Tuesday, September 22, 2015

በዛሬው የኢሳት ሬዲዮ ስርጭት


በዛሬው የኢሳት ሬዲዮ ስርጭት 
_በዚህ ሳምንት ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይየሚመራውን መንግስት በመቃወም ወጣቶች ወደ ትግል ሜዳ እየገቡ መሆኑ እየተገለጸ ነው። የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን ባቀረበው የዜና መረጃ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ30 በላይ ወጣቶች ድንበር አቋርጠው ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል።የትህዴን አመራሮች ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አድረሰዋል። ዛሬም እንደሁልጊዜው ለኢትዮጵያ አንድነት ይታገላል ይላሉ።
_በመጨረሻም አቅቶናል አሉ የመንግስት ባለስልጣናት። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ራሳችን እንወጣዋለን ካሉ ከ1 ወር በኋላ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ እርዳታ እንፈልጋለን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። ወደ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ በረሃብ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን የህወሀት መንግስት አምኗል። በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዲዮ ዞን ረሀብ የከተማ ፍልሰተን አባብሷል። በብዙ ሺህ የሚቆጠር የገጠር ነዋሪ ከተሞች እየገባ ነው።
_የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ዲሪባ ኩባ የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ዙሪያ አከባቢዎችን በተመለከተ ደም ያፋሰሰውን ማስተር ፕላን ሲቀረጽ የማውቀው ነገር የለም አሉ። ኦህዴድ ባይተዋር መሆኑ የተጋለጠበት ተብሏል የከንቲባ ዲሪባ ንግግር።

No comments:

Post a Comment