሰጡ የሚደነግግ ቢሆንም የኬንያ መንግስት በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳልፎ በመስጠ ይወቀሳል።
ይህንንሚስጥራዊ ሰነድ ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ። እንዲሁም ሼር በማድረግ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያግዙ። > >> http://goo.gl/ySIv8U
No comments:
Post a Comment