Mesay Mekonnen
Edited ·
The second strong man in TPDM has returned to Asmara.
ታጋይ ግደይ አሰፋ የትህዴን ቁልፍ ሰው ነው። የፕሮፖጋንዳ ክፍሉ አንቀሳቃሽ ሞተር ነው። የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በመሆን ይስራ እንጂ የትህዴን ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሚናው ከፍተኛ ነው። ባለፈው ሞላ የከዳ ጊዜ ግደይም አብሮት እንደነበረ ስሰማ በጣም ነበር የገረመኝ። ሞላ በፍጹም ግደይን ሊያታልለው አይችልም። ግደይ አብሮት ሄዷል ሲባል የታወሰኝ ከግደይ ጋር ከአስመራ ምጽዋ ያደረግነው ጉዞ: ራስ አሉላ የጣሊያኑን ወራሪ ጦር ድባቅ የመቱበት በመንገዳችን ላይ ያየነውን ታላቁን የዶጋሊ ስፍራን በስሜት ሆኖ ያጫወተኝ አጋጣሚ ነው። ግደይ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነው። ከሌሎች ሃይሎች ጋር ትህዴን በጋራ እንዲሰራ አቅሙም ስልጣኑም የፈቀደውን ያህል ሲጥር ታዝቤአለሁ። እናም በሞላ አቅም ተወናብዶ ህወሀትን ይቀላቀላል የሚል ጥርጣሬ ለአፍታም ውስጤ የሚገባ አይደለም። የዚያን ሰሞን ከሞላ ክህደት በላይ የግደይ አብሮት ሄዷል መባል አስገርሞኝ ነበር።
.
.
ከአንድ ወር በኋላ ከወደ አስመራ የሰማሁት ያልተጠበቀ መረጃ ነው። ግደይ ወደ አስመራ ተመለሰ.......ዝርዝሩ ገና አልደረሰኝም። ግደይ ትግሉን ዳግም መቀላቀሉን ግን አረጋግጬአለሁ። ሞላ ከመሄዱ ይልቅ የግደይ አብሮ ሄዷል መባሉ ለእኔ ጥሩ ወሬ አልነበረም። አሁን ደግሞ አለመሄዱ ተሰምቷል። ....ላገኘው እሞክራለሁ።
No comments:
Post a Comment