Wednesday, September 30, 2015

"ESAT Tamagne new" By Yemechereshaw Tewled. Feb 16, 2013

ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ከእስር በነጻ ተለቀቀ

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን
http://www.hiberradio.com/archives/1164ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን
በሀሰተኛ ክስ ተከሶ ከትላንት ማለዳ ጀምሮ በየመን ሰንኣ እስር ላይ የነበረው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ዛሬ በፖሊሶች ተጣርቶ የቀረበበት የፈጠራ ክስ ላይ በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ ማምሻውን በነጻ መለቀቁን ባለቤቱ የላከችልን መረጃ አመለከተ።
ገጣሚ ጸሀይ በየነ በላከችው በዚህ መረጃ በጋዜጠና ግሩም መታሰር ላዘኑ ፣

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ


(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
‪#‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡
=========================================================
አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡
ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡
'መሳይ መኮንን
'ትጥቅ ትግል የራስን ሕይወት ለወገን ነፃነት መሥዋዕት ማድረግ ነው። ሌላ ዓለማ የሌለው ሰው መሣሪያ ሲያነሣ፥ እንዴት ይኸንን የሚሰነዘርበትንና የሚሰነዘርለትን ምክር ሳያስብበት ራሱን ለመሥዋዕትነት ያቀርባል? የሚካኼደው የትጥቅ ትግል የሚያዋጣ የመሰለው እርዳታውን ያቅርብ፤ የማያዋጣ የመሰለው ለምንድን ነው የሚቃወመው? ተቃውሞው ማንን ለመጥቀም ነው? ለታጋዮቹ አስቦ ከሆነ፥ ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው። “የኔን ያህል የማሰብ ችሎታ የላችሁም” ማለት ነው። እንዴት ነው ለታጋዮቹ ያልተገለጠ ሥጋት ለምክር ሰጪዎቹ የተገለጠው?''...ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ.
getachew

የትጥቅ ትግልና ግራ የሚያጋባ አስተያየት – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

getachewበኢትዮጵያ ትከሻ ላይ የተቆለፈውን ቀምበር ለማላቀቅ ቍልፉ የትጥቅ ትግል መሆኑ በተነሣ ቍጥር ከአንዳንድ ሰዎች የሚሰጠው አስተያየት ግራ የሚያገባ ነው። ገዢዎቹና ደጋፊዎቻቸው ቢቃወሙ ይገባኛል። የሚሰጡት አስተያየት ግን ሕፃንን ሳይቀር የሚያሥቅ ነው። “ጦርነት በቃን” ይላሉ። “አትንኩን” ማለታቸውን የማናውቅ ይመስላቸዋል። ጦርነት ካላስፈለገ፥ ለምን ከንጉሣዊው አስተዳደር ጋር ተዋጉ? ለምን ከደርግ ጋር ተዋጉ? ጨቋኝ ገዢ የት አገር ነው በሌላ መንገድ ሥልጣን ለሕዝብ ሲለቅ የታየው? የምሥራቁ ዓለም ጨቋኞች የወደቁት በሕዝብ ዐመፅ ነው ማለት፥ የምዕራቡን ዓለም ከባድ እጅ ሚና መርሳት ይሆናል። የኛዎቹ ጦርነት ከመረራቸው፥ ሕዝብን ወደጦርነት የሚመራ በደል አይሥሩበት። ምን ጊዜም ቢሆን የትጥቅ ትግል የመጨረሻው አማራጭ ነው። የትጥቅ ትግል የሚያደርሰው ጉዳት በአንዱ ወገን ላይ ብቻ አይደለም። መሣሪያ የሚያነሣ መሣሪያ ማንሣት የሚያመጣበትን ጉዳት ሳያውቅ አይነሣም። ሰው ሆኖ እንደከብት መገዛት ያልቻለ ሰው በቃኝ ሲል፥ ክብሩን በመጠበቁ ከተቀመጡበት ተነሥቶ “ነወር” የሚባል እንጂ፥ በባርነት ጥላ ሥር ተቀምጦ የሚተች አይደለም። “ጦርነት መርሮናል” የሚለውን ምክር መገዛት ለመረረው አይመክሩም። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ግራ አጋቢ አስተያየት “ጦርነትስ አስፈላጊ ነው፥ ግን . . .” የሚለው ነው። ይህ አስተያየት በቅን አሳብ፥ የተሰጠ ሊሆን ይችላል። ግን አዛኝ መስሎ፥ ቀምበረኛውን ለመደገፍ የተሰጠ አስተያየት አለመሆኑ በምን ይታወቃል? እውነተኛ አሳቢና ሠጊ ሰው አስተያየቱን የሚሰጠው ሲጠየቅ፥ ካልተጠየቀም በግሉ ትጥቅ ያነሡትን ፈልጎ በጨዋ ደምብ መንገር ነው። ሳይጠየቁ ተነሥቶ በይፋ ምክር መስጠት ግን ሰሚው ሕዝብ ትግሉን እንዳይደግፍ መገፋፋት ነው።

ዜና

አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡ ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡ ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ በህዝብ ላይ ሴራ በማቀነባበር የሚታወቀው ህወሓት ራሱ ግንብቶ ለግለሰቦች ያከራየውን የንግድ ማዕከል ነው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ድርጊቱን እንደፈፀሙት በማስመሰል ከህዝብ ለመነጠል ሲል ነው በተቀነባበረ ሂደት በእሳት የለቀቀው ፡፡

Tuesday, September 29, 2015

ESAT Radio Mon 28 Sep 2015

ESAT Radio Mon 28 Sep 2015

አርባ‬ ምንጭ የነበረው የአሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን አካባቢውን ለቆ እየወጣ ነው -

