Friday, October 23, 2015

ኢሳት ዜና

*እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ አምባገነን ሥርዓት ፊት አሸባሪ ነው። ከታሰረበት 2004 ዓ.ም ወዲህ ዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለ4 ጊዜ ለሞያው ባለው ጽናት ሸልመውታል።
የተበባሩት መንግስታት ድርጅት አጣሪ ቡድን የእስክንድር ክስ መብቱን ተጠቅሞ በመናገሩና በመጻፉ ነው ብሎ በህወሓት ፍርድ ቤት የተቀነባበረበት ክስ ፖለቲካዊ እንደሆነ ገልጿል።
ሰሞኑን ፔን ካናዳ ለእስክንድር ሽልማት መስጠቱን ተከትለን አንድ ዝግጅት አሰናድተናል።

*የሎሚ መጽሔት ሥራ አሰኪያጅ ግዛው ታዬ መክስረም 27 2007 ዓ.ም ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት፣ ሀሰተኛ ወሬዎችን አሳትሞ በማሰራጨትና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ በመንቀሳቀስ በሚሉ ወንጀሎች ክሶች በሶስት አመት ከሶስት ወር እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ።
ሰሞኑን ደግሞ በታክስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ተብሎ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት እና የ100 ሺህ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት። ግዛው ከሀገሩ ተሰዷል። ኢሳት አገኝቶት ስለፍርዱ አነጋግሮታል።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ዛሬ እና ነገ በሚል ርዕስ የተካሄደው ውይይት በሲሳይ አጌና ተዘጋጅቷል
ኢሳት የናንተው የሕዝብ ልሳን!

No comments:

Post a Comment