Wednesday, September 30, 2015

ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ከእስር በነጻ ተለቀቀ

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን
http://www.hiberradio.com/archives/1164ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከልጁ ጋር እና የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን
በሀሰተኛ ክስ ተከሶ ከትላንት ማለዳ ጀምሮ በየመን ሰንኣ እስር ላይ የነበረው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ዛሬ በፖሊሶች ተጣርቶ የቀረበበት የፈጠራ ክስ ላይ በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ ማምሻውን በነጻ መለቀቁን ባለቤቱ የላከችልን መረጃ አመለከተ።
ገጣሚ ጸሀይ በየነ በላከችው በዚህ መረጃ በጋዜጠና ግሩም መታሰር ላዘኑ ፣
አብረዋቸው ለተጨነቁ ወገኖች ሁሉ፣በውጭ ላሉ የሙአ አጋሮቹ፣የግሩም የሶሳል ሚዲያው ቤሰተቦችና በዋትስ አፕ በአረብ አገር አለውን መፍትሄና ችግሮቹን ለሚወያዩ የቡድን አባላት ምስጋና አቅርባለች።
የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠና የሆነው ግሩም ተ/ሀይማኖት በአገር ቤት በሳተናው፣በአስካልና ምንሊክን ጨምሮ በተሌአዩ የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ላይ የሰራና በተደጋጋሚ የታሰረ፣በተደራራቢ ክስ የነበረበት ሲሆን በአስቸጋሪ ሁኔታ ከአገር ወጥቶ ወደ የመን ተሰዶ ከአስር ኣመት በላይ በየመንና በተለያዩ አረብ አገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ሁኔታ በመከታተል ሲጽፍ ቆ ሲሆን የሞት ጉዞ መጽሐፉም የወገኖቻችን አስከፊ ስደት ውጤትን በብዕሩ ከትቦ ለንባብ አብቅቷል።

No comments:

Post a Comment