Wednesday, September 16, 2015

ወጣቱዋን በአፈቀርኩ ስም ተኩሶ የገደለው የፌዴራል ፖሊስ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርብ ተጠየቀ

የሃያ ዓመቷ ሟች ሰሎሜ ጉልላት
የሃያ ዓመቷ ሟች ሰሎሜ ጉልላት
በአዲስ አበባ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ከትላንት በስቲያ ሰኞ  ምሽት አንዲት ወጣት ተገድላለች፡፡ የጥቃቱ አድራሽ  ራሱን ለማጥፋት ሞክሮ ተርፎ በሕክምና ላይ እንደሚገኝ ተዘግባል። በአገር ቤት የሚገኙ አገዛዙ ሬዲዮ ጣቢያዎች የወጣቱዋን ገዳይ ማንነት በቀጥታ የፌዴራል ፖሊስ ከማለት የፖሊስ ልብስ የለበሰ በሚል ለማስተባበል መሞከራቸው በማህበራዊ ሚዲአው ላይ የበርካታ ኢትዮጵአውአንን ቅሬታ ያስከተለ ሲሆን ገዳዩ ሕክምናውን እንደጨረሰ ቶሎ ለፍርድ እንዲቀርብ ብዙዎች አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ ከትላንት በስቲያ መስከረም 3 ቀን 2008 ዓ.ም ምሽት  በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር መገናኘታቸውን ስሜን ለጊዜው መናገር አፈልግም ያለቸውን የሟች ገደኛ የተጠቀሱ ዘገባዎች ወጥተዋል።
ሟችና ከጓደኛዋ ጋር በነበረችበት  በመዝናኛው መጸዳጃ ቤት የጠበቃቸው ታጣቂው ወደ ሰሎሜ ተጠግቶ ‹‹አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድነው?›› ብሎ በጥፊ እንደመታትና እንደወደቀች የገለጸችው የሟች ጓደኛ፣ እሷ በሁኔታው ተደናግጣ ወደ መፀዳጃ ክፍሉ ገብታ መቆለፏን ትናገራለች፡፡ በክፍሉ ውስጥ እንዳለች የተኩስ ድምፅ መሰማቱን፣ የማቃሰት ድምፅ ስትሰማ መውጣቷን ለመገናኛ ብዙሃን ተናግራለች። በወቅቱ ጓደኛዋ ሰሎሜም እና ፖሊሱ ወድቀው እንዳየቻቸው ዕርዳታ ፈልጋ ሰዎች እንዲደርሱላት ብትጮህም በጊዜው የደረሰላት እንደሌለ ገልጻለች።
የሟች ወጣት ሰሎሜ ጓደኛ ዘግይታ ከደረሰችላት አንዲት እንስት ጋር በመሆን እስትንፋሷ የነበረውን ጓደኛዋን ለመርዳት እየሞከረች ሳለ፣ ፖሊሶች እንደደረሱና በሥፍራው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ በፒክ አፕ መኪና ይዘዋት መሄዳቸውን፣ ነገር ግን የጓደኛዋ ሕይወት ማለፉን ለማወቅ ተችሏል።
ተጠርጣሪው የፖሊስ ባልደረባ ጭንቅላቱን በጥይት መትቶ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሕይወቱ ባለማለፉ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገለት የሚገኝ ሲሆን ዜናውን ተከትሎ በኢትዮጵያውን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ከዚህ ቀደም በተለያየ መንገድ የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ነጻ የሕግ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቀው የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር በአገዛዙ ጫና ተሽመድምዶ መሪዎቹ ከአገር መሰደዳቸው ይታወሳል።
የፌዴራል ፖሊስ ባልደረባ የሆነውን የወጣት ሰሎሜ ገዳይ በአገር ውስጥ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን የፖሊስ ልብስ የለበሰ በሚል ፖሊስነቱን ለማስተባበል መሞከራቸው በማህበራዊ ሚዲያው ላኢ ብዙዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የወጣት ሰሎሜ በፌዴራል ፖሊሱ በጥይት ተደብድቦ ሞት ከዚህ ቀደም በ<<አፈቀርኩ>> ስም የተፈጸሙ ወንጀሎች የአንድ ሰሞን ትኩረት አግኝተው ተመልሰው ማህበራዊ ለውጥ ሳያስከትሉ፣ ቀኑ ሙሉ የአውሮፓ ካስና፣የሆሊውድ አክተሮችን ዕለታዊ ዜና ሚያሳድዱት መገናና ብዙሃን ችግሩ ላይ አንድ ሰሞን ተንቻጭተው ካልሆነም እንደዛሬው <<የፖሊስ ደንብ የለበሰ>> በሚል ሀሰተኛ ማስተባበያ ለመስጠት እተሞከረ መሰራታዊ ለውጥ አልመጣም ሲሉ የሚቆቹ አሉ።
ከዚህ ቀደም ካሚላት አፈቅራታለሁ በሚል አሲድ የተደፋባትንና በሕክምና ዕርዳታ ቆማ ለመራመድ ብትችልም ልጅነታን ለህክምና ውታ ውረድ ለማሳለፍ መገደዱዋን የሚያስታውሱ ወገኖች ከዚያ ቀደም ብሎም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆነችውን ወጣት አበራሽ ዐይኗን በስለት ያጠፋውን የተለያት ባል ያደረሰውን ጥፋት በምሳሌነት ይጠቅሳሉ።
የህብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል በወጣቷ ሞት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቿና ወዳጅ እና ለመላው በድርጊቱ ያዘኑ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ጸሐፍት የሰጧቸውን አስተያየቶች ለማስተናገድ እንሞክራለን።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩበ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

No comments:

Post a Comment