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
‪‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡

ሑመራ ከተማ የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነው የገበያ ማእከል በእሳት ቃጠሎ ሙሉ ወድሟል -

12063766_917178921707098_4961080571353682314_nቃጠለው ሓሙስ 13/ 01 / 2008 ዓ/ም ሌሊት ያጋጠመ ሲሆን የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነ ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ንብረት በቃጠለው መውደሙ ታውቋል።
ህብረተሰቡ ቃጠለው ለማጥፋት የተቻለው ቢጥርም ሊሳካ እንዳልቻለ ኑዋሪዋሪዎች ገልፀዋል።
ከሁሉም በላይ ሒመራን የምታክል ትልቅ ከተማ የእሳት ማጥፍያ መኪና መንግስት ባለማዘጋጀቱ ቅሬታቸው ኣሰምተዋል።
የቃጠለው መነሻ እስካሁን ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
‪#‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡ 
====================================================
አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡

በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡
ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ 
የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡
ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

Monday, September 28, 2015

ህብር ሬዲዮ

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጥኖ ደራሽ ጦር እንዳይቋቋም እንቅፋት ሆነዋል ተባሉ ፣ ኢትዮጵያ የሶማሊያ ወጣቶችን ለጦርነት እያሰለጠነች ነው ተባለ፣ በዲሲ በፖለቲካ ተሰደዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብርቱ ፈተና ገጠማቸው ፣በሳውዲ ለሐጂ ሄደው በአደጋ ሳቢያ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ዛሬም አልታወቀም ፣የሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ገሰሰ ልደት በማህበራዊ ሚዲያው እንዲከበር ጥሪ ቀረበ፣ኦብነግ በአልሸባብ አንገታቸው ተቀልቶ ከተገደሉ ሁለት አመራሮቹ ጀርባ የኢህአዴግ ደህነትን ጠረጠረ እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ መስከረም 16 ቀን 2008 ፕሮግራም
<… በሳውዲ በሚና በደረሰው አደጋ የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን ሓጃጆች ቁጥር ለማወቅ የጋራ ጥረት የተቀናጀ ስራ መስራት ግድ ይላል ብዙ አገሮች ተቀናጅተው ሰርተው የሞቱ ዜጎቻቸውን ማንነት በቀላሉ ለይተዋል። እኔ እንኳን እዚሁ ሳውዲ ውስጥ የአምስት ሟች ወገኖቻችንን ለቅሶ ደርሻለሁ። ሁለት ሰዎች ብቻ የሚለው …>   ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ አረቢያ በሐሙሱ አደጋ ሳቢያ የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን አለመታወቁን በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ
በቬጋስ የመስቀል በዓል አከባበር (ልዩ ቃለ መጠይቅ)

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ አረፉ

colonel bachaኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአንቦ አካባቢ በጊንጪ ከተማ ተወለዱ ።በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በ1965 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኢትዮጵያ አየር ሃይል በአውሮፕላን ጥገና አገራቸውን ለማገልገል ተቀጥረው ስልጠናቸውን እንደጨረሱ ከክፍላቸው ያመጡት ውጤት የላቀ በመሆኑ እና የተዋጊ አውሮፕላን በራሪ ለመሆን ባሳዩት ከፍተኛ ፍላጎት ሙያው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት በማሟላት ወደ በረራ ትምህርት ቤት ገቡ ።
የሚፈለግባቸውን የበረራ ትምህርት እንደጨረሱ ወደ ተዋጊ ስኳድሮን በመመደብ የኤፍ 86 አውሮፕላን ሲበሩ ቆይተው የኢትዮጵያ አየር ሃይል F-5E የሚባል አዲስ አውሮፕላን ሲገዛ ወደ አሜሪካን አገር ተልከው በዚሁ አውሮፕላን ስልጠና በመውሰድ እና በማጠናቀቅ ወደ አገራቸው ተመልሰው በወቅቱ አገራችንን የወረሩትን የሱማሌ ወራሪዎች ጋር ፍልሚያ ውስጥ በመግባት በአየር ላይ ውጊያ ሁለት የሱማሌ ሚግ አውሮፕላኖችን መትተው የጣሉ ሲሆን በዚህም ላሳዩት ከፍተኛ ጀግንነት ከኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሜዳ የላቀ ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ሆነዋል።
ኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአየር ሃይል ሰራዊት ዘንድ እንዲሁም በጓደኞቻቸው በጣም ተወዳጅ ከነበሩት መካከል እና በስራቸውም አሉ ከሚባሉት የተዋጊ አውሮፕላን አብራሪዎች አንዱ እንደነበሩ ይታወቃል።

Famine Rides a Light Train in Ethiopia

Ethiopia’s annual harvest of famine
Ethiopia’s annual harvest of famine

The Black Horseman of the Apocalypse is showing his fearsome face once again in Ethiopia.
This time he is riding a light train.

Sunday, September 27, 2015

ESAT Radio Sat 26 Sept 2015

ESAT Radio Sat 26 Sept 2015

Launching an Effective Resistance against TPLF Tyranny – a tyranny which is the Real Driver of Instability and Civil Strife in Ethiopia

Launching an Effective Resistance against TPLF Tyranny – a tyranny which is the Real Driver of Instability and Civil Strife in Ethiopia

September 26, 2015

logo-timeret

United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy

Launching an Effective Resistance against TPLF Tyranny – a tyranny which is the Real Driver of Instability and Civil Strife in Ethiopia, (pdf)

Ethiopia is one of the oldest nation-states in the world. Both written and oral history and recent archeological discoveries, despite regional rivalries, suggest the historical continuity of the nation. It was a Monarchy until 1974. From 1974 to 1991 the country was declared to be ‘Peoples Democratic Republic’ by the military junta, Derg, and went through a traumatic experience. Tigrai Peoples Liberation Front (TPLF), a guerrilla force from a minority ethnic group that led the rebellion against the military junta and captured the institutions of the State, has been in power for the past 24 years. The country is ruled as a one-party state under a façade of multi-party system since 1991.

