ይህ የምናደርገው መሰዋእትነት በሂዎታችን ለአንዴና ለመጨረሻ የሚደረግ ታሪካዊ መሰዋእትነት ነው ፤ ይህ የመጨረሻው እንደሚሆን አትጠራጠሩ ትግሉ እየፈጠነ ነው.. አቶ ናእምን የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የውጪ ዘርፍ ሃላፊ በሜኒሶታ ካደረጉት ንግግር
Oct 19, 2015
የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ ሂደት ቀጥሎ ቅዳሜ በሜኒሶታ ያደረገው ህዝባዊ ስብሰባ የተዋጣና በአይነቱ ልዩ የሆነ እንደነበር ተገልጾል።
የከተማው ነዋሪ ታላቅ ተሳትፎ ያድረገበት ፣ የሁሉም የእምነት አባቶች የተሳተፉበት በዚህ ዝግጅት አቶ ናእምን የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የውጪ ዘርፍ ሃላፊ ና የግንባሩ የምክር ቤት አባል በተገኙበት ታሪካዊ የተባለለት ደማቅ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሂደት ተደርጎል። አቶ ናእምን ህዝቡ አሁን ሁሉም ተሞክሮ የቀረውን ብቸኛና ወደን ሳይሆን ተገደን የገባንበትን ታሪካዊ ሀገርን የማዳን የነጻነት ትግሉን የምንቀላቀልበትና የምንረዳበት ጊዜ አሁን ነው። ምናልባትም በሂዎታችን ለነጻነት የምናደርገው የመጨረሻ እርዳታ እና መሰዋእትነት ሊሆን የሚችል ትግል ላይ ነው ያለነው። ኢትዮጵያ በታሪኮ እንደ ወያኔ ያለ የሀገር ውስጥ ወራሪ ጠላት ገጥሞት አያውቅም። ይህን ትግል በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዴሞክራሲ; የነጻነት የፍትህ ትግል የመጨረሻ እንደምናደርገው አትጠራጠሩ ብለዋል።
በሜኒሶታ አዘጋጅ ኮሚቴ የጣይቱ ልጆች ፎቶ ግራፍ ለጫራታ ቀርቦ ከፍተኛ በሆነ ሽያጪ መሸጡን ገልጸው በርካታ ገንዘብ ለድርጅት ማስገባታቸውን አስታውቀዋል። ይህን ዝግጅት ያዘጋጀው በሜኒሶታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው እንደሆነም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በጆርጂያ አትላንታም ድርጅቱ የተሳካ የገቢ ማሰባሰብ እንዳደረገ ገልጾልናል። የአትላንታ የአርበኞች ግንቦት 7 ቻፕተር እንደገለጸው በዚሁ ዝግጅትም አቶ ናእምን ተገኝተው ሰፊ ማብራሪያ በቪዲዮ የተደገፈ ዝግጅት ለተሳታፊው አቅርበዋል።
የአርበኞች ግንቦት 7 የሀገር የማዳንና የድጋፍ ዘመቻ በመላው አለም ቀጥሎ የፊታችን ኦክቶበር 24, 2015 በቺካጎ ኢሊኖይ፣ በተመሳሳይ ፍራክፈርት ጀርመን፣ ኦክቶበር 25, 2015 በሳንሆዜና ቤይ ኤሪያ፣ ኦክቶበር 31, 2015 በሲዊዲን፣ በኖምበር 1, 2015 ቦስተን, በኖቨምበር 7, ፊኒክስ አሪዞና, በኖቨምበር 14, 2015 ኖርዝ ካሮሊና እና በመጨረሻም በኖቨምበር 22, ሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ በማድረግ ዘመቻው እንደሚጠናቀቅ አዘጋጅ ኮሚቴው ለኢሳት አስታውቆል። በዚህ የ4ወር ዘመቻ ድርጅቱ አቅዶ የተነሳው ግብ መምታቱን ኮሚቴው አስታውቆል።
ባአጠቃላይም የኢትዮጵያን ተሳትፎ ጎልቶ የታየበት የሀገር ፍቅርና ቤተሰባዊነት የተንጸባረቀበት ዝግጅቶች በየከተማው መታዩትን አስታወሰዋል።
No comments:
Post a Comment