Saturday, October 10, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ

በህወሓት ቁጥጥር ስር በሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚከዱ፣ የሚሞቱ እና አካላቸው እየጎደለ አትጠቅሙም ተብለው የሚባረሩ አባላት ቁጥር ዕለት ከዕለት እየናረ በመምጣቱ ምክንያት ሬጅመንቶች ተመናምነው ክፍለ ጦሮች ከሚጠበቀው በታች በመሆናቸው በጎደለ ሙላ አዲስ የሰው ኃይል ድልድል እየተሰራ መሆኑ ታወቀ፡፡

‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በምዕራብ ኢትዮጵያ ጠረፍ ወቅት አየጠበቁ ለጉልበት ስራ በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ላይ ከስልጣን ህልውናው ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረበት ተነገረ፡፡
===================================================
በህወሓት ቁጥጥር ስር በሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚከዱ፣ የሚሞቱ እና አካላቸው እየጎደለ አትጠቅሙም ተብለው የሚባረሩ አባላት ቁጥር ዕለት ከዕለት እየናረ በመምጣቱ ምክንያት ሬጅመንቶች ተመናምነው ክፍለ ጦሮች ከሚጠበቀው በታች በመሆናቸው በጎደለ ሙላ አዲስ የሰው ኃይል ድልድል እየተሰራ መሆኑ ታወቀ፡፡
የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት በሁሉም የአገሪቱ ጠረፎች በየጊዜው ያለማቋረጥ በሚከሰቱ የማያባሩ ጦርነቶች ለዕለት ጉርሳቸው ብለው ብቻ በግዴታ እሳት ውስጥ እየተማገዱ ስለሚያልቁ እና በሶማሊያ ምድር ሳይቀር በተደጋጋሚ እንደ ቅጠል ስለሚረግፉ እንዲሁም በተጨማሪ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚከዱ ከታች ከጓድ ጀምሮ እስከ ዕዞች ድረስ የሚገኙ የቀድሞ መዋቅሮች በሰው ኃይል ተክለ ቁመናቸው አካለ ጎደሎ ሆነው ቆይተዋል፡፡
በመሆኑም አሁን አንዳንድ ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸውን ክፍለ ጦሮች እና ሬጅመንቶችን በማፍረስ ሌሎችን በተነፃፃሪ ደህና የተባሉ ክፍለጦሮችና ሬጅመንቶችን በሰው ኃይል በመሙላት የማደራጀት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ከዚህ ቀደም በአብዛኛዎቹ ክፍለ ጦሮች ስር የሚገኙ ሬጅመንቶች እያንዳንዳቸው የነበራቸው የሰው ኃይል ቁጥር ከ650-700 የሚጠጋ ሲሆን አሁን ሌሎችን ከዚህ ከተጠቀሰው ቁጥር በታች ያላቸውን በማፍረስ በተደረገው በጎደለ ሙላ ድልድል ከ1100-1300 አባላት እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡
ነገር ግን ይህም ቁጥር ቢሆን በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ከታች እስከ ላይ የሰፈነው ዘረኝነት፣ ኢ-ፍህታዊ አስተዳደር እና አገዛዙ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው በደል እስከቀጠለ ድረስ በትንሹ ለአንድ ወር ጊዜ እንኳን ተጠብቆ ሊቆይ አንደማይችል እና እንዴውም ከከዚህ ቀደሙ በከፋ ሁኔታ እንደሚያሽቆለቁል የተረጋገጠ መሆኑን ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙት ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ በምዕራብ ኢትዮጵያ ጠረፍ ወቅት አየጠበቁ ለጉልበት ስራ በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ላይ ከስልጣን ህልውናው ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረበት ተነገረ፡፡
ሰሊጥ በሚዘራበት፣ በሚታረምበት እና በሚታጨድበት የተለያዩ ወቅቶች ከመሃል እስከ ዳር አገር የሚኖሩ እልፍ አዕላፍ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጠረፍና የኢትዮጵያ አዋሳኝ የሆኑ የሱዳን መሬቶች በኃይለኛው ይተማሉ፡፡
እነዚህ ወቅት ጠብቀው ለጉልበት ስራ ወደ በረሃ የሚወርዱ ወጣቶች ተግባራቸውን በሚያከናውኑባቸው አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶችን እንደሚቀላቀሉ በእጅጉ የሰጋው የህወሓት አገዛዝ ወጣቶቹ ለሰሊጥ አጨዳ ሊዘምቱ የተዘጋጁበትን ወቅት ጠብቆ በየሚኖሩበት አካባቢ በጠብመንጃ አስገድዶ በመሰብሰብ እያንገራገረ ይገኛል፡፡
በተለይም በላይ አርማጭሆ በበርካታ የገጠር ቀበሌዎች የሚኖሩ ወጣቶችን "በስብሰባው ላይ ያልተገኘ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል እና አሸባሪ ነው!" በማለት ፈርጆ እያሸማቀቀ በግዴታ ሰብስቦ በካድሬዎቹ አማካኝነት የተለመደ የልማት ሰበካ ዲስኩሩን በማሰማት እና ወጣቶቹ ሳይመለሱ በዛው ቢቀሩ በቤተሰቦቻቸው ላይ የከፋ እርምጃ እንደሚወስድ በመዛት የማስፈራራት እና የማሸማቀቅ ሙከራ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡
ድል ለነፃነት ዱር ቤቴ ላሉ!ድል ‪#‎ለአርበኞች_ግንቦት_7‬

No comments:

Post a Comment