‹‹ልጄ..የበኩሬ...ልጄ..ከሰፈር ልጅስ አስ
(አሌክስ አብርሃም @ ኢትዮቮይስ)ጣልኩሽ መሳሪያ ከታጠቀ ሰዉ በምን አቅሜ ላስጥልሽ"
የሟች እናት ለቅሶ ነበር … ይሄ ግን የአንዲት እናት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጲያዊ ጥያቄ ነው ለእኔ ....ይታያችሁ ይች ትላንት ህልፈቷን የነገርኳችሁ ወጣት ሶሎሜ ጉልላት ….ስትገደል አብራት የነበረችው ጓደኛዋ እንደገለፀችው ….. የታመመ ሰው ለመጠየቅ ጆሞ ቁጥር 1 ወደሚባለው ኮንዶሚኒየም ይሄዳሉ … የሄዱበትን ጉዳይ ጨርሰው ወደ ከኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ኣጠገብ ከሚገኝ ካፌ አንድ ካፌ ይገቡና ሲወጡ ወደመፀዳጃ ቤት ይሄዳሉ ….መፃዳጃ ቤቱ ውስጥ ክላሽንኮቭ የታጠቀ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰ ሰው ቁሟል አልፈውት ገብተው ሲመለሱ የመፀዳጃ ቤቱ የውጭ በር ተቀርሮ መታጠቢ ክፍሉ ውስጥ ሰውየው ቁሟል …
ሟችን ጠርቶ ‹‹ሰላም በይኝ›› ይላታል …ሰላም ለማለት ፈቃደኛ አልሆነችም …እናም ይህ ሰው በቦክስ ሟችን ይመታትና መሬት ላይ ይጥላታል ….ቀጣዩ ጉዳይ ለማመን የሚቸግር ነበር …ጓደኛዋ ወደአንዱ መፀዳጃ ክፍል ገብታ ከውስጥ ቀረቀረችው … ወዲያው ግን አካባቢው በተኩስ ድምፅ ተናወጠ …አራት ጥይቶች ተተኮሱ ሰውየው በሶስት ጥይት ሶሎሜን ነበር የደበደባት …በመጨረሻም ራሱ ላይ ተኮሰ … ሶሎሜ ህይወቷ ወዲያው ሲያልፍ ገዳይ ይሙት ይትረፍ አልተረጋገጠም !!
እንግዲህ መሳሪያ የታጠቁና የመንግስት እና ህዝብ አደራ የተሸከሙ ሰዎች የግል ስሜታቸውን መቆጣጠርና ሃላፊነትን ከግል ጉዳይ መለየት ካልቻሉ ምን እንላለን ! ከዚህ በፊት ባህር ዳር ላይ በተመሳሳይ የወደድኳት ልጅ ተወችኝ በሚል ምክንያት በርካታ ሰዎችን ተኩሶ በመግደል ራሱን ስላጠፋው የፌዴራል ፖሊስ አባል ብዙ ተብሏል ….ለመሆኑ ለእንደዚህ አይነት ለህዝብም ህዝብ እጠብቃለሁ ለሚለውም አካል አሳፋሪና አሳቃቂ የሆነ ድርጊት ተጠያቂው ማነው ? በቃ የሆነው ሆነ ተብሎ ዝም ማለቱስ እስከመቸ??
No comments:
Post a Comment