Tuesday, September 15, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በመከላከያ፣ በደህንነቱና በፖሊስ ተቋሞቹ በሚገኙ አባላት ላይ የጀመረውን እስር አሁንም በርትቶ እንደገፋበት ነው፡፡ ‪#‎ህዝባዊ‬ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በአርማጭሆ ህዝብ ላይ አሁን ደግሞ ሌላ የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ ===========



(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በመከላከያ፣ በደህንነቱና በፖሊስ ተቋሞቹ በሚገኙ አባላት ላይ የጀመረውን እስር አሁንም በርትቶ እንደገፋበት ነው፡፡
‪#‎ህዝባዊ‬ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በአርማጭሆ ህዝብ ላይ አሁን ደግሞ ሌላ የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡

====================================================
ህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ በመከላከያ በደህንነትና በፖሊስ ተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ከትግራይ ብሄር ተወላጆች ውጭ በሆኑ አባላቱ ላይ ጆሮ ጠቢዎችን በማሰማራት የ24 ሰዓታት ያልተቋረጠ ክትትል እያደረገ የሚገኝ ሲሆን እስሩንም ጎን ለጎን አጧጡፎታል፡፡
የህወሓት አገዛዝ በመከላከያ በደህንነትና በፖሊስ ተቋሞቹ አባላት ላይ እየወሰደው የሚገኘው የስለላና እስር ተግባር በተለይም በጎንደር ከተማና ወረዳዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ 
በጎንደር ከተማ የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ የሆነው ማረልኝ፣ በጎንደር ከተማ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ አባል የሆነው አባይ አለማየሁና የጭልጋ ወረዳ ፖሊስ መርማሪ የሆነው ወርቅዬ ከሰሞኑ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ተይዘው ወደ ወህኒ ከወረዱት የፖሊስ አባላት መካከል እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በተጨማሪም በጎንደር ከተማ የፖሊስ አባላት ብቻ ሳይሆን ሲቪሎችም ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ እየተባሉ በገፍ በመታሰር ላይ ናቸው፡፡ ከታሰሩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሲቪሎች መካከል አቶ ሽመልስ አልታየው የተባለ በድለላ ስራ የሚተዳደረው ግለስብ አንዱ ነው፡፡
የህወሓት አገዛዝ በመከላከያ በደህንነቱና በፖሊስ ተቋሞቹ ውስጥ ደጋፊዎቹ የሆኑትንና ያለሆኑትን ለመለየት ከፍተኛ የማጥራት ስራ ላይ እንደሚገኝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬደዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያመለክታል፡፡

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በአርማጭሆ ህዝብ ላይ አሁን ደግሞ ሌላ የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡
ህወሓት በምዕራብ አርማጭሆ በልዩ ልዩ ቦታዎች የሚገኙትን ሰፋፊ የግጦሽ መሬቶች በጠቅላላ ሙጥጥ አድርጎ ደጋፊዎቹ ለሆኑ ግለሰቦች እየሸነሸነ በማደሉ ህዝቡ ከብቶቹን የሚያሰማራበት አጥቶ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል፡፡ 
የህወሓት የበቀል በትር ደጋግሞ እየደበደበው በሚገኘው ምዕራብ አርማጭሆ ብቻ ከ50ሺ በላይ የቀንድ ከብቶች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

No comments:

Post a Comment