Wednesday, October 21, 2015

እንግሊዝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይን “ለንግድ ጥቅሟ ” ስትል እንዳትረሳው ተየቀች


ለእንዳርጋቸው መታፈን ተጠያቂ የተባሉት ዶ/ር ቴዎድሮስን ሎንዶን ላይ መጋበዝ እደጋ አለው ተባለ 
ከታምሩ ገዳhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/47565
ካለፈው አመት የፈረንጆቹ ሰኔ ወር መባቻ ላይ ወደ ኤርትራ ሲጓዙ የመን(ሰነኣ ) አለም አቀፍ አወሮፕላን ጣቢያ ላይ ታፈነው ለ አዲስ አበባ መንግስት ተላለፈው የተሰጡት እና ቀደም ሲልም በሌሉበት ኢትዮጵያ ውስጥ በ 2009 አኤአ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የግንቦት 7ቱ ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እጣ ፈንታ ያሳሰበው አንድ ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእንግሊዝ መንግስት “ለጥቅሙ ሲል “የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይን ችላ እንዳይል ዳግም እስጥነቀቀ።
በሰው ልጆች ላይ የሞት ብይን እንዳይተገበር የሚሟገተው እና መቀመጫውን ሎንዶን(እንግሊዝ) ያደረገው አለማቀፉ ሪትሪቪው ድርጅት በነገው እለት (ጥቅምት 21 2015 )ሎንዶን ላይ በእንግሊዝ መንግስት ከፍተኛ የውጪ ጉ/ሚ/ር ባለሰልጣናት እና በኢትዮጵያ አቻዎቻቸው መካከል የሚደረገውን ንግድ እና ኢንቨስትመንት ተኮር ፎርምን በማሰመልከት ዛሬ ባወጣው መግለጫው “ ፎረሙ የሚካሄደው እንግሊዝ እንደ ኢትዮጵያ እና እንደ ስውዲ አርቢያ ከመሳሰሉት በሰበዊ መብት ይዞታቸው ከመወገዙ አገሮች ጋር ያላት ቁርኝት አወዛጋቢ በሆነብት ወቅት ነው ።” ያለው የመብት ተማጋቹ ድርጅት “ ከዚህ በሁዋላ የሰበዊ መብት ጉዳይ የእኛ ቅድሚያ አይሆንም ያለው የእንግሊዝ መንግስት አንዳርጋቸውን አፍነው ከወሰዷቸው ባለሰልጣናት (እነ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ይገኙበታል ተብሏል ) በንግድ ዙሪያ ፎረም መክፈቱ እና የእንግሊዝ ዜግነት ላላቸው ፣በሌሉበት የሞት ፍርድ ለተበየነባቸው እና የሶስት ልጆች አባት ለሆኑት ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ዋንኛ ተጠያቂ የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስን በንግድ ሽፋን መቀበል ተጨማሪ ስጋት እና የተሳሳተ መልእክት ያሰተላልፋል።” በማለት የሪትሪቪው ዋና ሃላፊ የሆኑት ሚሲስ ማያ ፎአ ሰጋታቸውን ገልጸዋል።

በሰተመጨረሻም ሚሲስ ማያ “ እንግሊዝ ከአጋሮቿ የንግድ ሽርክና ማደረጓ አንደ ተጠበቀ ሆኖ በሌላ ጎኑ ግን ከእንደ ኢትዮጵያ እና እንደ ሰወዲ አረቢያ ከመሳሰሉት አገሮች ጋር ግብይት ሰታደረግ የሰበኣዊ መብት ረገጣ ሰለባዎችን (እንደ አቶ አንዳርጋቸው የመሳሰሉትን) በጭራሽ መዘንጋት የለባትም።የእንግሊዝ የውጪ ጉ/ሚ/ር ባለሰልጣናት የነገው ፎርምን በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ በቀጥታ የሚጥይቅበት አጋጣሚ ሊያደረገው ይገባል።” በማለት ሎንዶን አቋሟን እንድትፈተሽ የመብት ተማጋቹ ድርጅት ባለሰልጣኑዋ አሳስበዋል።የአቶ አንዳርጋቸው ላለፉት 16 ወራት ከቤተሰቦቻቸው አይታ ፣ከህግ አማካሪዎቻቸው ፣ ከኢምባሲ ሰዎች ፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከመሳሰሉት ርቀው መታሰራቸው አንዳለ ሆኖ የአገዛዙ የውጪ ጉ/ሚ/ር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም በቅርቡ ከአሜሪካ ራዲዮ የአማሪኛው ክፍል ጋር ባደርጉት ቃለ ምልልስ “አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ አዲሱ የናዝሬት ጎዳናን ጎብኝተዋል፣ ላፕ ቶፕም ተሰጥቷቸው ከእስር ቤት መጽሐፍ ለማሳተም በማገባደድ ላይ ናቸው ።”ማለታቸው በበርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ በዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም። የህንኑ በነገው እለት በማእከላዊ ሎንዶን የሚከናወነውን የእንግሊዝ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሰልጣናት ፎረምን በተመለከት በመዲናይቱ እና በእካባቢዋ የሚገኙ በርካት ኢትዮጵያዊያን እና ተወለደ ኢትዮጵያዊን እንደ ከዚህ ቀደሙ በሰፍራው በመገኝት ተቃውሟቸውን እና ስጋታቸውን በሰላማዊ መንገድ ያሰማሉ ተብሎ የጠበቃል።በሌላ ተመሳሳይ ዜና የ16 አመቷ ሴት ልጃቸው ሕላዊት አንዳርጋቸው ከ 5 የት/ቤት ጉደኞቿ ጋር በመሆን በአባቷ መታሰር ዙርያ የሚያውጠነጥን ተውኔት በቅርቡ ሎንዶን ከተማ ውስጥ ለበርካታ ታዳሚዎች በማቅርቧ የተነሳ ላይበሪቲ(ነጻነት ) ከተባለ ድርጅት የአመቱ ተሸላሚ ሆና ሰሞኑን መቅረቧ አና ሸልማቱም እስርኛው እና ወላጅ አባቷን ለማስፈታት እርሷ ፣ ቤተሰባቸው እንዲሁም የተቀረው የእቶ እንዳርጋቸው ደጋፊዎች ለጀመሩት ሰላማዊ ትግል ጉልበት እና ብርታት እንደሚሰጥ 

No comments:

Post a Comment