Wednesday, October 28, 2015

ቴፒ በተኩስ ስትናወጥ አመሸች


ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ "የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ" በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቆርጫ ህብረት ፍሬ ቀበሌ ማምሻውን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። አንድ የአይን እማኝ እንደተናገሩት ፣ ሰሞኑን እንደገና በብዛት የሰፈሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህብረት ፍሬ በሚባል ቀበሌ የሚገኙ ሴቶችን " ሽፍቶችን የምትቀልቡት እናንተ ናችሁ አውጡ" በማለት ሲደብድቧቸው ፣ መረጃ የደረሳቸው ወጣቶች ፈጥነው በመድረስ ባደረሱት ጥቃት 14 ወታደሮች መገደላቸውንና ከወጣቶች መካከልም 2ቱ መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት የወታደሮች አስከሬን ሌሊት ላይ በ4 መኪኖች ተጭነው ሲወሰዱ ፣ የወጣቶችን አስከሬን ግን ህዝቡ መቅበር እንዳልቻለ ገልጸዋል የወጣቶች አመራሮች ማምሻውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ 20 የልዩ ሃይል አባላትን መግደላቸውንና በእነሱ ወገን 2 ታጋዮች እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል። የሞቱ የመንግስት ወታደሮች ሌሊት ሲጓጓዙ ማደራቸውን የሚገልጹት ወጣቶቹ፣ የተገደሉባቸውን ወታደሮች ስምም ይፋ አድርገዋል። አንደኛው ሟች ቀድሞ የፖሊስ አባል የነበረና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም የወጣቶችን ትግል የተቀላቀለው ሳጅን አብርሃም ፈይሳ ሲሆን፣ ሌላው ሟች ደግሞ ዘሪሁን ባሳ የሚባል ነው። እኩለ ቀን ላይ በከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የሚገኙት የመንግስት ወታደሮች የሁለቱን ወጣቶች አስከሬን ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት ሲጎትቱት ታይተዋል። ኢሳት ሞቱ ስለተባሉት የመንግስት ወታደሮች ከመንግስት ወገን የሚሰጥ መረጃ ካለ ለማጣራት ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም። የአካባቢው ነዋሪዎች ምሽት ላይ ከባድ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርና ተጨንቀው ማደራቸውን ገልጸዋል። አካባቢው በመከላከያ መወረሩንም ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም ከመንግስት ወታደሮች የሚደርሰውን ጥቃት በመሸሽ ወደ ጫካ መሄዳቸውን በአካባቢው ካሉ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችለናል። አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ፣ "ቴፒ ከሞቃዲሾ በላይ ህዝብ የሚዋከብባት ከተማ ሆናለች" ብሎአል። በቅርቡ አንድ ወጣት በደረሰበት ድብደባ መሞቱን እንዲሁም ብዛት ያላቸው ወጣቶች በድብደባ ብዛት አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን ገልጿል። ድብደባውን በመሸሽም ወጣቶቹ እየተሰደዱ ነው። የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰሞኑን ለኢሳት በላከው መግለጫ፣ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ካላቆመ ጠንካራ አጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆ ነበር። ማስጠንቀቂያውን ተከትሎ እስከ ትናንት ድረስ በሄሊኮፐተር የታጀበ ወታደራዊ አሰሳ በጫካዎች አካባቢ ሲካሄድ ነበር። ወጣቶች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ አለመቻሉ ፣ የመንግስት ወታደሮች ፊታቸውን በህዝቡ ላይ እንዲያዞሩ እንዳደረጋቸው የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ። ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው የሚገልጹት ወጣቶች ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ለኢሳት በላኩት መግለጫ ጠቅሰዋል።
Netsanet Beqalu Mannet's photo.
ብድቧቸው ፣ መረጃ የደረሳቸው ወጣቶች ፈጥነው በመድረስ ባደረሱት ጥቃት 14 ወታደሮች መገደላቸውንና ከወጣቶች መካከልም 2ቱ መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት የወታደሮች አስከሬን ሌሊት ላይ በ4 መኪኖች ተጭነው ሲወሰዱ ፣ የወጣቶችን አስከሬን ግን ህዝቡ መቅበር እንዳልቻለ ገልጸዋል የወጣቶች አመራሮች ማምሻውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ 20 የልዩ ሃይል አባላትን መግደላቸውንና በእነሱ ወገን 2 ታጋዮች እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል። የሞቱ የመንግስት ወታደሮች ሌሊት ሲጓጓዙ ማደራቸውን የሚገልጹት ወጣቶቹ፣ የተገደሉባቸውን ወታደሮች ስምም ይፋ አድርገዋል። አንደኛው ሟች ቀድሞ የፖሊስ አባል የነበረና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም የወጣቶችን ትግል የተቀላቀለው ሳጅን አብርሃም ፈይሳ ሲሆን፣ ሌላው ሟች ደግሞ ዘሪሁን ባሳ የሚባል ነው። እኩለ ቀን ላይ በከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የሚገኙት የመንግስት ወታደሮች የሁለቱን ወጣቶች አስከሬን ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት ሲጎትቱት ታይተዋል። ኢሳት ሞቱ ስለተባሉት የመንግስት ወታደሮች ከመንግስት ወገን የሚሰጥ መረጃ ካለ ለማጣራት ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም። የአካባቢው ነዋሪዎች ምሽት ላይ ከባድ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርና ተጨንቀው ማደራቸውን ገልጸዋል። አካባቢው በመከላከያ መወረሩንም ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም ከመንግስት ወታደሮች የሚደርሰውን ጥቃት በመሸሽ ወደ ጫካ መሄዳቸውን በአካባቢው ካሉ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችለናል። አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ፣ "ቴፒ ከሞቃዲሾ በላይ ህዝብ የሚዋከብባት ከተማ ሆናለች" ብሎአል። በቅርቡ አንድ ወጣት በደረሰበት ድብደባ መሞቱን እንዲሁም ብዛት ያላቸው ወጣቶች በድብደባ ብዛት አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን ገልጿል። ድብደባውን በመሸሽም ወጣቶቹ እየተሰደዱ ነው። የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰሞኑን ለኢሳት በላከው መግለጫ፣ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ካላቆመ ጠንካራ አጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆ ነበር። ማስጠንቀቂያውን ተከትሎ እስከ ትናንት ድረስ በሄሊኮፐተር የታጀበ ወታደራዊ አሰሳ በጫካዎች አካባቢ ሲካሄድ ነበር። ወጣቶች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ አለመቻሉ ፣ የመንግስት ወታደሮች ፊታቸውን በህዝቡ ላይ እንዲያዞሩ እንዳደረጋቸው የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ። ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው የሚገልጹት ወጣቶች ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ለኢሳት በላኩት መግለጫ ጠቅሰዋል።

No comments:

Post a Comment