Saturday, September 26, 2015

ርካሽ ፖለቲካን በቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ===========================


ርካሽ ፖለቲካን በቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ
===========================
ቤተ ክርስቲያኒቱ በእዚህ ደረጃ የዘረኛ ፖለቲከኞች መቀለጃ እንደሆነች ያልገባን ይህንን ተመልክተን የህሊና ፍርዳችንን እንስጥ።
=============================
ይህ የምትመለከቱት ፖስተር አዲስ አበባ መንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን መግቢያ በር ላይ የተለጠፈ ነው ነገ አዲስ አበባ የሚገቡት የግብፁ ፓትርያሪክ አቡነ ቴዎድሮስ እና የአቡነ ማትያስ ፎቶ ከዳር እና ከዳር ተደርጎ በመሃል የአቶ መለስ ፎቶ ተለጥፏል። ምን ማለት ነው? በሁለት ጳጳሳት ፎቶ መሀል የአቶ መለስ ፎቶ ምን ማለት ነው?
''የሰማይ ደጅ'' በተባለች ቤተ ክርስቲያን በር ላይ ይህንን መለጠፍ ምን አይነት ሃይማኖታዊ አልለውም ችግሩ ከሃይማኖቱ ስላልሆነ ግለሰባዊ ዝቅጠት ግን ነው።ይህንን የሚያህል የሀገር ገፅታ ለዓለም በሚታይበት የመስቀል ደመራ ወቅት የሚመጣ እንግዳን ከማይሆን ነገር ጋር አገናኝቶ ማሳከር አላማው ምንድነው? ርካሽ ፖለቲካን በቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ የምትለጥፉ እናንተ የጥጋባችሁ ጥግ መድረሻ ያጣ አልመሰላችሁም?
Getachew Bekele

Yeserawitu Dimtse: Who is Mola Asgedom? (Discussion with former army off...

የስብሰባ ጥሪ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላት በሙሉ !!

Norway - Satenawጉዳዩ፦ አመታዊ ጠቅላላ የአባላት መደበኛ ስብሰባ !
ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላት በሙሉ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ አመታዊ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 25.10. 2015 ከቀኑ 14፡00 ሰአት ጀምሮ ስለሚያደርግ አባላት ሁሉ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን በስብሰባው ላይ
1. አመታዊ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ስድስትወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት
2. እንዲሁም ለቀጣይ ስድስት ወራት የምንደግፋቸው ድርጅቶችን መገምገምና ማጽደቅ
3. ድርጅቱን ለቀጣይ የስራ ዘመናት የሚመሩ የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ

በመሆኑም በዚህ ስብሰባ ላይ አባላት በሙሉ በመገኘት የድርጅት ግዴታቸውን ይወጡ ዘንድ ድርጅቱ በታላቅ አክብሮት ያስገነዝባል በማያያዝም የተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች በቦታው ተዘጋጅቶል
የስብሰባ ቦታውን በቅርብ ጌዜ እናሳውቅ አለን


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል በ "ለጥያቄዎ መልስ" ዝግጅት ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀ፣ በኢትዮጵያ ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት አስወግዶ አገሪቱን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማመቻቸት ነዉ ብለዋል።

http://amharic.voanews.com/content/gimbot-seven-discussion-ethiopia-/2979458.html
 የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀ፣ በኢትዮጵያ ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት አስወግዶ አገሪቱን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማመቻቸት ነዉ ብለዋል
ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አ

ESAT Radio Fri 25 Sep 2015

ESAT Radio Fri 25 Sep 2015

አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርበው ህዝብ ቁጥር ጨምሯል

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው። የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለድርጅቱ የሚደወሉ ስልኮች በእጥፍ ጨምሯል። ምንም እንኳ አብዛኛውን ጥሪ የሚያደርጉት ወጣት ወንዶች ቢሆንም፣ ጎልማሶችና ሴቶችም ይገኙበታል ሲል የመረጃ ክፍሉ ለኢሳት ገልጿል። ድርጀቱ ትግሉን እንቀላቀል ለሚሉት ሃይሎች " በአገር ውስጥ ሆነው ራሳቸውን እንዲያደራጁ ምክር እንደሚሰጥ " የገለጸ ሲሆን፣ ሁኔታዎችን ላመቻቹ ወጣቶች ደግሞ ጉዞአቸውን በምን መንገድ ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚገልጽላቸው ገልጿል። የደሚት ሊቀመንበር ሞላ አስጎደም መክዳት ለድርጀቱ በሚደውሉ ሰዎች ቁጥር ላይ ያመጣው ተጽእኖ እንደሌለ የገለጸው የመረጃ ክፍሉ፣ እንዴያውም ህዝቡ በቁጭት ስሜቱን እና ድጋፉን ሳያቋርጥ እንዲገልጽ አድርጎታል ሲል አክሏል። ህዝቡ በአገር ውስጥ ባለው አፈና በመማረር አስቸኳይ ለውጥ እንዲመጠብቅ የሚገልጸው ድርጅቱ፣ ትግሉ ትእግስትንና ጽናትን የሚጠይቅ በመሆኑ ታግሶ በውስጥ የሚያደርገውን ትግል እንዲገፋበት ጠይቋል።
መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ...
ETHSAT.COM

በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት

በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት
_አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርቡ ወጣቶች ቁጥር በተለይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ከንቅናቄው አከባቢ የተገኘው መረጃ አመለከተ። ወደ ንቅናቄው ከተደወሉ ስልኮች 80 በመቶ የሚሆኑት ትግሉን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ናቸው። ንቅናቄው በሀገር ውስጥም ወጣቱን የማደራጀት ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል። የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጪያ ወደ ትግል ሜዳ የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ነው።
_በቅርቡ በኤርትራ የተመሰረተው የሀገር አድን ንቅናቄ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋሙንና ዓላማውን የሚዘረዝር ወረቀት አዘጋጅቶ አሰራጨ። ሀገር አድኑ ንቅናቄ በስልጣን ላይ ያለውን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራውን መንግስት ለማስወገድ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን አስታውቋል። ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆምም ንቅናቄው ጠይቋል።
_የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የአባይ ግድብን በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ አርብ ይፋ አደረገ። የግብፅ ባለስልጣናት የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ላቀረቡት የውሃ እጥረት ዘገባም፣ ሃገሪቱ የአባይ ግድብን የውሃ መሙላት ሂደት በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ በመከታተል ላይ በመሆኑ የተደበቀ ነገር አይኖርም ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል።
-የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማስረጃ (TVET) እንደ ትምህርት ማስረጃ እንደማይቀበለው ገለጸ። ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ የአሜሪካንን የትምህርት ደረጃ የሚጠብቅ ባለመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በቴክኒክና ሙያ የሰለጠኑ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የ2015 የዲቪ ዕድለኞች ወደአሜሪካ መግባት አይችሉም፡፡http://ethsat.com/?p=34544

Friday, September 25, 2015

ESAT's Dereje Habtewold presents the highlights of Gigi's musical works

ESAT Radio Thu 24 Sep 2015

ESAT Radio Thu 24 Sep 2015

በሰበታ አይነስውራን ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ

መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ፣ ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በፖሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመሰጠቱ ፣ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ፣ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት ገብቶ አይነሰውራን ተማሪዎችን ደብድቧል። ተማሪዎቹ የመኝታ ክፍሉ እንዲመለስላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቢቆዩም መለስ በማጣታቸው የትምህርት ማቆም አድማ አድርገዋል። ፖሊሶች፣ ተማሪዎቹ ከመኝታ ክፍላቸው እንዲወጡ ትእዛዝ ቢሰጡም፣ ተማሪዎቹ ግን ፈቃደኛ አልሆነም። ፖሊሶች ወደ ክፍል እየገቡ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ተማሪዎች ላይ ከባድ ድብደባ የፈጸሙ ሲሆን፣ ብዙዎቹ እጆቻቸውና እግሮቻቸው በድብደባ ብዛት ተጎድቷል። አንድ ተማሪ " ሩጠን ለማምለጥ በማንችልበት ሁኔታ ፖሊስ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዶብናል" ብሎአል። የታሰሩት 17 አይነስውራን ተማሪዎች እንስካሁን አልተፈቱም። ትምህርትም አልተጀመረም። የፌደራል ፖሊስ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።








መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማዬት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ፣ ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንሳታቸው በፖሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን፣...

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ 1. ከወያኔ ውድቀት በኋላ የሽግግር ጊዜ መንግስት ምን መምሰል አለበት? 2. የሽግግር መንግስት ዋና ዋና ስራዎች ምን መሆን አለባቸው? 3. የወደፊቱ ስርኣት ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ? ለምን? 3. በዘውግ የተደራጁ ፓርቲዎችና ሌሎች ድርጅቶች በምን መልኩ በሽግግርና በቋሚው መንግስት ይካተቱ? 4. የማህበረሰባችችን የሞራል መሰረት እንዴት እንገንባ? የሚሉትን እና ሌሎች ተመሳሳይ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ቁልፍ ጥያቄዎች ይዳስሳሉ። መልካም ንባብ!

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
1. ከወያኔ ውድቀት በኋላ የሽግግር ጊዜ መንግስት ምን መምሰል አለበት?
2. የሽግግር መንግስት ዋና ዋና ስራዎች ምን መሆን አለባቸው?
3. የወደፊቱ ስርኣት ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ? ለምን? 
3. በዘውግ የተደራጁ ፓርቲዎችና ሌሎች ድርጅቶች በምን መልኩ በሽግግርና በቋሚው መንግስት ይካተቱ? 
4. የማህበረሰባችችን የሞራል መሰረት እንዴት እንገንባ? የሚሉትን እና ሌሎች ተመሳሳይ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ቁልፍ ጥያቄዎች ይዳስሳሉ። መልካም ንባብ!

