ጫት የምቅመው የረኀቡን ስሜት ለመግደል ነው"በድርቁ ምክንያት ካሉኝ 8 ከብቶች መካከል 4ቱን ሽጬ እህል ገዝቻለሁ። በሦስት የዘር መዝርያ ጊዜ የዘራሁት በቆሎ እና ገብስ መና ቀርቷል:: ሰዎች አካባቢውን ጥለው እየሄዱ አንተ ሰውዬ እዚህ የምትሆነው እስክትሞት ድረስ ነው ወይ?" ይሉኛል
*በሐረርጌ ሚኤሶ የሚኖሩት አቶ ያሲን መሐመድ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ "የገበሬዋ ሀገረ ኢትዮጵያ በአደገኛ የድርቅ አደጋ ውስጥ ገባች" በሚል ርዕስ ስር በተጻፈው ጽሑፍ ላይ የሰጡት ቃለምልልስ ነው።በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ዳይሬክትር በ2016 የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 15 ሚሊዮን እንደሚደርስ ገልጸዋል።
*አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በብሪታኒያ አምባሳደር ለ5ኛ ጊዜ ተጎብኝተዋል። ለአንድ ዓመት ያህል በጨለማ ቤት ስውር ቦታ ታስረው የነበሩት የነፃነት ታጋዩ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ከተዘዋወሩ በኋላ ከቤተሰባቸው የሚጎበኛቸው ቢኖር 80 ዓመት ያለፋቸው አባታቸው ብቻ ናቸው። እህታቸው ወይዘሮ ብዙአየሁ ተጨማሪ መረጃ ይሰጡናል።
*በተክለኀይማኖት እና በአሜሪካን ግቢ አካባቢ የንግድ ቤቶች ሁሉ ሊፈርሱ ታሽገዋል። ለማህበረሰቡ ምንም መረጃ ሳይሰጥ የተወሰደው እርምጃ ግብታዊነት እንደሆነ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ነዋሩዎች የመገበያያ ቦታ አጥተዋል።
ኢሳት የናንተ፣ የሕዝብ ድምጽ!
No comments:
Post a Comment