Sunday, September 20, 2015

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት አዲሱን ካቢኔያቸውን አዋቀሩ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት አዲሱን ካቢኔያቸውን አዋቀሩ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ዛሬ መስከረም 9/2008 ዓ.ም አዲሱን ካቢኔያቸውን ለብሄራዊ ምክር ቤቱ አቅርበው አፀድቀዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል 10 የካቢኔ አባላትን ብሄራዊ ምክር ቤቱ እንዲያፀድቅላቸው ያቀረቡ ሲሆን የደህንነት እና የአባላት ክትትል ሆነው ለምክር ቤት የቀረቡት ዕጩ ራሳቸውን ሲያገልሉ፣ ለፋይናንስና ወጣቶች ጉዳይ የቀረቡት ዕጩዎች አብላጫ ድምፅ ስላላገኙ በካቢኔው ሳይካተቱ ቀርተዋል፡፡ አብላጫ ድምፅ አግኝተው የአዲሱ ካቢኔ አባላት የሆኑት፡-
1. አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ም/ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ (ከቀድሞው አንድነት)
2. አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ አበበ አካሉ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ (ከቀድሞው አንድነት)
4. አቶ ጋሻው መርሻ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
5. ወ/ሮ መዓዛ መሃመድ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
6. አቶ እስክንድር ጥላሁን የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ
7. አቶ አዲሱ ጌታነህ የህግ ጉዳይ ኃላፊ ናቸው፡፡ ሊቀመንበሩ ለደህንነትና አባላት ክትትል፣ ለወጣቶች ጉዳይና ፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊነት ዕጩዎችን በቀጣዩ ምክር ቤት ስብሰባ አቅርበው ያስፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ የፓርቲው የኦዲትና ምርመራ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን አቶ አበራ ገብሩ ሰብሳቢ፣ አቶ ሳምሶም ገረመው ምክትል ሰብሳቢ እና አቶ ሀይለገብርኤል አያሌው ፀሃፊ ሆነዋል፡፡

No comments:

Post a Comment