በዲሞክራሲያዊ ሀይሎች መሀል መተማመንን ለማዳበር ሶስት ሀሳቦች
በግንቦት 1-2 2007 አ.ም. (May 9-10) አለክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ኢሳት ባዘጋጀው “ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ የወደፊት አቅጣጫዎች” ሲምፖዚየም ላይ ለውይይት የቀረበ
ለግንቦት 9 (May 9th) ስብሰባ ለውይይት የቀረበ
ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር)
መግቢያ:
የወያኔ ሥርዓት ለሀገሪቱ የማይበጅ፤ አገሪቱን አደገኛ ችግር ውስጥ የከተተና የበለጠ ጊዜ እስካገኘ ድረስ የሚያመጣው መዘዝ ዘላቂና መውጫ የሌለው ምስቅልቅል ውስጥ አገሪቱን የሚከታት መሆኑን ብዙው ህዝብ ይገነዘባል ማለት ይቻላል:: ስለ ሕዝቡ በጥቅል እንኳን መናገር ባይቻል የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታተሉና በተለይም በተቃዋሚ ድርጅቶች አካባቢ የሚገኙ ያገሪቱ ዜጎች በግልጽ የተረዱት ጉዳይ ነው:: በተለይ በቅርብ ጊዜ የወያኔ መንግሥት በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚወሰደው የጭካኔ እርምጃ (ኦሮምያ፤ አማራ፤ አፋር፤ ሶማሊ፤ ጋምቤላ፤ ሲዳማ፤ሐረሪ፤...ወዘተ) እንዲሁም ሆን ብሎ ማህበረሰቡን በዘውግ ከፋፍሎ ለማባላት የሚያደርገውን መሰሪ እንቅስቃሴ በቅርብ የሚመለከቱ በዘውግ የተደራጁ የፖለቲካ ሀይሎች ሳይቀር የወያኔ አካሄድ ለነሱም የማይበጃቸው መሆኑን በመገንዘብ የስርዓቱ እድሜ ማጠር እንዳለበት ያምናሉ፤ ምንም እንኳን ይህንን ችግር በዘውግ መሰረት ላይ የቆመ ፖለቲካ የፈጠረው መዋቅራዊ ችግር አድርገው ሳይሆን የወያኔ የተለየ አምባገነናዊ ባህርይ የፈጠረው ችግር አድርገው የሚመለከቱት ቢሆንም:: በዚህ ጉዳይ ላይ በርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አደረጃጀትና እንቅስቃሴን በሚመርጡና የሀገሪቱን ፖለቲካ በዘውግ መነጽር በሚያዩ ኃይሎች መሀከል ያለው ሰፊና መትከላዊ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ የወያኔ ሥርዓት በቶሎ መቀየር እንዳለበት ሰፊ ሀገራዊ ስምምነት አለ ማለት ይቻላል::
ለአቡነ ጴጥሮስን ክብር የተቀመጠው ታሪካዊ ሃውልት ለባቡር መንገድ እንቅፋት ሆነ ተብሎ ሲነሳ መንገዱ ተስርቶ ሲያልቅ በቦታው እንደሚመለስ ተገልፆ ነበር ። ሆኖም ግን ዛሬ ያ መንገድ ተስርቶ አልቆ ግልጋሎት ላይ እየዋለ ሲሆን የአቡናችን ሃውልት ግን በክብር በቦታው አልተቀመጠም ።
አቡነ ጴጥሮስ ቅርሳችን ታሪካችን ናቸው ። ለውጭ ወራሪ እጅ አልሰጥም ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እጅ አይሰጥም ማለታቸው ነው ። የአቡነ ታሪክ በተወሳ ቁጥር ፋሽሽት ጣልያን አንገቱን በእፍረት የሚደፋበት ነው ። እና እኝህን ትልቅ አባታችንን ከፊታችን ሲያገሉብን ለምን ብለን አንጠይቅም ? መቼ ነው ግን እኛ ለምን እና እንዴት ብለንስ የምንጠይቀው ? ብዙ የጠፋ ነገሮችን ለግዜው ዋይ ዋይ ብለን የዘነጋናቸው አሉ እና ብንችል የአባታችን የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት በቦታው በክብር ለማስቀመጥ እንሞክር ። ዝም ከማለት የሚገኝ ወይም የሚመጣ ነገር የለም ። እኛም የፋሽሽትን ፍላጎት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አናስፈጽም።

ረሀብን ለማጥፋት ህወሓትን ማስወገድ


September 3, 2015
def-thumb
ረሀብ በአገራችን ላይ እያንዣንበበ ነው። በአፋርና በሱማሌ ከከብቶች አልፎ ሕፃናት እየሞቱ ነው። የረሀቡ አደጋ ወደ ኦሮሚያና ሌሎች የደቡብ ገጠሮች እየተዛመተ ነው፤ ሰሜን ኢትዮጵያም ከአደጋ ውጭ አይደለም።

“ከአስር ዓመታት በላይ በተከታታይ በየዓመቱ ከአስር በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት አሳይተናል” የሚለው ዓይን ያወጣ ውሸት፤ “ድህነትን ተረት እናደርጋለን” የሚለው ጉረኛ መፈክር፤ “መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ተርታ እንደርሳለን” የሚለው ባዶ ተስፋ፤ የወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው በፎቅና ቪላዎች መንበሽበሽ፤ የድግሶችና የስብሰባዎች መብዛት ለሕዝባችን ቁርስ፣ ምሳና እራት አልሆኑም።
አገዛዙ ጉራውና ባዶ ተስፋ መስጠቱ እንዳለ ሆኖ የረሀቡን ምክንያት በተፈጥሮ ላይ ማላከኩን ተያይዞታል። ለመሆኑ ተፈጥሮ ብቻውን እየተደጋገመ ለሚመጣ ችጋርና ቸነፈር በቂ ምክንያት ሆኖ ያውቃልን? አስከፊ የረሀብ ዜናዎች የሚሰማባቸው አገሮች በሙሉ ነፃነት የታፈነባቸው አገሮች መሆናቸው የአጋጣሚ ጉዳይ ነውን? ለምንድነው አንድ ዓይነት ችግር እየተደጋገመብን መላ መፈለግ ያቃተን? መልሱ አጭርና ቀጥተኛ ነው።

