ዛሬ ደግሞ የትግል ጥሪ ወረቀቶቹ የክልል ዋና ዋና ከተሞችን ጨምሮ በአንዳንድ የዞን ከተሞች እየተሰራጩ መሆኑ ታውቋል!
የነፃነት ትግሉን የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን የትግል ጥሪዎችን በመበተኑ ላይ እንዲሳትፉ ከንቅናቄው ጥሪ ቀርቧል!
በአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የተዘጋጁት ከታች የምትመለከቷቸው የትግል ጥሪ ያዘሉ በራሪ ወረቀቶች አዲስ አበባን አጥለቅልቀዋታል። በራሪ ወረቀቶቹ ዛሬ ደግሞ የክልል ዋና ዋና ከተሞችን ጨምሮ በአንዳንድ ታላላቅ የዞን ከተሞች በስፋት እየተሰራጩ ነው። በወረቀት ስርጭቱ ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 ትን የነፃነት ትግል የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን በስፋት እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል። በራሪ ወረቀቶቹ የሚደርሷቸው ኢትዮጵያውያን በጥንቃቄ በ 5 ኮፒ በማባዛት (ወይም የትግል ጥሪዎቹን በወረቀት ላይ በፓርከር በመገልበጥ) እንዲያሰራጩና የነፃነት ትግሉን እንዲያፋጥኑ ከንቅናቄው ጥሪ ቀርቧል።
በባህር ዳር የተደራጁት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች ከጥቂት ሳምንታት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ከተማዋን የትግል ጥሪዎችን ባዘሉ ወረቀቶች አጥለቅልቀዋት እንደነበር አይዘነጋም።
ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ወደ ፊት!
No comments:
Post a Comment