የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው ራሱን በመንግስትነት ስም የሰየመው የህወሓት አገዛዝ ምንም እንኳን ትምህርትን አስፋፍቻለሁ ብቻ ለማለት ያክል በየአካባቢው ከ30 በላይ የይስሙላህ ዩኒቨርሲቲዎችን ቢከፍትም የትምህርት ጥራት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቶ የኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በድንቁርና ማዕበል ተመትቶ ባላዋቂነት ባህር ሰጥሞ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበት ይገኛል፡፡ -በአሁኑ ጊዜ አንጋፋውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማለት በሚቻል ሁኔታ ወጣቶች በእውቀት እና በግብረገብነት የሚቀረፁባቸው ሳይሆኑ የካድሬ መፈልፈያዎች ሆነው ይገኛሉ
፡፡ዩኒቨርሲቲዎች በየዓመቱ ዕውቀት ሳይሆን ክርታስ ብቻ እየቸሩ የሚያስመርቁት በርካታ ቁጥር ያለው ወጣት ስራ ስለማያገኝ በሱስ ተጠምዶ ማንነቱን ከማጣት አለያም ተሰዶ በየበረሃው ረግፎ ከመቅረት በዘለለ ለአገራችን እያበረከተ የሚገኘው እዚህ ግባ የሚባል ጉልህ አስተዋፅኦ የለም፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ ላይ የሰፈነውን ፍፁም የሆነና የለየለት የባርነት አገዛዝ እና ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት አድባር መሆናቸው ቀርቶ ወደ ካድሬ ትምህርት ቤትነት መቀየራቸውን በመቃውም እንዲሁም በተጨማሪ ከምረቃ በኋላ በአገሪቱ ምንም አይነት የተስፋ ጭላንጭል ባለማየቱ ነው ወጣቱ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ራሱን አንቆ ለመግደል የበቃው፡፡ ዘረኛውን የህወሓት አገዛዝ በመቃውም ራሱን ያጠፋው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አካባቢዎች ግፍ ያንገሸገሻቸው ወገኖቻችን ስርዓቱ ራሳቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ጨክነው እንዲገድሉ ጋብዟቸዋል፡፡ ራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር የኔሰው ገብሬ ሁሌም ሲታወስ የሚኖር ጀግና የፖለቲካ አክቲቪስት ነበር፡፡ በአሁኑ ስዓት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47435#sthash.QWwKTBdY.dpuf
No comments:
Post a Comment