-ነዋሪዎች "መሰረታችን ሕገ መንግስቱ ነው ተብሎ የወልቃይት ነዋሪዎች ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገና የሕዝቡን ስነ ልቦናዊ፣ ባሕላዊ ወግን ያላማከለና ያላጠቃለለ ክልላዊ አከላለል በማድረግ የወልቃይት ሕዝብ የማይፈልገውንና የማያምንበትን በመጫን በግድ ወደ ትግራይ እንድንካለል መደረጋችን በውስጣችን ያለውን ማንነታችንን በመጨፍለቅ እንድንቀበል እየተደረግን ነው ፣ዛሬ ስነ ልቦናችን የማይቀበለውን ሕወሃት በዘዴ ማንነታችንን ለማሸማቀቅ እየሞከሩ ነው" ብለዋል ። በማህበራዊ የመገናኝ ብዙሃን በተለቀቁ የስብሰባ ቪዴዮዎች ላይ አንድ ተናጋሪ ''እኛ እንደ ሲም ካርድ እኮ አይደለም አማርኛን የምንናገረው።
በውስጣችን፣በደማችን፣በስጋችን በዘራችን ሁሉ የመጣ ቋንቋ፣የመጣ ባሕል፣የመጣ ስነ ልቦና ፣የመጣ ሕይወትና ኑሯችን ነው ያሉት ተናጋሪው፣ እኛነታችን ይበልጣል ታሪካችን ይበልጣል የአማራነታችን ጥያቄ በሕገ መንግስቱ ይፈታልን።'' ሲሉ ጠይቀዋል፡ ሁለተኛው ተናጋሪ በበኩላቸው ''ባሕላችን እየተረገጠ ነው።አንድ ብሔር ብሔረሰብ ማለት አንድ ዓይነት ቋንቋ፣ባሕል መልክዓምድር ያለው ይላል በዚህም ከአማራ ጋር ነው መሆን ያለብን።ቋንቋ መናገር ብቻውን ማንነቱን አይገልጽም።እኔ ነኝ አማራም ትግሬም መሆን መወሰን ያለብኝ በስነልቦና ስለተሳሰርን ወደ አማራ ክልል መካለል አለብን'' ብለዋል። "ሕገ መንግስቱ የፈቀደልን መብቶች ተጥሰው በቋንቋችን እንዳንጠቀም በግድ ተደርገናል የአማራነታችን ማንንነት በሕገ መንግስቱ ይፈታልን እኛነታችን እና ታሪካችን ይከበርል።ብዙ በደሎች ደርሶብናል፣ንብረቶች ተዘርፈውብናል፣ ዜጎች ተገለውብናል የደረሱብን በደሎች ይታዩልን" ሲሉ ሰቆቃቸውን አሰምተዋል። የወልቃይት ነዋሪዎች ችግራቸውን አስመልክተው ለፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልልና ለአማራ ክልል ቢያመለክቱም እስካሁን ድረስ ሰሚ አለማግኘታቸው ነዋሪዎቹ ጠቁመው አሁን እስከመጨረሻው ድረስ በጥያቄያቸው እንደሚገፉት አሳስበዋል። ሌላ ተናጋሪ ደግሞ ነጻ የሆነ መድረክ ካገኘን እንናገራለን ካሉ በሁዋላ፣ ዛሬ አማራ ነኝ አማራነቴ ይከበር ብለዋል ይህ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ቪዲዮ መቼ እንደተቀረ የተገለጸ ነገር የለም ይሁን እንጅ ከቪዲዮው ለመረዳት የሚቻለው ቀረጻው በቅርብ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ነው።
No comments:
Post a Comment