VOA Interview with Neamin Zeleke Sep 22 2015

አብዮቱና ትዝታዬ (ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ)፣ አዲስ መጽሃፍ – አዲስ ምስጢር

ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ ቀደም ሁለት የአብዮቱ መጽሃፍቶችን አበርክቶልናል። የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም – “ትግላችን” እና ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ – “እኛና አብዮቱ”። የኮ/ል ፍሥሓ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” ከቀድሞዎቹ ትንሽ ለየት ይላል። ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ተድበስብሶ የቆየውን የወታደራዊ መንግስት ውስጣዊ ገመና ብቻ ፈልፍለው አላቀረቡም። በአብዮቱ ሂደት ለተከሰቱ ጥፋቶች ከራሳቸው ጀምረው ተጠያቂው የሆነው ወገንን ከማመልከትም አልታቀቡም። ደራሲው ብዙ ምስጢሮችንም ያስነብቡናል።
Fisseha Desta's book
መጽሃፉ ዳጎስ ያሉ ምዕራፎች ይዟል። በአምስት ክፍሎች የተመደቡ አስራ አምስት ምእራፎች ተካትተውበታል። ከቅድመ 1966 ዓ.ም. ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ፣ በደራሲው አገላለጽ – እስከ የ”መጨረሻዋ እራት” የነበሩትን ሂደቶች በስፋት ይቃኛል። ባጭሩ በአፄው መንግሥት ላይ የተነሱ ዓመፆችን በቀላል አማርኛ እያስነበበ የአብዮቱን አፈጣጠር፣ “የየካቲት አብዮት ከነገሌ እስከ መሿለኪያ” በሚል ምዕራፉ ያስነብበናል። ስለ አብዮቱ ውስብስብ ሂደት፤ ስለ ነጭና ቀይ ሽብር፣ የሶማሊያ ወረራ፣ የሕወሓት እንቅስቃሴ፣ የኤርትራ ችግር፣ የግንቦት 8 መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ … በስፋት ያወጋና በመጨረሻዎቹ ምዕራፍ ግዙፉ ሠራዊት ለምን እንወደቀ ይነግረናል።

Thursday, September 24, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት
ክፍል 8

በአየር ኃይልና በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ውስጥ ያሉት በህወሓታዊያን ብቻ የተያዙ ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች
====================================================
• ብ/ጀነራል መዓሾ ሀጎስ የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ (ህወሓት) 
• ኮ/ል ደሳለኝ አበበ የአየር ኃይል የዘመቻ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ሰለሞን ገ/ስላሴ የማዕከላዊ አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ፀጋዬ አርፋይኔ የማዕከላዊ አየር ምድብ ዘመቻ (ህወሓት)
• ሻምበል ገ/እግዚአብሄር ኃ/ስላሴ የምዕራብ አየር ምድብ 3ኛ ሚሳይል ክንፍ አዛዥ (ህወሓት)
• ሻምበል ዝናቡ አብርሃ የምዕራብ አየር ምድብ የ301ኛ አየር መቃወሚያ አዛዥ( ህወሓት)
• ኮ/ል ኪዱ አሰፋ የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ(ህወሓት)
• ሌ/ኮ ክብሮም መሃመድ የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ኃይሌ ለምለም የሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ፀጋዬ ካህሳይ የሰሜን አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የአስተዳድርና ፋይናንስ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል አበበ ተካ የምስራቅ አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ሙሉ ገብሬ የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ (ህወሓት)
• ሻላቃ ፀጋዘዓብ ካሳ የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ክንፍ አዛዥ(ህወሓት)
• ሻለቃ ሀብቶም ዘነበ የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ምክትል ኃላፊ (ህወሓት)

• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር የስምንተኛ ታንከኛ ሻምበል አዛዥ ሻላቃ ተክላይ ወ/ገሪማ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር ምክትል የኃይል አዛዥ ብ/ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት) 
• በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 9ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ጥጋቡ ተወልደ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር 10ኛ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ገ/ህይወት አደራ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል መለስ ብርሃን (ህወሓት)
• በዳርፉር የኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር ድጋፍ ሰጭ ቡድን አስተባባሪ ኮ/ል ዮሴፍ አሮን (ህወሓት)
• በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ተክላይ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት )
• በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ የዘመቻ አዛዥ ሻለቃ ሀጎስ ነጋሽ (ህወሓት )

በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሰራዊት አመራሮችና…

በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል አለመተማመን እና ጥርጣሬ መስፋፋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አስረድተዋል፣
የሕዝብን መብት እና በልማት ስም በፕሮፓጋንዳ በመደለል በስልጣን ላይ ያለው በወያኔው አመራሮችና እና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል አለመተማመን እና ጥርጣሬው እየሰፋ መምጣቱን ለምድር ጦር ክፍል ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልፀው። ባለፉት አመታት በሰራዊት ውስጥ ወታደራዊ ደህንነቶች መሰግሰጋቸው ከሰራዊቱ ጥያቄዎች ጋር ተደምሮ በተለይ በምስራቅ ደቡብ እዝ እና በሰሜን እዝ ከፍተኛ የሆነ የውስጥ ውጥረት እንዳለና እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ በየስብሰባው ሶማሊያ ስለዘመቱ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቁን ታውቋል፣
በሰራዊት ውስጥ በወታደራዊ ደህንነት ቦታ የሚያገለግሉ ምንጮች እንዳሉት ሰራዊቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና ጥርጣሬ እየጨመረ የመጣው አሁንም በየእዙ የሚጠረጠሩ መኮንኖች እስራት እንደቀጠለ ተናግረዋል::ለሆዳቸው ያደሩ የሰራዊት አባላት ቢኖሩም ይህን ያህል አይደሉም የሚሉት ምንጮቹ ሰራዊቱ ግን በመፈራራት እና እርስ በርስ ጥርጣሬ ውስጥ እየተጓዘ እንደሆነ ገልጸዋል::በተለያዩ ግምገማዎች ከ10 የሰራዊቱ አባላት ሰባቱ በማስጠንቀቂያ መታለፋቸውን በራሱ በሰራዊት ውስጥ ያለው ችግር አንደኛው ገጽታ መሆኑም አውስተዋል::

