Sunday, October 11, 2015

ከሕዝብ እያታ የሚያመልጥ ከቶም አይኖርም. -----------------------------------


የአዲስ አበባን ፎቆች የነማን ናቸው ,እንዴትስ ተሰሩ,በማን ተሰሩ ,በማን ስም ነው?
እነዚህ ጥያቄዎችን ምናልባት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቢቀርቡለት መልሱ ቀላል ይሆናል ወደፊት ምናልባትም ሕዝብ ይህንን በቅደም ተከተል ለመለየት እንደማትቸገሩ እርግጠኞች ነን.
ከኢትዮጵያ የኑሮ ሁነታዎች በመነሳት ምናልባት የአንድ ከፍተኛ የወያኔ ባልስልጣን ደሞዝ አዜብ መስፍን የመለስ ደሞዝ 5000 ብር ነው ካለችውም በመነሳት አንድ ጄኔራል ደሞዙ 10,000 ብር ይሆናል ብንል እንኳን እንዴት ነው ይህንን ባል 3 መቶ ሚሊዮን ብር የሚያውጡ ፎቆችን መስራት የሚቻለው?
እንግዲህ አብዛኞች የነዚህ ፎቆችና የንግድ ተቋማትን ጨምሮ ባለቤቶቹ ወያኔዎችና ከነሱ በስተጀርባ ካሉ ዘመዳሞች ነው የተያዘው ገንዘብ ኬት መጣ ልሚለው ጥያቄ መልሱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንተወ .
ጠያቂ በሌለባቸው እነሱ ብቻ የወያኔ ባለስልጣናትና ግብራበሮቻቸው የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት በመዝረፍ ሌላው ቀርቶ በደሃው ሕዝብ እየለተለመነ ግን ወያኔና ግብራበሮቹ ለግል ጥቅማቸው በማዋል ሃብት በሃብት ላይ ከመመፀደቅ አልፎም የሕዝብ ንብረት የሆኑትን የአየር መንገዳችንን ወያኔ ልክ እንደ ግል ንብረታቸው ያለክፍያ ሚስቶቻቸውንና ዘመዳሞች ዱባይና አቡዳቢ ለሽርሽር የሚመላለሱበት የሕዝብን ሃብት ያለአግባብ እየባከነ ነው .
ወያኔ የሚዘርፉት ገንዘብ ወደ ዶላር በመለወጥ በውጭ ሀገር ባንኮች ውስጥ በማስቀመጥ የቡዙዋኑን ኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ በመዝጋት ወያኔ ይቅር የማይባል ወንጀል ሰርቷል .
ወያኔዎች የንብረት ዝውውርን በማድረግ ላይ ስለሆኑ እንግዲህ በተለይ ከነሱ ውጭ የሆናችው በዚህ ውስጥ እጃችውን እንዳታስገቡ የወያኔና የግብራበሮቹን ንብረት የገዛ የለወጠ ከወንጀለኝነት አያመልጥም ይልቁንም ተንቀሳቃሽና ቋሚ ንብረቶችን ከወያኔ ላይ ከመግዛትና ከመለዋወጥ ብትጣቀቡ ወደፊት ለሚጠየቀው የሕዝብ ንብረት ከተጠያቂነት ትድናላችው.

No comments:

Post a Comment