Monday, September 21, 2015

ኦብነግ ሁለት መሪዎቼ በአልሸባብ ተገደሉ ሲል መግለጫ አወጣ

መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መግለጫ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነው አቶ አብዲሳ ሙሃመድ አዲር እና ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ከባይዶዋ ወደ ኦጋዴን ለሚያደርጉት ጉዞ የክትትል ስራ የሚሰራው ሌላው አባል በፈረንጆች አቆጣጠር ሜይ 8፣ 2015 ፣ በአልሸባብ ታጣቂዎች ከተያዙ በሁዋላ፣ የኦብነግ አባላት መሆናቸው ሲታወቅ ያቅ ባድህወይን በተባለ ቦታ ላይ ተገድለዋል። አልሸባብ ከዚህ ቀድም ሌሎች ስምንት የኦብነግ አባላትን መግደሉን ድርጅቱ አስታውቋል፤ ከተገደሉት መካከልም የቀድሞው የኦብነግ የመከላከያ ሃላፊ ኢሊ ሺ አሊ ይገኝበታል። አልሸባብ የኢትዮጵያን መንግስት እየተዋጋ እንደሆነ ቢገልጽም፣ በኦብነግ ታጣቂዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ፣ ብዛት ያላቸው የአልሸባብ አባላት ከኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ጋር አብረው እንደሚሰሩ ማሳያ ነው ብሎአል። ኦብነግ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለው እየተባለ በተደጋጋሚ ሲወነጀል ቆይቷል። በሌላ በኩል ኦብነግና የኢህአዴግን መንግስት ለማደራደር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም እስካሁን አልተሳካም። አልሸባብ በኦብነግ አባላት ላይ እርምጃ መውሰድ የጀመረው፣ ኦብነግ ከኢህአዴግ ጋር ድርድር በመጀመሩ ተቃውሞውን ለመግለጽ ይሁን፣ ወይም ኦብነግ እንዳለው በአልሸባብ ውስጥ ያሉ የኢህአዴግ የመረጃ ሰራተኞች የኦብነግ አባላት እንዲመቱ የአልሸባብ አመራሮችን በማሳመናቸው የታወቀ ነገር የለም።
መስከረም ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መግለጫ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነው አቶ አብዲሳ ሙሃመድ አዲር እና ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ከባይዶዋ ወደ...







ETHSAT.COM

No comments:

Post a Comment