ስለአንዳርጋቸው አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየሁ ነው። አንዳርጋቸው በጣም ደህና ነው ። አያያዙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ ቢመጣም፣ በጥሩ መንፈስ ላይ ይገኛል። ህክምና፣ በህግ ባለሙያ መጎብኘት የመሳሰሉት መሰረታዊ መብቶቹ ሊጠበቁለት አልቻለም። የእንግሊዝ አምባሳደር በቅርቡ ቃሊቲ ሄደው ሲጎበኙትም አያያዙ አስከፊ መሆኑን ነግሯቸዋል። በቃልቲ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ ታስሯል። ሃይላችንንና ትኩረታችንን ነጻይቱን ኢትዮጵያን በመመስረት ላይ እናውል እንጅ በአሉባልታ ጊዜያችንን አናጥፋ ። ሁሌም ማዬት ያለብን ግን ትግልና መስዋትነት የማይነጣጠሉ ነገሮች መሆናቸውን ነው። መሰዋትነትን የሚፈራ ትግል አይጀምርም፣ ትግል ውስጥ ያለም መሰዋትነትን ከፈራ ድል አያደርግም፣ ጉዞውም በአጭር ይቀራል። አንዳርጋቸው ማንኛውንም መስዋትነት ለመቀበል ተዘጋጅቶ ወደ ትግል የገባ በመሆኑ፣ የሚረበሽበት አንዳች ምክንያት የለውም። ይህን ደግሞ እኔ አይደለሁም የምለው፣ በተደጋጋሚ በሰጣቸው ቃለምልልሶች ላይ ሲገልጸው የነበረ ሃቅ ነው።
No comments:
Post a Comment