የትህዴን ድርጅት በወያኔ የደህንነት…


ታጋይ መኮነን ተስፋይ ሞላ ከወያኔ የደህንነት ሃይሎች ጋር ለአንድ አመት ያህል ስሰራ ቆይቻለሁ ይላል የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ሞላ ይህን የማድረግ አቅም እንደሌለውና የትህዴንም ትልቅ ድርጂት እንደመሆኑ መጠን ጠላቱንና ወዳጁን ለይቶ የሚያውቅ ጠንካራ ድርጂታዊ የስልያና የፀረ ስለያ ማዕከል የገነባ ስለሆነ የወያኔ የደህንነት ሃይሎች ይህን የማድረግ አቅም የላቸውም ሲል አረጋግጧል፣
ታጋይ መኮነን ተስፋይ ጨምሮም ሞላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ድርጂታዊ ጉባኤ እንደሚካሄድ ፈርቶ አመለጠ እንጂ ከወያኔ ጋር አልነበረምየመሆን ሃቅምም የለውም ካለ በኋላ ይህ ለአንድ አመት ግንኙነት ነበረኝ ያለው መግለጫም ሃይለኛ መስሎ ለመታየትና የወያኔ የስለላ ማዕከል ጠንካራ እንደሆነ ለማስመሰል ህዝቡን ለማደናገር የተጠቀመበት የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ሲል ገልፁኣል፣
ሞላ 700 የሚሆኑ ታጋዮችን ይዠ የሚለውም ቢሆን በስርኣቱ በል ተብሎ ስለተገደደ እንጂ ከዚያ ባለፈም የነበረውን ድክመት ለመሸፈን ሃይለኛ መስሎ ለመታየት ካልሆነ በስተቀር ሞላ የወሰደው ታጋይ መጠኑ ከ115 የማይበልጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 48ቱ ታጋዮች ተደናገረው ስለነበር ወደ ድርጂታቸው መመለሳቸውን አስታውቋል፣
በተጨማሪም በሱዳን መሬት አካባቢ በርከት ያሉ ታጋዮች ሞላን በመቃወም ተበታትነው የሚገኙ ሲሆን ትህዴንም ወደ ድርጂታቸው ለመመለስ ሁኔታዎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ ጨምሮ አስረድቷል፣

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎የኢትዮጵያ‬ ንግድ ባንክ አዲስ የዘረጋውን የባንክ አሰራር ስርዓት በትክክል መተግበር ስለተሳነው ደምበኞቹ ለከፍተኛ መጉላላት እና ለገንዘብ ኪሳራ መዳረጋቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
‪#‎ህወሓት‬ የፌደራል ፖሊሱንና የልዩ ኃይል ሰራዊቱን በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ሳንጃና ሌሎች አከባቢዎች በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በማሰራጨት ድሃውን ገበሬ በማሸበር ላይ መሆኑ ታወቀ
====================================================

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የዘረጋውን የባንክ አሰራር ስርዓት በትክክል መተግበር ስለተሳነው ደምበኞቹ ለከፍተኛ መጉላላት እና ለገንዘብ ኪሳራ መዳረጋቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
ምንጮቻችን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደምበኞችን ጠይቀው እንዳረጋገጡት ባንኩ በዘረጋው የኢንተርኔት መረብ፣ የካርድና የሞባይል የባንክ አገልግሎቶች ምክንያት በርካታ ቴክኒካዊ ችግሮች በመፈጠራቸው ህዝቡ ለከፍተኛ ኪሳራና መጉላላት ተጋልጧል፡፡
በተለይ ደግሞ ችግሩ በባህር ዳር፣ በጎንደርና አካባቢው (ወረዳዎች) የከፋና ህዝቡን እያንገሸገሸ የሚገኝ መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

ህወሓት የፌደራል ፖሊሱንና የልዩ ኃይል ሰራዊቱን በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ሳንጃና ሌሎች አከባቢዎች በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በማሰራጨት ድሃውን ገበሬ በማሸበር ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡
በላይ አርማጭሆ በየገበሬው መንደር ተሰራጭተው የሚገኙት የህወሓት ፌደራልና ልዩ ኃይል ታጣቂዎች የገጠሩን ህዝብ አገዛዙን በነፍጥ ለመዋጋት በረሃ የወጡ ልጆቻቸውን እንዲያስመልሱ በማስፈራራትና በማንገራገር ላይ ናቸው፡፡
የፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ቡድኑ አባላት ገበሬው የትጥቅ ትግል እያደረጉ የሚገኙ ልጆቹን የሚያስመልስበትን ቀነ ገደብ በማስቀመጥ አለበለዚያ ግን እያፈሱ እንደሚወስዱት ካስፈለገም በጥይት እንደሚጨፈጭፉት በግልፅ እየተናገሩ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

