Friday, October 9, 2015

ከሕወሓት መከላከያ የሚጠፉ መኮንኖች በርክተዋል * አትጠቅሙም እየተባሉም የሚባረሩት በዝተዋል -

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በህወሓት ቁጥጥር ስር በሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚከዱ፣ የሚሞቱ እና አካላቸው እየጎደለ አትጠቅሙም ተብለው የሚባረሩ አባላት ቁጥር ዕለት ከዕለት እየናረ በመምጣቱ ምክንያት ሬጅመንቶች ተመናምነው ክፍለ ጦሮች ከሚጠበቀው በታች በመሆናቸው በጎደለ ሙላ አዲስ የሰው ኃይል ድልድል እየተሰራ መሆኑ ታወቀ፡፡የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት በሁሉም የአገሪቱ ጠረፎች በየጊዜው ያለማቋረጥ በሚከሰቱ የማያባሩ ጦርነቶች ለዕለት ጉርሳቸው ብለው ብቻ በግዴታ እሳት ውስጥ እየተማገዱ ስለሚያልቁ እና በሶማሊያ ምድር ሳይቀር በተደጋጋሚ እንደ ቅጠል ስለሚረግፉ እንዲሁም በተጨማሪ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚከዱ ከታች ከጓድ ጀምሮ እስከ ዕዞች ድረስ የሚገኙ የቀድሞ መዋቅሮች በሰው ኃይል ተክለ ቁመናቸው አካለ ጎደሎ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም አሁን አንዳንድ ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸውን ክፍለ ጦሮች እና ሬጅመንቶችን በማፍረስ ሌሎችን በተነፃፃሪ ደህና
የተባሉ ክፍለጦሮችና ሬጅመንቶችን በሰው ኃይል በመሙላት የማደራጀት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአብዛኛዎቹ ክፍለ ጦሮች ስር የሚገኙ ሬጅመንቶች እያንዳንዳቸው የነበራቸው የሰው ኃይል ቁጥር ከ650-700 የሚጠጋ ሲሆን አሁን ሌሎችን ከዚህ ከተጠቀሰው ቁጥር በታች ያላቸውን በማፍረስ በተደረገው በጎደለ ሙላ ድልድል ከ1100-1300 አባላት እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ይህም ቁጥር ቢሆን በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ከታች እስከ ላይ የሰፈነው ዘረኝነት፣ ኢ-ፍህታዊ አስተዳደር እና አገዛዙ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው በደል እስከቀጠለ ድረስ በትንሹ ለአንድ ወር ጊዜ እንኳን ተጠብቆ ሊቆይ አንደማይችል እና እንዴውም ከከዚህ ቀደሙ በከፋ ሁኔታ እንደሚያሽቆለቁል የተረጋገጠ መሆኑን ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙት ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47280#sthash.0bOxcKSJ.dpuf

No comments:

Post a Comment