Thursday, September 24, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎የኢትዮጵያ‬ ንግድ ባንክ አዲስ የዘረጋውን የባንክ አሰራር ስርዓት በትክክል መተግበር ስለተሳነው ደምበኞቹ ለከፍተኛ መጉላላት እና ለገንዘብ ኪሳራ መዳረጋቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
‪#‎ህወሓት‬ የፌደራል ፖሊሱንና የልዩ ኃይል ሰራዊቱን በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ሳንጃና ሌሎች አከባቢዎች በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በማሰራጨት ድሃውን ገበሬ በማሸበር ላይ መሆኑ ታወቀ
====================================================

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የዘረጋውን የባንክ አሰራር ስርዓት በትክክል መተግበር ስለተሳነው ደምበኞቹ ለከፍተኛ መጉላላት እና ለገንዘብ ኪሳራ መዳረጋቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
ምንጮቻችን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደምበኞችን ጠይቀው እንዳረጋገጡት ባንኩ በዘረጋው የኢንተርኔት መረብ፣ የካርድና የሞባይል የባንክ አገልግሎቶች ምክንያት በርካታ ቴክኒካዊ ችግሮች በመፈጠራቸው ህዝቡ ለከፍተኛ ኪሳራና መጉላላት ተጋልጧል፡፡
በተለይ ደግሞ ችግሩ በባህር ዳር፣ በጎንደርና አካባቢው (ወረዳዎች) የከፋና ህዝቡን እያንገሸገሸ የሚገኝ መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

ህወሓት የፌደራል ፖሊሱንና የልዩ ኃይል ሰራዊቱን በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ሳንጃና ሌሎች አከባቢዎች በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በማሰራጨት ድሃውን ገበሬ በማሸበር ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡
በላይ አርማጭሆ በየገበሬው መንደር ተሰራጭተው የሚገኙት የህወሓት ፌደራልና ልዩ ኃይል ታጣቂዎች የገጠሩን ህዝብ አገዛዙን በነፍጥ ለመዋጋት በረሃ የወጡ ልጆቻቸውን እንዲያስመልሱ በማስፈራራትና በማንገራገር ላይ ናቸው፡፡
የፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ቡድኑ አባላት ገበሬው የትጥቅ ትግል እያደረጉ የሚገኙ ልጆቹን የሚያስመልስበትን ቀነ ገደብ በማስቀመጥ አለበለዚያ ግን እያፈሱ እንደሚወስዱት ካስፈለገም በጥይት እንደሚጨፈጭፉት በግልፅ እየተናገሩ መሆናቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

No comments:

Post a Comment