Thursday, September 24, 2015

የትህዴን ድርጅት በወያኔ የደህንነት…


ታጋይ መኮነን ተስፋይ ሞላ ከወያኔ የደህንነት ሃይሎች ጋር ለአንድ አመት ያህል ስሰራ ቆይቻለሁ ይላል የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ሞላ ይህን የማድረግ አቅም እንደሌለውና የትህዴንም ትልቅ ድርጂት እንደመሆኑ መጠን ጠላቱንና ወዳጁን ለይቶ የሚያውቅ ጠንካራ ድርጂታዊ የስልያና የፀረ ስለያ ማዕከል የገነባ ስለሆነ የወያኔ የደህንነት ሃይሎች ይህን የማድረግ አቅም የላቸውም ሲል አረጋግጧል፣
ታጋይ መኮነን ተስፋይ ጨምሮም ሞላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ድርጂታዊ ጉባኤ እንደሚካሄድ ፈርቶ አመለጠ እንጂ ከወያኔ ጋር አልነበረምየመሆን ሃቅምም የለውም ካለ በኋላ ይህ ለአንድ አመት ግንኙነት ነበረኝ ያለው መግለጫም ሃይለኛ መስሎ ለመታየትና የወያኔ የስለላ ማዕከል ጠንካራ እንደሆነ ለማስመሰል ህዝቡን ለማደናገር የተጠቀመበት የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ሲል ገልፁኣል፣
ሞላ 700 የሚሆኑ ታጋዮችን ይዠ የሚለውም ቢሆን በስርኣቱ በል ተብሎ ስለተገደደ እንጂ ከዚያ ባለፈም የነበረውን ድክመት ለመሸፈን ሃይለኛ መስሎ ለመታየት ካልሆነ በስተቀር ሞላ የወሰደው ታጋይ መጠኑ ከ115 የማይበልጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 48ቱ ታጋዮች ተደናገረው ስለነበር ወደ ድርጂታቸው መመለሳቸውን አስታውቋል፣
በተጨማሪም በሱዳን መሬት አካባቢ በርከት ያሉ ታጋዮች ሞላን በመቃወም ተበታትነው የሚገኙ ሲሆን ትህዴንም ወደ ድርጂታቸው ለመመለስ ሁኔታዎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ ጨምሮ አስረድቷል፣

No comments:

Post a Comment