Wednesday, September 23, 2015

“አዲስ አበባ ውሸት የሚነገርበት መዲና ሆናለች” (በኤፍሬም ማዴቦ – ከአርበኞች መንደር)

Madeboየተናገሩት ከሚጠፋ… ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት
ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ። ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ

በውቤ በረሃ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ቦታቸውን በግዳጅ ሊነጠቁ ነው

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ እየታሸጉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። የከተማው አስተዳደር ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና እያንዳንዳቸው 25,000 ብር በማዋጣት በባንክ እንዲያስቀምጡ እንዲሁም በየወሩ ከ2000 ብር በላይ ገቢ እንዲያደርጉ ያቀረበውን ሐሳብ መቀበላቸውንና ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ ፣ በንግድ ቦታቸው ላይ ግንባታ ተካሂዶ እያንዳንዳቸው 25 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ሁሉ ታጥፎ በቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኑ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር እኩል ሊባል የሚችል ዕድሜ ያስቆጠሩ ንግድ ቤቶች በአንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ብቻ ለማፍረስ መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ ፣ አስተዳደሩ የገባላቸውን ቃል በማጠፍ ‹‹ተለዋጭ ቦታ የምሰጣችሁ አሁን ያላችሁበትን የንግድ ቦታ አፅድቼ ስጨርስ ነው›› ማለቱ ከሕግ አንፃር የዜጐችን መብት የማያስከብር በመሆኑ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውንና ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት የሚመግቡትና ራሳቸውንም እያኖሩ የሚገኙት በያዙት ንግድ ቤት እየነገዱ በሚያገኙት ገቢ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ ፣ በሕገወጥ መንገድ በ‹‹አፍራሽ ግብረ ኃይል›› አማካይነት ወደ ጎዳና ተገፍተው ከመጣላቸው በፊት ለሌሎች ነጋዴዎች የተሰጠው ዕድል ለእነሱም መነፈግ ስለሌለበት ተለዋጭ የኮንዶሚኒየም የንግድ ቦታዎች እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለባለሃበቶች እየተባለ በሚሰጡ ቦታዎች ህዝቡ ምሬቱን እያሰማ ነው።
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አፍንጮ በር...

ኢሳት ዜና

መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮምሽነሩ ሰሞኑን በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ ከ95 ሺህ በላይ ተሿሚ፣ ተመራጮችና የመንግስት ሠራተኞች ሐብት ኮምሽኑ መመዝገቡን፣ እንዲሁም ከ14 ሺህ በላይ ሐብት አስመዝጋቢዎች የቤተሰቦቻቸውን ሐብት አሳውቀው ማስመዝገባቸውን አረጋግጠዋል፡፡ «ይህ መረጃ ለምን ይፋ አይደረግም» ለሚለው ጥያቄም ሲመልሱ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር ግዴታ እንደሌለባቸው በመግለጽ በግል መረጃ ለሚጠይቁ ሲሰጥ መቆየቱንና ይህ አሰራርም እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ኮምሽኑ በ2007 በጀት ዓመት ብቻ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ከኮምሽኑ አቃቤ ሕግ በተጠየቀው መሰረት 137 የሃብት አስመዝጋቢ መረጃዎችን በጹሑፍ መልስ መስጠቱን ገልጿል፡፡ ኮምሽኑ በምዝገባ ወቅት እያንዳንዱ ምዝገባው የሚመለከተው አካል ሐብትና ንብረቱን ሳይደብቅ ማስመዝገቡን በትክክል ማረጋገጥ የሚችለው ተመዝጋቢው አምኖ የሰጠው መረጃ ለሕዝብ ደርሶ ከሕዝብ በሚመጣ መረጃ መሰረት ቢሆንም፣ ኮምሽኑ መረጃውን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለሕዝብ ለመግለጽ ፈቃደኛ አለመሆኑ መግለጹ ምዝገባውን ፋይዳ ቢስ እንዳደረገው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን እየሰጡበት ይገኛሉ፡፡ የኢህአዴግ አብዛኛዎቹ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በቀበሌ፣ በወረዳና በክፍለከተሞች አካባቢ የሚገኙ ትናንሽ ተሿሚዎች በሙስና በመዘፈቅ ከገቢያቸው በላይ እንደሚኖሩ የሚታወቅ ሲሆን ፣ ኮምሽኑ መረጃ ለመከልከል ገዥው ፓርቲ እስከአንገቱ የተዘፈቀበትን የሙስና ቅሌት ለመሸፋፈን የታለመ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ኮምሽኑ ከዚህ ቀደም የባለስልጣናት ሐብት ምዝገባ መረጃን ይፋ የማያደርገው መረጃውን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አውቶሜት የማድረግ ስራ ባለመጠናቀቁ መሆኑንና ስራው ሲጠናቀቅ በድረገጽ አማካይነት መረጃው ይፋ ይሆናል የሚል ምክንያት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጅ "የባለስልጣናትን የሃብት መጠን የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም "፣ በሚል ኮሚሽኑ የሚያቀርበው አዲስ ምክንያት ቀድም ብሎም ይህ ነው የሚባል ህዝባዊ አመኔታን የሌለውን ተቋም ይበልጥ የሚገድለውና ለሙስናና መስፋፋት አዲስ በር የሚከፍት መሆኑን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን አስተያየት ሰጪዎችን ጠቅሶ የላከው ሪፖርት ያብራራል።
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮምሽነሩ ሰሞኑን በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ...
ETHSAT.COM