Saturday, September 26, 2015

በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት

በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት
_አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርቡ ወጣቶች ቁጥር በተለይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ከንቅናቄው አከባቢ የተገኘው መረጃ አመለከተ። ወደ ንቅናቄው ከተደወሉ ስልኮች 80 በመቶ የሚሆኑት ትግሉን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ናቸው። ንቅናቄው በሀገር ውስጥም ወጣቱን የማደራጀት ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል። የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጪያ ወደ ትግል ሜዳ የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ነው።
_በቅርቡ በኤርትራ የተመሰረተው የሀገር አድን ንቅናቄ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋሙንና ዓላማውን የሚዘረዝር ወረቀት አዘጋጅቶ አሰራጨ። ሀገር አድኑ ንቅናቄ በስልጣን ላይ ያለውን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራውን መንግስት ለማስወገድ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን አስታውቋል። ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆምም ንቅናቄው ጠይቋል።
_የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የአባይ ግድብን በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ አርብ ይፋ አደረገ። የግብፅ ባለስልጣናት የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ላቀረቡት የውሃ እጥረት ዘገባም፣ ሃገሪቱ የአባይ ግድብን የውሃ መሙላት ሂደት በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ በመከታተል ላይ በመሆኑ የተደበቀ ነገር አይኖርም ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል።
-የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማስረጃ (TVET) እንደ ትምህርት ማስረጃ እንደማይቀበለው ገለጸ። ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ የአሜሪካንን የትምህርት ደረጃ የሚጠብቅ ባለመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በቴክኒክና ሙያ የሰለጠኑ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የ2015 የዲቪ ዕድለኞች ወደአሜሪካ መግባት አይችሉም፡፡http://ethsat.com/?p=34544

No comments:

Post a Comment